ሉዓላዊ - ዘማሪ በረከት ደጀኔ "SOVEREIGN" BEREKET DEJENE Lualawi NEW PROTESTANT AMHARIC WORSHIP SONG

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 08. 2024
  • በዚህ ዝማሬ እንደተባረካችሁ እናምናለን። ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰባችን እንድትሆኑ እኛንም እንድታበረቱን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን እንወዳችኋለን!!!
    / @ephyman78
    Song Lyrics
    Sovereign
    Through the path of life that I trail,
    Where every day I struggle and toil
    I could not understand several things and keep asking why? to whom? when? where? then what?...
    When all these things trouble my soul,
    knowing something calms me down
    Sovereign, You alone are sovereign
    Sovereign God You are Sovereign
    You are not to be asked why you did this or that
    There is none that can stand before you and ask that
    Weaver, You are the weaver of my life *2 |
    Potter, You indeed are the Potter of my life *2 |
    Those who wanted to help judged me and
    They gathered all sorts of reasons
    I was silent and became what they said I was
    When they told me it is for good,
    I said amen and stood
    When they told me this is because you trespassed
    I repented and asked for mercy of God
    When they told me it is the enemy’s dart
    I stood up to fight
    When they pointed me to human evil
    I cried out for my God’s help to prevail
    When they told me God is fixing you, be patient
    I said ok and clenched my teeth
    And stood firm and stout and strengthened my faith
    Sometimes life is like that, but God has the explanation
    Whether I understand it or not, in my life, He is sovereign
    Sometimes life is like that, but God has the explanation
    Whether I understand it or not, in my life, He is sovereign
    Sovereign, you cannot be asked for a reason
    And, You will never be asked “why” by anyone.
    ሉአላዊ
    በማልፍበት መንገድ በህይወት ጎዳና
    በየለት ውሎዬ ሳልፍ በጎንበስ ቀና
    ሊገቡኝ አልቻሉም ለምን ከዛስ እንዴት
    ለማ መቼ በማ ቀጣዩስ ወዴት
    በዚ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ
    ያረጋጋል አንድ ነገርን ማወቅ
    ሉዓላዊ ብቻህን ሉዓላዊ ነህ
    ሉዓላዊ እግ/ር ሉዓላዊ ነህ
    ሉዓላዊ ለምን እንዲ አደረክ አንተ አትባልም
    ሉዓላዊ አንተን ደርሶ ሚጠይቅ የለም
    ሸማኔው አንተ የህይወቴ ሸማኔ
    ሸክላ ሰሪው አንተ የህይወቴ ሸክላ ሰሪ
    ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ
    አሰቡ ምክንያት ሰበሰቡ
    ዝም አልኩኝ ኦሆኦሆኦሆ
    እንዳሉኝ ሆንኩኝ
    ለበጎ ነው ቢሉኝ አሜን ብዬ ጮህኩኝ
    አጥፍተሃል ቢሉኝ ማረኝ ማረኝ አልኩኝ
    ጠላት ነው ያሉኝ ለት ቆምኩኝ ለጦርነት
    የሰው ክፋት ጠቆሙኝ አድነኝ አልኩኝ ጮህኩኝ
    ሊሰራህ ነው ታገስ እሺ አልኩኝ ጥርሴን ነከስኩኝ
    እምነቴን አበረታሁ ቆምኩኝ በረታው ፀናው
    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግ/ር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው
    ሉዓላዊ (4*)
    Follow me on Instagram
    www.instagram....
    Telegram
    +971 50 301 5484
    EPHRAIM AMARE

Komentáře • 2,6K

  • @ephyman78
    @ephyman78  Před 2 lety +984

    በዚህ ዝማሬ እንደተባረካችሁ እናምናለን። ሰብስክራይብ (SUBSCRIBE) በማድረግ ቤተሰባችን እንድትሆኑ እኛንም እንድታበረቱን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን
    እንወዳችኋለን!!!

    • @marthazkmkc3596
      @marthazkmkc3596 Před 2 lety +30

      አምላኬ ይባርካችሁ! ይሄ ለብዙ ጥያቄዎች ለትውልድ መልስ ነው :: ❤

    • @tigistyidig5580
      @tigistyidig5580 Před 2 lety +10

      ተባረኩ በጣም ተባርካለሁ። ሁላችሁም♥♥♥♥

    • @rahel977
      @rahel977 Před 2 lety +5

      Tbareku ♥♥♥

    • @moliyoneseh2685
      @moliyoneseh2685 Před 2 lety +3

      Tebarekuuuuuuu❤❤❤🙏🙏🙏

    • @jesusislord9447
      @jesusislord9447 Před 2 lety +1

      I subd

  • @fraolnasir427
    @fraolnasir427 Před rokem +101

    አራተኛ ልጄ በተወለደ በሀያ ቀኑ ሲሞትብኝ እንድፅናና የረዳኝ ዝማሬ

    • @hailutulu74
      @hailutulu74 Před 5 měsíci +1

      አይዞሽ ጌታ አዋቂነው😭😭🙏

    • @user-gn1vz5cg6n
      @user-gn1vz5cg6n Před 3 měsíci

      Ayzosh😢

    • @user-pw6pi2ot6r
      @user-pw6pi2ot6r Před 3 měsíci

      AYZOH😢😢😢😢

    • @jemo5716
      @jemo5716 Před 20 dny

      እግዚአብሔር እሡ ያፅናና።አይዞ አይዞሽ የባሠ ሖድ ባር ባር ያደርጋል የእግዚአብሔር ማፅናናት ግን የዘላለም እረፍት ነዉ።እግዚአብሔር በመንፈሡ ያፅናናችሑ

  • @netnati5709
    @netnati5709 Před 2 lety +781

    ኦርቶክስ ተዋህዶ አማኝ ብሆንም ይሄ ድንቅ ዝማሬ ገዝቶኛል:: ጌታን ሚወድ ሁሉ ሊሰማውና ሊወደው ሚገባ ዝማሬ ነብስን ያድሳል:: እወዳችዋለው ፕሮቴስታንት ወንድምና እህቶቼ 💒❤️🙌🏽

    • @abebechwalelegn8388
      @abebechwalelegn8388 Před 2 lety +24

      ተባረክ ወድማችን እየሱስ አንተንም ይወድሀል ሕይወቱን ለሰጠይህ ጌታ ሕይወትህን ስጠው መዳን በሌላ በማንም የለም ከሰማይ በታችን የተሰጠን ስም እየሱስ ነው ፍርድ ሳይመጣ አምልጥ ናወደ እየሱስ

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety +1

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

    • @denekesamuel852
      @denekesamuel852 Před 2 lety +8

      እኛም እንወዳችሁሃለን! ተባረክ!

