Ethiopia

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 7. 05. 2024
  • ኧረ ደሴን ደሴን ያላየ ያየ ዕለት
    ቆሞ ይሂድ እንጅ ልቡንስ እንጃለት
    የጦሳ ተራራ ውሀው ምን ጉድ አለው
    ሸጋ ሸጋውን ነው ወሎ የሚያበቅለው
    አማን በርሱ መጀን አማን በርሱ መጀን
    ወሎ እንደፈለገው እስኪ ያበጃጀን
    የደሴ ጥንታዊ ሰፈሮችና ትዝታዎችን ጨልፈን በክፍል 1 መሰናዷችን አንሷር አህመድ የተባለው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰፈረውን ጽሁፍ መነሻ አድርገን ታሪክ ነጋሪዎችንም ጨምረን ባዘጋጀነው ፕሮግራም ላይ በርካቶች ትዝታችሁን አጋራችሁን፣ ፕሮግራሙ ሰፋ ተደርጐ ደግሞ ሌላ ትዝታን ጨምራችሁ አዘጋጁ በሚል የተሰጠንን የአድማጭ ተመልካቾቻችንን አስያየት መሰረት አድርገን ፣ የፀሐፊውን አንሷር አህመድ ተጨማሪ ጽሁፍ ተጠቅመን ደሴ ከተማ ተወልደው ያደጉ አቶ ሄኖክ ጉግሳ፣ አቶ መሐመድ ሰይድ እና አቶ በላይነህ ሀይሉ ደነቀን ታሪክ ነጋሪ አድርገን ይህንን ፕሮግራም አዘጋጅተናል፡፡ አብራችሁን ቆዩ፣ እናንተም በኮሜንት ላይ ትዝታችሁን አጋሩን፡፡
    እናመሰግናለን

Komentáře • 45

  • @MohammedMohammed-dm3ie
    @MohammedMohammed-dm3ie Před měsícem +3

    ጸሃፊው አንሷር አህመድ ይህንን ሁሉ ትውስታ እንዴት ማምጣት እንደቻለ ነው እጅግ በጣም የገረመኝ ሙሉ የደርግ ዘመንን፣ በከፊል የንጉሱን፣ በጥቂቱ የኢህአዴግ ዘመን የደሴ ትዝታዎችን በሚገርም አገላለፅ ነው ያጋራን። ታሪክ ነው የተሰነደው ማለት ይቻላል።
    አዘጋጆች፣ ተራኪ፣ እንግዶች ሁሉም በጣም ደስ የሚል ነው። ይህ ፕሮግራም ከዚህ በላይ መስፋት እና ረጅም ተከታታይ ፕሮግራም መሆን እንደሚችል ግልፅ ነው ምክንያቱም እጂግ በጣም ብዙ ያልተነኩ የደሴ ታሪኮች ስላሉ። በተጨማሪም ደሴ ሰብሳቢ አጥተው የተበተኑ ልጆቿ መልሰው ይሰባሰቡ ዘንድ መሰል ፕሮግራሞች ፋይዳቸው ከፍ ያለ ነውና እባካችሁ አሁንም ይቀጥል በርቱ እኛም ከያለንበት እናግዛለን

  • @ahlamalhydr9764
    @ahlamalhydr9764 Před měsícem +2

    የደሴ ልጅ ስትሁን ትለያለህ 🥰🥰🥰

  • @seifukebede9824
    @seifukebede9824 Před 27 dny +1

    ተባረክ አባቴ👍👍👍❤

  • @seifukebede9824
    @seifukebede9824 Před 27 dny +1

    በጣም ጎበዝ ጋዜጤኛ👍👍💪💪👍👍

    • @andinetnahusenay151
      @andinetnahusenay151  Před 27 dny

      ስለ አስተያየትዎ በእጅጉ እናመሰግናለን። ክፍል አንድንም እንዲከታተሉ እየጋበዝን ሀሳብ አስተያየትዎ ጉልበት እየሆነን ለቀጣይ ስራ እንደምንዘጋጅ በደስታ እንገልፃለን።

  • @ahlamalhydr9764
    @ahlamalhydr9764 Před měsícem +1

    ሸዋበር ❤❤

  • @brooknegusei8570
    @brooknegusei8570 Před měsícem +1

    born and grew up in (Salayesh seffer) Dessie, I appreciate making it possible for me to remember my childhood.
    Thank you!

