#ተሳስቼ_ነበር

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 17. 05. 2024
  • የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇
    / nikodimosshow
    ፕሮግራማችንን እየተከታተላችሁ ገንቢ አስተያየታችሁን ሁል ጊዜ ስለምትለግሱን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ፡፡
    This Video Clip is Dedicated Only to Nikodimos Show Channel /Tigist Ejigu/!
    Subscribe today for latest Videos Here:- / nikodimosshow
    Facebook:- / nikodimosshow
    Instagram:- / tigisttg
    Awtaru Kebede,Ethiopia,Ethiopian Gospel Song,Amharic Gospel
    © Copyright:- #Tigist Ejigu /Nikodimos Show/ 2024

Komentáře • 314

  • @eyobgetachew8148
    @eyobgetachew8148 Před 2 měsíci +72

    ትግስት እንዳንቺ ሚዲያውን ለጌታ ክብር የሚዋጁ ጌታ ያብዛልን ተባረኪ።

    • @tatekabuye6486
      @tatekabuye6486 Před 2 měsíci +2

      ፓር ዳን እንዳንተ ያሉ ቅዱሳንን እግዚአብሔር ያብዛልን ፤በእውቀትና በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ስለምታገለግል ያስነሳህንና የቀባህን እግዚአብሔር አመሰግናለሁ። ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክ። አንቺ ብርቱ ሴት አንቺንም ሳላመሰግን አላልፍም። ቲጂ ዘመንሽ ይባረክ!

  • @mitselal
    @mitselal Před 2 měsíci +26

    ፓስተር ዳን ሰላየሁህ ደስ ብሎኛል ፣ እኔ የማቅህ ልጅ ሆኜ ቤተሰቦቼ የከታተሉህ ነበር ቢቢድዮ ካሴት ስብከቶችህ ን በ አስመራ ከተማ፣ እህቴ ታማ መራመድ አትችልም ነበር እና እስራኤል ሆነህ ያገለገልከውን ስብከት እየሰማን እያለ በቅፅበታዊ ፈውስ መጣ መራመድ ቻለች፣ ሁሌ አስብህ ነበር የት ነው ያለው ብዮ፣ ስላየሁ ደስ ብሎኛል ፣መጉስህ እንዳለ ነው፣ ዘመንህ ይለምልም፣ ቲጂ ተባረኪልን ሰላቀረብሽልን፤፤

    • @user-cj2li2gy9h
      @user-cj2li2gy9h Před 2 měsíci +1

      Wow ደስ የሚል ምስክርነት ጌታ ኢየሱስ ይባረክ❤❤❤❤

    • @senaitsolomon2737
      @senaitsolomon2737 Před 2 měsíci

      Me too

    • @EldanaTewelde
      @EldanaTewelde Před 2 měsíci

      Wawwww amennnnn ❤❤❤❤❤❤ buzu gzie endezi mskrnet etebqalew ena malet qal stakafl fews hone ehie mezmur sizemer fews hone yemil neger hyaw mskrnet betame yaxenalu leqalu degmo kef yadergalu ena slezi mskrnet gietan amesegnalew mknyatu yefews program sayhon qal singer fews nsha lewengel menesasat bexega mebertat bemenfes momolat des ylal ye egziabhier mengst India Nat be nggr bca sayhon behaylm chmr Nat ena tebareku❤❤❤

  • @alazarshalom2198
    @alazarshalom2198 Před 2 měsíci +59

    ሲያወራ ዉሎ ቢያድር የማይሰለች የእግዚአብሔር ሰው

  • @bereketgetu1081
    @bereketgetu1081 Před 2 měsíci +45

    ፓስተር ዳን ስለሺን ሳስብ ወደ አሀምሮዬ የሚመጣው “የተከፈተ ሰማይ” የሚለው ስብከት ነው። አሁንም በተከፈተ ሰማይ ስር ስላየዋቸው በጣም ደስ ብሎኛል።

    • @ritafiorentino8721
      @ritafiorentino8721 Před 2 měsíci +2

      እኔም እና ልጅ ሆኜ አማኑኤል አሞፅ

    • @sileshisisay3387
      @sileshisisay3387 Před 2 měsíci +1

      የሰይጣን አሠራሮች የሚለውን ትምህርት መቼም አልረሳውም።

  • @dao-107
    @dao-107 Před 2 měsíci +11

    የሀገር መሪ ወይም ጀነራል ሆኖ ቢሆን ትውልድን ያድስ ነበረ … ፖስተር ዳን ለኢትዮጵያ ሰራዊት ..በተለየ ሁኔታ ወንጌልን ብታደርስ …❤

