ውሎ አዳር - የውሎ አዳር አዘጋጅ አስካለ ተስፋዬ በባልደረቦቿ ሰርፕራይዝ ተደረገችEtv | Ethiopia | News

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 26. 08. 2024
  • ውሎ አዳር - የውሎ አዳር አዘጋጅ አስካለ ተስፋዬ በባልደረቦቿ ሰርፕራይዝ ተደረገች
    #ebc #etv #news
    #EthiopianBroadcastingCorporation
    #ethiopiannews #newsdaily

Komentáře • 453

  • @tgstamre2724
    @tgstamre2724 Před 2 lety +66

    እንዲህ ነው ሰውን በቁሙ ማድነቅና ፍቅርን መግለፅ በጣም አድንቅያችሁ ነኝ ደስ ትላላችሁ ጎበዞች

  • @sultanassen9986
    @sultanassen9986 Před 2 lety +125

    አስኩ እንኳን ፈጣሪ ለዚህ አበቃሽ..የ እውነት የ EBC የስራ ባልደረቦቿ እንዲህ እንዳከበራችሃት ፈጣሪ ያክብራችሁ ይሄ ለሷ ያንሳታል እናንተን ግን ሳላመሰግን አላልፍም

  • @user-gz7cl7uu3t
    @user-gz7cl7uu3t Před 2 lety +38

    አስኩቲ ምንም ማለት አልችልም። እግዚአብሔር ይመስገን🙏🙏🙏ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ ስለረዳችሽ እሷም እንደክብሯ ምስጋና ይድረሳት። ከምንም ከማንም በላይ ደስ ብሎኛል። ምክንያቱም አንቺ ኢትዮጵያ ነሽ ሁሉንም ትወክያለሽና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከቦረና እስከ ባድመ ከአሶሳ እስከ አፋር ሶማሌ እንዲሁም አ.አ "ከዳር እስከ ዳር" ሁሉንም አንቺን የማይወድሽ የለም❤❤❤❤

  • @mmmsss9657
    @mmmsss9657 Před 2 lety +35

    በደስታ አለቀስኩ በጣም ደስ አለኝ አስኩ እንኳን ለዝህ አበቃሽ ጨርሶ ይማርሽ የኔ እናት

  • @sabrihassen7383
    @sabrihassen7383 Před 2 lety +17

    መልካምነት መልሶ ይከፍላል ጥሩ ሰው ስለሆንሽ ነው በርቺ እንኳን አላህ አፊያ አደረገሽ

  • @tube-ph7gw
    @tube-ph7gw Před 2 lety +13

    እንዴት እንደምወዳት ትክክለኛው የጋዜጠኝነት ገፀ ባህሪ የተላበሰች ጀግና ጋዜጠኛ ነች በተለይም የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለአለም ያስተዋወቀች ብርቱ ሴት ነች ኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ ድምፅ አሁን ድረስ
    በአዕምሮዬ ተቀርጿል ረጅም እድሜና ጤና ይስጥሽ❤️❤️❤️❤️

  • @ummoalmi8477
    @ummoalmi8477 Před 2 lety +31

    የስውመውደድ ያለው ስው ምን እጣው ሊል ይችላል !!! እስኩዬ እንኮን ለዚህ እበቃሽ መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልሽ እንወድሻለን ኢቢስ ምርጦች ናችሁ 🙏🏾💚💛❤️

  • @wudneshasfaw7786
    @wudneshasfaw7786 Před 2 lety +4

    በእውነት ለፈጣሪ ምን ይከፈለዋል ከሞት መንጋጋ ፈልቅቆ ያወጣሽ አምላክ ይመስገን እንኩዋን ለዚህ አበቃሽ አስኩዬ ድምጽሽ ስራሽ ናፍቆን ነበር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ድምጽሽን ልንሰማ ነው ቀሪ ዘመንሽ ከተሟላ ጤንነት ጋር እንዲሆንልሽ እመኝልሻለሁ መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልሽ ኢቢሲዎች ስላደረጋችሁት ምስጋና ይገባችኋል አይለያችሁ

  • @tsehayweldesadil1771
    @tsehayweldesadil1771 Před 2 lety +31

    በጣም አስብሽ ነበር
    እንኳን ጌታ ፈውሶሽ በሰላም ወደምትወጅው
    ሥራ መጣሽ አሁንም እድሜና ጤና ይስጥሽ።

  • @birtukanadmase194
    @birtukanadmase194 Před 2 lety +2

    ይቅርታ ቅድሚያ የታየኝ የጋዜጠኛዋ አለባበስ ነው በእውነት ጥሩ አይደለም ጥሩ ቅርፅ እንኳን ቢኖር እድሜ ያስተምራል ሀሉ ነገርሽ ይታያል እራሰሽን እያየሽ ብትለብሽ መልካም ነው እላለሁ ።
    ጋዜጠኛ አስካለ እንኳን እግዚአብሔር በምህረቱ ጎበኝሽ እህቴ በጣም ደስ ብሎኛል ድነሽ በማየቴ እግዚአብሔር ይመስገን

