ዳኞችን እምባ ያራጨችው ያለም ወርቅ ጀምበሩ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 10. 06. 2022
  • #ፋና_ላምሮት #fana_lamrot
    ወይ ምጣ ወይ ልምጣ (ያለምወርቅ ጀምበሩ) "እራሷ ሙዚቃ ናት"

Komentáře • 1,2K

  • @user-pf5qj4ew7x
    @user-pf5qj4ew7x Před 2 lety +1106

    የዚህ ሙዚቃ ስራ ሚስጥሩ የገባዉ ብቻ ነዉ ሚያለቅሰዉ 😭😭😭😭ኤሊያስ መልካ በገዛ ሀገሩ ስንት በሰራለት ወገኑ ታሞ ብቻዉን ሆኖ ሲሰቃይ ወይ ልምጣ ወይ ምጣ ብሎ ለፈጣሪዉ የፃፈዉ ነዉ ።

    • @lulululu3892
      @lulululu3892 Před 2 lety +2

      😭😭😭😭

    • @hb6990
      @hb6990 Před 2 lety +23

      የኔ ጌታ ሰው ሞሆኔ እስጠላኝ

    • @narditube1684
      @narditube1684 Před 2 lety +6

      ትክክል 😥😥😥

    • @minetube322
      @minetube322 Před 2 lety +58

      😭😭😭
      ሰዎች ቆመህ ስትሄድ ነው ደጋፊህ መስለው የሚቀርቡህ ካነከስክ ግን አጠገብህ እንኳን አይሆኑም

    • @etsevidalemma4786
      @etsevidalemma4786 Před 2 lety +1

      😭😭😭😭

  • @tajudinumer3094
    @tajudinumer3094 Před 2 lety +22

    የመሰሉ ፋንታሁን 'ወይ ልምጣ ወይ ምጣ' የተሰኘ በኤሊያስ መልካ የተሰራውን ገራሚ ስራ ዛሬ የፋና ላምሮት አየጠገቤዋ ያለምወርቅ በሚገርም ብቃት ተጫውታው ስመለከት ልክ ብሩክ እናዳለው በሳቅ እና በሲቃ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህ ዘፈን አንድ የኤሊያስ መልካ አድናቂ ለዚህ ሙዚቃ መሰሉ ፋንታሁን የሰራችለትን የሙዚቃ ክሊፕ የተነተነበት እይታ በጫም ደስ ስላለኝ አጋርቼዋለው፡፡ እውነት ለመናገር ትዕግስት ያስጨርሳል። ምክንያቱም ዘፋኑን ገና እንደሰማሁት ነበረ የወደድኩት። በቀላሉ ጆሮ ገብ ስራ ነው። ከላይ ከላይ ሲሰሙት ደስ የሚል የናፍቆት ስራ ይመስላል። ግን እንደዛ ብቻ አልነበረም። ኋላ መሰሉ ፋንታሁን ስለዚህ ስራ ስታወራ 'ኤሊያስ መልካ በህመሙ ሲስቃይ ፣ ጣሩ ሲበዛበት....
    'አገሩ እና ደጁ ሩቅ እየመሠለኝ
    እንደ ወፍ እንግዳ እያብሰለሰለኝ
    ዘመድ እንደ ሌለዉ እንደ ባእድ አገር ሰዉ
    እንደ ቀልድ ባይተዋር ሆዴን እየባሰዉ
    ወይ ምጣ ወይ ልምጣ
    ከሆንክ የእኔ ዕጣ
    በምን ጥፋቱ ነው
    ልቤ እንዴ የሚቀጣ'
    እያለ ከአምላኩ ጋር 'ወይ እኔን ውስደኝ አሊያም አንተ ና' በማለት ሙግት የገጠመበት ስራው ነው ስትል ሰማኋት። ወዲያው ደጋግሜ ሰማሁት። እውነቷን ነበረ። ዘፈኑ ተራ ለአንዲት ሴት የተሰራ የፍቅር ዘፈን ብቻ አልነበረም። መሰሉ ካወራቸው ታሪክ ጋር አያይዤ ሳዳምጠው እንደ አዲስ የተለየ ስሜት ነበረ የሰጠኝ። ግጥሞቹ ውስጥ የኤልያስ መልካን የተለየ ህመሙን ፣ መከፋቱን ፣ አምላኩን መናፈቁን ቁልጭ ብሎ ተቀምጦ አገኘሁበት። ከዛ በኋላ ይሄን ዘፈን መስማት እሱ እያስታወሰ ስለሚረብሸኝ ተራው ደርሶ እንደመጣ ሳልሰማው ነበር የማሳልፈው። "እኔ እንኳን ይህን ዘፈን አልዘፍነውም ይቅርብኝ ብዬው ኤሊያስዬ በግድ ነው ያዘፈነኝ..." ትላለች እዛው ቃለመጠየቋ ላይ መሰሉ ፋንታሁን። 'ለምን ?' ስትባል ፣ ምክንያቱም እሷ እንኳን ዘፈኑን እየሰራችው በጣም ትረበሽ እንደነበረ ትገልፃለች። ኤሊያስም ይሄ ዘፈን ሲሰራ የተለየ ስሜት እንደነበረው ጨምራ ትነግረናለች። እንግዲህ ይሄን የኤሊያስ መልካ እውነተኛና የመጨረሻ ታሪኩ የሆነውን ስራ ነው አውታሮች ተራ የፍቅር ዘፈን አድርገው ክሊፕ ሰርተውለት የልጁን መልዕክት ያጣረሱበት።
    "እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበረ
    የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ በዛው ባይቀር..."
    በማለት ኤሊያስ መልካ አምላኩን መናፈቁን ፣ ሞት ከእሱ መራቁን በቁጭት የፃፈውን ስንኝ ፣ አውታሮች በድፍረት መሰሉ ፋንታሁን ሶፋ ላይ ተቀምጣ አንድን ወንድ በናፍቆት ስትጠብቅ አድርገው የዘፈኑን ትርጉም'ና ወዝ አጥፍተው ያሳዩናል። እንደ'ኔ ዘፈኑ እንዲሁ ተራ ብቻ አይመስለኝም። ስለኤሊያስ ስለዚህ ስራ ብዙ መመራመር ፣ ብዙ መፃፍ ፣ በብዙ አይነት መንገድ መተንተን ያለበት ይመስለኛል። ከእሱ ስራዎች ውስጥ የተለየ ስፍራ ልንሰጠውም ይገባል ብዬ አምናለሁ። ኤሊያስም በመጨረሻው ሰዓት በዚህ ስራው ምንም ሳይደብቀን ከአጠገቡ ሰው ማጣቱን ፣ ከአምላኩ እቅፍ ለመግባት ምን ያህል መጓጓቱን ፣ ሞትና እንቅልፍ እንዴት እኩል እንደራቁት ፣ ህመሙን ፣ የለሊት የብቻ ስቃዩን ሳይቀር በቁጭት በግልፅ ነግሮናል። ኤሊያስ መልካ ግጥሙ ሲፅፍው በምን ሁኔታ ላይ ነበረ ? በምን ተከፍቶ ነበረ ? ስንት ቀን ፈጀበት ? ምን ያህል አለቀሰ ? ወይስ በናፍቆት ተስፋ እያደረገ ብቻ ነበረ የፃፈው ? ከዛ መሰሉ ተጫውታው ዘፈኑ አልቋ ሲሰማው ምን ተሰምቶት ይሆን ? አምላኩስ 'ወይ ልምጣ ወይ ምጣ..' የሚለው መልዕክቱ ደርሶት ነው ወይ ዘፈኑ ሳይወጣ 'አረ አንተ ና ልጄ...' ብሎ የወሰደው ? እኚ ሁላ መልስ ሊፈለግላቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው ! የሚገርመኝ መሰሉ ፋንታሁን በግጥሙ ተረብሻ ጨክና ይሄ ዘፈን አልጫወተውም ካለች ፣ እንዴት ደስተኛና ያማረባት ሴት ሆና ይሄን ክሊፕ ለመስራትስ አላንገራገረችም ? ዝግጅቱን የሰሩትስ ሰዎች ስለዚህ እውነተኛ ታሪክ የሚያውቁት ነገር አልነበረም ወይ ?! ብቻ እሷም ሆነች እዚህ ክሊፕ ላይ የተሳተፉት ሰዎች በሙሉም ብሽቆች ናቸው። በተራ የውሸት ክሊፕ ፣ እኛ አይምዕሮ ውስጥ የተሳለውን ውብ ምስል ለማጥፋት የተሽቀዳደሙ እንከፎች ! ሊያውም የቅርቡ ሰዎች ሆነው ሁሉንም በቅርበት እያወቁ !
    "እህህ ወየዉ ጉድ ስንት አለ በሆዴ
    አምቄዉ ነዉ እንጂ ኑሮዬን በዘዴ
    አለ ጋደም ጋደም ሰዉ ሁሉ ሊተኛ
    እኔ ቁጭ ብያለዉ ያንተ በሽተኛ"
    ይቺን ስንኝ ብቻ በኤልያስ መልካ ህመምና መብሰልሰል ልክ ወደ ምስል ለመቀየር እንደሱ መታመም ባይቻል ፣ ወደ እሱ አስተሳብ መቅረብ ብቻ ብዙ ነገር ያቀልላችሁ ነበረ....