  • @birhanusintayehu9397
    @birhanusintayehu9397 Před 2 měsíci +23

    በክርስቶስ የተሰራ ማንነት ! አቤት ብስለት !አቤት ትህትና ቀን ሙሉ ብደመጡ አይሰለቹም!!! ተባረክ ፓ/ር።

  • @user-od1mg8qx8t
    @user-od1mg8qx8t Před 2 měsíci +12

    ብዙ የተጠቀምኩበት አገልጋይ አሁንም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብታውቅበት ብዙ ልትጠቀምበት የምትችል እግዚአብሄር እውቀት የጠቀጠቀበት አገልጋይ ተባረክ የእግዚአብሔር ሰው

  • @samitefery5580
    @samitefery5580 Před 2 měsíci +17

    ከሰው ውስጥ የማይጠፋ እና የማይሰለች የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ተባረኩ።

  • @Sam-xx3tu
    @Sam-xx3tu Před 2 měsíci +11

    እጅግ ጌታ የረዳህ ሰው እንደሆንህ አየሁ ክርስቲያን ያለው ነገር ሁሉ ቢወሰድ ክርስቶስ በእርሱ እንደጎላ ይቀጥላል ቅንነት ግልጽነት ተባረክ

  • @lyonnaise6395
    @lyonnaise6395 Před 2 měsíci +61

    የመጀመሪያ ሰው ነኝ ላይክ ተመልካች ያደረኩት ዛሬ

  • @kidanhabtu2939
    @kidanhabtu2939 Před 2 měsíci +30

    ፓስተር መርገም መስበር ከሚለው ትምህርት ጀምሮ እከታተለዋለሁ ዛሬ ድረስ መንፈሱ ሳይወረድ የገለገለ የጌታ ባሪያ ተባረክ እወድሀለሁ

  • @goldenshadow1968ec
    @goldenshadow1968ec Před 2 měsíci +24

    ሥተት አልባ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ብቻ ነው።ተባረኩልኝ❤❤❤❤❤❤❤

  • @kalkidanTeshomeWoldesilase
    @kalkidanTeshomeWoldesilase Před 2 měsíci +14

    የተወደድሽ የጌታ ፀጋ ከመንፈስሽ ጋር ይሁን!

  • @meseretsemeani360
    @meseretsemeani360 Před 2 měsíci +30

    ፓስተር ድሮ ልጆች ሆነን እሳችው የሰበኩትን ስብከት ካሴት መሬት አንጥፈን ልክ በመሃከላቺን አንዳለ ሆነን ነበር የምናዳምጠው ::ታማኝ አገልጋይ

    • @tinatinu8009
      @tinatinu8009 Před 2 měsíci +1

      እውነት ነው እኔደው በልጅነቴ መልአክ ይመስለኝ ነበር በጣም የምወደው የእግዚአብሔር ሰው ነው

  • @nogate9562
    @nogate9562 Před 2 měsíci +4

    ለመጀመርያ ጊዜ መንፈሰ ቅዱሰ የተሞላሁት እና በአዲሰ ቋንቋ ደንገት መናገር ምን እንደሁን ያወኩት ትምህርቱን በካሴት እየሰማሁ ነበር በጣም የተባረክ ሰው ነው