  • @debrituhalelo8383
    @debrituhalelo8383 Před 2 lety +21

    እሤይ እንኳን ተሻለሽ አስኩየ። በጣም ደስ ብሎኛል። ዋናው ጤንነትሽ ነው የኔ ቆንጆ።

  • @hidayaa7171
    @hidayaa7171 Před 2 lety +2

    ፈጣሪ እድሜሽን ያርዝምልን 😍😍😍😍🇪🇹

  • @aselefechselassie3968
    @aselefechselassie3968 Před 2 lety +10

    እንካን ደህና መጣሽ ኢትዮጵያን ያስተዋወቅሽን ጀግና እግዚአብሔር ይመስገን ሰለተሻለሽ አይዞሽ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅሻል❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @selamawitghiwot2745
    @selamawitghiwot2745 Před 2 lety +2

    አስኩ ተጠፋፋን ይሄንን ፕሮግራም ሳይ በጣም ነው ደስ ያለኝ ተመስገን የማያልፍ የለም እንኳን ለዚህ አበቃሽ ጌታ ፣መጨረሻውን ያሳምርልሽ ወደ ስራሽ ተመልስሽ ለማየት ያብቃኝ፣

  • @user-we8je5jb4d
    @user-we8je5jb4d Před 2 lety +15

    አስኩዬ. መዳህኒአለም ይክበር ይመስገን ደህና መጣሽ። በጣም ደስ አለኝ ሳይሽ አስቤ ነበር በጣም💚💛❤💞።

  • @selamademsung5995
    @selamademsung5995 Před 2 lety +7

    በጣም ነው የምወዳት አስካለን
    እንካን እግዚአብሔር ለዚህ አበቃሺ አስኩዬ

  • @aregashchibessa1749
    @aregashchibessa1749 Před 2 lety +5

    ለእግዚአብሔር:ሁሉን:የምችል:አምላክ:ነው:እንኮን:ለዝህ:አበቃሽ:በርቺ:የኔ ቆንጆ::

  • @kediraliradia6048
    @kediraliradia6048 Před 2 lety +20

    የናትፋንታ ውቤ ስላየውሽ ደስ አለኝ ያቺ ልጅነቴ የ11 ሰአቷ የሬድዬ ድራማ ቅዳሜ የዘጠናዎቹ የድራማው ማሳረጊያ ሙዚቃ ያቃጭልብኛል

  • @asratbegna2759
    @asratbegna2759 Před rokem

    ይህን ፕሮግራም አላየሁትም አስኩዬ ለውሎ አዳር ሥራ የምትሄጅባቸውን ቦታዎች ስመለከት አምላኬ ጠብቃት ብዬ ጭንቅ እላለሁ። በጤንነት ስላየንሽ ደስ ብሎኛል። አንዳንዴ ቆጣ የሚሉ ወይም ትሁት ያልሆኑ ሰዎች ሳይ ድንግጥ ስል ከውስጥና ከልብ የሆነው ፍልቅልቅነቷን ታመጣውና ሁኔታዎችን ቀይራ የሥራ ፍቅሯን ትጀምራለች። ፈጣሪ አምላኬ እነኳን ለዚ አበቃሽ ፈጠሰሪ ከአንቺ ጋር ይሁን።

  • @libamset
    @libamset Před 2 lety +7

    ሁል ጊዜ አስብሽ ነበር! እንኳን እግዚአብሔር በምህረቱ ጎበኘሽ የኔ እህት💕💕💕

  • @kubromhabte1418
    @kubromhabte1418 Před 2 lety +4

    ልጅ ሆኜ ነው የማዳምጥሽ ግን በእድሜ የምንበላለጥ አይደለንም የምታቀርቢው ሁሉ በጣም ነው ደስ የሚለኘ እንኳን ደህና ሆነሽ ወደ ስራሽ ተመለሽ ውድዋ አንቺን የማይወድ አለ ብዬ አላምንም

