የዮሐንስ ራዕይ 2ቱ አውሬዎች ሊገለጡ ለመሆኑ ምልክት ታየ!!እባካችሁ አትዘናጉ!!Abiy Yilma, ሳድስ ቲቪ, Ahadu FM, Fana TV

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • Abiy Yilma Media ....ሣድስ ቲቪ .......በጠቅላላ ዕውቀት እና የሥነምግባር ሳይንስ ላይ የሚያተኩር የቴሌቪዢን ፕሮግራም ነው፡፡ በአሐዱ ቲቪ ዘወትር እሁድ ምሽት ከ2፡00-3፡00 እጅግ አስተማሪ ፕሮግራሞችን ያቀርብላችኋል፡፡ እስከ 2014ም የራሱን የ24 ሰዓታት የቴሌቪዢን ጣቢያ ለመክፈት እየተጋ ያለ ሚዲያ ነው፡፡ ሣድስ የሬዲዮ ፕሮግራም ዘወትር ማክሰኞና አርብ ከ8፡00 - 10፡00 በተወዳጁ ሚዲያ አሐዱ ኤፍ.ኤም 94.3 ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ የአድማጭ ቁጥር (በአቢይ ይልማ ሚዲያ በኩል) እየተደመጠ ያለ የጠቅላላ ዕውቀት ፕሮግራም ነው፡፡
    ከዚያም በተጨማሪ ጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 3 መፅሐፍትን በከፍተኛ ፍጥነትና በብዙ 10 ሺህዎች ኮፒ እያስነበበ ይገኛል፡፡ 1ኛው/ ፀረ-666 የተባለ መፅሐፍ ነው፡፡ 2ኛው/ ሣድስ የጠቅላላ ዕውቀት መፅሐፍ ፣ እንዲሁም 3ኛው/ “አልፈራም!!” የሚል የፍርሃትን ማስወገጃ መንፈሳይንሳዊ መፅሐፍ ለገበያ አቅርቧል፡፡ እጅግም ተሳክቶለታል!! ያንብቧቸው፡፡
    ሐሳብ አስተያየት ካላችሁም በ0945-03-0505 ወይም በ09-30-306960 ላይ ለማርኬቲንግና ሽያጭ ክፍላችን ይደውሉልን!! Abiy Yilma Media

Komentáře • 205

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před rokem +38

    የተፃፈው የአምላካችን የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ይፈፀማል ልክ እሱ እንዳለ አለም ወደ ፍፃሜዋ ትሄዳለች

  • @shitayehabteyes1689
    @shitayehabteyes1689 Před rokem +28

    ኦ አምላኬ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ እንደቸርነትህ እንጂ እንደበደላችን አይሁን ፣በጥሪያችን ጊዜ ሁላችንንም በንስሀ ተዘጋጅተን ይሁንልን አሜን።

  • @FikreFikre2619
    @FikreFikre2619 Před rokem +22

    እግዝአበሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንድማችን አብይ። አንተ ማለት የእኛ አላርም ነህ። እጅግ በጣም እድለኞች ነን እንዳተ አይነት ወንድም ስለሰጠን ምክንያቱም የሁሉም ሐይማኖት አባቶች በዝምታ እያሳለፋ ባሉበት ጊዜ እንዲህ በድፍረት ወተህ ወገኖችህን እየታደክ በመሆንህ።

  • @bettybelete9100
    @bettybelete9100 Před rokem +7

    ጥሩ ማነቃቂያ ነዉ ኑሮ ሞልቶ ላያቅ እኛም እነደሮጥን ጌታ ሆይእባክህ እርዳን በንስሀ ታጥበን በስጋዉ ደሙ ታትመን የመንግስትህ ወራሾች አድርገን አሜን

  • @yeamanuellej2721
    @yeamanuellej2721 Před rokem +17

    ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እምነት ጨምርልን ጨምርልኝ በእምነታችንም ፃንተን እንቆም ዘንድ በርታትን አድለን ✝️