  • @Chris-Alone
    @Chris-Alone Před 2 měsíci +2

    እግዚአብሔር ይባርክ ፓስተር። ቲጂ አይወሰድብሽ ደስ የሚል አቀራረብ ነው

  • @Sr.AsterMathewos
    @Sr.AsterMathewos Před 2 měsíci +6

    እበክሽ ደዊት ፈስልን አቅርብን
    ስላንቺ ኢየሱስን አመሰግናለሁ

  • @user-en7ho9dj4d
    @user-en7ho9dj4d Před 2 měsíci +8

    በህይወቴ በጣም የማከብረውና የምወደውን ሰው ስላቀረብሽ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ በጣም ከድሮ ጀምሮ በካሴት የተቀዱ የሱን ስብከቶች ሰምተን ነው ያደግነው እኔ በጣም ላየው የምፈልገው ሰው ነበር ጌታ ይባርክሽ ጌታ አብዝቶ ይባርከው አሁንም ጨምሮ ጨምሮ የተባረከ ይሁን:: በእውቀት ላይ መሰረት ያደረገ እምነት ፣ መሬት የረገጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ መመሪያ የሚከተል የተረጋጋ ሰው ዘመኑን ሁሉ ኢየሱስን የሚያሳይጌታ ይባርከው ስለ እምነት፣ ስትሮንግ ሆልድ መርገምን መስበር ያስተማራቸውን እስካሁን የማይረሱ ትምህርቶችን ያኔ ደጋግመን በካሴት / በቴፕ / እንሰማው ነበር

  • @barnabaszemene7530
    @barnabaszemene7530 Před 2 měsíci +5

    የታነጽኹበት ቃለ መጠይቅ ነው፤ ጸጋ ይብዛላችሁ!

  • @lamesginkassa8353
    @lamesginkassa8353 Před 2 měsíci +6

    በእውነት ዘመንህ ይባረክ በሀገር ቤት ስታገለግል ባላይህም የተከፈተ ሰማይ የሚለውን ስብከትህን በካሴት በተደጋጋሚ ሰምቸዋለሁ በተለይ የሐዋሳ መዝሙር ቤቶች በየቀኑ ያሰሙት ነበር

  • @medhanitrugato3499
    @medhanitrugato3499 Před 2 měsíci +6

    ፓስተር ዳን ,ስወድህ ስብከትህን ሠምቼ ሠምቼ የማልጠግብህ,አንተና ፓስተር ሀብቴ አዳነ ጌታን የተቀበልኩኝ ጊዜ በጣም ነበር በvideo ካሴት እሠማቹ የነበረው በአካል አላቃቹም እናንተም አታዉቁኝም ግን በህይወቴ ትልቅ ቦታ አላቹ እወዳቸዋለሁ ,የሚገርመው ከሀያ ዓመት በዋላም ድምፅህ ያው ነው በጣም የተባረክ ነህ እወድሃለሁ ,አከብርሀለው

  • @kassuedae4961
    @kassuedae4961 Před 2 měsíci +4

    ጌታ ዘመንዎን ይባርክ የተከፈተ ሰማይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ስብከት ተባረኩ በብዙ ተባረኩ፡፡

  • @abeltesfaye6973
    @abeltesfaye6973 Před 2 měsíci +2

    በድሮ አገልግሎቱ ብቻ ሳይሆን በኮሮና ጊዜ ፓ/ር ዳን ያስተላልፍ የነበረው መልዕክት ከቤት ሳልወጣ እሰማው ነበር በጣም ጠቅሞኛል የጎደለኝ አንዳች አልነበረም። በዚያ ዝግ ዘመን ላይ ለኔ የተለዬ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ!

  • @user-hf8wx7pq6d
    @user-hf8wx7pq6d Před 2 měsíci +4

    ተባረኩ ትልቅ ትምህርት ነው ዛሬ ጌታን እዩ ሳይሆን እኔን እዩ የሚል በዛ ከስር መተካትማ እንደመቀማት ስለሚቆጥሩት አያስቡትም እንዲያውም ማስጨንገፍ ይቀናቸዋል በጣም አሳዛኝ ጊዜ ጌታ ይድረስልን

  • @metasebiaseboka1347
    @metasebiaseboka1347 Před 2 měsíci +10

    tigji አትጠገብ ብለንሻል: ስጦታችን ነሽ

  • @mesfindebebe9572
    @mesfindebebe9572 Před 2 měsíci +4

    በእውነት ጠቃሚ ፕሮግራም ነው አይለውጥ እንደዚህ ጠቃሚ ሰዉ ብቻ ይቅረብ

  • @Abayabay814
    @Abayabay814 Před 2 měsíci +5

    ጌታ ይባርካችሁ! ቀጣዩን በጉጉት እጠብቃለሁ ቲጂዬ ❤

  • @Huluselam-hx5hp
    @Huluselam-hx5hp Před 2 měsíci +3

    ለዘመናት ያንተን ትምህርት አዳምጫለሁ ተምሬያለሁ እግዚአብሄር ሞገስ ሰቶሀል
    '' አለአይደለ'' የምትላት ቃል በጣም እወዳታለሁ
    እግዚአብሄር በጠላቶችህ ፊት ለፊት ራስህን በዘይት ይቀባ አሁንም ሞገሱ እንደጋሻ ይክበብህ
    ረጅም እድሜ ከጠና ጋር ይስጥህ እግዚአብሄር ልጆችህን የልጅ ልጆችህን ከክፊ ነገር ይጠብቅልህ
    ኡሜን!