  • @mussiekaleab9979
    @mussiekaleab9979 Před 2 lety +3

    አስካል ተስፋዬ እኔ ኤርትራዊ አድናቂሽ ነኝ ኢትዩጵያ ሬዲዩ እያልሽ የምታቀርቢያችው ፕርግራምሽ እስከዛሬ ከአዕምሮዬ አልጠፋም እግዛብሔር እንካን ለዚ አበቃሽ 🇪🇷🇪🇷🇪🇷

  • @tesgaengeda957
    @tesgaengeda957 Před 2 lety +4

    በጣም ደረሰ የምትሉ እግዚአብሔር የጠብቃችው አስካለዩ 💜🙏 እንኳን ደስ ያለሺ

  • @user-jz3br8ur5g
    @user-jz3br8ur5g Před 2 lety +1

    ውሎ አዳር ባች ቀረ በጣም ጎበዝና ተግባቤ ምርጥ ጋዜጠኛ ነሺ እኳን አላህ ጤናሺን መለሰልሺ የምር አስታውስሺ ነበር

  • @tsehayregassa6853
    @tsehayregassa6853 Před 2 lety +14

    እንኳን እግዚአብሔር ማረሽ አስኩዬ መልካም ሰው ነሽ እንወድሻለን!!

  • @zedotube6461
    @zedotube6461 Před 2 lety +3

    አልሀምዱሊላህ ጌታዬ ሰው ተሽሎት እደማየት የሚያስደስት ነገር አላህ ቀሪው ጊዜሽ ሰላም ያድርግልሽ

  • @abbechuyamyhero7507
    @abbechuyamyhero7507 Před 2 lety +6

    አስኩዬ የኔ ኩንስንስ እሰይ እንኳን እግዚአብሔር ለዚህ አበቃሽ ያ ማግኔት የሆነ ድምፅሽን እንደገና በውሎ አዳር ዝግጅትሽ ላይ መስማት ጏጉቻለሁ የእግዚአብሔር ስራ ድንቅ ነው will see you soon my beautiful 🙏🏼🙏🏼🙏🏼😘😘💚💛❤️

  • @user-lw5vi7kl9u
    @user-lw5vi7kl9u Před 2 lety +1

    አስኩ የኔ ልዩ ትዝታ ነሽ፣ እንኳን እግዚአብሔር ማረሽ የኔ መልካም ቅን ልብ እንኳን ለዚህ አበቃሽ የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒአለም ምስጋና ይድረሰዉ።በእዉነት በዚህ ሁኔታ ስላየሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል

  • @fesihamebratu3807
    @fesihamebratu3807 Před 2 lety +2

    አስኩዬ እንኳን ለዚህ አበቃሽ እንደዚህ ሆነሽ ጤንነትሽ ተመልሶልሽ በድጋሜ ስላየሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል ሰላሙን ሁሉ እመኝልሻለሁኝ

  • @tenasewderese9400
    @tenasewderese9400 Před 2 lety +2

    እፎይ አስኩየ እንደዚህ ሁነሽ በማየቴ በጣም በጣም በጣም ተደስቻለሁ ኢቢኤስ ይለምልም

  • @ebcc-lv4741
    @ebcc-lv4741 Před 2 lety +1

    በጣም የምትገርሙ EBC ዎች እንዴት
    የምትወደዱ ናችሁ ሰውን ከአመድ አንስቶ ከጎን ቆሞ አበርትቶ ታስፈልገናለህ ብላችሁ እንዲህ የተነሳችሁበትን ሳትረሱ ስላደረጋችሁት ትልቅ ሥራ ከልቤ እያመሰገንኩ የአስኩን ሥራ በጣም እወደዋለሁ እንደውም የእርሷ ፕሮግራምን ስከታተል የእኔ ፍልፍል መጣች እላለሁ እኔ ከአገሬ ከወጣሁ 32ዓመት ሆኖኛል የኢቢሴ መዝናኛ አቅራቢዎች አገሬን እንዳልረሳ አድርጋችሁኛል ተባረኩ ስፉ አሁንም የብዙ አዲስ ትውልድ መፈጠሪያ ያድርጋችሁ በነገራችን ላይ እግዚአብሔር በአንቺ ሊሰራ የሚፈልገው ያልጨረስሽው ሥራ ስላለው ነው በሕይወት ያኖረሽ ቀሪ ዘመንሽ እግዚአብሔርን በማክበር ሕዝብን በመጥቀም እደራን ሌሎች እንድትሰጪ ነውና "እግዚአብሔርን መፍራት የጥብ ሁሉ መጀመሪያ ነው " ይላልና ዘመንሽ እግዚአብሔርን በመፍራት ይለቅልሽ ዛሬ በምድር ጮክ ብሎ እንደተሰማ ተልዕኮሽን ጨርሰሽ ወደ አምላክሽ ስትሰበሰቢ እዛም ጮክ ብሎ የሚሰማ በፊቱ ያለሃፍረት እንድትቆሚ ያድርግሽ እንደተመልካች አደንቅሻለሁ
    Pastor Emebet Getaneh
    from Las Vegas