  • @salamontube
    @salamontube Před rokem +20

    ሰላም ፍቅር አንድነት ለሃገራችን 💚💚💚💛💛💛❤❤❤ የሀገሬ ልጆች በያላችሁበት ፈጣሪ ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

    • @jesusway3790
      @jesusway3790 Před rokem +1

      አንተንና ያንተ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ ወንድምዬ

    • @jemayineshjemayinesh2455
      @jemayineshjemayinesh2455 Před rokem

      አሜን 🤲🤲🤲

  • @user-oc9ju9ue2w
    @user-oc9ju9ue2w Před rokem +15

    ጌታ እየሱስ ሆይ ቶሎ ና ማራናታ 🛐🛐🛐🙏🙏🙏🙏🙏

  • @user-vr6tt5ik2y
    @user-vr6tt5ik2y Před rokem +6

    ትላንት መፅሐፍ ቅዱስ ሳነብ የዮሐንስ ራእይ ሳነብ ነበር የእውነት አንቀጠቀጠኝ አምላካችን ልቦና ይስጠን ለንሰአ ያብቃን😭😭😭

  • @henokmatyas9704
    @henokmatyas9704 Před rokem +12

    በፍጻሜው ዘመን ንዑ ሀቤየ ቡሩካኑ ለአአቡየ ብሎ ከሚጠራቸው ከቅዱሳን ወገን ያርግልን ክበርልን መምሕራችን

  • @ronamaquilan2150
    @ronamaquilan2150 Před rokem +9

    ጌታ ሆይ በእምነታችን አበርታን

  • @user-bv3eh4tj4i
    @user-bv3eh4tj4i Před rokem +1

    ከእግዚአብሔር የተሰጠህን እንቁ መምህራችን አንቂያችን መምህር አብይ ይልማ ረዥም እድሜ እና ጤና ይስጥህ ኑርልን ብዙ ነብስን እያዳንክ ነው እኔ በበኩሌ ከብዙ ጓደኞቼ ጋር ድኛለሁ ብዙ የማላውቀውን አውቄአለሁ ከተኛሁበት ተነስቻለሁ ኑርልን እንወድሀለን እናመሰግናለን🙏🙏🙏💚💛❤💚💛❤💚💛❤💚💛❤ ወገኖቼ ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ እንፁም ክንፀልይ እንስገድ ከልባችን እግዚአብሔር ከዲያብሎስ አጀንዳ አስፈፃሚዎች ይጠብቀን መምህራችንን መምህር አብይ ይልማን ይጠብቅልን 🙏🙏🙏💚💛❤💚💛❤💚💛❤💚💛❤💚💛❤

  • @serkalemshibeshi4921
    @serkalemshibeshi4921 Před rokem +5

    መምህር አብይ ይልማ እንድንነቃ እና እንድንዘጋጅ ስለምታስተምረን እናመስግናለን እግዚአብሔር ያገልግልት ዘመንህን ይባርክ

  • @elsategenie1317
    @elsategenie1317 Před rokem +6

    በትክክል ወንድማቾን እንግዲህ ልብ ያለው ልብ ይበል ዘመኑን ይዋጅ አንተ ግዲታህን እየተወጣህ ነው ዘመንህን እግዜአብሔር ይባርክህ

  • @titiseyfu4213
    @titiseyfu4213 Před rokem +5

    በዚ ዘመን ለብዙ ሰው የተሰወረውንና በስውር እየተሰራ ያለውን እውነት እየገለጥክ ስላለህ እናመሰግናለን እግዚአብሔር ከክፉ ይሰውርህ አብይ

  • @user-zm4yi8tl4r
    @user-zm4yi8tl4r Před rokem +1

    ተባረክ ወንድማችን ከዚህ ሁሉ ማምለጫ ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው በልጅ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምንአሁን ተፈርድበታል ይላል ቅዱስ ቃሉ ወገኔች መዳን በክርስቶስ ብቻ ነው

