ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምን ይላል? በተለያየ ጊዜ የተላለፉ ውግዘቶች ክህነትን በሙሉ አስረዋል? እነሆ ልዩ ዝግጅት!

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2024
  • #መልአከ_ብርሃን_ቀሲስ_አስተርአየ_ጽጌ #ክብር_አቶ_ዘውገ_ግድሉ #መምህር_ፋንታሁን_ዋቄ #ዮሴፍ_ከተማ
    የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን ከአቶ ዘውገ ገድሉ ጋር ባደረግነው ተከታታይ ቆይታ በተለይ አቡነ ተ/ሃይማኖት በእነ አቡነ ጳውሎስ እና አቡነ ማትያስ ላይ፤ አለቃ አያሌው ታምሩ በአቡነ ጳውሎስ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት ታሪክ አንስተናል። ይህም ብዙ አነጋግሯል። ዛሬ ሳምንት በገባነው ቃል መሠረት ይህን ጉዳይ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከሕግ እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የምንዳሥሠው ይሆናል።

Komentáře • 16

  • @Eyobs90
    @Eyobs90 Před 16 dny

    አሜን!!
    እግዚአብሔር በቅንነት ለቤቱ የሚቀኑትን፣ የሚተጉትን ያብዛልን!!

  • @YonasYoni-bz3kg
    @YonasYoni-bz3kg Před 25 dny

    አሜን አሜን አባታችን

  • @user-nx5fx3ob8d
    @user-nx5fx3ob8d Před 26 dny

    ትክክል አቶ/ ዘውገ

  • @Belay-lm4sl
    @Belay-lm4sl Před 26 dny +2

    በጣም ደስ የሚል ውይይት ነው ቀጥሉበት እግዚአብሔር ይርዳን

  • @daniminneapolis
    @daniminneapolis Před 25 dny

    IT WAS VERY INTERESTING
    THANK YOU ALL YOU GUYS 🙏✌️👌💯

  • @MilkiiAyana
    @MilkiiAyana Před 25 dny +1

    በጣም ጥሩ ውይይት ነው። ንቅናቄው ከጥቢያ ነው መጀመር ያለበት። ቢደጋገም እንደ እኔ የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል። የሃይማኖት፣ የሃቅ ትግል ነው የያዛችሁት እ/ርም ያግዟችኋል። በርቱ።

  • @abugida794
    @abugida794 Před 23 dny

    ይገርማል ለካስ" ከተቆረጠ ዛፍ "ነው ተጠልለን ያለነው😢😢😢😢አምላኬ ሆይ ይኸ ዛፍ እዳቆጠቁጥ እኛ ልጆችህ እንድንጠለል የምታደርግልን መቸ ይሆን😢😢😢

  • @user-nx5fx3ob8d
    @user-nx5fx3ob8d Před 26 dny +2

    ስለ ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘት ማስተላለፍ እያነሳችሁ ነው:: ግን ለምእመኑ ግልፅ እንዲሆን በትለይም ምንም ስለውግዘቱ በቂ ግንዛቤ ለሌለው በእውነትና በትክክል አለቃ ይወገዙት ቀሲስ እንዳሉት ብሳቸውና በአባ ጳውሎስ ውዝግብ ወይም በግል ጉዳያቸው አይደለም::
    አባ ጳውሎስ (ጳጳስ ይባሉ የነበሩት የሲኖዶሱን መሰረቱን ንደው አበው ያስቀመጡልልን ስርአት ሽረው እራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ ተክተው ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለ አባ ጳውሎስ(ጳጳሱ ነው ብለው እራሳቸውን ሲሾሙ አብረዋቸው (ተስማምተው) የፈረሙ ጳጳሳት እንዳሉ ሁላችሁም ታውቃላችሁ::
    ይህንን መመስከር የእያንዳዱ የተዋህዶ ልጅ ግዴታውም ነው:: ስለዚህም ይህንን ምስኪን ምእመን ጉዳዩን በትክክል ተናግራችሁ ማሳወቅ ሲገባ ዋናውን የውግዘቱን ምክንያት አሁን እድል እያላችሁ ተ ና ገ ሩ
    እንቢ ካልን ፈራጁ ፍርዱ ይፈርዳል ጅምሩን እያየንም ነው

  • @rahelassefa1766
    @rahelassefa1766 Před 20 dny

    አቡነ ተ/ ሀይማኖት በዛ ዘመን እግዚአብሔር የለም በሚባልበት ጊዜ በሳቸዉ ፀሎት ነዉ ኢትዮጵያ በዚያን ጊዜ ከነበረዉ መጥፎ ነገር የተጠበቀችዉ!