  • @girmaabriham9043
    @girmaabriham9043 Před 2 měsíci +2

    ቲጂ የምር ጌታ ይባርክሽ። ፓስተር ጌታ ደግሞ ይባርክህ!

  • @pastorberhanubiru4095
    @pastorberhanubiru4095 Před 2 měsíci +8

    ፓስተር ዳን ትልልቀ ነጥቦች አንስቶ መልስ ስለ ሰጠኸን እናመሰግናለን።
    አዘጋጅ ትእግስትም ጌታ ይባርክሽ።

  • @tsionseyoum6760
    @tsionseyoum6760 Před 2 měsíci +3

    What a gentlemen very graceful may God bless you!!! ልቤ እየቀለጠ ነው የሰማሁት ።

  • @godislove9841
    @godislove9841 Před 2 měsíci +6

    I know pastor Dan in the 90s. We were blessed by his teaching when he comes to our church in DC. We missed you.. Praise God for the anoiting and wisdom he put in you. We want to see more of you. Praise our lord Jesus Christ.

    • @livesinusa7116
      @livesinusa7116 Před 2 měsíci

      Me too i know him 90s. he youth to share with us the word of God in city of Atlanta Georgia
      the only change from his physical Appearance is got Bald heiress Doctor Don silesh good to see you. On #TG-Egogu show

  • @girumfantaye8841
    @girumfantaye8841 Před 2 měsíci +2

    ለጌታ ነገር ያለው ፍቅር ቅናት ሁሌም ይገርመኛል ። አስተማሪ ቃለመጠየቅ !

  • @ethiopiannewsofficial6432
    @ethiopiannewsofficial6432 Před 2 měsíci +2

    የእግዚአብሔር ስው ዳን ሳውዝ አፍሪካ በመጣ ግዜ የተናገረው ትንቢት 100% ተፈፅሟል❤::

  • @mihretunikola8
    @mihretunikola8 Před 2 měsíci +1

    እግዚአብሔር እንዳንተ እንድይረገኝ እፀልያለው! በጣም ደስ ያልኝ ነገር ብኖር እግዚአብሔር ሁሌም ሰው አልው! በዝህ በከፋ ዘመን እውነትንና ውሸትን መለየት ከባድ በሆነበት ጊዜ እንድህ ዓይነት ሰው መኖሩ የሚገርም ነው! እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ አንተ ደግሞ እግዚአብሔር ዕድሜህን ያርዝምልህ! እስከመጨረሻ እንትፀናህ እግዚአብሔር ይርድህ! ቲጅዬ ድንቅ ሰው ለምልምልኝ!!!

  • @wakumageleta4782
    @wakumageleta4782 Před 2 měsíci +3

    WOW!!!Dr Dan SilSh በጣም በኣንተ ምስክርነትና ወደ ኢትዮጵያ መምጣትህ እጅግ ኣሰገርሞኛል Truelly አገልግሎትህ ስበከት ህን ኣልጠግበወም።🧑‍🎨 ከልቀረ እንደንተ መሆን ዕድሜና ጤና ይስጥልን long leave❤❤❤

  • @laveleable
    @laveleable Před 2 měsíci +2

    እህታችን ትግስት ጠቃሚ ጥያቄ በመጠየቅ እንድንማር ለምታደርገው ነገር ሀሎ እግዚአብሔር ይባርክቨ። ✝️🙏✝️🙏

  • @godsgloryinternationalmini1938
    @godsgloryinternationalmini1938 Před 2 měsíci +1

    Glory Be To Our God!!! Great Lesson!!! Many More Blessings!!!