    • @techreview7892
      @techreview7892 Před 2 lety +1

      ልክ ነህ ወዳጄ።
      ኤልያስን ሁሌ በስራዎቹ በሰማሁት ቁጥር አይኖቼ በአንባ ይሞላሉ።
      ኤሉ ሁሌም በልባችን ነግሠህ ትኖራለህ🥰🥰😥

  • @yoditendalmaw8360
    @yoditendalmaw8360 Před 2 lety +68

    እኔም እምባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ኤልያስ አንተ ትለያለህ ነብስህ በሰላም ትረፍ።ያለምወርቅ እናመሰግናለን

  • @Eyobadmasu
    @Eyobadmasu Před 2 lety +293

    ያለም ወርቅ 👏👏👏👏ግጥም ዜማ ቅንብር እጀ ወርቁ ኤልያስ መልካ ነብስን በገነት ያኑራት

    • @veryrelitrans3025
      @veryrelitrans3025 Před 2 lety +1

      But who singed the song first??

    • @Gozhini
      @Gozhini Před 2 lety +3

      አዎ ኤልያስ መልካ፣ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑር !!!

    • @bezawitwondimu
      @bezawitwondimu Před 2 lety +1

      @@veryrelitrans3025 Messelu Fantahun

    • @veryrelitrans3025
      @veryrelitrans3025 Před 2 lety

      @@bezawitwondimu thank you Pl give me a link which is the same song

    • @aghsepda
      @aghsepda Před 2 lety +1

      ኤሉ ❤❤❤

  • @helenmulugeta9081
    @helenmulugeta9081 Před 2 lety +20

    እኔ ዘፈን አልወድም አልሰማም ጭራሽ ግን ትርጉሙን ከሰማሁ በኋላ ሳዳምጠው እጅግ በጣም ልቤ ተሰበረ ያን የመሰለ መልከ መልካም እንደዛ ሆኖ ሄደ አይ የሰው ልጅ ነፍሱ በሰላም ትረፍ የኔ ጌታ እንዴት ብትሰቃይ ነው

    • @mesaydella9445
      @mesaydella9445 Před 2 lety

      ኤልያስ ጥሪው እና እግዚአብሔር የሰጠው ፀጋ በገናን የመደርደር ፀጋ ለጌታ ለሚዘምሩት እንዲቀኙለት ነበር እሱ ግን ለምድር እውቀት አዋለው ወዳጅ ያላቸውም ከዱት በመጨረሻም ሽሮ እያማረው እርሀብም ተደምሮ በላው ነፍሱን 😭😭😭😭🙏

    • @addisababanazareth1525
      @addisababanazareth1525 Před 2 lety

      Mesay: እምነቱን የሚዪውቅ እሱ እንጂ አንተ ምናገባህ? የራስህን ፈትፍት እንጂ ስለሌላው ዝምበል::

  • @saratube9100
    @saratube9100 Před 2 lety +33

    ዋው ዋው የሚገርም የሚደንቅ ድምጽ ማመን አቃተዝን ሁሉም ትዝታን ቀሰቀሰብኝ

  • @fasilberhanu4983
    @fasilberhanu4983 Před 2 lety +48

    ኢትዮጵያ ላይ ሰው ሲሞት ውድ ነው የመረዳዳትና የመተዛዘን ባህላችን ጠፍቷል ሰውን ሲኖር መደገፍ ነው ያለብን። አይዞሽ በርች ያለምወርቅ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከፍ እንደምታረጊው ሳይታለም የተፈታ ነው

  • @henokasrat5402
    @henokasrat5402 Před 2 lety +9

    ያለም ወርቅ በእውነት አንቺ በጣም ድንቅ የሆነ ልብን በትዝታ የሚያነጉድ ድምፅ ነውያለሽ። አንቺ በጣም ትለያለሽ። እባክሽ እህቴ ይህንን እንቁ የሀገር ሀብት ጠብቂው። ቀሪው ዘመንሽ ሁሉ በበረከት በስኬት እና በደስታ የተሞላ እንዲሆን እመኛለሁ። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ።

  • @christianbirhanudagne
    @christianbirhanudagne Před 2 lety +417

    ኤልያስ መልካ ነፍስህ በሰላም ትረፍ ። ህመምህን ፣ ብሶትህን የገለጽክበት ዘፈን ነውና አንተን ያስታውሰናል 😭😭😭😭😭😭😭😭😭 ። እውነትም የአለምወርቅ 🙏🙏🙏🙏🙏

    • @amarkedir6848
      @amarkedir6848 Před 2 lety

      ሲዖል ውስጥ

    • @yaredmichael5282
      @yaredmichael5282 Před 2 lety +3

      @@amarkedir6848 esun egzabiher new mawkew yete .end .mayiasrfew mayakew eshi leke end k kersto gara endtskalew wenbde malet new eshi atfred yefrdbkal eshi wendm!