    • @mihretkebede8378
      @mihretkebede8378 Před 2 lety +4

      Blessed 🙏

    • @alemmouhamd1086
      @alemmouhamd1086 Před 2 lety +4

      ❤❤👭👬👫

  • @surakinfe9507
    @surakinfe9507 Před 2 lety +510

    ይሄንን መዝሙር የሰማሁት ለሶስት አመት ያላየሁትን አባቴን ለማየት ካለሁበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ስገባ በሁለት ቀን ልዩነት ተላለፍን 😭
    አባቴን በህይወት አጣሁት በሳምንቱ ለምን ግን እንዲህ ሆነ ብዬ በትልቅ ጥያቄ ውስጥ ሆኜ ይሄንን መዝሙር ጴንጤ ያልሆነ ልጅ ላከልኝ እውነትም ሉአላዊ ነህ አልኩኝ በጣም ምንወደውን ምንፈልገውን ነገር ለመዳሰስ አንድ እርምጃ ቀርቶ ቢነጥቀንም እግዚአብሔር የእውነት ሉአላዊ ነው🙌🙌🙌
    እግዚአብሔር ይባርክህ 🙏

    • @enkutatashmebrahtu8947
      @enkutatashmebrahtu8947 Před 2 lety +3

      Sorry for your lost, I know what is like to lose a dad

    • @kalMHe
      @kalMHe Před 2 lety +2

      May his soul rest in the heavenly peace !!

    • @shewitghebrebrhan1112
      @shewitghebrebrhan1112 Před 2 lety +1

      May The Blood of Jesus CHRIST flow in your life and heart.

    • @footballhighlights3899
      @footballhighlights3899 Před 2 lety +1

      Ayizok wendime egizaber melkam new ayiteyeqem antenim lezelalem yitebiqikal

    • @DrBahiruLegesse-SCIsurvivor
      @DrBahiruLegesse-SCIsurvivor Před 2 lety +1

      ምን ይባላል?የመጽናናት ሁሉ አምላክ መጽናናትን ይስጥ ከማለት ውጭ !

  • @selamasfaw689
    @selamasfaw689 Před 2 lety +74

    እኔየኦርቶዶክስ አማኝ ነኝ ግን ይሄ መዝሙር በጣም ነው ውስጤን የነካኝ

  • @teferaassefa8835
    @teferaassefa8835 Před 2 lety +575

    በረከትን የዛሬ ከ 13 ዓመት በፊት ባህር ዳር university poly የኢንጀነሪንግ ተማሪ እያለ ነው የማቀው ህይወቱ ይገርመኛል አውርቶ ሰብኮ ዘምሮ ሳይሆን ኑሮው ክርስቶስን የሰብካል

    • @godisgoodallthetime836
      @godisgoodallthetime836 Před 2 lety +24

      ክርስትና ማለት ኑሮ ነው እኔም በምላስ ምስክርነት ሳይሆን ህይወታቸው በሚመሰክር ወጣቶች ነው ከ 25 አመት በፊት ጌታን ያገኘሁት ክርስቶስን ለብሰው የሚመላለሱ ብዙ ናቸው ፀጋ ይብዛላቸው

    • @yemisrachababula6599
      @yemisrachababula6599 Před 2 lety +19

      ለዚህ ነው ኑሮው ክርስቶስን የሚሰብክ ስለሆነ ነው መዝሙሩ ላዳመጥነው ለሁላችንም መልስ የሆነልን

    • @godisgoodallthetime836
      @godisgoodallthetime836 Před 2 lety +13

      @@yemisrachababula6599 በትክክል እግዚአብሔር እውነተኞችን ይባርክ

    • @eyerusalemtagesse9475
      @eyerusalemtagesse9475 Před 2 lety +2

      Antes men eyeserak new ahun

    • @teferaassefa8835
      @teferaassefa8835 Před 2 lety +13

      @@eyerusalemtagesse9475 ደምፅ የለኝም ስራ ግን እሰራለሁ

  • @kedestmichael3555
    @kedestmichael3555 Před 2 lety +483

    🎤 በጣም የምወዳትን እህቴን አጥቼ ባዘንኩበት ሰአት ይህንን መዝሙር ሰው ላከልኝ እና ከማስበው በላይ ተፅናናሁበት:: ጌታ ይባርክህ::⏱

    • @deehope9477
      @deehope9477 Před 2 lety +19

      Me too! My cousin lost her precious son at age 17 & ask God why? And I just share this song for her comfort! Anyone who read this... pls pray for her & her family to be normal again!! She's broken beyond repair & God alone can fix her!! Her son should be freshmen in college this year & God chose him to be in heavenly college & Her question is Why him?? Hope, this song can minister to her and comfort her + families!! Amen 🙏

    • @ts3909
      @ts3909 Před 2 lety +2

      @@deehope9477 I just prayed for your cousin. May holy spirit comfort her and the whole family.

    • @deehope9477
      @deehope9477 Před 2 lety

      @@ts3909 so sweet, thank you!!

    • @seyoumgebraselase2703
      @seyoumgebraselase2703 Před 2 lety

      God bless you be strong

    • @elizabethsam5476
      @elizabethsam5476 Před 2 lety +1

      @@deehope9477
      Lord Jesus please comfort them in their grief and loss, cover them with your peace and presence, as only your Spirit can do. I pray in Jesus name amen & amen
      Matthew 19:26
      But Jesus looked at them and said, ‘With man this is impossible, but with God all things are possible.'

  • @Tina-wz4nl
    @Tina-wz4nl Před 2 lety +144

    "አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ሕይወት ልዑላዊ ነው!!! ❤️

  • @zelalemmengistuofficial9706
    @zelalemmengistuofficial9706 Před 2 lety +228

    ጌታ ሆይ ስለዚህ መዝሙር አመሰግናለሁ በዚህ ልጅ የጀመርከውን ስታቋርጥ ቀጥል ⛪⛪🎼✞

  • @surafelhailemariyamofficia6728

    #ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ .💎🤗ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ.. ❗️ ወዳጄ በጣም የሚባርክ ዝማሬ ነው እልፍ ሁንልኝ ፀጋው ይጨምርልህ ተባረክ🎹🎻🎺💎🎼🎬🎸🎷🥁

    • @bereketzelekedejene45
      @bereketzelekedejene45 Před 2 lety +3

      God bless u brother

    • @14nadu
      @14nadu Před 2 lety +6

      @@bereketzelekedejene45 God bless you brother. I thank the God of grace for you! Will you please share your heart behind this song? ጌታ share አድርግ ካለህ ማለት ነው! I’m curious and I’m sure it’ll bless many more people. Stay blessed 😇