  • @zebibaanderson5107
    @zebibaanderson5107 Před 2 měsíci +6

    ተወልጀ ያደግኩት ውቧ ደሴ ከተማ ነው ይኸን ፕሮግራም ሳየው እያለቀስኩ ነው ያየሁት አገላለፅህም በጣም ምርጥ ነው ቀጥልበት በጣ ነው የማመስግንህ ወደ ኻላ በሀሳብ ነው የመለስከኝ እድሜና ጤና ይስጥህ እንዳትጠፋ ቀጥልበት የኔ ወንድም

  • @user-nt2gz5rk5h
    @user-nt2gz5rk5h Před měsícem +1

    የደሴ ትዝታ አሁንም ሀገር ስገባ. ደሴየ. ነው የምኖረው. በፍቅር ነው የምወዳት ❤❤❤❤❤

  • @EndrisHassen-wf3rv
    @EndrisHassen-wf3rv Před měsícem

    አቤት ትዝታ ይመቻችሁ አቦ የሀገሬ ልጄች ዋው አቤት ደስስስስ ሲል ትረካው ታሪኩ ሁሉንም ነገር በሚገባ ገልጻችሁልናል ። እናመሰግናለን ፣ እንዲያው ለተጨማሪ የስሬ ውሃን የውሉቆን ወረድ ብለህ ደስ ድልድይን ከዚያም የቦርከና ድልድይን ከድልድዩ ዘለው እ የገቡ ከጎርፍ የሚታደጉንን ጀግኖች ዋናተኞችን ከዚያም በቦርከና ውንዝ ከስላሴ በር በታች የያለውን መዋኛችንን ለምን እረሳሃው ወዳጀ ?

  • @user-sg1wj6jy6z
    @user-sg1wj6jy6z Před měsícem +1

    እናመሰግናለን

  • @HabibaOumer
    @HabibaOumer Před měsícem +3

    ሀጂይመርዳውግንብ አጠገብነበር ቤታችን እኘአቡከርኡመር እነአጽበሀ ጌታሁን ሀይለማርያምሞላ እኘፍቅርተስንቅኘህ እነሉላኡመር ወሎሻሂቤት ኢሌኒ ምግቤት እረ ሰንቱ

  • @user-gc3ng8sw3j
    @user-gc3ng8sw3j Před 2 měsíci +2

    ጌታ የባርክህ ሀገሬን አሰቃኘሄኝ ❤❤❤❤ሰፈሬ አሊጉሎ ሰላም ላቺ እ

  • @sarazelalem2930
    @sarazelalem2930 Před měsícem +1

    ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️👈🙏

  • @user-xj8zw8fe2o
    @user-xj8zw8fe2o Před 29 dny +1

    አይ ደሴ ተወልጄ ያደጉት የተማርኩት የተዳርኩበት ትዝታየ ሱቃችን ፒያሳ የጉራጌ ልጅ ትዝታየን ቀሰቀሰከው

    • @andinetnahusenay151
      @andinetnahusenay151  Před 29 dny

      ስለተከታተሉንና ሀሳብ ስለሰጡን እናመሰግናለን። ክፍል አንድንም በእንገር ቲዩብ play list ውስጥ ገብተው ይከታተሉ።
      እንገር...
      ሁሉም በሀገር!!

  • @endalegerma2521
    @endalegerma2521 Před měsícem +1

    ሰላም ጤና ይስጥልኝ ለዚህ ፔጅ ባለቤት ጥሩ ነበር ግን በቪዲዮ ቢሆን ደስ ይለን ነበር ስደት ላለነው ናፍቆት ስላለብን 🎉

    • @andinetnahusenay151
      @andinetnahusenay151  Před měsícem

      ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን። ቀጣይ ስራዎችን በቪዲዮ መረጃዎች የታገዙ እንዲሆኑ ጥረት እናደርጋለን።

  • @user-gc3ng8sw3j
    @user-gc3ng8sw3j Před 2 měsíci +2

    የዘወዱ እናት አድባር ነበረች አየሀገሬ

  • @zumerazuzu1717
    @zumerazuzu1717 Před měsícem +1

    አይ ትዝታ ደሴዋ እንደ ሙዚቃ ደጋግሜ የሰማሁት ነገርሰ አይ እሰኪ ደሴ የት ሰፈር ናቹሁ እኔ በርበሬ ገንዳ ከሸርፍ ተራ መዉረጃ

    • @andinetnahusenay151
      @andinetnahusenay151  Před měsícem +1

      በጣም እናመሰግናለን። ሸር በማድረግ፣ ሌሎችም ትዝታቸውን እንዲያጋሩ ስለጋበዙ ምስጋናችን ከልብ ነው! በሌሎችም ጣፋጭ ስራዎች እንገናኛለን።
      ክፍል 1ንም እንዲያደምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።

