ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ | TPLF | Debretsion | Tigray| ethiopiainsider| zena

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2024
  • ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
    ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያጠናቅቅ ነው። በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ተከናውኗል።
    ፓርቲው ከስድስት ዓመት በፊት ባከናወነው ጉባኤ ከመረጣቸው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ በአሁኑ ምርጫ የተካተቱት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ብቻ ናቸው። ከጠቅላላ ጉባኤው ራሳቸውን ያገለሉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ 6 የፖሊት ቢሮ አባላት በአዲስ ተመራጮች ተተክተዋል።
    የህወሓትን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከተቀላቀሉት ውስጥ ያልተጠበቀውን ከፍተኛ ስልጣን ያገኙት፤ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በፊት የትግራይ ክልል የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አማኑኤል አሰፋ ናቸው። አቶ አማኑኤል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
    🔴 ዝርዝሩን በጹሁፍ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ ethiopiainside...
    --------------------------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

Komentáře • 16