    • @happygirma4759
      @happygirma4759 Před 2 lety +4

      ሱሬ አንተንም ይባርክክ ጌታ ተባርከናል በመዝሙሮቻቹ

    • @hanechohanecho7063
      @hanechohanecho7063 Před 2 lety +1

      Sura ya geta leje tebarake

    • @user-nf4dc5wh9h
      @user-nf4dc5wh9h Před 2 lety

      @@bereketzelekedejene45 PleaseCZcams lay subscribe እንደራረግ። በአማርኛ የተተሮገመ ቃለ

  • @georgeasfaw8985
    @georgeasfaw8985 Před 2 lety +1599

    በማልፍበት መንገድ በህይወት ጎዳና
    በየለት ውሎዬ ሳልፍ በጎንበስ ቀና
    ሊገቡኝ አልቻሉም ለምን ከዛስ እንዴት
    ለማ መቼ በማ ቀጣዩስ ወዴት
    በዚ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ
    ያረጋጋል አንድ ነገርን ማወቅ
    ልዋላዊ ብቻህን ልዋላዊ ነህ
    ልዋላዊ እግ/ር ልዋላዊ ነህ
    ልዋላዊ ለምን እንዲ አደረክ አንተ አትባልም
    ልዋላዊ አንተን ደርሶ ሚጠይቅ የለም
    ሸማኔው አንተ የህይወቴ ሸማኔ
    ሸክላ ሰሪው አንተ የሂወቴ ሸክላ ሰሪ
    ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ
    አሰቡ ምክንያት ሰበሰቡ
    ዝም አልኩኝ ኦሆኦሆኦሆ
    እንዳሉኝ ሆንኩኝ
    ለበጎ ነው ቢሉኝ አሜን ብዬ ጮህኩኝ
    አጥፍተሃል ቢሉኝ ማረኝ ማረኝ አልኩኝ
    ጠላት ነው ያሉኝ ለት ቆምኩኝ ለጦርነት
    የሰው ክፋት ጠቆሙኝ አድነኝ አልኩኝ ጮህኩኝ
    ሊሰራህ ነው ታገስ እሺ አልኩኝ ጥርሴን ነከስኩኝ
    እምነቴን አበረታሁ ቆምኩኝ በረታው ፀናው
    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግ/ር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ልዋላዊ ነው
    ልዋላዊ (4*)

  • @AbeniAbenu
    @AbeniAbenu Před 6 měsíci +22

    በጣም ውጣ ውረድ ውስጥ ነኝ ግን እግዚያብሄር ሉዓላዊ ነው አሜን

  • @dawitmercy5428
    @dawitmercy5428 Před 2 lety +122

    በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዳልና።John3፡16

  • @dinadhuga4418
    @dinadhuga4418 Před 2 lety +313

    በጣም በከፋኝ ሰዓት ነበር ይህን መዝሙር የሰማውት እጅግ በጣም ደስ አለኝ ተፀረናናውም
    ተባረኩ!

    • @belaymola6186
      @belaymola6186 Před 2 lety

      Me too

    • @user-gf8bj5ij1g
      @user-gf8bj5ij1g Před 2 lety +2

      እኔም በጣም ልቤ ባዘነ ሰአት ከግራ ቀኝ ግራ ስጋባ ጌታ ይባረክ ተባረኩ

    • @yetnayettesfa7663
      @yetnayettesfa7663 Před 2 lety +1

      Emem betam gra begeban gize ....yenen yalehubetn new yezemerewu

    • @sarasari7184
      @sarasari7184 Před 2 lety

      Same here

    • @beimnetnegash6169
      @beimnetnegash6169 Před 2 lety +1

      እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤
      መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤
      የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣
      ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም (ኤሎሂም) እርሱ ነው። ዘዳ 32:4

  • @maye.e6611
    @maye.e6611 Před 2 lety +268

    ድካማችንን ያየ አምላክ የምንፅናናበትንና የምንበረታበትን መዝሙሮች እያፈሰሰልን ነው
    ቤኪ ተባረክልን😘😘😘

    • @eskenderkadir1099
      @eskenderkadir1099 Před 2 lety +2

      ኦ በጣም🙏 ቀኔን አስተካከለልኝ። ሉአላዊ ጌታ!

    • @maye.e6611
      @maye.e6611 Před 2 lety +2

      @@eskenderkadir1099 እውነት ከባድ ሁኔታ ላይ ሆኜ ነበር ለመጀመሪያ ያዳመጥኩት የሚገርመው ሁሉን ነው ያስረሳኝ።

    • @eskenderkadir1099
      @eskenderkadir1099 Před 2 lety +3

      @@maye.e6611 እይዞሽ፤በእግዚአብሔር መገኘቱ ውስጥ ስንሆን ሁሉን እንረሳለን።ይህ ዝማሬም በእውነት ድንቅ ነው።ለብዙዎቻችን መፅናናትን ሰጥተዋል እና።

    • @hannajesus5594
      @hannajesus5594 Před 2 lety

      😭❤

  • @delinatesfay1857
    @delinatesfay1857 Před 2 lety +151

    I'm Eritrean i don't know Amharic language but I can't stop listening, coz i feel blessing. May God bless you all 💖💖💖

    • @godislovellove3611
      @godislovellove3611 Před rokem +3

      """Lualawi""" mens olmaytee God. yes Very nice Song

    • @abebechkinduabebechkindu136
      @abebechkinduabebechkindu136 Před rokem

      Amen you too bless

    • @godisalmighty8896
      @godisalmighty8896 Před rokem +11

      ንስኻ ኣብ ህይወተይ ልዑላዊ ኢኻ
      ኣብ ህይወተይ ሰራሒ ኢኻ
      ሓደ ሓደ ግዜ ህይወት ከምዚ'ያ መልሲ ግን ምስ እግዚኣብሄር' ዩ ይረዳኣኒ ኣይረዳኣኒ
      ኣብ ህይወተይ ልኡላዊ ኢኻ እግዚኣብሄር

    • @delinatesfay1857
      @delinatesfay1857 Před rokem +1

      @@godisalmighty8896 amennnn thank u tebareki

    • @godisalmighty8896
      @godisalmighty8896 Před rokem

      ኣሜን ብርኽቲ

  • @SirakDesta
    @SirakDesta Před 2 měsíci +5

    ብዙ ጊዜ የሰማሁት ቢሆንም ዛሬ ግን ስለ ዘሪቱ ልጅ ሳስብ😢😢 ለማፅናናት ብዬ ........

    • @hangma8983
      @hangma8983 Před 2 měsíci +1

      የሚገርም ነው እንኔም ወደ ውስጤ ዘሪቱ ነች የመጣችው

  • @yetenayet812
    @yetenayet812 Před 2 lety +918

    የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ መዝሙሩን መስማት ማቆም አልቻልኩም ልቤን ያፅናናልኝ መዝሙር ነው የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ይባርክህ ወንድሜ

    • @eyerusalemtagesse9475
      @eyerusalemtagesse9475 Před 2 lety +26

      Ye Egzihabeher Lij Eyesus Yibarek!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    • @eyerusalemtagesse9475
      @eyerusalemtagesse9475 Před 2 lety +16

      Ye Egzihabeher Lij Eyesus Yibarek!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    • @azruabtubabebe1266
      @azruabtubabebe1266 Před 2 lety +46

      የእግዚአብሔር ልጁ ይባረክ ኦርቶዶክስ ለምንድነው የእግዚአብሔር ልጁ ማለት የምትፈሩት

    • @ambassadorofchrist6372
      @ambassadorofchrist6372 Před 2 lety +6

      Eyesus yadinal

    • @selamtesfaye7108
      @selamtesfaye7108 Před 2 lety +39

      እሰይ እንኳን ተፅናናሽበት አሁንም እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርክሽ

  • @olly.k
    @olly.k Před 2 lety +40

    ህይወት ቁልቁል ስትጥልህ እግዚአብሔርን ለምን ሳይሆን ሉዓላዊ ነው ሚባለው🙏🙏🙏🙏🥺

  • @abeb2342
    @abeb2342 Před 2 lety +34

    እንደገና የልጅነት ጌታዬን እንድናፍቀው ያደረገኝ መዝሙር ነው. ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነበርኩ እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ አብልጦ የጎዳኝ መስሎ እየተሰማኝ ነበር . ይህ የማልፍበት መንገድ የኔ ብቻ መስሎኝ ለምን እያልኩ ከእግዚአብሔር ጋር እየተከራከርኩ ነበር ለካ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ወንድሜ አንተም ጠጥተህዋል 😭😭😭