  • @user-mc2qb8fr5g
    @user-mc2qb8fr5g Před rokem

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህራችን በእውነት እቁዋችን ነህ ያንተ አይነቱን ያብዛልን በጣም እያነቃህን ነው እንቃ ወገኖች ጊዜው ቀርቧል ምልክቶችንም እያየን ነው ቃለ ህይወትን ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ያገልግሎት ዘመንህን ይባርከው አሜን፫

  • @saronyegeta6382
    @saronyegeta6382 Před rokem +10

    እግዚአብሔር ይባርክህ አይምሮህ የተባረከ ይሁን እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ ትልቅ የማንቂያ ትምህርት ነው ለሰው ልጅ ሁሉ ጌታን የሚወድና የሚከተል የእግዚአብሔር መንፈስ የሚከተል ሁሉ መንቃትና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ፀንቶ መቆም ይሁንልን ሙሽራው እየሱስ ክርስቶስ ዳግም በክብር ይመጣል ሀሌሉያ

  • @addisalem8276
    @addisalem8276 Před rokem

    አቤቱ በምህረትህ ታደገን አብያችን እድሜ ይስጥህ እውቀቱን ያብዛልክ

  • @eshetubacha4092
    @eshetubacha4092 Před rokem +1

    አመሠግናለው ምህር ተባረክ!

  • @betitesfaye2620
    @betitesfaye2620 Před rokem

    መምህራችን አብይ ይልማ ፈጣሪ ፀጋውን አብዝቶ ይባርክ ከተኛንበት እየቀሠቀስከን ነው ያለህው አምላካችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ግዜ አስበን እዳንተ ቸርነት ኢትዮጵያ ሀገራችንን አተው ጠብቃተ ህዝቦቻን ባርክልን🙏🙏🙏🙏

  • @betebete4627
    @betebete4627 Před rokem +10

    እንኳንደና መጣህ መምህር በርታ እግዚአብሔር ይጠብቅህ ጀግናችን

  • @mekuriyahaile6893
    @mekuriyahaile6893 Před rokem

    አንተ ውነድሜ አግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ::: በጣም የሚያሳዝነኝን ነገር ሰነግ ር ህ ግን በዚህ ባለቀ ዘመን ቤ / ክ ቸል ማለቷ ነው!!!! አንተ ግን ይብዛልህ!!!" I wished all could listen to you!!!

  • @jesusway3790
    @jesusway3790 Před rokem +7

    እግዚአብሔር በሰማዩም በምድሩም ይባርክህ አብይ ወንድሜ

  • @dawitassefa8575
    @dawitassefa8575 Před rokem

    አቅም ቢኖረኝ በብዙ በረዳሁ እሱ ይርዳህ የምታቀርበው ፕሮግራሞች ምርጥ ነው።

  • @loyidgirma8504
    @loyidgirma8504 Před rokem +1

    መምህር አንተ መልካም ልብ አለክ የቅዱሳን አምላክ ይጠብቅህ ትውልድንእያዳንክ ነው

  • @elsajefter5596
    @elsajefter5596 Před rokem +2

    Selam selam memhirachin fetari xegawun yabzalot bizu temrenal bewunetun berta from 🇪🇷🇪🇷🇪🇷

  • @merontamrat851
    @merontamrat851 Před rokem +7

    እውቀት ታላቁን እግዚአብሔርን ታከብራለች🙏🙏🙏

  • @danadana2967
    @danadana2967 Před rokem

    እግዚአብሔር የባርክህ ጤና ፀጋ በረከቱን ያድልህ ጥሩ መረጃ ነው እናመሰግናለን

  • @mistyswenson8147
    @mistyswenson8147 Před rokem +2

    The power of God is with you 🙏
    Thanks for your a wake ⏰️ millions of people.