    • @askaletesfaye5916
      @askaletesfaye5916 Před 2 lety

      አመሰግናለሁ እህቴ እግዜር ይስጥልኝ

  • @banchamlakmengistie4832
    @banchamlakmengistie4832 Před 2 lety +1

    እረ እንዴት ደስ ይላል እንኳን በሰላም ወደምትወጃት ሀገርሽ በሰላም መጣሽ በጣም ደስ ብሎኛል ጀግናዋን እህቴ ።

  • @burtetesfaye4015
    @burtetesfaye4015 Před 2 lety +1

    አስኩዩ እንኳንም ፈጣሪ ምሮሽ ለዚህ አበቃሽ የኢትዮጽያ ህዝብንና ኢቢኤሶችን ከሴፉ ሾው ጀምሮ ፈጣሪ ብርከርክ ያርጋቹ!

  • @kaleabhaile3234
    @kaleabhaile3234 Před 2 lety +9

    ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል አስክዬ

  • @user-ce5mu3qn4i
    @user-ce5mu3qn4i Před 2 lety +2

    አስኩዬ የእናቴ ፌቨራይት ሾው እንኳን ፈጣሪ አምላክ ለዚህ አበቃሽ። እውነተኛ የኢትዮጵያን ገጽታ ያሳየሽን እህታችን ነሽ ። አሀንም ፈጣሪ ወደጥንካሬሽ ወደ ብርታትሽ መልሶሽ ድጋሚ ፕሮግራምሽን ለማየት ያብቃን።

  • @yetnayetbelay64
    @yetnayetbelay64 Před 2 lety

    አስኩየ እንክዋን ለዚህ አበቃሽ በጣም ነው የምወድሽ የማከብርሽ ለተደረገላት አቀባበል እጅግ ደስ ብሎኛል ያንሳታል እንጅ አይበዛባትም በህይወት ኖሮ እንደዚህ መደናነቅ በጣም ደሥ ይላል ሁላችንም እንክዋን አደረሳችሁ

  • @biruktawitandargachew7102

    እንኳን እግዚአብሔር እረዳሽ አንቺ በጣም ድንቅ ሴት ነሽ ኢትዮጵያን እንድናውቃት ያደረግሽ ነሽ በጣም አደንቅሻለው። እንኳን ተፈወሽ አሁንም ብዙ እንጠብቃለን በርቺ።

  • @yigermalmetew4360
    @yigermalmetew4360 Před 2 lety +2

    ውሎ አዳር ፕሮግራም አስካለ እና ባልደረቦችዋን በመሰሉ በትህትናና በመረዳዳት ያቀረቡት ፕሮግራሞች በብዛት የሐገራችን እናቶችን የዕለት ኑሮ ነው ያስታወስንና ያስተማረን ነው። እንዳለችውም ሀገራችን ሳንዘራው ነው የምናመርተው። ሳንስራም ነው የምንፋጨው። እናቴ እንዳለችው አትመመኝ አይባልም ማረኝ ነው እንጂ። ከሐገራችን ከወጣሁ አምሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው። በእዚህ ፕሮግራም በእርስዋም ትህትና እና ማስተዋል የደኩበትን አስታወሰኝ። እንኩዋን ጌታ ለእዚህ አበቃሽ። በርቱልን። አይዞአችሁ። እንደርስበታለን።

    • @askaletesfaye5916
      @askaletesfaye5916 Před 2 lety

      አመሰግናለሁ አድናቂዬ አብረን እንክረም

  • @mulugebreselassie3800
    @mulugebreselassie3800 Před 2 lety +10

    To GOD be the Glory that healed you. I loveeeeeeee ❤️ the show. I left when I was 15 and lived in US over 30 years and I learned about my beloved Ethiopia watching your program. It is so wonderful to see you back. To all the coworkers GOD bless you and 🙏🏽 for showing ❤ to this outstanding journalist. Money- Fame - notoriety mean’s nothing without LOVE. So Thanks for showing her true love. Great to see you back. Can’t wait to see your shows.