  • @pazalex9139
    @pazalex9139 Před 2 lety +289

    I'm Orthodox Christian, but I love this spiritual song ❤ May God bless you more and more my brother 🙏 ❤

  • @hellotiktok9600
    @hellotiktok9600 Před 2 lety +659

    እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን በጣም ነው የወደድኩት ሁሌ ነው ምሰማው ተባረኩልኝ ❤❤❤

    • @seyoumgebraselase2703
      @seyoumgebraselase2703 Před 2 lety +8

      Blessings

    • @user-zx2ch1bp3n
      @user-zx2ch1bp3n Před 2 lety +46

      ወንድሜ የእግዚአብሔርን ሉአላዊነት ተረድቶ ለማመስገን የሀይማኖት ስያሜ ቦታ የለውም ነፍስህ ከገባት በእውነት ብቻ አመስግነው

    • @user-yi1gb1ub6z
      @user-yi1gb1ub6z Před 2 lety +30

      Christianity is not religion. It is life.

    • @senaityohannes1957
      @senaityohannes1957 Před 2 lety +24

      ሃይማኖት አያድንም ማመን በክርስቶስ ከሓጥያት ሁሉ ነጻ ያውጣል እግዛብሄር ሉአላዊ ነው ብቻውን ያድናል ይታደጋል አምልጥ

    • @yabebala
      @yabebala Před 2 lety +7

      የግሪክ ወይስ የራሺያ ኦርቶዶክስ? እንዲህ ያለ መዝረክረክ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዘንድ የለም።

  • @astersamuel6513
    @astersamuel6513 Před 2 lety +310

    የአመቱ መጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ሰኞ ቀን የሰማሁትና የተባረኩበት መዝሙር ኡፍፍፍ!"ሉዓላዊ ነህ ብቻህን እግዚአብሔር አሜን!!

    • @fifishiferawe2051
      @fifishiferawe2051 Před 2 lety

      Amen

    • @tizitagirma2447
      @tizitagirma2447 Před 2 lety

      Yessss geta ybarkachu🙏❤️

    • @adiesberihun767
      @adiesberihun767 Před 2 lety

      @@tizitagirma2447 llllllll

    • @Baslel
      @Baslel Před 2 lety

      በእርግጥ እግዚአብሔር ሉዓላዊ አምላክ ነው። ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ!

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @BrookMereja
    @BrookMereja Před 2 lety +373

    በጣም በከፋኝ በዚህ ሰዓት ይህ መዝሙር አሁን አገኘሁ!! በመጽናናት መንፈስ አልቅሼ ልሞት ነው 🥺😭😭😭 አባቴ እግዚአብሔር ይባርክህ ወዳጄ 🙏🙏🙏

    • @habeshamollethiopia5826
      @habeshamollethiopia5826 Před 2 lety +9

      Ayzon bro fetari ale

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety +2

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

    • @jh2500
      @jh2500 Před 2 lety +4

      Ayzoh wendeme egziyabher melkam new🙏

    • @ethiosolomon3315
      @ethiosolomon3315 Před 2 lety +4

      Yalfal ayzohe.

    • @aregaayalew215
      @aregaayalew215 Před 2 lety +5

      እኔም በአንተ አይነት ስሜት ውስጥ ነበርኩ አና የሚገርም መፁናናት ነው የሆነኝ አግዚአብሔር ዘመኑንይባሬክ

  • @solomonmersha4892
    @solomonmersha4892 Před 2 lety +62

    ይህ ድንቅ መዝሙር የዘማሪው የሕይወት ገጠመኝ ብቻ ሳይሆን የሃገራችን ፍቺ ያጣ እንቆቅልሽ ጉዞ ቅኔ ነው:: አዎ በኢትዮጵያ ላይ ሉዓላዊ ነው ::

  • @Binyamyonas
    @Binyamyonas Před 2 lety +385

    በጣም እጅግ በጣም ነው የተባረኩበት 🙏 ደግሞ ስሰማው ግጥም እና ዜማ ብቻ እንዳልሆነ ገብቶኝ ነበር በሰማሁት በነጋታው surprisingly አጋጣሚ በሚመስል ለእኔ በሚገባኝ መንገድ ጌታ ከዘማሪው ጋር አገናኘኝ ያለፈበትን አጫወተኝ እጄን በአፌ ጭኜ የአምላኬን ሉአላዊነቱን ከማሰብ ውጭ ምንም አልልም። ፀጋ እና ምህረት ይጨመርልህ ወንድሜ።
    ኢዮብ 40
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ¹ እግዚአብሔርም መለሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው፦
    ² በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።
    ³ ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦
    ⁴ እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፤ የምመልስልህ ምንድር ነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።
    ⁵ አንድ ጊዜ ተናገርሁ፥ አልመልስምም፤ ሁለተኛ ጊዜም፥ ከእንግዲህ ወዲህ አልናገርም።
    እንዴት የሚባርክ ዝማሬ ነው 🙏

  • @mulukeneasrat1387
    @mulukeneasrat1387 Před 2 lety +34

    ይህ የክርስትና ትልቅ እውነት ነው እርሱ ብቻውን ሉዓላዊ መሆን ነው ። ተባረኩ

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @Alex-zq2hs
    @Alex-zq2hs Před 2 lety +110

    ይሄ መዝሙር ብቻ አይደለም በዚህ የምድሩን ነገር ላይ የሚያተኩሩ አገልጋዮች በበዙበት ዘመን የጌታን ልዑአላዊነት እንድናስብ የሚያሳስብም ስብከትም ጭምር ነው። ያብዛልህ በብዙ ተባረኩ ።

  • @ashenafizeleke54
    @ashenafizeleke54 Před rokem +7

    እኔ የአኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ መዝሙሩ እጅግ ልብ የሚነካ ነው ሁሉም ፐሮቴስታንት እንዲህ ጠንካራ መልእክት ያለው ረጋ ያለ ዝማሬ ቢዘምር መልካም ነው እላለሁ

  • @juliateka
    @juliateka Před 2 lety +107

    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው መልሱ እግዚአብሔር ጋር ነው ቢገባኝም ባይገባኝም በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው አሜን ጌታ ፀጋውን ያብዛላቹ!

  • @sarawolde2126
    @sarawolde2126 Před 2 lety +253

    ከህይወት የተቆረሰ ዝማሬ...can't stop listening❤

    • @Dani-Harer
      @Dani-Harer Před 2 lety +2

      ለዛውም ከእዮብ 👌

    • @user-nf4dc5wh9h
      @user-nf4dc5wh9h Před 2 lety

      በአማርኛ የተተሮገመ ቃለ ምልልስ CZcams lay subscribe እንደራረግ። salha እና ሌሎችም በጣም አስቂኝ

    • @misrakhora1778
      @misrakhora1778 Před 2 lety +1

      Galseshewal bedenb tebareki

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

    • @mestewatbekele1499
      @mestewatbekele1499 Před 2 lety +1

      ግልጽና የጊዜው መዝሙር ነው:: ጸጋና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይብዛልህ::

  • @mussie5576
    @mussie5576 Před 2 lety +10

    በህይወቴ በጣም ከባድ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሳለሁ ነው ይህን መዝሙር የሰማሁት ፤ ሰዎች ለማልፍበት ችግር ምክንያቱ፦
    - ለበጎ ነው ብለውኛል
    - ንስሃ ግባ ብለውኛል
    - የጠላት ፈተና ነው ብለውኛል
    - በሰው ክፋት ተደግሞብህ ነው ብለውኛል
    - አይዞህ ሊሰራህ ነው ታገስ ብለውኛል።
    በዚህ ሁሉ ግን እግዚዓብሔር ብቻውን ሉዓላዊ ነው!