  • @tilahune1213
    @tilahune1213 Před rokem +5

    ሠላም ሠላም ሠላም ዐብዬ የሣድስ ሚዲያ ሠራተኞች በሙሉ

  • @elaeluw.9416
    @elaeluw.9416 Před rokem +2

    Bless you Memher Abiy. May Gods support be with you in what you are doing. We pray for that. 🙏🏻

  • @maymrobi
    @maymrobi Před rokem +3

    አብይዬ እመብርሀን እድሜና ጤና ትስጥህ! እውነቴን ነው የምልህ በጣም ሰው አክባሪ ነህ ወንድሜ🙏

  • @abebabereket7468
    @abebabereket7468 Před rokem +1

    መምህር ሰለምትሰጠን ትምህርት በጣም እናመሰግናለን🙏👏❤😊

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před rokem +2

    እግዚአብሔር ስለአንተ ይመስገን መምህርና ጋዜጠኛ ፀሀፊው አብያችን ሀገርህንና ህዝብህን የምትወድ ስለሆክ

  • @addisbefkadu2726
    @addisbefkadu2726 Před rokem +1

    ደስ የሚል ተስፋ ነው የተሰጠን እድሜና ጤና ይስጥህ

  • @asnakeshewaseyasib2284

    🙏🙏🙏 ወቅታዊ ጉዳይ ነው ያቀረብክልን ትውልድ ከእርኩሰት እራሳችንን ጠብቀን የመንፈሳዊ እድገት ላይ መምጣት መቻል አለብን የአውሬው (ሲስተም) አሁን ሁሉም (ኖርማላይዜሽን)ህይወት እንዲኖረን የጥርጊያ መንገድ ላይ ነን ልንነቃበት የሚገባን ወቅት ነው።

  • @libebeegezebeheretsena8643

    Selma memere egzebehere ka anet gar yehon geta hoy anet erdegn aleman yemeneshenfew ba anet new emenet cherelani 🤲🤲🤲

  • @hiwot3828
    @hiwot3828 Před rokem +1

    Abetu geta hoye be damiy shefinen eyesus hoye tolo na 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @bosenagashu1673
    @bosenagashu1673 Před rokem +3

    አብያችን ቃለሕይወት ያሰማልን በእውነት 🤲🏿😥እግዚአብሔር ይማርሽ ሀገሬ 🙇🏿‍♀️

  • @biniYam5661
    @biniYam5661 Před rokem +1

    ቃሉ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው አምላክ መንፈሳዊ ጥንካሬ ይስጠን ወንድሜ ለአንተም የእርሱ ጥበቃ አይለይህ I respect u

  • @tigestmulugeta7810
    @tigestmulugeta7810 Před rokem

    ማራናታ ጌታሆይ ቶሎ ና ክርስቲያን ሆይ ፀንተህ ቁም በግዜውም አለግዜውም የእ/ርን ቃል ብላ።ፀንተን የምንጠብቀውን ጌታን
    ለመቀበል እንትጋ
    መምህር እናመሠግናለን

  • @kidesttesfaye9808
    @kidesttesfaye9808 Před rokem +3

    ሰላክ የተከበርከው ውዱ የተዋህዶ ፍሬ እንኳን ደህና መጣህልን

  • @kassaleykun7880
    @kassaleykun7880 Před rokem +1

    ቅድመ እውቅና የሌለው ንግግር የሚያደርግ አፍ
    ቅድመ እውቅና የሌላቸው ጸሐፊ እጆች ያሉት
    ቅድመ እውቅና የሌላቸው እግሮች
    የተሣሣተ መንገድ ላይ ሲቆሙና ሲገኙ
    የቋንቋ ብልሽት በአፉ እና በእጆቹ በእግሮቹ አጋዥነት ማሰራጨት ሲጀምር
    የፎረጀዱ የጆሮ ምንዛሪዎችን አጋዥነት ያለገደብ የሚጠቀም እርሱ
    ያለምንም ጥጥር አውሬው እና ያውሬው ነው ።
    🌈

