መልአኩና ጦቢት / ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 6. 09. 2024
  • #_ቅዱስ_ጦቢት 00:20
    #_ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት_09:56
    welcome to" መክሊት ዘተዋሕዶ " CZcams channel This channel is the official channel of Meklit the Tewahido" መክሊት ዘተዋሕዶ " .it prepared the Old history of Ethiopian Orthodox Tewahido.
    #ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ_መላዕክት#Meklit_the_Tewahido#መልአኩና_ጦቢት
    ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመላዕክት እና ጦቢት
    ✝ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝
    ✞ የቅዱስ ሩፋኤል ታሪክ ✞
    ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
    ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::
    ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡.........የመልአኩ ሩፋኤልና የጦቢትን ታሪክ ያድምጡ የመክሊት ዘተዋሕዶ ቤተሰብ ይሁኑ
    ፨፨፨፨፨

Komentáře • 39