  • @deborahabraham7283
    @deborahabraham7283 Před 2 lety +39

    እኝኝ ከማለት እግዚአብሔር ላይ ከማጉረምረም የሚገላግል መዝሙር ነው ። ኡፍፍፍፍ ይሄ መዝሙር አሳረፈኝ ተባረክ ወንድሜ እንዳንተ አይነቱን አሁንም እግዚአብሔር ያብዛልን!!!

  • @amiireborn5909
    @amiireborn5909 Před 2 lety +199

    I can't stop listening and I can't even control my tears😭😭😭 Stay Blessed #Bekye!
    "አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ #እግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት #ሉዓላዊ ነው "

    • @abebaseyum8637
      @abebaseyum8637 Před 2 lety +4

      I can't stop listening God bless you

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety +1

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

    • @natsinetgirmay7451
      @natsinetgirmay7451 Před 2 lety +1

      Yeah same here😭😭😭😭couldn't control it ...more and more grace up on U Bereket bro blessings 🙏

  • @bayushabaya1391
    @bayushabaya1391 Před 2 lety +15

    በማልፍበት መንገድ በህይወት ጎዳና
    በየ ዕለተ ውሎዬ ሳልፍ ጎንበስ ቀና
    ሊገቡኝ አልቻሉም ለምን ከዚያስ እንዴት
    ለማን መቼ በማን ቀጣዩስ ወዴት
    በዚህ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ
    ያረጋጋል አንድ ነገር ማወቅ
    ሉዓላዊ ብቻህን ሉዓላዊ ነህ
    ሉዓላዊ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነህ
    ሉዓላዊ ለምን አንዲህ አደረግህ አንተ አትባልም
    ሉዓላዊ አንተን ደርሶ የሚጠይቅ የለም
    ሸማኔ አንተ የህይወቴ ሸማኔ /*2
    ሸክላ ሰሪ አንተ የህይወቴ ሸክላ ሰሪ /*2
    ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ
    አሰቡ ምክንያት ሰበሰቡ
    ዝም አልኩኝ ........
    እንዳሉኝ ሆንኩኝ .......
    ለበጎ ነው ቢሉኝ... አሜን ብዬ ቆሙኩኝ
    አጥፍተሀል ቢሉኝ... ማረኝ ማረኝ አልኩኝ
    ጠላት ነው ያሉኝ ዕለት...ቆምኩኝ ለጦርነት
    የሰው ክፋት ጠቆሙኝ..አድነኝ አልኩ ጮህኩኝ
    ሊሰራ ነው ታገስ..እሺ አልኩኝ ጥርሴን ነከስኩ
    ዕምነቴን አበረታሁ..ቆምኩኝ በረታሁ ፀናሁ
    አንዳንዴ ህይወት አንዲህ ነው
    መልሱ አግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው

  • @kidutsega6272
    @kidutsega6272 Před 2 lety +14

    እጅግ በጣም በተከፋሁበት ግራ በገባኝ ሰዓት ነበር ያዳመጥኩት የእውነት ተፅናናሁበት በእርግጥ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን በመዝሙሩ ተፅናናው በረታው ተባረክ

  • @GM-zu6hy
    @GM-zu6hy Před 2 lety +66

    አሜን ብቻውን ሉአላዊ ሆኖ የሚኖር ጌታ:: ድንቅ ዝማሬ ፀጋ ይብዛላችሁ፡፡

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @abigiaayele269
    @abigiaayele269 Před 2 lety +21

    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግ/ር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ልዋላዊ ነው

  • @selamebegetamulunawe
    @selamebegetamulunawe Před 2 lety +38

    ይሄ የሂወት ጭማቂ መንፈሳዊ ጁስ መሆኑ በፈውሱ ያስታውቃል እንዲህ የሂወት ጭማቂ የሆኑ ዝማሪዎችን የሚያሰሙንን ጌታ ይስጠን

  • @Mimi-ex4si
    @Mimi-ex4si Před 2 lety +24

    ልቤ ሀዘን ተስፋ መቁረጥ በሞላበት ወቅት ይሄን መዝሙር ሰምቼ ውስጤ በእምነት ተሞላ 🙏እግዚአብሔር ሆይ በምድራችን ላይ አንተ አሁንም ሉአላዊ ነህ አስበን 🇪🇹🙏

  • @abeniezersileshi8094
    @abeniezersileshi8094 Před 2 lety +7

    ሸማኔ
    አንተ የህይወቴ ሸማኔ(2*)❤
    ሸክላ ሰሪ
    አንተ የህይወቴ ሸክላ ሰሪ(2*)❤

  • @israelelnathan6435
    @israelelnathan6435 Před 2 lety +29

    በእሳት ውስጥ እያለፍኩ ነው😭😭 አምላኬ ግን ሉዓላዊ ነው የሚያደርገውን ያውቃል!!! ስሙ ይክበር!!!!

  • @amennetsanet7492
    @amennetsanet7492 Před 2 lety +265

    የናፈቀኝ እንደዚህ አይነት መዝሙር ነበር ወንድሜ እግዚአብሄር ይባርክህ ዘመንህን ሁሉ እግዚአብሄርን በመስማት ተቀኝለት!!!!!

  • @denekesamuel852
    @denekesamuel852 Před 2 lety +9

    ምገልጽበት ቃላት የለኝም! አደሰኝ፣ አበረታኝ፣ አጽናናኝ፣....!

  • @saraalbalooshi1346
    @saraalbalooshi1346 Před 2 lety +11

    ልቤ ነካኝ እግዚአብሔር ሉአላዊ ነው በሕወቴ የበሆነው ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ ሉላዊ ❤️❤️

  • @michaelberhanu245
    @michaelberhanu245 Před 2 lety +197

    I hope other singers learn from this song, this song is all about the Almighty God💙💙💙

    • @Eyerusalem_
      @Eyerusalem_ Před 2 lety

      Amen

    • @user-nf4dc5wh9h
      @user-nf4dc5wh9h Před 2 lety

      CZcams lay subscribe እንደራረግ።

    • @manuheyohannes655
      @manuheyohannes655 Před 2 lety

      በእኔ

    • @senaityimam142
      @senaityimam142 Před 2 lety

      Yesss glorifying God..

