የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ | የሮሜ መልዕክት| ክፍል 2 | አስፋው በቀለ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 21. 08. 2024
  • ለመዳን እግዚአብሔር ያዘጋጀው የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ መሆኑን በክፍል አንድ ተመልክተናል፤ በዚህ ክፍል ደግሞ ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፊቱ ወደ አይሁድ መዳን ወይ አለመዳን ጉዳይ ከአህዛብ ጋር ይሟገታል። በዚህ ክፍል ጨምረን ተግባራዊ በሆነ መንገድ ክርስቲያናዊ ኑሮን ሃዋርያው የተናገረውን በዳሰሳና በወፍ በረራ እንመለከታለን። መልካም ቆይታ!

Komentáře • 44

  • @hanamamo6648
    @hanamamo6648 Před 2 lety +7

    እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ሰላም የእግዚአብሔር ሰው ፓስተር አስፋው የእግዚአብሔር ሰላም ጸጋው ይብዛሎት ፓስተርዬ በትምህርት በጣም በብዙ ድንቅ ትምህርት ተምሬአለሁ ትልቁ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይባርኮት አባቴ እግዚአብሔር እንደ እርሶ አባቶችን ያብዛልን በዚህ አንድ ዓመት ትልቅ ትምህርት ተምሬአለሁ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሴንም ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ አንብቤ በጣም ብዙ እዉቀትንም ቀስሜአለሁ በጣም ደስተኛ ነኝ አባቴ እርሶ ቸርች ውስጥ የምገለገሉት ምዕመናን በጣም እድለኞች ናቸው ።
    እግዚአብሔር በብዙ በረከት ይባርኮት አባቴ!! እኔ ሐና ከዱባይ ነኝ። እናም ከተወሰኑ ወራት ቦኃላ ወደ ኢትዮጵያ እገባለሁ እናም ትምህርቱን እንዴት አገኛለሁ ብዬ አስባለሁ ግን እግዚአብሔር መልካም ነው።

  • @meseretgetachew3744
    @meseretgetachew3744 Před 2 lety +5

    ተባረክልን የእውነት አየተጠቀምን ነው ጌታ ጸጋ ያብዛልህ

  • @tsegeredaabebe4084
    @tsegeredaabebe4084 Před 2 lety +3

    በማይጎድል እየጨመረ በሚበራ በጻደቃን ፀሐይና ፀጋ ጌታ ጨምሮ ጨምሮ ይባርክህ የወንጌል ሰደድ እሳት ይሙላብህ ።

  • @user-lf8zg2kn9d
    @user-lf8zg2kn9d Před rokem

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤

  • @senaitteshale6835
    @senaitteshale6835 Před 2 lety +1

    ከመጨረሻው ጸሎት በኃላ ያለው መዝሙር ማነው ዘማሪው ከግብህን የምጎስሰኝ.........

  • @eyerusalemhaile6802
    @eyerusalemhaile6802 Před 2 lety +3

    እግዚአብሔር ይመስገን!! የቃሉን እውነትና የፀጋውን ኃይል ተቀብያለሁ!! እግዚአብሔር የመንግስቱን ፀጋና ስራ ያብዛልህ!!

  • @nadiaasfoor990
    @nadiaasfoor990 Před 2 lety

    የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ወንድሜን ፓስተር አስፋዉን ዘመኑን ቤተሰቡን አገልግሎቱንና የእርሱ የሆኑትን ሁሉ ባርክ።አባ በቤትህ ውስጥ ዘመን ብቆጥርም ብዙዎችን አላዉቅም ነበረ። ዛሬ ጌታ ኢየሱስ ከፍ ይበል አንተን ተጠቅሞ የውስጥ አይኖቼን አበራልኝ።ወንድሜ የምልህ ወይም የምሰጥህ የለኝም ፣ግን በጌታዬ ፊት እጸልይልሃለሁ። በአባታችን ዙፋን ፊት ለዘለዓለም አብረን እንኖራለን ፣ፀጋዉንና ብርታቱን ይጨምርልህ አሜን።

  • @tsyontesefaye9195
    @tsyontesefaye9195 Před 24 dny

    ተባረክ

  • @zahraala6507
    @zahraala6507 Před 2 lety +2

    Amen amen

  • @almaznegash1889
    @almaznegash1889 Před 2 lety

    Shalom paster asfaw.