    • @tigiste637
      @tigiste637 Před 2 lety +4

      @@amarkedir6848 የቁም ሪሳ ከሁሉ ቀድመሕ ሲኦል አንተ ትገባለህ

    • @veryrelitrans3025
      @veryrelitrans3025 Před 2 lety

      Don't forget Elias melka geresu is Oromo Ethiopian

    • @cacapoop9180
      @cacapoop9180 Před rokem

      Rest in peace Aliyas Mallek

  • @berhanubanti9482
    @berhanubanti9482 Před 2 lety +30

    ምርጥ ድምጽና ቅንብር ነው ። ብዙ የድምጽ ቃና አላት የበለጠ መሥራት ትችላለች ። ለእርሷና አብረዋት ለደከሙ ሁሉ ምሥጋና ይገባቸዋል።

    • @kibrewossenguadie8875
      @kibrewossenguadie8875 Před 2 lety

      Elias Melka asking God to end his suffering from Kidney Failure due to DM. Heart touching music. Ela, RIP.

  • @kurdkurd288
    @kurdkurd288 Před 2 lety +35

    ዘፈን እንደዚህ ነው ከአለባበስ እስከ አዘፋፈን የኛ ዘመን አመጣሾች ዘፈንን እያሉ እሚበራገዱ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ከዚች ልጅ ብዙ ነገር መማር አለባቸው ሁሉም ለዛ ሲኖረዉ እንደዝች ልጅ አንጀት ይላወሳል በጣም አድናቂዋ ነኝ

  • @user-hs7hw4km6z
    @user-hs7hw4km6z Před 2 lety +50

    እኔ ከድምጷ ከስራዋ በላይ አለባበሷ በራሡ ከጀመረ ጀምሮ አንደኛ ያስወጣታል ይገባሻል 1ኛ ስለወጣሽ ደስ ብሎኛል የኔ ምርጥ እንድሁም ዳኒኤል አዱኛ 2ተኛ ስለወጣ ደስ ብሎኛል ሁሉም አንደኛ ናቸው አራቱም ተባረኩ

  • @tigabukassa5725
    @tigabukassa5725 Před 2 lety +12

    ኢትዮጵያ ለዘላለም አታፍርም ልጆች አሉዋት ያለምወርቅ እውነት ወርቅ ነሽ አንችን የወለዱ ቤተሰብ ኩራት ይገባቸዋል ውቢቷ ጎንደር እንኳን ደስ አላችሁ በርቺ ፋናም ብሮድካስትም ክብር ይገባችኋለሁ

  • @abebawagegnehu2162
    @abebawagegnehu2162 Před 2 lety +31

    የአሁኗቹ ተወዳደሪዎች ብዙ ኢትዮጵያዊያን ከአሁኑ ጅዋጅዊ ሙዝቃ አወጣቸው የሚገርም ነው ስንት ቦታ ሂደን ሙዝቃ መስማት ጀመርን ተባረኩልኝ ድንቅ ናችሁ ሁላችሁም ።ጋሼ ተሾመ አስግዶ እናመሰግናለን አባታችን

  • @abiyabiyum6653
    @abiyabiyum6653 Před 2 lety +24

    አንችን አለማድነቅ ንፉግነት ነው😍
    የዘመናችን ምርጧ ወርቅ😍😍

  • @temesgenfikire7377
    @temesgenfikire7377 Před 2 lety +37

    በ ደቡብ አፍሪካ ስደት ለይ ነኝ ብዙም አልቆያሁም በለኝ ነገር ሀገሬ ልሰረ ከፍቅረኛዬ ርቄ መኖር አልቸልኩም በቅርቡ ልመለስ አስበለሁ ጌታ እንድያሰከልኝ ተመኙልኝ 💔🙏💕💔 በዘ ለይ ሙዝቀዉ አስጨነቀኝ💕

    • @Hustlers_hab
      @Hustlers_hab Před 2 měsíci

      ተመለስክ እንዴ ወንድሜ

  • @embetabebe8274
    @embetabebe8274 Před 2 lety +31

    ያለም ወርቅበጣም ቆንጆ ነው እናመሰግናለን መልካም እድል

  • @tsegazeab19
    @tsegazeab19 Před 2 lety +56

    ሙዚቃን ተራቃበታለች ይገባታል 👏
    Congratulations 🎉🎊💚💛❤️

  • @user-lw4zi3xx4r
    @user-lw4zi3xx4r Před 2 lety +535

    እጅግ በጣም ያሳዝናል፤ ትዕግስትንም ይፈታተናል ዛሬ የፋና ላምሮት አሸናፊዋ ያለመወርቅ '' ወይ ምጣ ወይ ልምጣ'' በተሰኘ ግሩም ዜማ የተዳፈነውን እሳት ዳግም ቆሰቆሰችው። "ወይ ልምጣ ወይ ምጣ" የተሰኘውን ሙዚቃ የዛሬ አመት መሰሉ ፋንታሁን የሰራችው ልብን የሚነካ ክሊፕ ነበር። ግጥምና ዜማው የኤልያስ መልካ ሲሆን ዘፈኑ የናፍቆት ወይንም የፍቅር ይመስላል ግን እውነታው ሌላ ነው። መሰሉ ስለዚህ ሥራ ስታወራ ኤልያስ መልካ በህመሙ ሲሰቃይና ጣር ሲበዘባት
    "አገሩና ደጁ ሩቅ እየመሠለኝ
    እንደ ወፍ እንግዳ እያብሰለሰለኝ
    ዘመድ እንደሌለው እንደ ባዕድ አገር ሰው
    እንደ ቀልድ ባይተዋር ሆዴን እየባሰው
    ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
    ከሆንክ የእኔ ዕጣ
    በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
    እህህ... እህህ ..እህህ...
    እህህ ..ወየው ጉድ ስንት አለ በሆዴ
    አምቄው ነው እንጂ ኑሮየን በዘዴ
    አለ ጋደም ጋደም ሰው ሁሉ ሊተኛ
    እኔ ቁጭ ብያለሁ ያንተ በሽተኛ" በማለት ከአምላኩ ጋር "ወይ እኔን ውሰደኝ አሊያም አንተ ና" በማለት ሙግት የገጠመበት ሥራው ነው ስትል ተናግራ ነበር።
    በርግጥም እውነቷን ነው። ዘፈኑ ለፍቅር የተዘፈነ አልነበረም። ኤልያስ መልካ ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት ሥራውን ባጠናቀቀው “ወይ ምጣ ወይ ልምጣ” ሙዚቃ ውስጥ ሰዋዊ ሕመሙን ለመተንፈስ የሞከረበትና ህመሙን፣ መከፋቱን፣ ማዘኑን፣ አምላኩን መናፈቁን ያሳየበት ሥራው ነው።
    "እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር
    የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ በዛው ባይቀር" በማለት ኤልያስ መልካ አምላኩን መናፈቁን፣ ህመም ሲበዛበት ሞት ከሱ መራቁን በቁጭት የፃፈው ስንኝ ነበር።
    እውነት ለመናገር ከመሰሉ ንግግር በኋላ ይሄን ሙዚቃ ላለማዳመጥ ወሰኜ ነበር። ዛሬ ደግሞ ምታሃተኛዋ ያለመወርቅ ብሶታችንን ቆሰቆሰችው፥ ሁሉም ኤልያስ መልካን እያሰበ በዕንባ ተራጨ። ዳኞችም ዕንባቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ዋለ።
    መሰሉ እንኳን "ይሄን ዘፈን አልዘፍነው ይቅርብኝ ብዬ ኤልያስ ነው በግድ ያዘፈነኝ" ትላለች እዛው ቃለመጠይቋ ላይ "ለምን?" ስትባል ምክንያቱም እሷ ዘፈኑን ስትሰራው በጣም ትረበሽ እንደነበረ ተናግራለች።
    ኤልያስ መልካ በመጨረሻም በዚህ ሥራው ምንም ሳይደብቅ ከአጠገቡ ሰው ማጣቱን፣ ከአምላኩ እቅፍ ለመግባት ምን ያህል መጓጓቱን፣ ሞትና እንቅልፍ እንዴት እኩል እንደራቁት ነግሮን ነው የተሰናበተው።
    Please subscribe to my channel to get amazing short videos about aircrafts