  • @birhanumamo4966
    @birhanumamo4966 Před rokem +2

    እንኳን ደህና መጣህ መምህር

  • @asfaw8154
    @asfaw8154 Před rokem +2

    አሁንም በውቀትላይ እውቀት ፈጣሪ አምላክ ይጨምርልህ 🙏

  • @sarasolomon2002
    @sarasolomon2002 Před rokem +1

    ይህን ቀን አያሳየን ፈጣሪ ልጆቻችንን ይጠብቅ

  • @proud_Orthodox27
    @proud_Orthodox27 Před rokem +3

    መምህራችን እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  • @user-ys4gx1uf9d
    @user-ys4gx1uf9d Před rokem

    መምህር የዘመናችን እንቁ እግዚአብሔር እውቀቱን አብዝቶ ይግለጽል የህዝብ አንቂ ነህና እመቤቴ ትጠብቅህ

  • @almazzeme1888
    @almazzeme1888 Před rokem

    ወንድሜ የራዕይን መጽሐፍ የተነተንክበት መንገድ በጣም አስተማሪና ዘመኑን እንድንመረምር አድርጎናል ፈጣሪ ይባርኪህ በርታ❤❤❤

  • @trunigussie7471
    @trunigussie7471 Před rokem

    አሜን ጌታ ሆይ ቶሎ ና

  • @tigi_habeshawit
    @tigi_habeshawit Před rokem +4

    መምህሬ ሌት ከቀን የምትለፋው ለኛ ነው ከልብ አመሰግንሀለው ትንቢቱ ወይም ቃሉ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው የኔ አባት የተናገራት ሁሉ እየተፈፀመ እያየን ነው ተዘጋጅተን እንጠብቀው ንሰሀ እንግባ ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ እላለሁ

  • @hanaalmaz312
    @hanaalmaz312 Před rokem +1

    Bless u more እየሱስ ሆይ ናልን 😭😭😭

  • @user-pe2fd6lk2s
    @user-pe2fd6lk2s Před rokem

    ጌታዬ ሆይ ይህን ቀን አታሳየን አምላኬ ሆይ ቶሎ ና 😢 ቃሉ ና ትንብቱ ይፈፀማል😢 አይቀረም 🤲

  • @ritarita8258
    @ritarita8258 Před rokem +1

    በጣም እናመሰግናለን እድሜና ጤና ይስጥህ

  • @adu-genet
    @adu-genet Před rokem +3

    ወዳጄ ወደ ማይቀረው እየሄድን ነው መፍትሄው በስጋው ደሙ ከብሮ መጠበቅ ነው ።

  • @jemayineshjemayinesh2455

    yaa waqqayoo umaa kenyaa akkaa baay'inaa cubbuu kenyaa nutii hin ilalinii arjumaa ketiin nuyaadadhuu🤲🤲🤲
    *እግዚአብሔር አምላኬ ረጅም እድሜና ጤና ይስጦት ማምራች አኛንም የታምርነውን ፍሬ እንድናፈር የሱ ማልካም ፍቃድ ይሁንልን 🤲

  • @rahelbelete9283
    @rahelbelete9283 Před rokem +1

    Igziabher yestlan

  • @tsionjacques4334
    @tsionjacques4334 Před rokem

    Big Respect Abiy

  • @demelashgebrehiwot1125

    እመብርሃን ትጠብቅህ መምህር

  • @rozakebede6767
    @rozakebede6767 Před rokem +1

    ወንድሜ እግዚአብሔር ባለህበት ይጠብቅህ

  • @Ab_lyrics1522
    @Ab_lyrics1522 Před rokem

    በጣም እናመሰግናለን መምህራችን ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን🙏🙏🙏

  • @okoo3056
    @okoo3056 Před rokem +1

    Wow it's Amazing Topic,.... with Good explanation 👏👏I Know the Book Called "The Great Controversy"