  • @ayyaana-659
    @ayyaana-659 Před 2 lety +1

    Amen

  • @mekdasm5343
    @mekdasm5343 Před 2 lety

    ተባርክ ፓስተር በትምህርትህ ተባርኬአለሁ

  • @assefabekele8885
    @assefabekele8885 Před 2 lety

    ፓሰተር የእግዚአብሄርን ትምህርት እንዲበዛልን እያስተማርከን ስላለህ ጌታ ይባርክህ ለብዙዎች የመዳናችን መሠረት የሆነውን ወንጌል የማወቅ እድል ሠጠኸናል ።

  • @samt7785
    @samt7785 Před 2 lety +1

    ያ ከቤተክርስትያን የቀረና: ከተጠመቅቁኝ በኋላ ልክ እንደጓደኛየ እሆናለሁኝ ብሎ እንዲጠብቅ ያረገው እኮ ፓስተረይ: ጥምቀት(የውሃ ማለቴ ነው) ምንም ጥቅም ሳይኖረዉ: በጣም ኣስፈላጊ መሆኑን በትምህርትም: በቤተክርትያን ባህልም እየተነገረ ዘመናት ስላለፈ ነው: በኔን ትእዝብት።የውሃ ጥምቀት: በጣም ትልቅ በር: ለ religiousness ወይ ሃይማኖታዊነት ሆነዋል። ጌታ ግን ስለ ውሃ ጥምቀት ኣላስተማረም ለማንምም በውሃ ኣላጠመቀም። ጳውሎስም እኔን ወንጌል እንድሰብክ እንጂ: እንዳጠምቅ ኣይተጠራሁም ብለዋል። የውሃ ጥምቀት: በእምነት: በጸጋ ብቻ መዳን የሚለውን ሃሳብ በጣም ወደ ጥያቄ ያስገባ ነው። ከኔ ይበልጥ ኣንተን ስለዚህ ታውቃለህ ፓስተር ሓወይ። እኔ ግን መንፈሰዊ መዳናቀፍያ የሚሆን: ሃዋርያት እኛን መሸከም ያልቻልነውን: በኣህዛብ ጫንቃ ኣንጭነውም እንዳሉ ሁላ: ይሄ የውሃ ጥምቀት ቢቀር:ለሚያምኑ ኣዳሲስ ነፍሳት ጥቅሙ ቡዙ በሆነ ብየ አምናለሁኝ።

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  Před 2 lety +2

      sam hawna, ስለጥምቀት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ አለማስተማር ጉዳት እንዳለው ያልከው ትክክል ነው፤ ሆኖም ግን ጥምቀት ሞቱን በሚመስል ሞት ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ የምንተባበርበት ምሳሌያዊ ምስክርነት ነው። እንጂ ጥምቀት አያድነንም ... ትክክል ነው፤ ሆኖም ግን ጌታ አስፈላጊነቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ያመነ የተጠመቀ ይድናል... ተብሎ ተጽፎልናል... እንዳልከው አስተምህሮአችን በጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አምናለሁ። ጌታ ይባርክልኝ።

  • @abnett.6429
    @abnett.6429 Před 2 lety +1

    ተባረክ ፓስተር

  • @fasikagebru4568
    @fasikagebru4568 Před 2 lety +2

    God bless you more pastor Asfaw 🙏🙌❤

  • @meazamusazghi1778
    @meazamusazghi1778 Před 2 lety +1

    God bless you more and more

  • @abelo6917
    @abelo6917 Před 2 lety +1

    እየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ጌታ ነው!!!
    ጸጋውን እና ምህረቱን ያብዛሎት!!!
    ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  • @samiabdu3877
    @samiabdu3877 Před 9 měsíci