  • @yoannesalta3930
    @yoannesalta3930 Před 25 dny +1

    ...ከዚያም ለዓዲስ አመት መስከረም 1, 1987 ዓ.ም ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ወደ ሮም ሄደው፡ በጊዜው የሮም ቫቲካን ጳጳሳት ጋር አብረው ተመግበው፡ ከእነሱም ጋር ቡራኬ ተቀብለው መምጣታቸው ተነገረ። በጊዜው የነበረው የቫቲካን ሬድዮ የአማርኛው አገልግሎትም የነበረን ሁኔታ በቀጥታ ስርጭት መስከረም 8,1987 ዓ.ም ዘገበው።
    የአለቃ አያሌው ተማሪወች ከዚያም ቀጥሎ የተከሰተውን ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ "የጥቅምት ጉባኤ ላይ 'እስክንድርያ እናቴ ፥ ማርቆስ አባቴ' የሚለው እንዲቀር እና እሳቸው(ፓትርያርኩ) ያደረጉትም ጉዞ፡ በቤተክርስትያኒቱ የክብር መዝገብ ላይ እንዲጻፍ የሚል አጀንዳ ተያዘ"።
    አለቃ አያሌውም ይህንን ተቃውመው "ከሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ብዙ አመት የቆየ ውግዘት አለ። እርሶ ያደተጉት ጉብኝትም በቤተ ክርስትያኒቱ የክብር መዝገብ ላይ አይጻፍም። እርሶስ የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንን እንዲጎበኙ እና በጸሎትም ከ እነሱ ጋር እንዲሳተፉ ማን ፈቀደልወት?" በማለት ተናገሩ። አባ ጳውሎስም መልሰው ብዙ ደስ የማይል ነገር ተናገሯቸው። አለቃ አያሌውም ነገሩ ሁሉ እንደተበላሸ ስላወቁ በጊዜው ለሲኖዶሱ አባላት ሁሉ ፡ በአካልም፥ በፖስታም በየ አድራሻቸው ያነሷቸውን ነጥቦች አቀረቡ።
    ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እየቀጠለ እንዳለ፡ አንድ አመት ከ ሰባት ወር አካባቢ እንዳለፈ ጥር ወር ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና የውጭ ግንኙነት" የሚል አርዕስት ያለው ብዙ ኑፋቄ እና ክህደትን በውስጡ የያዘ መጽሀፍ በፓትርያርኩ አባ ጳውሎስ ሥም ታትሞ ወጣ።
    ከዚያም ጥር 24 በደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስትያን ላይ አለቃ አያሌው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ "ሰውየው ኃይማኖት ክደዋል፥ ካቶሊክ ሆነዋል። ከዛሬ ጀምሮ አውግዤያለሁ" አሉ። ነገሮች ሁሉ ተደበላለቁ። ከካህናቱም ከምእመኑም ወገን በሁለት ጎራ ተከፈለ። ምዕመኑ ማጉረምረም ጀመረ። ነገሮች ሁሉ በፍጥነት በየቦታው መሰራጨት ጀመሩ።
    እነ አባ ገሪማን ጨምሮ በፓትርያርኩ ወገን የሆኑት፡ ከአለቃ አያሌው እና ሃሳባቸውን ከሚደግፉ ሁሉ ጋር እልህ መጋባት ጀመሩ።
    ሚያዝያ 17 ቀን እነ መልአከ ታቦር ዘሩ ተሾመ፣ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ፣ መምህር ሀብተማርያም ተድላ እና መልአከ ሰላም ዳኛቸውን የያዘ "የሰላም እና ቅሬታ አስወጋጅ ኮሚቴ" የሚባል ቡድን ተቋቋመ። አላማውም በአለቃ አያሌው ጉዳይ ላይ መመርመር እና ክስ መስርቶ ውሳኔ ማሳለፍ ነበር።
    ከዚያም የተቋቋመው ኮሚቴ ከሚያዚያ 1 ቀን ጀምሮ ከሥራ ተባረካል የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለአለቃ አያሌው ሰጣቸው። አለቃ አያሌውም ለ35 ዓመት ካገለገሉበት የሊቃውንት ጉባኤ አባልነት እና ዋና ሰብሳቢነት እስከመጨረሻው ታገዱ።
    ወቅቱ የግንቦት ሲኖዶስ ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት 6 የሚካሄድበት ጊዜ ነበር።