  • @dawitjenbere9329
    @dawitjenbere9329 Před rokem

    Thanks God bless you

  • @ronamaquilan2150
    @ronamaquilan2150 Před rokem +2

    ሰላም ላንተ ይሁን መምህር

  • @geresugezahegn8390
    @geresugezahegn8390 Před rokem

    ሰላም ስላም ሰላም ጤና ፍቅር ለሁላችን ይሁን ዐቢያችን አመሰግናለሁ በርታልን

  • @alemayehubelay9135
    @alemayehubelay9135 Před rokem

    ወንድሜ አግዚአብሔር ይባርክህ

  • @luyabh9172
    @luyabh9172 Před rokem

    እግዚአብሔር የትንቢት መፈጸሚያ አያድርገን ከዚህ ክፉ ዘመን ይጠብቀን መምህር ተንትነክ እንድንረዳ ሰለምታቀርብልን እናመሰግናለን

  • @alemalemu6951
    @alemalemu6951 Před rokem +1

    እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን አደራ 😭😭😭🙏🙏🙏

  • @user-so5ge3wn6y
    @user-so5ge3wn6y Před rokem +1

    እግዚአብሔር ይመሰገን እንኳን ደህና መጣህልን መምህር

  • @nebu5224
    @nebu5224 Před rokem

    Abyi egziabher ybarkh 🙏

  • @asteraster4785
    @asteraster4785 Před rokem +1

    እግዚአብሔር ይጠብቅህ ይባርክህ

  • @sebieylove5190
    @sebieylove5190 Před rokem +3

    ቃሉ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነወ!! ክበርልን መምህር 🙏 ሀይል የእግዚአብሔር ነው 🙏 ኢትዮጵያ ፈጣሬዋን ይዛ ታሸንፋለች 🙏

  • @fanasaifou4847
    @fanasaifou4847 Před rokem

    Thanks a lot, dear teacher. God bless and protect you.🙏🙏🙏

  • @solomonsolomon6619
    @solomonsolomon6619 Před rokem +1

    ዐቢይ እንዴት ነህ ? ፈጣሪ በእምነታችን ያፅናን ።

  • @sewkefuegezabehermelkam7878

    ለንስሃ ሞት ያብቃን የኔስ ሀጥያቴ ብዛቱ 😭😭😭 በፀሎት አስብኝ

  • @jesusisvisaofheaven
    @jesusisvisaofheaven Před rokem +2

    እግዚአብሔር አምላካችን ከድንዛዜ ያዉጣን አሜን፯

  • @amarechasefa4045
    @amarechasefa4045 Před rokem

    abetu maren yeqer balen🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @kirakifle1813
    @kirakifle1813 Před rokem

    አብያችን እየተከታተልንህ ነው በርታልን

  • @gedimarley1328
    @gedimarley1328 Před rokem +1

    ሠላም ሠላም ሠላም ወንድማችን። ኑርልን!!!

  • @user-ll7oj5st7x
    @user-ll7oj5st7x Před rokem +1

    ጌታ ሆይ ይቅር በለን

  • @user-lp4zd3jg1u
    @user-lp4zd3jg1u Před rokem

    ሳድስ መንፈሳዊን ና ሳይንሳዊ መረጃዎች👍👍

  • @manuel2445
    @manuel2445 Před rokem

    ሰላም ሰላም እኔም ሰላምብያለው ውድ ወድሜ 💚💛❤🙏🙏🙏💚💛❤🙏🙏🙏💚💛❤🙏🙏🙏👏👏👏👏

  • @lizaermias3778
    @lizaermias3778 Před rokem +1

    You're blessed

  • @merryjon4888
    @merryjon4888 Před rokem +2

    መንግስት ሰምያት ቀርባለች እና ነሰሀ ግቡ
    መንግስት ሰማያት ቀርባለች እና ነስu ግቡ
    መንግስት ሰማያት ቀርባለች እና ነሰሀ ግቡ
    መምህር እግዚአብሔር እድሜን ከ ጤና ጋር ይስጥልኝ
    በርታልኝ ብዙ አየትማረን ነዉ 🙏🙏🙏
    ልፋተህ n ከንቱ አይደለም