  • @ethiopiaethiopia3849
    @ethiopiaethiopia3849 Před 2 lety

    ምርጥ ለእኔ ትልቅ አንጋፋ ጋዜጤኞ ማለት አስካለች ነች እንኮንም የሰማይ አምላክ ለዚህ ክብር አበቃሽ እንኮንም የኢትዮጵያ አምላክ ማርሽ በጣም ነው የምንውድሽ የምናክብርሽ ጀግና ኢትዮጵያን የምታስታዋውቂ ጋዜጤኛ ነሽ አሁንም ውድ ስራሽ ትመልስሽ ማየት እንፋልጋለን

  • @messiethio4895
    @messiethio4895 Před 2 lety +1

    አስኩዬ የኔ ውድ እግዚአብሔር እንኳን ለዚህ አበቃሽ ማርያምን አሱኩ ከታመመች ጀምሮ ውሎ አዳርን አይቼ አላውቅም እሰየው እንኳንም ተመለሽልኝ የኔ እናት እግዚአብሔር ጨርሶ ይመርሽ በጣም ነው የምወድሽ ባልደረቦቿ በጣም ነው ደስ የምትሉት ከዚህ በላይ የፍቅሩን ሸማ ያላብሳችሁ ኑሩልን

  • @asnakech1destwi1
    @asnakech1destwi1 Před 2 lety +1

    አስኩዬ ተሽሎሽ እዲህ አምረሽ ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል ፈጣሪ ምን ይሳነዋል በቅርብ ወደስራሽ ተመልሰሽ ለማዬት በጉጉት እጠብቃለን እድሜ ና ጤና ይስጥሽ ዘመንሽ ይባረክ🙏

  • @enush7338
    @enush7338 Před 2 lety +5

    እሰይ ማማዬ እንኳን እግዚአብሔር ለዚህ አበቃሽ🙌...አንቺ እኮ የኢቲቪ ድምቀት ነሽ😍🥰

  • @emebetabebe3331
    @emebetabebe3331 Před 2 lety

    አስኩዬ እግዚአብሄር ይመስገን በዚህ መልኩ ስላየሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል ለእግዘአብሄር ምን ይከፈለዋል ምስጋናው ሲያንስበት በርቺ ቀጣዩ ዘመንሽ የተባረከ የጤና የሰላም የስራ ዘመን ይሁንልሽ፡፡

  • @muludegene6121
    @muludegene6121 Před 2 lety +4

    አግዚአብሔር እመቤታችን ክብሩን ለነሱ በጤና ስላየንሽ ደስ ብሎናል

  • @tsehayalyou3864
    @tsehayalyou3864 Před 2 lety +8

    ወይ አሰኩዬ እንኳን ለዚህ አበቃሸ እግዚአብሔር ይመሰገን ውሎአዳር ባአንቺ ነው የሚያምረው አሰኩቲ🙏🙏🙏🙏❤

  • @wosenyeleshadmassu1968
    @wosenyeleshadmassu1968 Před rokem +1

    አስካለ እንኳንም ለዚህ አበቃሽ።ስትታሚ በጣም አዝኜ ነበር ። ፕሮግራምሽን በጣም በጉጉት እጠብቀው ነበር።

  • @user-cf3yl3ww1t
    @user-cf3yl3ww1t Před 2 lety +3

    አስኩ ኩንስንስ እንኳን ድነሽ ወደ ስራሽ ተመለሽ ስራውን ሁላችሁም ስትስሩት ደስ ይላል አንቺ ደግሞ ልዩ የሆነ ተሰጥኦ ለስራው አለሽ ምን ብትሉኝ አላውቀውም ግን ስራውን በጣም ታጣፍጠዋለች ልዩ ቅመም ነች እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርሽ ተባረኪ የኢትዮጵያ አፍቃሪ ጀግና ወጣት ሴት እንወድሻለን💕🤗😁🇪🇹🙏🇪🇹😁🤗💕

  • @seblimagha5800
    @seblimagha5800 Před 2 lety +1

    Wow EBC በጣም ደስ የሚል ፕሮግራም ነው የሰራችሁት የሰራ ሠው በቁሙ ማመስገን ሊለምድብን ይገባል፡፡ አስኩዬ ፈጣሪ ዕንኳንም ምሮሽ ለዚ አበቃሽ🥰🥰🥰

  • @tsehaygebrale3801
    @tsehaygebrale3801 Před 2 lety

    ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት እንዴት ደስ ይላል አስኩ ከዝህ በላይ ይገባታል

  • @ruthgirmay6832
    @ruthgirmay6832 Před 2 lety +1

    አንኮን ደህና መጣሽ ፈርቼ ነበር ደስ ብሎኛል ተሽሎሽ በማየቴ

  • @mahammedahmed5837
    @mahammedahmed5837 Před rokem

    Thank you for your service. I really like Wolo Adar program.