    • @yohannestesfatsion7066
      @yohannestesfatsion7066 Před 2 lety +37

      ግልፅ ስላርክልን አመስግናለሁ ለምን እንዳለቀሱ አልገባኝም ነበር የበለጠ ወደድኩት ሙዚቃውን

    • @bestgmicheal5780
      @bestgmicheal5780 Před 2 lety +7

      Thank you

    • @Master_ofElements
      @Master_ofElements Před 2 lety +6

      ግጥሙም የኤልያስ መልካ ነዉ እንዴ

    • @user-lw4zi3xx4r
      @user-lw4zi3xx4r Před 2 lety +4

      @@Master_ofElements yes

    • @Master_ofElements
      @Master_ofElements Před 2 lety +7

      @@user-lw4zi3xx4r ዉይ በጣም ያሳዝናል

  • @solekebe7628
    @solekebe7628 Před 2 lety +227

    እውነትም የአለም ወርቅ የቀዘቀዘውን ሙዚቃ ነፍሥ ዘራችበት ሠላምሽን ያብዛልሽ

    • @impacttube1
      @impacttube1 Před 2 lety

      ይህስ czcams.com/video/ro5oiKXFelw/video.html

    • @veryrelitrans3025
      @veryrelitrans3025 Před 2 lety

      Who is the original singer??

    • @merrrrrrrt1812
      @merrrrrrrt1812 Před 2 lety +1

      @@veryrelitrans3025 meselu fantahun

    • @addisababanazareth1525
      @addisababanazareth1525 Před 2 lety

      አልቀዘቀዘም:: አሁንም ለቀጣይ ትውልድም አስተማሪ ሙዚቃ ነው:: ያላቸው እየመሰለን ግን ላይኖራቸው እንደሚችል እንድናውቅ የሚያስተምር ሙዚቃ ነው::😭

    • @teferitadesse1370
      @teferitadesse1370 Před rokem

      ድንቅ የጥበብ ብርሃን ትዝታን ፈጠረች

  • @tejealene2386
    @tejealene2386 Před 2 lety +13

    የኔ ልጅ እደጊልኝ እድሜና ጤና ይስጥሽ የዳኞቹ ስሜት በራሱ እጅግ ገራሚ ዳኝነት ነው ትክክለኛ ዳኝነት ካይን ያውጣሽ የኔ ድምፀ መረዋ 🙏🇪🇹❤️👍✅😘👌

  • @mikiman6670
    @mikiman6670 Před 2 lety +115

    እናቴ ትሙት ያለምወርቅየ የኔ ቆንጆ ልክ እንደ ስምሽ ወርቅ ነሽ 🥰አንች ምኑንም ብትዘፍኝ ያምርብሻል ልዩ ነሽ ኬኳ የአለባበስሽን ነገር እማ አይወራም በናትሽ በዚህው ቀጥይ 👌👌በአዲስ ሙዚቃ አንችን ለማየት እፈልጋለሁ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @user-so3sm3uo4j
    @user-so3sm3uo4j Před 2 lety +39

    የኔ ቆንጆ ጎንደር ምንግጊዜም ጀግና ታበቅላለች ምርጥ ነሽ

    • @WendradNiguse
      @WendradNiguse Před 7 měsíci

      በብሄር እና በመንደር ለምን እንታጠራለን ግን ሰፊ ህዝቦች እኮ ነን ኢትዮጽያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን መዘንጋት ባይኖርብን መልካም ነው

  • @dagnachewseifu1724
    @dagnachewseifu1724 Před 2 lety +46

    በጣም ጐበዝ 👏👏👏👏👏👏👏👏መረዋ ድምፅ ነው ያለሽ ።
    በርቺ በርቺ በርቺ !!! በመንገድሽ በስራሽ ሁሉ ቸሩ መድሐኒአለም አይለይሽ ! !!! ሐገራችንን ኢትዮጵያን ሠላም ያድርግልን !!
    ሁሉም በሐገር ነውና 💚💛❤️

    • @nesrya4292
      @nesrya4292 Před 2 lety

      ደሞ ሙዚቃ ላይም ቸሩ መዳኒያ አለም ያግዛል እንዴ

    • @mekdesmelkam7585
      @mekdesmelkam7585 Před 2 lety

      ድምፅ ተሠጣሻል እማ ደጋግሜ ሠማሁሽ

    • @dagnachewseifu1724
      @dagnachewseifu1724 Před 2 lety

      @@nesrya4292 አምላክ በማንኛውም መንገድ ቢያግዛት ምን አለበት ??? በሁሉም ነገር ምቀኝነት ፣ ቅናት:
      መድሐኒአለም ይማርህ(ሽ)

  • @nejatliben6293
    @nejatliben6293 Před 2 lety +440

    እስቲ ለዚች ምርጥ ልጅ በላይክ ክስተት ነሽ እንበላት

    • @mulugetaareru4584
      @mulugetaareru4584 Před 2 lety +2

      ነጁ የመሰሉ ኣይደለም

    • @nejatliben6293
      @nejatliben6293 Před 2 lety +3

      ሀይ ሙሌ የማን ነው

    • @user-pg7iu9rs9p
      @user-pg7iu9rs9p Před 2 lety +1

      YANA. MAR. MLKAM. EDEL❤❤❤❤

    • @gashawendeshaw3463
      @gashawendeshaw3463 Před 2 lety +1

      አንች ራስሽ ለኔ ክስተት ነሽ!

    • @LamdaAlpha65
      @LamdaAlpha65 Před 2 lety +3

      ነጆ በዚህ እማ እንስማማለን። በጣም የተዋጣላት ኣርቲስት ነች። ፖለቲካሽ ግን ኣልወደውም😛

  • @endrismohammed8081
    @endrismohammed8081 Před 2 lety +66

    በዘመን ሂደት ከሙዚቃዉ መድረክ ላይ ያጣናቸዉን እነዛን የልጅነት ትዝታችን የሆኑትን ብርቱካን ዱባለን፣ የሽመቤት ዱባለን፣ እናና ዱባለን እና አሰፉ ደባልቄን ተክታ ብቅ ብላልናለች እና ፈጣሪ ከሙሉ ክብሯና ሞገሷ ጋር ዘመኗን አብዝቶ ይባርክልን የራሷን አልበም ሰርታ በስራዎቿ ለመደመም እና ሀሴት ለማድረግ ያብቃን!!!
    አባቴ ይሙት ትችላለች የሚለዉ ቃል አይገልፃትም!!!