  • @LidiyaAshagre
    @LidiyaAshagre Před 2 měsíci +2

    Wow three generation worship same God definatily it is blessing

  • @user-lh9zj5bw6y
    @user-lh9zj5bw6y Před 2 měsíci +2

    ተባረኪ,,,ጌታ,በብዛት,ይባርክሽ,እድሜና,ጤና,ይስጥሸ

  • @user-pk8lw6jq4i
    @user-pk8lw6jq4i Před 2 měsíci +3

    ፓስተር ዳን ስለሺን አዲስ አበባ ሁለት ጊዜ ሲያገለግል አይቼዋለሁ 6ኪሎ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እና ምርጦች 7000 ቤተክርስቲያን ደንቅ ትምህርት አስተምሮናል። 🙏🙏🙏🙏

    • @bayushegame5760
      @bayushegame5760 Před 2 měsíci

      ምርጦች 7000 ቤተክርስቲያን የሚባለው ከምን ተነስቶ ነው ማነው የመረጣቸው ብታሰረዱኝ

  • @user-hm2pv9vb6j
    @user-hm2pv9vb6j Před 2 měsíci

    ፖስር ተባረክ እድሜ ይስጥ እህቴም ተባረኪ

  • @hannameshesha4854
    @hannameshesha4854 Před 2 měsíci +3

    ዋው በሚድያ የምታቀርቢያቸውን ታውቂያለሽ ቲጂዬ ተባረኪ ዘመንሽ ይባረክ። ፓስተር ዳን የተወደድክና የምትናፈቅ የእግዚአብሔር ታማኝ ባሪያ አሁንም ፀጋውን በአንተና በዘርህ ይጨምር !!!!!!!

  • @ayalneshshuke6142
    @ayalneshshuke6142 Před měsícem

    ፓስተር ዳን በልጅነቴ በካሴት ስብከትህን ስሰማ ነው ያደኩት አሁንም በግለት ውስጥ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል ።ሀሰተኛ ነብያትንንና ልምምዶችን በስም ጠርቶ ማውገዝ ከእንተ አባቶች ይጠበቅነበር አሁን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናት ጥቂት ወጣቶች በሶሻል ሚዲያ እየተቃወሙ ቢሆንም እናንተ አባቶች ተቃውሞውን ብትመሩት ከፍተኛ ለውጥ ይመጣ ነበር

  • @user-oy4rn4jo3e
    @user-oy4rn4jo3e Před 2 měsíci +1

    ፓስተር ዳን ቁጭ ብለህ ኢንተርቪ ስትደረግ ራሱ፣ቸርች ውስጥ ቁጭ ብዬ እያደመጥኩ ያህል ነው የተሰማኝ፣ነፍሴ የምትወድህ ምርጥ የእግዚአብሔር ሰውና፣የቃሉ አስተማሪ ነህ።ምናለበት ኢትዮጵያም እያመጣህ ብታገለግል?
    አያት መሆንህን ስለሰማውም በጣም ደስ ብሎኛል።
    እግዚአብሔር ይባርክህ።

  • @weynits571
    @weynits571 Před 2 měsíci +1

    Tigiye GETA ZEBENSH YIBAREK የምታቀርብያችው ኣገልጋዮች ኣባቶች አደንቃለሁ የሚያብረቱ የሚምክሩ የሚገስጹ ጌታ ዪባርካችው በርከታችን ናችሁ❤❤❤

  • @sintayehugalcha7496
    @sintayehugalcha7496 Před 2 měsíci +1

    ፓስተር (ዶ/ር ) ዳን ስለሺን እንዴት እንደምወደው በጣም ወሳኝ የጊዜው ምክርና ትምህርት ነው በጉጉት ቀጣይ ክፍል እጠብቃለሁ ቲጂ አንቺንም ይሠጠን ጌታ ስሙ ይባረክ በርቺ ❤❤❤

  • @mesfinberise3977
    @mesfinberise3977 Před 2 měsíci +1

    የእውነት ስላገኘሁት ፓስተር ዳን ሲለሺ በእኔ ሕይወት ተጽዕኖ ካሳደሩት አገልጋዮች የመጀመሪያ ናቸው በካሴታቸው ብቻ ነው የሚሰማቸው።

  • @user-ho8qf9wq1l
    @user-ho8qf9wq1l Před 2 měsíci

    እህታችን ትግስት ከአፍሽ የምታወጪውን አይደለም በውስጥሽ ያለውን የሚፍለቀለቅ የእግዚአብሔርን ክብር ሳይ ደስታ ይሰማኛል።ብሩክ ሁኚ።ፓ/ር በልጅነታችን ከሩቅ ሆኖ ያበረታታን እውነተኛ ወንድም።በእውነት ቀሪ ዘመኑን በኢትዮጵያ እያገለገለ ቢኖር እንዴት ደስ ይለን ነበር።ወደፊት በእውነት ከአንቺ ጋር አገለግላለሁ።