  • @gisheba7022
    @gisheba7022 Před 2 lety

    እዉዉዉ እንኳን ተመለሽ በፀሎቴ አሰብሽ ነበር ግን ደንነትሽን በምን እንወቅ በጣምበጣም ደስ ብሎኛን ወደጤናሽ ስለተመለሽስ

  • @seblezanni4804
    @seblezanni4804 Před 2 lety +1

    አስካለ እንኳን ለዚህ አበቃሽ እኔ በጣም ማዉቅሽ አንቺ ማታዉቂኝ እንደ ልጄ እንደ ወንድሜ ያሳደኩት አንቺ ግን አክስቱ ነሽ ከፈለግሽ እንተዋወቅ

  • @saraamagreedavid6763
    @saraamagreedavid6763 Před 2 lety +6

    እግዚአብሄር መሃሪ አምላክ ነው አስካል እንኳን ለዚህ በቃሽ የሰራሻቸው ስራዎች የማይረሱ ናቸው ።

  • @tizitasisay7533
    @tizitasisay7533 Před 2 lety +1

    Welcome back asiku ስለሁሉም እግዝአብሄር ይመስገን

  • @gashogasho1859
    @gashogasho1859 Před 2 lety

    ከአስር አመት በፊት የብሄርብሄረሠቦችን ሙዚቃና ባህል የሚያሥተዋዉቅ ፕሮግራም ታቀርብ ነበር ሁሌ አባቴ በሬድዮ ይከታተል ነበር ያን ፕሮግራም የፕሮግራሙን ስም አላሥታዉሰዉም ብቻ የሆነ ትዝታ መጣብኝና አለቀስኩ😭።ፈጣሪ ረጅም እድሜ ከጤና ጋ ይሥጥሽ።

  • @perfectone8758
    @perfectone8758 Před 2 lety +2

    አስካል እንኳን እግዚአብሔር ምህረቱን አሳይቶ ወደ ስራ ገበታሽ ተመለስሽ፡፡ ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ የተናገረው እውነት ነው በልጅነት እድሜዬ የሰማሁትን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሉቀንን ዘፈን “ይቅርታሽ ደረሰኝ ዛሬ ከረፈደ” ስሰማ ሳቤላ ትረካን ነው የማስታውሰው፡፡

  • @user-bx2mm1wx2b
    @user-bx2mm1wx2b Před 2 lety

    ስላየሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል

  • @hannahilemariam247
    @hannahilemariam247 Před 2 lety +11

    I was 13 yrs old when "Sabela" was on air and I remember the final part and Mulukine Melese song just like yesterday .Thank you so much Asku for marking beautiful memories on my childhood @Ylijoch kefelegeza(Saturday morning), yemuzika sewochina serawechachew,etc. Long life ❤🙏

  • @emuyeyilma7752
    @emuyeyilma7752 Před 2 lety

    እግዚአብሔር ይመስገን ስለማረሽ ደስ ብሎኛል

  • @tadelechtasew727
    @tadelechtasew727 Před 2 lety

    እኳን ደና መጣሽ ተሽሎሽ ሰለተመለሽ ደስ ብሎኛል እኳን አደረሳቹ እኔ አቺን ካመመሽ ጀምሮ አይቼዉ አላቅም እና ወደ ስራሽ ስለተመለሽ በጣም ደስ ይላል እኳን ደና መጣሽ አስኩዬ

  • @hannahailu5420
    @hannahailu5420 Před 2 lety +1

    እንዲህ ተሽሎሽ በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ለዚህ አበቃሽ

  • @habibakemal2222
    @habibakemal2222 Před 2 lety

    አንቺ የታደልሽ ኢትዮጵያ ን ከ እግር እስከ ራሷ ስላየሻት ያንቺን ያህል ውዴታ ማግኘት ይከብዳል ስለ ተመለሽ በጣም ደስ ያለኝ እንኳን ደህና መጣሽ

  • @Fthyhtube
    @Fthyhtube Před 2 lety +12

    እንኳን በሰላም መጣሸ ጤናሸ ተሰተካክሎ እንዲህ ሰላየሆሸ ደሰ ብሎናል ይመቻችሁ

  • @smrimohamad3540
    @smrimohamad3540 Před 2 lety +1

    አስኩዬ ቆመሽ ስላይሁሽ ደስ ብሎኛል እንኳንም እግዚአብሔር ማረሽ

  • @tsigeyimer2034
    @tsigeyimer2034 Před 2 lety

    እሰይ እልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን ይህ ድምፅ እና መልክ ናፍቆኝ ነበር አስኩዬ እንኳን ለዚህ ለተቀደሰ ቀን አበቃሽ ለቤተሰብሽም ለኢትዬጵያ ህዝብ ለአፍቃሪዎችሽ እንካን ደስ አላችሁ አስኩዬ በድጋሚ እልልልልልልልልልልልል ምስጋና ለእናቱ እና ልጁ ተመስገን 🙏🙏🙏