    • @zufangirma2394
      @zufangirma2394 Před 2 lety

      ማነው የሚባርካት? እግዚአብሔር እዚህ ውስጥ እጁ አይገባም። ምክንያቱም ዘፈን ኃጢአት ነው።

  • @user-em6yb9vw6b
    @user-em6yb9vw6b Před 2 lety +54

    ዘፈኑ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ቀልብን እና ስሜትን የመሰብሰብ አቅሙ ከድንቅ አዘፋፈን ብቃት ጋር ከፍተኛ ደረጃ ነው።በርቺ

  • @adbe5876
    @adbe5876 Před 2 lety +5

    ጎንደር ተባረኪ ሌላ ምን ልበል እንደዚህች ድንቅ ልጅ ስለወለድሽ

  • @jorgbehailu9491
    @jorgbehailu9491 Před 2 lety +43

    በኢትዮጵያ ሙዚቃ ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያደርጉን በየዘመኑ ይፈጠራሉ እነዚክ ልጆች ታፍነው እንዳይቀሩ በማውጣት ለምትለፉት ፋና ላምሮት እና ባላገሩ ትልቅ ክብር ይገባችኋል እንጅማ የ CZcams ዘፋኞች ጥበብን አፍነው ሊገሏት ተባብረው ተነስተዋል በዚች ልጅ ድምፅ መንፈሱን እንውጋው 👊👊

    • @susesuse2429
      @susesuse2429 Před 2 lety +2

      ጥበብን አፍነው ሊገሏት ምርጥ አገላለፅ🤣🤣🤣

  • @fantahunastat1931
    @fantahunastat1931 Před 2 lety +12

    ኤልያሰ መልካ ነፍሰህን ከደጋጎች ጋ ያርግልህ ህመምህና ብቸኝነትህን ለኢትዬጰያ ህዝብ የገለፀህበት ሁሌም ይሄን ሙዚቃ ሳዳምጥ እንባየ ቀጉንጨ ይወርዳል እህህህህህህህህ

    • @user-ux4jh5sd4y
      @user-ux4jh5sd4y Před 3 měsíci

      እንደኔ ባይሆንም😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

  • @moneali7435
    @moneali7435 Před 2 lety +10

    ብቃት ማለት ይሄ ነው የሁሉንም ሰው ትዝታ ነው የቀሰቀሽው ሰው በሙያው እዴ ብቆ ሴሁን ይገርማል ከነ አለባበሷ ምርጥ ኤትዮጴያዌት

  • @yonidaniz2044
    @yonidaniz2044 Před 2 lety +41

    ነፍስህን ይማርልኝ ኤልያስዬ የኔ ቅን ህመምህን ስቃይህን ናፍቆትህን ነግረሀን ነበር አህ ያማል

  • @sisaysolomon1293
    @sisaysolomon1293 Před 2 lety +14

    ዘመን ሊመለስ ተስፋ አደርጋለው በርቺ ባህል ክብር ነው ድምፅሽም ሁሉም ማርኮኛል ሰላምና ጤናን እመኝልሻለው

  • @user-qk8os1qy7u
    @user-qk8os1qy7u Před 2 lety +11

    ለመጀመሪያ ጊዜ ጭቅጭቅ የለለው ውጤት ህዝብ በሙሉ የተስማማበት የያለም ወርቅ አሸናፊነት👌👌👌👌

  • @ayelebekalucherie4680
    @ayelebekalucherie4680 Před 2 lety +11

    እስከ አሁን በፋና ላምሮት ካየናቸው ድምፃዊያን ይች ልጅ ትልያለች የምርጦች ምርጥ ናት

  • @Wogera2833
    @Wogera2833 Před 24 dny +1

    እጅግ በጣም ግሩም የሆነ አዘፋፈን እና የድምፅ ቃና ተባረኪ

  • @samriethiopia6271
    @samriethiopia6271 Před 2 lety +10

    ኤልያስ መልካ ነፍስህን ይማረው ውዴ እጅግ ልብ የሚነካ ስራህ ነው። ያለምወርቅ እናመሰግናለን

  • @funnyclips4661
    @funnyclips4661 Před 2 lety +27

    ኤልያስ መልካ ሒዎቱን ነው ሰርቶልን የሞተው ያስብላል :: በጣም ያስለቅሳል ከፍቅር ውጭ ዘፈኑን ለሚረዳው:: ነፍስ ይማር ኤልያስ መልካ::

  • @samiabi3029
    @samiabi3029 Před 2 lety +87

    ኤልያስ ከማለፉ በፊትስለነበረበት ህመምና ሁኔታ ባጠቃላይ ስለሚሰማው ስሜት በረቀቀ መንገድ የተናገረበት ስራው ነው።ፈጣሪ ለነብሱ ይራራለት

    • @metadelalmayehu6388
      @metadelalmayehu6388 Před 2 lety

      Yegermal betam nefesu beselam terfe

    • @rkbd6652
      @rkbd6652 Před 2 lety

      በሙዚቃ ነው እሚራራለት 🤔

    • @wubitsirgew1238
      @wubitsirgew1238 Před 2 lety

      ኤልያስ በጣም የሚገርመው ሰው ሲሰራ እና ሲኖረው ብቻ ነው ኩላሊት የሚፈለግለት ከቤቱ ተሰብስበህ የምትውል ጉዋደኘቹ የትነበራችሁ ለምን አላገዣችሁትም እንደዛ ተቸግሮ ሰውሲናፍቀው በመጨረሻሰአት የትነበራችሁ የውሸት ሰዎች በጣም ዐየተቆጨን ዐንድኖር አደረጛችሁን አድናቂዎቹን የብርመዋጮ ማድረግ ትችሉ ነበር ኩላሊት የሚሰጠው ስው ያገኘ ነበር ሁሉነገር ተቀደምን አልደረስንለትም በቃ ሄደ እርሱ

    • @tigiste637
      @tigiste637 Před 2 lety +1

      @@rkbd6652 እንዳተ በድንቁርና ነዉ

    • @betelhemmelku3650
      @betelhemmelku3650 Před rokem

      Amen

  • @lemmaeshetu968
    @lemmaeshetu968 Před 2 lety +3

    ውይ ምን ልበል በወጣትነት እድሜው ብዙ መስራት በሚችልበት ጊዜ ኤልያስ መልካ ተለየን ፡፡ አንቺም አስለቀሽን !! ኤልዬ ነፍስህ በሰላም ትረፍ !!