  • @Tube-ib9go
    @Tube-ib9go Před měsícem +2

    ደሴ ተቋም ቦሩ ውስጤ ነው በቅርብ አሳየን አኑረኝ ያረብ

  • @sarazelalem2930
    @sarazelalem2930 Před měsícem +1

    🙏💚💛❤️☪️✝️💚💛❤️🌍🙏

  • @ahlamalhydr9764
    @ahlamalhydr9764 Před měsícem +1

    ትምርት ቤቴ ናፍቀኝ ካቱሊክ

  • @ahlamalhydr9764
    @ahlamalhydr9764 Před měsícem +1

    ደሴውች የት ናችሁ 😢😢😢❤❤

  • @richioendrias1535
    @richioendrias1535 Před 2 měsíci +1

    wowwwwww

  • @sulimanomer7668
    @sulimanomer7668 Před měsícem +1

    Tarikawi yehonewn be video btakerbut documentary yhon neber

  • @husenibrahim6283
    @husenibrahim6283 Před 2 měsíci +1

    ❤❤❤❤

  • @Lacomanza
    @Lacomanza Před 2 měsíci +1

    ያለትራንስፓርት ከለንደን እትብቴ የተቀበረበት ደሴ ሰፈሬ መናፈሻ ስላደረስከኚ አመሰግናለሁ የሁሉ እኩል ሀገር እምየ ደሴ

    • @ayshehghanem1998
      @ayshehghanem1998 Před měsícem

      ሴት ከሆሽ ከአረብ አገርዉሰጂ ያገሬ ልጂዋ

  • @BituElias
    @BituElias Před měsícem +2

    ምነው ሰይድ በላይ ሳታነሳ የደሴ ባለሀብት ብሎ አራት ውይይት

  • @sulimanomer7668
    @sulimanomer7668 Před měsícem +1

    Tru akerareb new

  • @guenettekebede9112
    @guenettekebede9112 Před měsícem

    ❤❤❤❤❤❤❤🎉

  • @BituElias
    @BituElias Před měsícem +1

    ምነው ሰይድበላይ ሳታነሳ በለአራት ውይይት ባለሀብት

  • @awolfedlu5443
    @awolfedlu5443 Před 2 měsíci +1

    Menber tshay the former Name is “welamo sefer “ why you forget this

  • @user-kz2pt2rf5c
    @user-kz2pt2rf5c Před měsícem +2

    ስለደሴ በጥሩ ሁኔታ ገልጸኸዋል ደጃች ዮሴፍ ና ሀረጎን አብረህ በትገልጸዉ ምክኒያቱምየዱበርቲዎችአርግማነ የነ ቀ አ ገሠሠ አነ አሊሀሽም ታሪክ አብረህ ብትገልጸው ታሪኩ ሙሉ ይሆናል ብየ አምናለሁ

  • @seifukebede9824
    @seifukebede9824 Před 27 dny +1

    ሸዋ በር መስጊድ ሲነሳ ደጃች ዮሴፍ ቡና ቤት ለምን ተረሳሳሳ🤔

  • @amyjackson8185
    @amyjackson8185 Před měsícem

    Ante swoye kewokt nsa yehonk Desse yemitawswo bzihe krakenbo nwo ende dnkoro!!

    • @negasheshetu5627
      @negasheshetu5627 Před měsícem

      አንተ ተሳዳቢ የወሎ አድባር ትጠየፍህ

  • @BituElias
    @BituElias Před měsícem +1

    ምነው ሰይድ በላይ ሳታነሳ የደሴ ባለሀብት ብሎ አራት ውይይት

    • @MohammedMohammed-dm3ie
      @MohammedMohammed-dm3ie Před měsícem

      ፀሃፊው አንሷር አህመድ የራሱን ትዝታ ነው የፃፈው። በዚያ ላይ በዋናነት ግለሰቦችን ለመጥቀስ ሳይሆን ሰፈሮች እና ትዝታዎችን ለመግለጽ ታስቦ ነው