  • @dumatube646
    @dumatube646 Před 2 lety +3

    እግዚአብሔር እንኳን ማረሽ አሰኩ❤❤❤❤❤️❤️🤣🤣😭❤❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹❤❤❤❤🌹🌹🌹🌹🌹🌹🥰🥰🥰💚💚💚💚💕💕💕👍👍💕💚💚🙏🙏🙏🙏🙏🙏ጓደንቿ እግዚአብሔር ይባረካቹ እንኳን ደስ አለቹ💚💚💚💚

  • @zahraabdo9944
    @zahraabdo9944 Před 2 lety +2

    አስካለ ስላየሁሽ በጣም ደስብሎናል ሀገራች ውብናት ሰላም ያምጣል ብቻ

  • @yonashagos1157
    @yonashagos1157 Před 11 měsíci

    አስካልዬ አምላክ እድሜና ጤና ይጨምርልሽ እወድሻለሁ ጌታ ይባርክሽ።

  • @mikekefale4099
    @mikekefale4099 Před 2 lety +1

    እግዜር የተመሰገነ ይሁን እንኳን በጤና መጣሽ ብዙ የማናውቀውን ኣሳውቀሽናል እኔ የመጀመሪይ በደርግ ግዜ ዘማች ስለነበርኩ ድካምሽን ኣውቀዋለሁ

  • @aberashayele66
    @aberashayele66 Před 2 lety

    በጣም የምትወደድ ሴት ነች አስኩ ረጅም ዕድሜ ይስጥሽ

  • @ef6079
    @ef6079 Před 2 lety +1

    አስካለ ፍቅር የሆንሽ እንክዋን ዳንሽልን የኛ ድንቡሼ ኑሪልን ወደስራሽ ተመለሽልን እኛ በስደት ያለን ውድድ እናረግሻለን በርቺልን💜💜🙏🏿🙏🏿

  • @jemilaahmed8311
    @jemilaahmed8311 Před 2 lety +2

    አስኩየ በጣም ነው የምወድሽ እንባየን መቆጣጣር አቃተኝ አላህ ይርዳሽ

  • @tesgaengeda957
    @tesgaengeda957 Před 2 lety +1

    አስካለ አስካለ እኔ ምን እላለሁ እግዚአብሔር ይመስገን አነች ድነሺ ማየት ለእኔ ታምርነው እግዚአብሔር የጠብቅሺ አራስሺን ጠብቂ ሁላችወም እግዚአብሔር የጠብቃው በጣም ደስ የሚል ሥራ ነወ የምትሰሩት አመሰግንሃለሁ

  • @dirshayemario897
    @dirshayemario897 Před 2 lety

    እንኳን አብሮ አደረሰን በጣም ነው የምወሽ አስኪዬ እከተታልሽ ነበር ስቲተመም በጣም ነው የዘንኩ እንኳን እ/መራሽ አትመማን አይበልም ማራን ነው ያምበለው