  • @fikerabi9151
    @fikerabi9151 Před 2 lety +16

    *OMG* 😱 _I can't stop Crying_
    😭😭😭😭😭

  • @fasilabebe1201
    @fasilabebe1201 Před 2 lety +28

    እውነት ትችያለሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ ❤❤❤❤🥰 ጎንደርን በሙሉ አኮራሽው 💪💪 Proud of you

  • @user-yf4sk1wf4l
    @user-yf4sk1wf4l Před 2 lety +55

    "ወይ ልምጣ ወይ ምጣ" ሙዚቃ ብቻ አይደለም። የኤልያስ መልካ የህመም ሲቃ ድምጽ አውጥቶ የሚሰማበት ፣ ሕይወቱ የተከወነው ጎርባጣው ክፍል ያሳየበት "ዘላለማዊ" ኑዛዜ ነው።

  • @mesimebrate9341
    @mesimebrate9341 Před 2 lety +8

    ኤሊያሴ ነብስህ በሠላም ትረፍ😭😭 ያለምወርቅ አንቺንም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

  • @user-dz2iu8lp9x
    @user-dz2iu8lp9x Před 2 lety +18

    አለምዬ የኔ ቆንጆ እንኳን ደስ ያለሽ እውነት ለአዘጋጆችም ትልቅ ክብር አለኝ።

  • @solomonmamo1061
    @solomonmamo1061 Před 2 lety +20

    ተስዕጦ እና ባለቤቷ ሲገናኙ እንደዚህ ነው ኢትዮጵያዊ ተስእጦ ከነ ክብሯ

  • @serkalemkebede9829
    @serkalemkebede9829 Před 2 lety +4

    ነብስህን ይማረው ኤልያስዬ ለእናቴ የምመኘውን ገነት ላንተም ተመኘው ውስጥህን ገለፅክበት ኢሄን ዘፈን እንደ አዲስ ስሰማው አንጀቴን አንሰፈሰፍከው ያለም ወርቅ በርቺ በእሱ ፎቶዎች ቢቀናበር መልካም ነው ምኞቴም ነው

  • @samitube9152
    @samitube9152 Před 2 lety +15

    ዋው ያለምየ የኔ ኩሩ በጣም ልዩ ነሽ 👌 በራስ ቀለም፣በራስ ልብስ በራስ ድምፅ ይሉሀል ይሄ ላይ ነው 🥰ምንግዜም ምርጫየ ነሽ የኔ ልዩ 👌ትልቅ ደረጃ እንደምትደርሽ ምንም ጥርጥር የለኝም 🥰የኔ እናት 😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘🥰🥰

  • @yeg.9665
    @yeg.9665 Před 2 lety +59

    ኤልያስዬ(ኤልያስ መላካ)አንተ የኔ ልዩ ደግሞ መጣህብኝ አንጀቴን ልትበላው ብቻ በአባትህ ቤት ሰላም እረፍልኝ። አንቺም እንደስምሽ ወርቅ ነሽ አቦ

  • @MIkItube
    @MIkItube Před 2 lety +195

    አንች የጎንደር ንግስት የአፄዎች ልጅ
    ድምፀ መረዋዋ የጀበሩ ልጅ
    እንደ ፋሲለደስ ታሪክ ልትሰራ
    ያለም ወርቅ ሆና ጎንደርን በድምፅዋ ስሟን ልታስጠራ
    ይህው ፋና ላምሮት ቆማለች በተራ
    አፄ ፋሲለ ደስ በፈረስ ተጉዞ ጎንደርን ሲሰራ
    አለምዬ ቆመች ይች የጎንደር ንግስት ቆማለች ከበሩ
    ታሪክ ልትሰራ
    በሉ ግቢ በሏት ድሮስ ማን ሊወሰደው። ማንስ ሊያሸንፋት
    ደሟ ከገብርየ ትውልዷ ከጋፋት
    ዘመንን የሁሊት እንድንቃኝ ያረገች
    ዳኛን ከተመልካች ሁሉን ያፈዘዘች
    አለምወርቅ ጀምበሩ የቴዎድሮስ ልጅ ነች
    ታሪኳ ሲመዘዝ
    ከወዲህ ወደ ቋራ በአርማጭሆ በኩል የራስ አሞራው ናት
    እንዲህ በሁመራም የቢትወደድ ልጅ ናት
    ወዲህ በጋይንትም በበለሳ በኩል የእነ አጂሬ ልጅ ናት
    የፋኖዎች እህት የደረጀ በላይ የእነ አረጋ እህት አረጋ
    አለባቸው
    ሀገርን ከጠላት የታደጉ ናቸው
    የአጋየ አድማስ እህት የአጋየ ጀግናው
    በቀኝ እጁ ብሬን በግራ እጁ ቦምብ ሚወረውረው
    ይች የጎቤ ልጅ የአባ ጃዊ ጎቤ
    ይች ባለ ማተብ ይች በጌምድሬ
    በል በቃ ሸልማት ይችን ኩሩ ቆንጆ
    ካልተዋሸ በቀር ካልጠፋ ኮሮጆ
    ማንም አይወስደውም ያለምወርቅን በልጦ
    ካባዋን አልብሳት ጀኖ ደርብላት
    ይች የጎንደር ቆንጆ ያ ባጃሌ ልጅ ናት
    💚💛❤🙏
    ፋኖ ሚኪያስ አዳነ
    ከእስራኤል

    • @marthabezabihzenebe299
      @marthabezabihzenebe299 Před 2 lety +3

      እውነት ነው

    • @dubaix5354
      @dubaix5354 Před 2 lety +3

      ዘሩ ዘርኞች ኢ /ዬ በሉ እስቲ

    • @addisken24
      @addisken24 Před 2 lety +2

      ትክክልነህ

    • @addisken24
      @addisken24 Před 2 lety +9

      @@dubaix5354 አማራ ሲባል ያማችሁአል።አዎ እርሷ የጎንደር እንቁ ምርጥ አማራነች።ዘር የሌለው የለም እርሷም የወጣችበት ዘር አላት።ኢትዮጵያ የጋራ ሀገር እንጂ ዘር ብሔር አይደለችም።

    • @user-gl1rl3hx9t
      @user-gl1rl3hx9t Před 2 lety +3

      @@addisken24 ትክክል

  • @berrythegreat1568
    @berrythegreat1568 Před 2 lety +1

    ኤልያስ መልካ በምድር ደግ ሰው መልካም ሰዉ ጥሩ ሰው ርሕሩሕ ሰው ነበርክ ስለ ጥሩነትህ ቃላት የለኝም ቸሩ አባታችን ሰማያዊ አባታችን በገነት ያኑርህ

  • @amanuelgoitom329
    @amanuelgoitom329 Před 2 lety +8

    Wowww every Nice vocalist 🇪🇷👍🙏🇪🇷

  • @yimer2543
    @yimer2543 Před 2 lety +20

    "ወይ ምጣ ወይ ልምጣ"የኤሊያስ መልካን የውስጥ ጥያቄ በግጥም እና ዜማ በግልፅ የነገረን ይመስለኛል ኤሉየ ሁሌም አንረሳህም😘✅

  • @bayeteketay511
    @bayeteketay511 Před 2 lety +16

    ምርጥ ኢትዮጲያዊ ሴት ነሽ ጭምቅ ያለሽ ከነ ዝግጂትሽ

  • @abdelwasiseid2825
    @abdelwasiseid2825 Před 2 lety +3

    ወይ ምጣ ወይ ልምጣ'' በተሰኘ ግሩም ዜማ የተዳፈነውን እሳት ዳግም ቆሰቆሰችው።she remember me long times my life
    i am happy when she wins
    thanks for fan samrot