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @mahidernunu7283
    @mahidernunu7283 Před 2 lety +18

    ሁሌ የሚደመጥ የማይሰላች ትልቅ መልእክት ተባረክ

  • @CHERNETURAGO
    @CHERNETURAGO Před 2 lety +9

    በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆኖ መዘመር እንደሚቻል መንፈሴን አነሳስቶታል ተባረክ በጌታ ወንድሜ ቤኪ

  • @user-je2od2mh3e
    @user-je2od2mh3e Před 2 lety +79

    የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ነኝ ይህን መዝሙር ስሰማ እጅግ በጣም ተጽናናው በቃ እግዚአብሔር በእኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው አልኩኝ

    • @tgjesustg2611
      @tgjesustg2611 Před 2 lety +1

      Ayzon Igziabiher melkam new.hulum le melkam.Yesus hulun negar weda melkam yikayiral

    • @user-je2od2mh3e
      @user-je2od2mh3e Před 2 lety

      @@tgjesustg2611 አሜን!

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @hannyzeleke4954
    @hannyzeleke4954 Před 2 lety +172

    This is my story ☺️ I can’t stop listening bless u🙌🙌

  • @enanuabate
    @enanuabate Před 7 měsíci +6

    እግዚአብሔር መልካም ነው እኔም ከዚህ የልጄን 😂 ሀዘንበመልካምነቱ እጽናናለሁ እየሱስ ጌታ ነው❤

  • @meserethaile291
    @meserethaile291 Před 2 lety +6

    ጌታሆይ ልዋላዊ ነህ ወደድሁህ እንደገና እገዛልሀለሁ

  • @netsanetshamebo2324
    @netsanetshamebo2324 Před 2 lety +11

    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግ/ር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ልዋላዊ ነው
    ሸማኔ አንተ የህይወቴ ሸማኔ
    ❤️❤️❤️

  • @bereketgetachew6810
    @bereketgetachew6810 Před 2 lety +15

    አዎ እግዚአብሔር ሉዋላዊ ነው። በትክክል ማንም እሱን ሊጠይቀው የተገባው የለም። እሱ እንደፈቀደ ይሆናል። አሜን

  • @loveyou7562
    @loveyou7562 Před 2 lety +3

    ይህየኔም ታሪክነው! !!!!!!ግንሁሌም ጌታዬን እጠብቃለሁ ምክንያቱም እኔን የሰራኝ "ሉአላዊው እግዚአብሔር ነው" ሌላውጭማሪነው! !!!!!ጠላታችሁን አትስሙ
    እግዚአብሔር አይዋሽም!!!
    አንድነገር አውቃለሁ
    አሁንም እግዚአብሔር ንእጠብቃለሁ
    አይቀርም አያረፍድም
    እሱሰውአይደለም
    ክፉ እዲህይላል ሲለውእደዚያ
    እያመጣ ያሳያልየሱንማባበያ
    እኔግንእላለሁ ለጠላቴ አረ ወዲያ
    ለኔየማይሆንይቅርብኝ ከየሱስወዲያ
    ያስጨነከኝ ያስጣልከኝከህይወቴ
    ስትመርጥነው ጥሩውን ውዱአባቴ
    በቃ ምንእላለሁ የቀረብኝ
    የማይጠቅመኝ
    የሆነልኝያሰብክልኝ
    የሰጠከኝለክብርነው
    ለኔደግሞለጥቅሜነው
    ምፈልገውብዙነበር
    የተሰጠኝጥቂትነገር
    ይሄንጌታ ያውቅነበር
    በዚህሁሉውስጥጌታ ልክነበር
    በማይጥመው ውስጥየሚጥመውየእየሱስነ

  • @wosengetachew8634
    @wosengetachew8634 Před 2 lety +14

    የአመቱ ምርጥ ሰማያዊ ዝማሬ

  • @kidistmathewos2123
    @kidistmathewos2123 Před 2 lety +85

    አማኝ ያለፈበትን የኖረውን ሲዘምር እውነታን እና ተኖረ ኑሮን ስለዘመረ የሰው ልብውስጥ አለመግባት አይችልም:: ይህ ዝማሬ በውስጤ ለሚመላለሰው ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው:: ብዙ ፀጋ ይጨመርልህ ወንድም ቤኪሻ::😄😇

    • @selamawitchanyalew2688
      @selamawitchanyalew2688 Před 2 lety +1

      ጌታ እየሱስ ዘመንህን ይባርክ
      በዚ መዝሙር በብዙ ተፀናንቼበታለው

  • @godisgood2164
    @godisgood2164 Před 2 lety +74

    ይህን መዝሙር ከሰማሁበት ቀን ጀምሮ ደጋግሜ መስማት ማቆም አቃተኝ ውስጤን እያረሰረሰ ፊቴን በእንባ ያርሰዋል 😇🙏🏽
    ሉዓላዊ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው......🙏🏽😇❤️

  • @netsanetgenetu7992
    @netsanetgenetu7992 Před 2 lety +13

    ተባረኩ ሂወትን የሚያንፅ መዝሙር ነው ፡፡

  • @abenezermekonnen5913
    @abenezermekonnen5913 Před 2 lety +1

    Besemaw besemaw yenayselech mezmur nw tebarek beheywetachn menm bigetmen Egziabher lualawi nw endihu endezemerk zemenh be betu yeleq kezi bebelete kebr agelgel tebarek zemenh yelemlem

  • @soltel1156
    @soltel1156 Před 2 lety +26

    ይህን ነው እኮ እምለው! ኢሳይያስ+ሕዝቅኤል+ አንድ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ+ ሥርዓታዊ ነገረ መለኮት = ክርስቲያናዊ አስተምህሮ በመዝሙር ... ጸሎቴ እነሆ "አቤቱ አምላኬ ሆይ ዐይኖቼ በዚህ መዝሙር ሲሰገድ እንጂ ሲዘለል እንዳያዩ ጠብቃቸው!" አሜን እንበል

  • @abyssinia5026
    @abyssinia5026 Před 2 lety +10

    ነብስም አልቀረልኝ መንፈስ የሞላበት ድንቅ ዝማሬ ነው

  • @meskermlaqew3190
    @meskermlaqew3190 Před 2 lety +5

    አንዳንዴ ህይወት እንድህ ነዉ ቢገባ ኝም ባይገኝም እግዚብሔር ለአላዊ ብቻህን ለአላዊ

  • @tikdemlegesse3405
    @tikdemlegesse3405 Před 2 lety +3

    Halaluyaaaa halaluyaaaa halalluyahhh aba ante bechu lwalaweiii

  • @kukuayalew1876
    @kukuayalew1876 Před 2 lety +32

    ቃላት የለኝም ለዚ መዝሙር ጌታ በብዙ ይባርካችሁ ከዚ መዝሙር መውጣት አልቻልኩም 🙏🙏🙏

  • @bereketdejene4172
    @bereketdejene4172 Před 2 lety +11

    አንዳንዴ ህይወት እንዲ ነው
    መልሱ እግዚአብሄር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው፡፡

  • @user-hr3he1ln7f
    @user-hr3he1ln7f Před 11 měsíci

    በሆነብንና ባጣነው ሁሉ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው ቢያመንም

  • @firaolteklu
    @firaolteklu Před 2 lety +2

    wow tebarekulin.