  • @meseretlema9655
    @meseretlema9655 Před 2 lety

    እሰይ የእግዚአብሔር ስራ ድንቅ ነው እንኳን ለዚህ አበቃሽ አስኩ

  • @menbigenana9675
    @menbigenana9675 Před 2 lety +1

    አስኩዬ የልጅነቴ ስወድሽ ዕድሜ ይስጥሽ

  • @bezakebede6562
    @bezakebede6562 Před 2 lety

    አስኩ እንደው እንዴት እግዚአብሄርን እንደማመስግነው ግራ እሲኪገባኝ ነው ደስ ያለኝ እንኳን ደስ ያለሽ እግዚእብሄር ይመስገን

  • @elizabethtirfe2176
    @elizabethtirfe2176 Před 2 lety +4

    አስኩዬ እንኳን ጤና ሆንሽልን።
    እግዚአብሔር ይመስገን ።
    💚💚💚

  • @wawaasrs5431
    @wawaasrs5431 Před 2 lety

    የኔ ፋሲካ በመልካም ጤንነት ሆነው ስላየሁሺ በጣም ደስ ብሎኛል የኔ ውድ

  • @workyeskitchen8370
    @workyeskitchen8370 Před 2 lety +1

    አስኩዬ አሁንም ጤናሽን አብዝቶ ይስጥሽ🙏🙏🙏♥♥♥♥♥♥♥♥💚💛❤

  • @hiruth9501
    @hiruth9501 Před 2 lety

    አስኩዬ እግዚአብሔር ይመስገን ስላየሁሽ ደሞ ድነሽ በጣም ደስ ብሎኛል🙏

  • @rahel2834
    @rahel2834 Před 2 lety +1

    የኔ ውድ አስኩየ ስላየሁሽ ደሰ ብሎኛን

  • @tarikuaselassa3498
    @tarikuaselassa3498 Před 2 lety +4

    እንኳን በሰላም መጣሽ አስኩዬ የኔ መልካም😘😘😘ሁላቹም በጣም ደስ ትላላቹ

  • @frehiwotbezabih5046
    @frehiwotbezabih5046 Před 2 lety +1

    እንኳን ፈጣሪ ወደ ስራሽ ለመመለስ አበቃሽ ኢትዮጵያዊ ነት ይሄ ነው ናፍቆትና አስኩዬ በጣም ነው የምወዳችሁ

  • @babyflower5176
    @babyflower5176 Před 2 lety +1

    ታምራላችሁ አርኩዬ እግዚያቢሄር ይመስገንድነሸ ሰላየሁሽአሁንም ኪዳነምህረት ትጠብቅሽ የኔ ልእልት👍👍

  • @mmmsss9657
    @mmmsss9657 Před 2 lety +4

    ግን ሠው በሂወት እያለ እንዲህ ሲመሠጋገን እንዴት ደስ ይላል ይልመድባችሁ

  • @getahungizaw20
    @getahungizaw20 Před 2 lety +3

    ክብር ምስጋና ለፈጣሪ ዳግም ህይወት እንትዘሪ ለደረገሽ ለልዑል እ/ር ምጋና ይገበሃል

  • @genethaile9003
    @genethaile9003 Před 2 lety +2

    አስኩዬ ናፍቀንሻል ስራሽን ጀምሪ በጣም ነው የናፈቀን

  • @lewtalexx8740
    @lewtalexx8740 Před 9 měsíci

    እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር ይመልስ

  • @elsayimenu5512
    @elsayimenu5512 Před 2 lety

    በዚህ መልኩ ስላየሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል እንኳን ለዚህ ቀን አበቃሽ

  • @emuhiba9188
    @emuhiba9188 Před 2 lety +2

    አልሀምዱሊላህ አስኩየ እውነት እኔ ባንች ነው ሀገሬን ያወኳት እና አንችን ደህና ያደረገ ፈጣሪ ሀገሬንም ህመሟን በቃ ይበላት

  • @fitsumgetachew9414
    @fitsumgetachew9414 Před 2 lety +2

    አስኩእግዚአብሔርእንኳንለዚህአበቃሽእውድሻለሁ።

  • @hanafikadue.t3743
    @hanafikadue.t3743 Před 2 lety +1

    Yigabashel Anche jagina sati nashe yan konjo egizabeher Ahunim cheriso yimarishe 💓💓💓

  • @kidisth.dukamo6638
    @kidisth.dukamo6638 Před 2 lety +3

    ፈጣሪ ይመስገን እንኳን ለዚህ አበቃሽ🙏❤

  • @kasechassefa2342
    @kasechassefa2342 Před 2 lety

    አስኩዪ የኔ ጎበዝ እኳን ለዚ አበቃሽ ድምጽሽ ናፈቆን ነበር ውሎ አዳር ባንቺ ነው የሚያምረው ጤናሽን ያብዛልሽ እህቴ

  • @aynalemtaye7450
    @aynalemtaye7450 Před 2 lety

    እንኳን ለዚህ አበቃሽ፡፡ የሥራ ባልደረቦቿንም ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ እግዚአብሔር ያክብራችሁ፡፡

  • @kidangebreegziabher1711

    የጋዜጠኞች ቁንጮ ነሽ የኔ ቆንጆ እህት እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ና ጤና ይስጥሽ እና ደሞ እባክሽ የራስሽ ቤተሰብ መስርቺ የሂወትሽ ብርሀን ይሰጥሻል።

  • @yalemworkhaile2522
    @yalemworkhaile2522 Před 2 lety +2

    እህት ወንድሞቼ የሃገሬ ልጆች እንዴት ደስ እንደምትሉ እንባይን መቆጣጠር አልቻልኩም ለካስ አሁንም ፍቅር አለ አስካለ ተሽሎሽ በእህቶችሽእናከወንድሞችሽ መካከል ደግሞ ስላየሁሽ በጣም ተደስቻለሁኝ.