  • @EAZy-Bzy
    @EAZy-Bzy Před 2 lety +52

    I am sure most of my generation enjoyed Elias' works without knowing the magic man behind, hope AAU or Yared Music School will take this and script his genuis for teaching the talented

  • @MIkItube
    @MIkItube Před 2 lety +17

    ዘመንን ወደሁላ ያሳየችን ምርጥ ልጅ።

  • @zenapzez460
    @zenapzez460 Před 2 lety +249

    ገና መዚቃውን ሳይጨርስ ለዚች እንቁ ቀድሞ ላይክ ሚያደርግ እንደኔ ብቃትዋ ይገርማል

    • @user-qs1pv5
      @user-qs1pv5 Před 2 lety +1

      ene demo hule sisemat eyalekisku new😢

    • @tamrrseid8557
      @tamrrseid8557 Před 2 lety

      ልክ እንደኔ ዘፈኑን ሳልሰማ ነው ላይክ የማደርገው

  • @kibruyisfaagonafir2304
    @kibruyisfaagonafir2304 Před 2 lety +2

    እ/ር አብዝቶ ከዚህ በላይ ይስጥሽ፡፡ እኔ ከምንም በላይ አድናቂሽ ነኝ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያቀርብሽ፡፡ በአለባበስሽም በጣም የሚደነቅ በተለይ አለባበስሽ ወደፊትም አሁንም በረጅም የቀሚስ አለበበስሽን ቀጥይበት ትክክለኛ የበፊቷ የኢትዮጵያ አለባበስ፡፡ በእኔ አይታ100%

  • @Ethiohabtina
    @Ethiohabtina Před 2 lety +18

    She makes me cry again. So touching. Amazing sirkrik dimts.

  • @sisaylemma4118
    @sisaylemma4118 Před 2 lety +11

    OMG, what dynamic muscail does this Girl. Excellent performance

  • @sisodire1209
    @sisodire1209 Před 2 lety +26

    You are so talented and blessed with gorgeous voice. In few years you will be an iconic figure in ethiopian music.

  • @berrythegreat1568
    @berrythegreat1568 Před 2 lety +2

    ያለምዬ ድምፅሽ ልክ እንደ ፓፓያ ጭማቂ ነው የሚጣፍጠው።
    ደስ ስትይ ሙሉ አልበምሽን እንጠብቃለን
    እስካሁን ካየሁዋቸው new Generation ያለምዬ ቁጥር ፩ Thank you ❤

  • @gemechuadugna6006
    @gemechuadugna6006 Před 2 lety +11

    respect for this beautiful sound plus great respect for iconic Eliyas Melka for those lyrics and melody rest in peace all time great artist

  • @senaitmiheretie7643
    @senaitmiheretie7643 Před 2 lety +7

    እውነትም የአለም ወርቅ ትችያለሽ 👏👏👏❤️❤️❤️

  • @dessalegntassaw2796
    @dessalegntassaw2796 Před 2 lety +6

    ቢያንስ ቢያንስ ባትንቁን !!! ከየሰፈራችን፣ከየመንደራችን፣ከየቀበሌአችን፣ከየወረዳችን ከየትም ቦታ መጥተው እንደልባቸው
    እየኖሩ ወገናችን እየበዘበዙ እየጨቆኑ በድህነት እና በጥቃት አረንቋ ከትተውን ከቆዩ በኋላ በሰላም ተዝናንተው በእኛ ላይ
    እየሳቁ ስጋቶች ናቸው እያሉ የሚያስረሽኑን ጠላቶች በአገራችን እየለሙ ፣እየከበሩ አገሬው እየታፈነ፣እየተገደለ
    አማራ ሁሉ ፋኖ ነህ እየተባለ በጎርፍ፣በብርድ፣በሃሩር ፣በአውሬ ተከቦ ትዳሩን እና ልጆቹን ላሞራ ሰጥቶ ዱር ከገባ እስከመቸ
    እንዘልቀዋለን ? ለነዚህ አሳዳጅ ከሃዲዎች አጸፌታዊ ምላሽ በየቀበሌአችን እናካሂዳለን ???

  • @mulualemmhretu
    @mulualemmhretu Před 2 lety +66

    wow she is so talented !. I can't stop listening her music . Thank Fana Lamrot for bringing such musicians even you disappointed us in the first final result in SMS problem .

  • @technewflix
    @technewflix Před 2 lety +4

    እንዳንቺ አይነት ድንቅ መዚቀኛ በእድሜዬ ስላየሁ እጂግ በጣም ደስ ብሎኛል!!!
    ሙዚቃሽን በጉጉት እየጠበቅሁ ነው!

  • @UserUser-yb1vi
    @UserUser-yb1vi Před 2 lety +3

    የሚገርም ስጡታ ዘፈን ባይበረታታም ግን ስንቴ ሰማሁሽ የምር በርች ገበዘ ፈጣሪ ይርዳሽ 1 ቢያሱጡሽ ደሞ ደስታዬ ይበልጥ ይጨምራል 😘😘😘😘😘😘💚💛❤️ እቆ ያገሬልጅ

  • @user-wm2wb8xy7x
    @user-wm2wb8xy7x Před 2 lety +11

    ከመሰሉ ይልቅ የአለም ወርቅ ምርጥ አርጋ ተጫውታዋች ሰውነቴን ነው የነዘረኝ
    መስዬም ምርጥ ብቃት ያላት ድምፃዊ ናት

  • @hondbhondc2632
    @hondbhondc2632 Před 2 lety +8

    I’m lucky ☺️ to grow up with this kind of song 🎧 . Love 💕 it

  • @iamfano1102
    @iamfano1102 Před 2 lety +15

    በእውነት የዚች ልጅ ድምፅ አጀት ይበላል

  • @tsedalukebede202
    @tsedalukebede202 Před 2 lety +19

    ዳኞቹን አደንቃለሁ 🙏🏽ምን ያህል ከሙዚቃ ጋር ያላቸውን ቀረቤታ ሁኔታቸው ይገልጻል ለሙያ ማልቀስ ሲያንስ ነው 🙏🏽🙏🏽

    • @user-si3um2jy9u
      @user-si3um2jy9u Před 2 lety +4

      ስለሙዚቃው ብቻ ሳይሆን የኤልያስ መልካን ስቃይ በግጥም ውስጥ ስላለ ነው መቼም እያለን አንጠያየቅም

    • @MickyCryptoC
      @MickyCryptoC Před 5 měsíci

      You misunderstood.....ዳኞች እንደዛ የሆኑት ከሙዚቃው ጀርባ ስላለው ድንቅ ሙዚቀኛ እንጂ

  • @walexyone5214
    @walexyone5214 Před 2 lety +17

    ኤሊያስ መልካ 😢😢😢

  • @wesoneamaha4804
    @wesoneamaha4804 Před 2 lety +1

    ያለምወርቅ በጣም ደስ የሚል ድምፅ አለሽ ከአለባበስሽ ጀምሮ አስከ መድረክ አያያዝሽ በጣም ልዩ ነው

  • @asmeromokube1162
    @asmeromokube1162 Před 2 lety +7

    እዚ ዘፈንቢሰማትበት ግዜ ከእንቅልፈ ነው የሚያስነሳኝ ፡እስኪ ኣሁን እንደዚ ድምጽ ኣልሰማሁትም ፡ኤርትራዊ ነኝ ፡ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ሰላምይሁን