  • @elijahelisha3808
    @elijahelisha3808 Před 2 lety +25

    "እኔ ብቻ አምላክ ነኝ።"
    ስነመለኮትን በዝማሬ ከመማር በላይ ምን ያስደስታል።
    ብዙ ስለ እኛ ዘምረን ዝገን ነበር። አሁን እውነተኛው ዝማሬ እየተመለሰ ይመስላል። ያቆይልህ። ከብልፅግና ወንጌል አስተማሪዎች እና ዘማሪያን ራቅ። ብቻህን መጣህ እንዲሁ ቀጥል እባክህ አትነካካቸው።

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      Thank you for listening to this song. You can find more of the singer's songs on his personal you tube channel. czcams.com/users/BereketDejeneofficial. Please like, subscribe and share his channel to get more of his future songs and also bless his family. God bless you all!!

    • @grace12127
      @grace12127 Před 2 lety

      በትክክል ወንድሜ

  • @askalemulisa9827
    @askalemulisa9827 Před 2 lety +10

    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ #እግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት #ሉዓላዊ ነው

  • @shalomwub9532
    @shalomwub9532 Před 2 lety +5

    ኦኦኦኦኦ እውነት ሲዘመርም ሲሰበክም ነፃ ያወጣል ተባረክ ያብዛልህ የማይጠገብ ሆነብኝ ።

  • @tigistdegife82
    @tigistdegife82 Před 2 lety +20

    ቤኪ ጌታዬ ያብዛልህ ።ከነ ልጆቼ በዚህ ዝማሬ ተባርኬበታለሁ ሰምቼዉ ደጋግሜ ልጠግበዉ አልቻልኩም የምወድህ ልጄ።

  • @seblewongelbishaw7766
    @seblewongelbishaw7766 Před 2 lety +8

    እውነት ነው አንተ ሉአላዊ ነህ። የሚያረጋጋ ሉአላዊ መሆንህን ማወቅ ነው እንጂ ሀብት፣ እውቀት፣ ዘመድ አይደለም!!!
    ዘመንህ ይባረክ።

  • @Mahimahi-tp2vx
    @Mahimahi-tp2vx Před 2 lety +20

    ምን አይነት ተአምር ነው የሰማሁት በእውነት ቃላት የለኝም ጌታ በብዙ የብዙዎችን ልብ አፆናና

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @ahemedsiraj2382
    @ahemedsiraj2382 Před 2 lety +7

    ሉአላዊ ተባረክ ድንቅ ዝማሬ

  • @shewayegelashe682
    @shewayegelashe682 Před 2 lety +2

    dnk nw Geta gena lbzu hizb yakomachwal zemenachihu yibarek etselylachihalhu Geta yiredagnal tebareku yabate brukanoch ewdachihualhu

  • @tesfalemdemissie5135
    @tesfalemdemissie5135 Před 2 lety +42

    አንዳንዴ ህይወት እንዲ ነው ፤መልሱ ግን እግዚአብሔር ጋር ነው ። ቢገባኝም ባይገባኝም እግዚአብሔር በእኔ ህይወት ሉአላዊ ነው ። Can't get enough of this song(see big picture of the message). Stay blessed

  • @kalkidanfeleke2870
    @kalkidanfeleke2870 Před 2 lety +23

    መስማት አጀመሮኩ ቀን አንስቶ ለማቆም ነው የተቸገርኩት ጌታ ኢየሱስ ዘመናችሁን ይባርክ❤❤❤

  • @theone-fh9mx
    @theone-fh9mx Před 2 lety +4

    አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በኔ ህይወት ሉዓላዊ ነው

  • @SA-vh2gv
    @SA-vh2gv Před rokem +1

    በማልፍበት መንገድ በሂወት ጎዳና
    በየለት ውሎዬ ስልፍበት ጎንብስ ቀና
    ሊገበኝ አልቻሉም ለኔ
    ከዛስ እንዳት ለማ መቼ በማን
    ቀጥዩስ ወዳት
    በዚህ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ
    ያረጋጋል አንድ ነገር ማወቅ
    ልዋላዊ ብቻህን ለዋላዊ ነህ
    ልዋላዊ እግዚአብሔር ልዋላዊ ነህ
    ሸማኔ አንተ የሁወቴ ሸማኔ(2)
    ሸክላ ሰሪ አንተ የሂወቴ ሸክላ ሰሪ(2)
    አንዳንድ ሂወት እንዲ ነው
    መልሱ እግዚአብሔር ጋር ነው
    ቢገባንም ባይገባኝም
    በኔ ሂወት ለዋላዊ ነው
    ልዋላዊ ብቻህን ልዋላዊ ነህ
    ልዋላዊ እግዚአብሔር ልዋላዊ ነህ
    ልዋላዊ አንተን ደርሶ እሚጠይክ የለም
    ልዋላዊ ለምን እንዱ አደረክ አትባልም

  • @cecew.2559
    @cecew.2559 Před 2 lety +31

    ተሰምቶ የማይጠገብ መዝሙር ነዉ!💖

  • @RahelAHafa-nx2on
    @RahelAHafa-nx2on Před 2 lety +52

    ''ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ.....'' that is exactly what happens sometimes. God bless you all it is amazing song.

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety

      You will find this song on Bereket Dejene official channel with the lyrics. If you want to get his songs directly visit his channel, like, subscribe and share. God bless! czcams.com/video/sfsMhNy3gLo/video.html

  • @betitube1100
    @betitube1100 Před 2 lety +5

    እውነት ብናገር በጣም ደጋግሜ ነው የሚሰማው ግን ውስጤ አልረከ አለኝ ኡኡ😭😭 ይሄንን መዝሙር ከሰማሁት በኋላ በእግዚአብሔር ላይ መግሮምሮም ተውኩኝ ከዚያ በኋላ በፕሮፋይሎቼ ላይ ብቻህን ሉዓላዊ ነው ብዬ መለጠፍ ጀመርኩ ከዚያ በኋላ ሕይወቴ መስተካከል ጀመረ ክብር ለጌታ ይሁን ድንቅ ዝማሬ ነው ዘማሪ ደጄ ዘመንህ ይባረክ ለእኔ ብቻ የተዘማረ መዝሙር ነው የመሰለኝ ኡኡኡፉፉፉፉፉ💪💪💪💪💪💪

  • @mekdesmekuria4207
    @mekdesmekuria4207 Před 2 lety +4

    መስማት ማቆም አልቻልኩም አሜን እግዚአብሔር ብቻ ሉዓላዊ የኔ ጌታ።

  • @philemonhailu2141
    @philemonhailu2141 Před 2 lety +18

    ይገርማል! ምን አይነት የመገለጥ አምልኮ ነው። ልክ ልካችንን የነብሳችንን እና የህይወታችንን ብቸኛ ገዢ በግልፅ የተነገርንበት እና ክብር ለእግዚአብሔር የታወጀበት አምልኮ በአምላኪያን @ ቤኪ ብዛልን!!!

  • @tsegayohannes5857
    @tsegayohannes5857 Před 2 lety +43

    እውነትና መንፈስ ያለበት ድንቅ መዝሙር ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ🔥❤

  • @menberebirhandemissie9771

    ጌታኢዪሱስጅማሬውንእንዳሳመርልህ መጨረሻውንም ያሳምርልህ!! ዘመንህ ! ዘርህ ይባረክ!!!!