    የአለቃ አያሌው ተማሪወች ሲገልጹ፤ ሚያዚያ 30,1988 ዓ.ም ሲኖዶሱ "ቤተክርስትያን እስካሁን ስትሰራባቸው እና ስትመራባቸው የነበሩ ህጎች በሙሉ በዚህ ህግ እና ደንብ ተሽረዋል በማለት ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ነው የሚል አምልኮተ ጣኦትን አወጁ" ይላሉ።
    አለቃ አያሌውም "ይህንን ህግ የፈረማችሁ 35 ጳጳሳት በአስቸኳይ ይህንን ህግ አሻሽላችሁ፡ አባ ጳውሎስን ከሥልጣን አንሷቸው፥ ምክንያቱም በሥጋ ወደሙ የማሉትን መሃላ አፍርሰዋል፤ የቤተ ክርስትያንን ሥርዓት እና ህግ ተላልፈዋል፥ ቤተክርስትያኒቱንም የካቶሊክ ምርኮኛ አድርገዋል" በማለት ተናገሩ። ሊሰሟቸው ግን አልፈቀዱም።
    አለቃ አያሌው ሰኔ 27, 1988 ዓ.ም ለሲኖዶሱ አባላት የመጀመሪያ ቃለ ግዝታቸውን ሰጡ። የቤተ ክርስትያናት፣ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪወችን እኚህ ሰው ሃይማኖት የለወጡ፥ የካዱ ስለሆኑ በጸሎተ ሃይማኖት ስማቸውን እንዳትጠሩ ብለው አወገዙ።
    ህዝቡንም ገንዘብ እየሰጣችሁ፣ ዳቦ እየደፋችሁ፣ ጠላ እየጠመቃችሁ፣ ሲወጡ ሲገቡ ቁጭ ብድግ እያላችሁ ሃይል የሆናችኋቸው እናንተ ናችሁ። ስለዚህ በእነሱ እጅ እንዳትሳለሙ፣ በእነሱ እጅ እንዳትቆርቡ፣ በ እነሱ እጅ ምስጢር እንዳትሳተፉ በማለት አወገዙ። ይህንን ስታደርጉ ምንድነው ጥያቄያችሁ ብለው ወደ እናንተ እጅ ይመጣሉ። ከዚያም ጥያቄያችሁን ሲቀበሉ ቤተ ክርስትያናችሁን ትቀበላላችሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ይህ ሊሆን አልቻለም።
    ከዚያን ጊዜ ጀምረው እስከ እለተ እረፍታቸው፡ በመኖሪያ ቤታቸው ጉባኤ ዘርግተው በማስተማር ቆይተዋል።
    የተወሰኑ ቤተክርስትያናት እና ገዳማት ግን አባ ጳውሎስ እስካረፉበት እና አዲስ ፓትርያርክ እስከተሾመበት ጊዜ ድረስ ቃለ ውግዘቱን በመጠበቅ በቅዳሴ ወቅት ስማቸን ባለመጥራት ቆይተዋል።
    በዚያ ሰሞን ማህደረ ስብሀት ቅድስት ልደታ ለማርያም በተፈጠረው ሃይማኖታዊ ጥያቄ ምክንያትም በመንግስት አካላ ብዙ ሰወች ህይወታቸውን አጥተዋል። ብዙወችም ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ፡ ሌሎችም ሃይማኖታቸውን ትተው ወጥተዋል። ቤተ ክርስትያኒቱም ለ አንድ ወር ከአስር ቀን ተዘግታለች።
    በሌሎች ቦታወችም የህገ ቤተ ክርስትያን ጥሰትን የተቃወሙ ባህታውያን አባቶች በዚያው በጥይት ተደብድበው እንደሞቱ በወቅቱ የነበሩ ሰወች ይናገራሉ።
    ቀስ በቀስም ቤተ ክርስትያናት ካቴድራል እየተባሉ መሰየም ጀመሩ፣ ተሃድሶ እና ምንፍቅና እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ መጣ፣ ሰንበትን ማክበር እየቀረ፡ ስርዓተ ቤተክርስትያንን መጣስ የአደባባይ ድርጊት ሆነ። ፈሪሃ እግዚአብሔር እየጠፋ፤ ትላንትን አልፈን ዛሬ ላይ ደረስን።
    በዚያን ዘመን በዓላት፣ ስርዓተ ቤተክርስትያን፣ ባህል እና ታሪክን በሚመለከት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ሚድያወች፣ ጋዜጦች እና ልዩ ልዩ ፕሬሶችን ከፊት ገጽ ላይ ያደምቁ የነበሩት ብዙ ሊቃውንትንም ያፈሩት ታላቁ የቤተ ክርስትያናችን እና የሀገራችን ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ነሀሴ 14, 1999 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
    በረከታቸው ይደርብን !!!
    ምንጭ:
    1.ደራሲ ዳንኤል ገብረ መስቀል/ያልተፈታ ውግዘት