  • @assaminewharegewoin19
    @assaminewharegewoin19 Před 2 lety +4

    እንባዬን እንዴት ልቆጣጠር፣ ኤልያስ መልካ ነብስህ በሰላም ትረፍ፣ ያለምወርቅ እናመሰግናለን።

  • @ZemaBeats
    @ZemaBeats Před 2 lety +13

    Future ETHIOPIAN MUSIC queen. Again amazing voice🎶😍

  • @samhabesha9251
    @samhabesha9251 Před 2 lety +4

    ዋው ያለምየ የኔ ኩሩ በጣም ልዩ ነሽ 👌 🥰ምንግዜም ምርጫየ ነሽ የኔ ልዩ 👌ትልቅ ደረጃ እንደምትደርሽ ምንም ጥርጥር የለኝም 🥰የኔ እናት 😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘😘🥰🥰

  • @g.k.9004
    @g.k.9004 Před 2 lety +20

    This is a special lady with a special voice - I am carried back in time every time I listen to this melody. I don't even know what or who she reminds me of. I just feel at home and homesick at the same time. ወቸ ጉድ!!

  • @meniliksolomon5833
    @meniliksolomon5833 Před 2 lety +5

    she is smart talented በቃ በጣም ምርጥ ተሰጥኦና ድምፅ።

  • @woinshetezewede1675
    @woinshetezewede1675 Před 2 lety +5

    ያሣለፍኩትን አስታሰወሠችኝ 😭😭😭❤❤❤🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

  • @EAZy-Bzy
    @EAZy-Bzy Před 2 lety +12

    I have to admit that the judges pitched well to Elias' untold story. I listened the song here first and fell in love with it since. The lyrics is just beyound words.

  • @sarahdemesew370
    @sarahdemesew370 Před 2 lety +3

    I don't watch (ፍና) however I had to watch this and she is very talented and like her style.
    I think she will go a long way and she is gifted by God .
    Peace for Ethiopia.

  • @Addisababa1
    @Addisababa1 Před 2 lety +5

    አንድን ሙዚቃ ሊያስወድድ የሚያስችል ሁሉን መሆን የሚችል ድምፅ። ይሄን ዘፈን እንደ አዲስ እንድወደው በድጋሚ ያስገደደኝ ድምፅ

  • @addisermyas8446
    @addisermyas8446 Před 2 lety +1

    እናመሰግናለን ምርጥ የክረምት ስጦታ። እንቁላሉን እንዳትርሺ

  • @user-og1bv3cn8e
    @user-og1bv3cn8e Před 2 lety +6

    ኤልያስ መልካ የሚታወስበት ምርጥ ስራ ነብስ ይማር

  • @EAZy-Bzy
    @EAZy-Bzy Před 2 lety +4

    ወይ ምጣ ወይ ልምጣ እንዴት አይነት ለዛ ያለው የኤልያስን ቱባ ባህልን አክባሪነት:: እናም ይህ ድምጽ ደግሞ ከዋናዋ ዘፋኝ ተቀብላ አጎላችው 🙏🙏🙏

  • @getshtube8058
    @getshtube8058 Před 2 lety +43

    እራሷ መሰሉ መድረክ ላይ እንዳንቺ perform አታደርገዉም::አስደማሚ!

    • @marmar803
      @marmar803 Před 2 lety +1

      I agree 100% !!!

    • @marmar803
      @marmar803 Před 2 lety

      I Agree 💯% !!!

    • @marmar803
      @marmar803 Před 2 lety +2

      መሰሉማ የፍቅር ( romantic) ክሊፕ ስርታለት አረፈችው 😥!!

  • @tesfayesemagn9045
    @tesfayesemagn9045 Před 2 lety

    ብርሀን ማላ ስላየውህ ደስ ብሎኛል ።የአለም ወርቅ ሁሌም ወርቅ ነሽ

  • @lubabamuhamed7704
    @lubabamuhamed7704 Před 2 lety +1

    ወየው የሠውየውን ታሪክ ከሠማሁ በሗላ አልቅሼ ልሞት ነው 😭😭😭😭😭😭😭😭

  • @amywolloatl5762
    @amywolloatl5762 Před 2 lety +30

    ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም አለባበስሽ ድምዝሽ መልክሽ እርጋታሽ ሁሉን የሰጠሽ የሚገርም ነዉ

  • @oromiabiyya1755
    @oromiabiyya1755 Před 2 lety +3

    🖖✋🤚👋🤙እጅግ በጠጣመም ያሳዝናል፤ወይ ምጣ ወይ ልምጣ

  • @melmeja
    @melmeja Před 8 dny

    ከግጥሙ ጀርባ ያለው ትርጉም የገባው ሰው ደም እምባ ነው የሚያለቅሰው! ---- ኤላ ነብስህ በገነት ትረፍ ፤ አሜን!

  • @lovej6750
    @lovej6750 Před 2 lety +4

    ህሞን የሚያቀው እሱ ኤልያስ መልካ ፈጣሪው ነው ያስዝናል I don’t even believe her voice how much strong she surprised me today I see her and I like her 🥹🥹😍😍🥰🥰🥰😘

  • @wasiboy278
    @wasiboy278 Před 2 lety +3

    ለ ራሱ ሳይኖር የሞተ ጀግና 😭😭😭❤️❤️❤️

  • @tofikkedir6564
    @tofikkedir6564 Před 2 lety +6

    የሚገርም ድምፀ መረዋ ናት የድሮወቹን አስታወሰችኝና ሰምጨ ቀረሁ

  • @user-mc9bb7qz3b
    @user-mc9bb7qz3b Před 2 lety +2

    የተወለድኩት ኣዲስ ኣበባ ነው።ያደጉት ግን ኤርትራ ነው።ሙዚቃ ሂወቴ ነው ያደግኩትም በ ኣማርኛ ሙዚቃ ነበር።ይህ ሙዚቃ ብሰማው ብሰማው ኣልጠገብ ኣለኝ አረ ተባረኪ በልዋት።በስደት ነኝ ኋላ ይመልሰኛል ኣልቅስ ኣልቅስ ይለኛል።ይህ ሙዚቃ ለኔ መድሃኒቴ ነው ይህ ሙዚቃ ለማይገባው በጣም ኣዝንለት ኣሎህ።

  • @honestygalor6748
    @honestygalor6748 Před 2 lety +1

    This is one of the best if not the best ever music. Hats off! !!

  • @user-yy4qp7ih2f
    @user-yy4qp7ih2f Před 2 lety +6

    ኤሊያስ መልካን ስለዘከርሽ እናመሰግናለን🙏🙏