  • @samuelejigu4686
    @samuelejigu4686 Před rokem

    ወድማችን መፅሐፍ ቅድስ ይዘህ ስላስተማርከን እጅግ በጣም እናመሠግናለን እግዚአብሔር አያክብርህ

  • @tesfansh6703
    @tesfansh6703 Před rokem +1

    ኑርልን፡ወድማችን፡ከነቤተሰብህ

  • @ABAB-sj3lb
    @ABAB-sj3lb Před rokem

    Wondm Memher Aby ylema betam amsegnalew egzabher abezto ybarkhe 🙏

  • @eyerusalemdinberu7097

    ሰላምህ ብዝት ይበልልን ውድ መምህራችን

  • @abiabe6796
    @abiabe6796 Před rokem

    መምህር እድሜና ጤና ይስጥልን ቃለሕይወት ያሰማልን

  • @andyketsela4196
    @andyketsela4196 Před rokem

    God bless

  • @elsacell7331
    @elsacell7331 Před rokem +1

    Wendemachen egzyaber yestelen ewketen yabezalek tebarek lela menem malet alechlem ewket talakuwa egzyaber takeberalech edemena tena yestek kenbetesebochek

  • @haymannotlema7757
    @haymannotlema7757 Před rokem

    ተባረክ

  • @edenadmasu3737
    @edenadmasu3737 Před rokem

    you are a gift

  • @ewnet-tube5213
    @ewnet-tube5213 Před rokem +3

    ከእንግዲህ ለአለም ፍፃሜ የሚቀሯችሁ ሦስት ዋነኛ ትንቢቶች የሚከተሉት ናቸው።
    🔴👉 1) ዓለም ብትመከር ፣ ብትገሰፅ ፣ እጇን እንድትሰጥ ብትጠየቅ "አሻፈረኝ ዲያቢሎሶ ይበልጥብኛል" ብላለች። እናተ የአዳምና የሒዋን ዘሮች ወደ እኔ በንስሐ አልመለስም ብላችኋል ፤ ከእኔ የሆነውን እውነት አልቀበልም ብላችኋል ፤እያንዳዱ አገር የዘራውን ያጭዳል ፤የዓመፃውን ፍዳ ይቀበላል ይህም የመጨረሻ ፍርዴ ሩቅ አይምሰላቹህ በደጃቹ ቆሟል ። እኔን ከመፍራትና ከማወቅ ስለራቃችሁ ማስተዋሉን አላገኛችሁም እንጂ ደጃችሁን አልፌ ከቤታችሁ ነኝ።
    🔴👉 2) የዓመፃ ስራና የአመፃ ልጆችን ከዚች ምድር ካፀዳው በኋላ በእኔ የተመረጠው የእናቴ የአደራ እናታችሁ የእመቤታችሁ ምርጥ ባለሟል ለሆነው ለኢትዮጵያዊው ሰው ይህችን የተቀደሰች ሀገርና ዓለምን በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። ፋቃዴን ይፈፅማል ፤ ያስፈፅማል። ፈቃዴ ሲፈፀም ይህችን አገርና ዓለምን በምህረት እጎበኛለውመልካም ዘመንን አመጣለሁ።
    🔴👉 3) በመልካሙ ዘመን መጨረሻ አንድ ቀን አሁን የሚደረገውን ማጥሪያና ማበጠሪያ ኀይሌን እንዲሁም መልካሙን ዘመን የሚዘነጋ ትውልድ በዓለም ይወለዳል ። በዚያን ጊዜ ዋናው የአመፃ ልጅ (ሐሰተኛው መሲህ) (ሐሰተኛው ክርስቶስ) (ሐሰተኛው አምላክ) ይነሳል በኀይል እና በድንቃድንቅ ተአምራት ለዓለም ይገለጣል ።
    ለሦስት ዓመት ተኩል ( ለአርባ ሁለት ወራት) ብቻ ባለ ጊዜ ሆኖ የሚያምኑትን ይፈታተናል ፣ ያጠቃል ፣ ያሰናክላል። ትዕቢት የተባሉት የፈርኦን ወንድምና እህቶች ፣ ክፋት የተባሉ የይሁዳ ወንድምና እህቶች ፣ አመፃ የተባሉት የአርዮስ ወንድምና እህቶች የክፉ ትንቢት ፈፃሚዎች በዋናነት ተከታዮቹና አጫፋሪዎቹ ይሆናሉ።
    ቁጣውን በመፍራት አእምሮ ሕፃናትና አእምሮ ቀላሎች ይከተሉታል ። አእምሮ አዋቂዎች ይሰናከሉበታል።
    ቁጣውንና ድንቃድንቅ ተአምራቱን በመመልከት አእምሮ ፅኑአን ይፈተኑበታል።
    በሦስት ዓመት ተኩል ውስጥ በእምነቱ የፀና እርሱ ለሰማያዊ መንግስት የተመረጠ ነው ። የዋናው የዓመፃና የዓመፃ ልጆች ባለጊዜነት ስሽር ዓለም እንዳልነበረች ትሆናለች ። የአመፃ ልጆች በመቅሰፍት በስቃይ ሞት ፣ የተመረጡ ሰዎች ደግሞ በምህረት ሞት ወደ ማረፊያ ቦታ ይጠራሉ። በዚህች ምድር ውስጥ ሆነ በዓለም ውስጥ በአይን የሚታዩት ፣ የማይታዩት ከመኖር ወደ አለመኖር ያለፋሉ ። የአለም ፍፃሜ በዚህ መልክ ይጠናቀቃል።
    ይላል አልፋና ዖሜጋ እግዚአብሔር፣
    የቅዱስ ሚካኤል ፣ ገብርኤል ፣ ሩፋኤል ፣ ዑራኤል ፣ ፋኑኤል ፣ ራጉኤል አምላክ።