  • @samt7785
    @samt7785 Před 2 lety +5

    ፓስተር ሓወይ: ያለመደባበቅ: የቅዱሳን የቤተክርስትያን ኣባቶች የተሳሳተ ግንዛቤ ስለ ኣይሁዶች በደንብ ስለኣብራራሀው: ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖረን ያግዘናል ።
    ኣንድ ያለችን reservation ግን ሊያጋርህ እወዳለሁኝ: ስለ eternal security ከ grafting ማለት የበርሀ ወይራን በተመለከተ። ኣንድ ተክል ከሌላ ግንድ grafted ከሆነ: ከግንዱ ጨምረህ ካልቆረጥከው በስተቀር እንዴት ብለህ ለይተህ ልትቆርጠው ይቻላል? ያ ከበረሀ ተቆርጦ የመጣ ወይራ ከቦታው ሲነቀል already ሞተዋል እኮ: ወደ ኣዲሱ ግንድ ሲፈልስ: የግንዱን ህይወት ነው የሚያስተነፍስ።
    በዚች ባለሁባት church የሮሜን መጽሓፍ ስናጠና: ይሂችን ሃሳብ እንዴት ብለን ነው የተረጎምናት;ሃዋርያው ጳውሎስ እያለ ያለውን; ኣንተ የበርሀ ወይራ: የእግዚኣብሄር ነጻ ስጦታ: በጸጋው የሚገኝ ጽድቅ ተቀብለህ ነው ወደ ግንዱ ማለት ክርስቶስ የተጣበቅ: ቡዙዎቹ ኣይሁዶች ግን: ይህንን በክርስቶስ ኣማካኝነት የሚሰጠውን የጽድቅ ስጦታ ኣንቀበለውም: በራሳችን ጥረን ግረን :ህጉን(የሙሴ) ጠብቀን ነው የምንጸድቀው እንዳሉ ሁላ: እኛ ኣህዛብ ደግሞ ከጸጋው ትምህርት: ማለት ጽድቅ ክርስቶስን በማመን ብቻ የሚገኝ ስጦታ መሆኑን: ይሀ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ የታተመ ኪዳን ስለ ሆነ eternally secured መሆኑን: ምክንያቱ: በእርሱ ያመነ የዘልኣለም ህይወት ያገኛል ስለሚል። የዘልኣለም: ማለት ደግሞ የዘልኣለም ነው እንጂ :እንደነገሩ :ማለት ኣይደለም። ስለዚ የኛ ድርሻ የተሰጠንን ጽድቅ acknowledge እንድናደርገው appreciate እንድናደርገው: በልባችን እንዳመንነው ሁላ: ለነፍሳችን ክፍልም (ማለት ለኣእሙራችን) ይህንን የእግዚኣብሄር perfect salvation እስከሚገባው ድረስ እንድንነግረው ነው። ኣእሙራችን: ይህንን ኣዲስ ማንነት(በክርስቶስ የሆነውን ኣዲስ ሰው) እሱ ነኝ: ብሎ ከተቀበለለው በኋላ: ራሱን የክርስቶስ ባርያ ኣርጎ እንደነጳውሎስ ለማገልገል በጣም ቀላል ይሆንለታል። ከዚህ ከጸጋው ትምህርት: ቤተክርስትያን ብታፈነግጥ ግን: ይሀው ሌላ ምስክር እኳ ኣንፈልግም: ለዘመናት ያንቀላፋችዉን :ማለት ብያንስ ለ 1600 ዓመታት እንተወው እና: ኣሁን እንኳን የ pentecostal movement ከጀመረ በኋላ እንኳን: ይህንን ጽድቅን ካልጠበቅከው ሸልኮ ይወድቃል የሚል ትምህርት: ለኣማኝ ሁሉ በፍርሃት ወጥመድ ኣስገብቶ: በጸጋው ኣርፎ: secured ሆኖ: ስለ ሌሎች ያልዳኑትን ብቻ እንዳያስብ: ጽድቄን ሾልካ እንዳትወድቅብኝ ሲል: በራሱ ዙርያ መኖር ብቻ ሳይሆን: በሆነ ስህተት ወይም የሃጥያት ስራ ከተያዘም: በንስሀ ተመለስ ይባል እና: በስንት ጸሎት እና ጾም ተመሊሻለሁ ብሎ ገና ሳያርፍ :እንደገና በሌላ የሰይጣን ክስ ወይም በቀደመዉ የሰራው ሃጥያት እንደገና ይያዛል: ከዛ: ስልችት ብሎት: I can't handle this anymore በቃ ጽድቅዋን ሾልካለች ብሎ ራሱን እንዲጥል ወይም ደግሞ በቤተክርስትያን እያለም paralyzed የማይንቀሳቀስ: ነጭናጫ ይሆናል። እንግዲህ ይሄ ሁሉ: ልክ እየሱስን እንዳልተቀበሉት ኣይሁዶች: እኛ ደግሞ በ performance ያልተቀበልነው ጽድቅ: perform ኣድርገን እንጠብቀዋለን ከሚል ትምህርትና: ባህል :የመጣ ጣጣ ነው። ስለዚህ ሃዋርያው ጳውሎስ: ወደ performance theology እንዳትወድቁ ኣደራ እያለ ነው: ይሀው እንደ ፈራው :ቤተክርስትያን ወደ performance trap ገባች። Eternal security ችላ ኣለችው: ስለዚ ልክ እንደ ፊተኛዎቹ የደረቁ ቅርንጫፎች(ያላመኑ ኣይሁድ): ከጸጋው ወንዝ ተቆርጣ: ይሀው እየኖረች ነው።
    ስለዚህ: መቆረጥ: በዚህ ሃሳብ: ያመነ ይቆረጣል ሳይሆን: እናንተ ኣህዛብ ኣማኞች (Paul ,is speaking as a category ,to the Gentile believers as a group) ወደ performance theology ከወደቃቹ ትቆረጣለቹ(ከምንጩ ማለት: ከጸጋው ስለምትፋቱ): እያለ መሆኑን ነው የወሰድነው። እርግጥ ይህንን ሃሳብ በቀላሉ የሚዋጥ ኣይደለም but I am so convinced to this kind of interpretation ፓስተር ሓወይ።
    በኣገልግሎትህ ቡዙ እየተጠቀምሁኝ ነኝ: ጌታ ኣብዝቶ ይባርክህ።