  • @yaredyilma9812
    @yaredyilma9812 Před 20 dny

    ከብጹእ ሊቀጳጳስ አቡነ ተክለኃይማኖት እና አለቃ አያሌው ውግዘት እንደ መነሻ ብትወያዩም ውግዘት መነሳት ካለበት በመጀመሪያ ከግብፅ (እስክንድርያ) በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ውግዘት ብትነሱ እንዴት ጥሩ ይሆን ነበር።

  • @asresbitew7105
    @asresbitew7105 Před 25 dny

    የተጠየቀትን ጥያቄ በቀጥታ እና በግልፅ ከማብራራት፣ ከማስረዳት ይልቅ ቄስ አስተርአየ ጽጌ ወደ ግለሰቦች ድርጊት ትንተና መዞራቸው ያልተገባ አካሄድ ነው። ለማናቸውም በአገራችን ኢትዮጵያ የገባብን ዝብርቅርቅ ኹኔታ በእንዴት ያለ አኳኋንና መቼ እንደሚሻሻል እጅግ አሳሳቢ ነው።

  • @yoannesalta3930
    @yoannesalta3930 Před 25 dny

    አዎ ለታሪክ ትተው አልፈዋል አለቃ
    ጥያቄ ፡ እንግዲህ ወደ ሥራዎት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤት ወስኖዎበታል፡፡ መንፈሳዊ መብትዎን ለማስከበር ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረቡት ጥያቄ አለ?
    ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ ሲመልሱ ፡
    ከዚህ በፊት ስለ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለሲኖዶስ ያቀረብኩት ጥያቄ ታፍኗል፡፡
    አሁን እንዳላቀርብ ቀደም ሲል የነበረው ሲኖዶስ ፈርሶ አባ ጳውሎስ የሾሙት የሮም ቤተ ክርስቲያን ቅኝ ግዛት ሲኖዶስ ነው ያለው ለእርሱ ማቅረብ አልችልም፡፡
    ጊዜ አጠብቃለሁ ፡ አለበለዚያም ለታሪክ ሰጥቼው አልፋለሁ አሉ፡፡ደም አልባ ሰማእት ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው

  • @belayhayleab249
    @belayhayleab249 Před 25 dny

    እንደ ዛሬ ደባሪ ውይይት አድርጋችሁ አታውቁም አባ አስተራዬ ጽጌ ቀጣፊ ሰው ነው: ተክለ ኃይማኖትን አውግዞ ሌባውን ማትያስን የሚያደንቅ? ቀላማጅ ቄስ :
    ረጅም እድሜ ለፋንታሁንና ለዘውገ : ሞት ለሌባ ድብተራ