መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ኮሚሽኑ ጠየቀ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 27. 06. 2024
  • የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የ2016 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን፣ ዛሬ ዐርብ፣ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ጠይቋል፡፡
    በስካይ ላይት ሆቴል ለምክር ቤቱ አባላት በቀረበው የኮሚሽኑ ዓመታዊ ሪፖርት፣ በ2016 ዓ.ም. የገጠሙት ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የሥራ ዕቅዶቹ ያካተተ ነው፡፡
    ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፣ ኮሚሽኑ የዝግጅት እና ከሁለት ክልሎች ውጭ የተሳታፊዎች ልየታ ምዕራፎችን አከናውኖ፣ አጀንዳን በማሰባሰብ ተግባር ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
    ግጭቶች መቀጠላቸውና ከተለያዩ አካላት የሚነሡ ቅሬታዎች፣ በኮሚሽኑ ሥራ ላይ ተግዳሮት እየፈጠሩ ነው፤ ብለዋል ፕሮፌሰር መስፍን፡፡ በኮሚሽኑ ገለልተኝነት ላይ የሚነሣው ጥያቄ አንዱ መኾኑንና በዚኽም ራሳቸውን ከሒደቱ ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንዳንድ አካላት ባሉበት ሥራው መቀጠሉን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
    አገራዊ የምክክር ሒደቱ ኹሉንም አካላት እንደሚያሳትፍ ዋና ኮሚሽነሩ አንሥተዋል፡፡ ግጭት ባለባቸው በተለይም በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ሒደቱን ማስቀጠል አዳጋች መኾኑን፣ እንዲሁም አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከአመራሮቻቸው እና ከአባሎቻቸው መታሰርና መሰል ጉዳዮች ጋራ በተገናኘ የሚያነሧቸው ቅሬታዎች ተግዳሮት እየኾኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
    በትግራይ ክልልም፣ ሒደቱን ለመጀመር እስከ አሁን ይኹንታ እንዳላገኙ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ለማስጀመር ያለመ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋራ ቢደረግም እንዳልቀጠለ አመልክተዋል፡፡ ስለዚኽም፣ መንግሥት አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ጠይቀዋል፤ ምክር ቤቱም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
    የዋና ኮሚሽነሩን ማብራሪያ ተከትሎ፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ተነሥተው ውይይት ተደርጓል፡፡
    ከዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ፓርቲ በመወከል ከዐማራ ክልል የተመረጡት ዶር. ደሳለኝ ጫኔ፣ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ስላለው ሒደት ጠይቀው፣ ዋና ኮሚሽነሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የትግራይ ክልልን ኹኔታ በሚመለከት ደግሞ አቶ መለሰ መና የተባሉ የምክር ቤቱ አባል ጥያቄ አንሥተዋል፡፡
    - - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
    🔷 የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
    ፌስቡክ - / voaamharic
    ኢንስታግራም - / voaamharic
    X - / voaamharic
    ዌብሳይት - amharic.voanews.com
    የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- / voaamharic
    ☎️የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
    📡 ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
    VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa, and the United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, and Sports Shows on different days, stay tuned.

Komentáře •