  • @israelmiso5552
    @israelmiso5552 Před 2 lety +1

    THAN YOU PASTER MY GOD BLESS YOU MORE.

  • @meseretgetachew3744
    @meseretgetachew3744 Před 2 lety

    ይህ ሁሉ በአንተ ወስጥ ባለው ጸጋ ጌታ እየጠቀመኝ ነው

  • @abrehettweldebrhan9313

    Egziabher ybarkkh yegziabher sew geta abzto abzto ybarkh Ante btam yetebarekk sew nehhh ❤

  • @marthakebede3845
    @marthakebede3845 Před 2 lety +1

    God bless you

  • @abiyadmasu823
    @abiyadmasu823 Před 2 lety

    God bless paster

  • @senaitteshale6835
    @senaitteshale6835 Před 2 lety +2

    ሰላም ላንተ ያ የመጨረሻው መዝሙር ማን ነው ዘማሪው አመሰግናለሁ

  • @mesfeneegebre4511
    @mesfeneegebre4511 Před 2 lety +4

    መጨረሻው ላይ የሠማነውን መዝሙር የማን እንደሆነ የምታዉቁ ሊንኩን አስቀምጡልኝ ተባረኩ

  • @senaitsolomon2737
    @senaitsolomon2737 Před 2 lety

    Shalom pastor thank you

  • @jesusislord3691
    @jesusislord3691 Před 2 lety

    Tebarek pasterye

  • @ameloshilo7756
    @ameloshilo7756 Před 2 lety

    God bless you more and more 🙏🙏🙏

  • @raheltsehaye1852
    @raheltsehaye1852 Před 2 lety

    Geta yebarkeh 🙏

  • @mm-bb8qx
    @mm-bb8qx Před 2 lety

    አብዝቱ ጌታ ይባርክ ፖስተር

  • @henockambaye1
    @henockambaye1 Před 2 lety

    Hi pastor

  • @workukassahun6525
    @workukassahun6525 Před rokem

    7

  • @gb6742
    @gb6742 Před 2 lety

    selamnew

  • @yeshitlamulat5703
    @yeshitlamulat5703 Před 4 měsíci

    ማለት የምችለው ጌታ ፐጰጋውን አእንዲያበዛልህ መጰለይ ብቻ ነው

  • @zahraala6507
    @zahraala6507 Před 2 lety +1

    Amen amen

  • @agerebinalfew4789
    @agerebinalfew4789 Před 2 lety

    ተባረክ ፓስተር

  • @selammoha7515
    @selammoha7515 Před 2 lety

    Amen

  • @mesfeneegebre4511
    @mesfeneegebre4511 Před 2 lety

    ተባረክ ፓስተር