የ1እና2 ቆሮንቶስ ታሪካዊ ዳራ - ክፍል 1

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • የ1 እና 2 ቆሮንቶስ መልእክትን ታሪካዊ ዳራ ለማወቅ ይህን ቪድዮ ይመልከቱ፤ በዚህም እነዚህ መጽሐፍት ለዘመናችን ያላቸውን ዘመን ተሻጋሪ እውነቶች በተሻለ መንገድ መረዳት ይችላሉ፡፡
    በዚህ ክፍል 1 ቪድዮ በጳውሎስ በኩል ከወንጌል መልእክት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከመገናኘታቸው በፊት በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የቆሮንቶስን ባህል ምን ይመስል እንደነበር እንማራለን፡፡ በተጨማሪም ጳውሎስ ለ18 ወራት በቆሮንቶስ ከተማ በቆየበት ወቅት እያደገች የነበረችን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደተከለ እንመለከታለን፡፡ በዚህ ቪድዮ ውስጥ ጳውሎስ ከተማዋን ለቅቆ እስኪሄድ ድረስ የነበረውን አጠቃላይ ነገር ኹሉ እንመለከታን፡፡ በቀጣዩ በክፍል 2 ቪድዮ ደግሞ ጳውሎስ ከተማዋን ለቅቆ ከሄደ በኋላ ኹለቱንም መልእክታት ማለትም 1 እና 2 ቆሮንቶስን እንዲጽፍ ያነሣሣውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር የነበረውን ግንኙነት እንመለከታለን፡፡
    www.thebibleeff...
    FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
    INSTAGRAM: / thebibleeffect
    ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
    SONG: Ancient Agora Greece (Seikilos Epitaph) Performed by Bluepanda
    #ቆሮንቶስ #TheBibleEffectAmharic #ፍቅር

Komentáře • 5

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  Před rokem +3

    ከ1 እና 2 ቆሮንቶስ ልናስተውላቸው የሚገቡ የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች፡፡
    1) አስተሳሰቤ፣ ዋጋ የምሰጣቸው ነገሮች ወይም ባህሪዬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ባህሌንና ልማዴን የሚያንጸባርቀው በምን በምን ጉዳዮች ላይ ነው? (ለምሳሌ ክርሰቲያናዊ አንድነት፣ ጋብቻና ጾታዊ ግንኙነት፣ የግል መብቶች፣ እርስ በርስ መዋደድ፣ ትንሣኤ፣ ልግስና፣ ወዘተ.)
    2) ጳውሎስ በ1ቆሮንቶስ 13 ላይ በገለጸው የፍቅር ሕይወት መመላለስ የምችለው እንዴት ነው?
    3) በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ዘንድ የተሻልኹ ኾኜ ለመታየት ድክመቶቼን ለመደበቅ የምሞክርባቸው መንገዶች አሉ? ድክመቶቼን በመጠቀም የክርስቶስን ታላቅነት ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?

  • @bereketgetachew
    @bereketgetachew Před rokem +3

    Great

  • @haime508
    @haime508 Před rokem +1

    pls continue dont stop

  • @selamawitbekele1845
    @selamawitbekele1845 Před rokem +2

    Many blessings!!