  • @wendesenmaru280
    @wendesenmaru280 Před 2 lety +2

    Ena mUslim negh gen mezmuru betam des selemel amen beya zemeralew lualawi lualawi

  • @aynalemderbe3256
    @aynalemderbe3256 Před 2 lety +14

    አሜን ለእኔ ይህ መዝሙር ልዩ ነው የተጻናናዉባት ነዉ እግዚአብሔር ሉዓለዊ ነው አዎ ነው መስከረም 1 ይሁን መዝሙር ሰመዉ ግን መስከረም 4 ዉድ የወንድሜን መሞት ሰመዉ ግን በዝ ሁሉ እግዚአብሔር ሉዓለዊ ነዉ እስከ ዛሬ እየተባረኩ ነዉ ዘሬ ቀን መስከረም 21 ነው እግዚአብሔር መልካም ነው ወሩን በሙሉ በዝ መዝሙር ዋዉ እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ!!🙏🙏

    • @peace4allc
      @peace4allc Před 2 lety +1

      Thank you for listening to this song. You can find more of the singer's songs on his personal you tube channel. czcams.com/users/BereketDejeneofficial. Please like, subscribe and share his channel to get more of his future songs and also bless his family. God bless you all!!

  • @sendukasaya1266
    @sendukasaya1266 Před 3 lety +5

    የህይወት ምንጭ ቤተሰቦች ዘማሪዎች ብሩካን ናቹ ፀጋ ይብዛላቹ በረከት የዝማሬ ምንጭ ይፍለቅ ከውስጥህ አሁንም ይብዛልህ

  • @eshitube1153
    @eshitube1153 Před rokem +2


    አንድ ጓደኛዬ ለማጽናናት በሚከብድ ነገር ውስጥ እያለፈ ነው፡፡ የማፅናናበት ቃላት ስላጣሁ ይሄንን መዝሙር ላኩለትና እኔም መስማት ጀመርኩ ይሄው ማቆም አልቻልኩም፡፡ ሉዓላዊነቱን መረዳት ያሳርፋል፡፡ አሜን ጌታ ሆይ አንተ ሉዓላዊ ነህ፡፡ ነፍሴን በዚህ መረዳት አጥምቃት፡፡ ይሄ ሲገባት ታሳርፈኛለች፡፡ የኔ ጌታ እውነትም ሉዓላዊ ነህ፡፡ ለዚህ ወንድም ይሄንን መረዳት ስለሰጠህው ስምህ ይባረክ፡፡

  • @ayicheshtesfaye6067
    @ayicheshtesfaye6067 Před 2 měsíci

    "አንድ አንዴ ሕይወት እንዲ ነው መልሱ እግዚያብሄር ጋር ነው መልሱ ቢገባኝም ባይገባኝም በኔ ሕይወት ሉአላዊ ነው ። 🙏 እርሱ ያክብርህ 🙏❤

  • @neladegefa6928
    @neladegefa6928 Před 2 lety +18

    ይህንን ዝማሬ ከመስማት ማቆም እልቻልኩም!! በብዙ ተባረክ!!

  • @lidiyatizazu3306
    @lidiyatizazu3306 Před 2 lety +7

    ሸማኔው አንተ የህይወቴ ሸማኔ ነህ
    ሸክላ ሰሪው አንተ የህይወቴ ሸክላ ሰሪ ነህ
    አሜን አሜን

  • @sosnatadesse8954
    @sosnatadesse8954 Před rokem +3

    እውነት እግዚሐብሄር ሉዓላዊ ነው ማንም ሊጠይቀው አይችልም በስራው ድንቅ ነው አሜን ተባረኩ

  • @hanamuluneh9181
    @hanamuluneh9181 Před 2 lety +4

    ነፍስን የሚያረካ አጥንትን የሚያለመልም ድንቅ መዝሙር

  • @wagayekassa760
    @wagayekassa760 Před 2 lety +4

    በማልፍበት መንገድ በሕይወት ጎዳና
    በየእለት ውሎዬ ሳልፍ ጎንበስ ቀና
    ሊገቡኝ አልቻሉም ለእኔ
    ከዚያስ እንዴት ለማን መቼ
    በማን ቀጣዩስ ወዴት?
    በዚህ ሁሉ ነፍሴ ስትጨነቅ
    ያረጋጋል አንድን ነገርን ማወቅ
    👇👇👇👇
    ሉአላዊ ብቻህን ሉአላዊ ነህ።
    ሉአላዊ እግዚአብሔር ሉአላዊ ነህ።
    ሉአላዊ ለምን እንዲህ አረክ አንተ አትባልም
    ሉአላዊ አንተን ደርሶ የሚጠይቅ የለም።
    ሸማኔ አንተ የሕይወቴ ሸማኔ /2/
    ሸክላ ሰሪ አንተ የሕይወቴ ሸክላ ሰሪ /2/
    ፈረዱ ሊረዱ የወደዱ
    አሰቡ ምክንያት ሰበሰቡ
    ዝም አልኩኝ እንዳሉኝ ሆንኩኝ
    ለበጎ ነው ቢሉኝ አሜን ብዬ ቆምኩኝ
    አጥፍተሃል ቢሉኝ ማረኝ /2/ አልኩኝ
    ጠላት ላሉኝ ሲሉኝ ደግሞ ቆምኩኝ ለጦርነት
    የሰው ክፋት አቆሙኝ አይደለም አልኩኝ፤
    ሊሰራ ነው ታገስ እሺ አልኩኝ ጥርሴን ነከስኩኝ
    እምነቴን አበረታው ቆምኩኝ በረታው ጸናሁኝ
    አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ነው
    መልሱ እግዚአብሔር ጋር ነው።
    ቢገባኝም ባይገባኝም
    በእኔ ሕይወት ሉአላዊ ነው።
    ሉአላዊ ብቻህን ሉአላዊ ነህ
    ሉአላዊ እግዚአብሔር ሉአላዊ ነህ
    ለምን እንዲህ አረክ አንተ አትባልም
    አንተን ደርሶ የሚጠይቅ የለም።

  • @berekethailemariam8296
    @berekethailemariam8296 Před 2 lety +11

    አንተ የተባረክ ወጣት ለህይወትህ ሸክላ ሰሪ የዘመርከው ዝማሬ ከአርያም የሆነ ዝማሬ እንደሆነ ልመስክርልህ፡፡ ተባረክ!! አብረውህ ጌታን ያከበሩ ወንድሞችና እህቶች በጌታ በረከት ይረስርሱ!!

  • @messelewoldemariam9308
    @messelewoldemariam9308 Před 2 lety +6

    ወንድሜ በረከት ይህን መዝሙር የሠማሁት አሁን በቅርብ በኮቪድ ክፋኛ ታምሜ ኦክሥጂን ተሠክቶልኝ ሚሊኒየም ተኝቼ ነው በእንባ። በሚገርም ሁኔታ የተፅናናሁበት ብቻ አልልህም በእግዚአብሔር ሉዐላዊ ችሎታ ድኜ ለቤቴ የበቃሁበት በዘመኔ ሁሉ በመታሠቢያነት ሳሥታውሠው የሚኖር መዝሙር ነው ጌታ ብርክ ያረግህ።

  • @tsedaleworku9364
    @tsedaleworku9364 Před 2 lety +4

    ብቻህ ንሉዓላዊ ነህ ጌታ ይባረክ ነፍሴ ለመለመች