  • @amyyohanns7301
    @amyyohanns7301 Před rokem +1

    መምህር ቃሌ ሂወት የሰመለን ❤️❤️❤️❤️❤️😍😘

  • @sunnights6561
    @sunnights6561 Před rokem +1

    ወድም አለም አብይዬ ስ ወ ድ ክ

  • @rahelwolde2112
    @rahelwolde2112 Před rokem

    enamesegenalen abyiachen temehertehen eketatelewalehu bezu ngr endenak adregehenal enam bezih agatami yemetelebsachewn sufoch wow saladenk alalfem betam new yemiamamrut

  • @jojolove791
    @jojolove791 Před rokem +1

    ግን ቤተሰብ አለህ ማለቴ ልጆች ወልደሀል ሰለነገ ሰለልጆችህ ሰታሰብ ምን ይሰማሀል? እኔ አዲስ እናት ነኝ በፊት ጌታ ሆይ ቶሎ ና እል ነበር አሁን ግን ፈሪ ሆንኩ በጣም ያሰጨንቃል እግዚአብሔር ይታደገን ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው የዘመን ፍፃሜ አታድርገን

  • @danielmamo4120
    @danielmamo4120 Před rokem +2

    አያሲው መሲህብ የተባለው የሚመጣው ዘመን በርግጥ ገና ነው ነገር ግን አሁን ህዝቡ ወደ ራሱ ተመልሶ ንስሐ ቢገባ ከመከራ ስጋና ነብስ ነፃ ይወጣል ህዝቤ አሁን የምትጨፋርበት ወቅት አይደለም የምታለቅስበትና ይቅር በለኝ የምትልበት ወቅት ነው

  • @kidesttesfaye9808
    @kidesttesfaye9808 Před rokem +2

    ጌታሆይ እምነትን ጨምርልን ከፊትህ መቆም እንዴት ይቻለናል