  • @betypos1003
    @betypos1003 Před 2 měsíci +2

    የሚገርም መሰጠት ነዉ ተባረክ ፓስተር

  • @samymulu7110
    @samymulu7110 Před 2 měsíci +10

    አብዛኛውን በእንግሊዘኛ የሚናገረውን በአማርኛ ይደግመዋል:: ስለዚህ አማርኛ ብቻ ለንትናገሩ ብዙም አላመለጣችሁም::

  • @mitikuelias4491
    @mitikuelias4491 Před 2 měsíci +2

    ባርኮቱን ና ምህረቱን ያብዛልሽ!!

  • @woineabate1201
    @woineabate1201 Před 2 měsíci

    ፓስተር ዳን ስለሺ ስላየሁህና ስለሰማሁህ ደስ ብሎኛል የዛሬ 30 አመት ገደማ ከዮሴፍና ከአስቴር ህይወት ተነስተህ ስለ"ሞገስ" የሰበከውን አልረሳውም የጸሎት አቅጣጫዬን ያስቀየረ ትልቅ ለውጥ በህይወቴ ያመጣ መልእክት ነበረ ተባረክ ቲጂዬ ጌታ ይባርክሽ

  • @mesfinabayneh1956
    @mesfinabayneh1956 Před 2 měsíci

    ፓስተር ዳን እግዚአብሔር ይባርክህ እውነተኛውን የጌታን የአገልግሎት መንገድ ስልሳ ይህን ጊታ ይባርክህ : ህግ ትዕግስት አችንም ጊታ ይባርክሽ

  • @ashewubie3269
    @ashewubie3269 Před 2 měsíci

    የዳን ስለሺ ትምህርቶች ህይወታችንን በእውነት ቃል እንድንመዝን የሚያስተምሩ የመንፈስ ምግቦች ናቸው።

  • @nigussietadesse7502
    @nigussietadesse7502 Před 2 měsíci

    ዛሬም መብልህ ደስ የሚያሰኝ ሃይልህም እንደ ዕድሜህ እግሮችህም በዘይት እንደጠለቁ ናቸው ልክ እንደ አሴር ከብዙ አመት በኋላ ሳገኝህ።ደስ ብሎኛል አሁንም ለምለም!!!!

  • @ferdosousman9649
    @ferdosousman9649 Před 2 měsíci

    ስለፓስተር
    ዳን ስለሺ ጌታ ይመስገን ❤❤ የማልረሳው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ስብከት የተከፈተ ሰማይ የሚል ነበር ጌታ ረዥም እድሜ ይስጥህ

  • @MHailu
    @MHailu Před 2 měsíci +4

    Love love him ❤❤ I praise the Lord for the anointing and God’s wisdom.

  • @Dan77779
    @Dan77779 Před 2 měsíci +7

    ፓስተር ዳን አዲስ አማኝ ሆኘ የሰማሁት የመጀመርያ ስብከትህ የተከፈተ ሰማይ (Open Heaven) የሚል ድንቅ ስብከት ነበር። ከ19 ዓመት በፊት እንግሊዝ አገር መጥተህ ያገለገልከንም አልረሳውም። ጌታ አብዝቶ ይባርክህ። ትዕግስትም ስለትጋትሽ ጌታ ይባርክሽ!!

  • @adebe4130
    @adebe4130 Před 2 měsíci +2

    Pastor Dan . I love your teaching . I remember When I was teenager you were preaching about forgiveness , I watched your video & I forgave one of my neighbor this happened 20 plus years ago .
    . I’m glad you still preaching gospel. All glory be to God. On top of that you didn’t forget Amharic.

  • @biniyamgebrehiwot1522
    @biniyamgebrehiwot1522 Před 2 měsíci +1

    ፓስተር ዳን ስለሺን ወደጌታ እንደመጣሁ ነው በትምህርቱ ያወቅኩት። በጣም ጌታን የሚወድና ለጌታ ትልቅ ቅናት ያለው ሰው ነው።መጀመሪያ በድምፅ ቅጂ እንሰማው ነበር። በኃላ ደግሞ ቪዲዮዎችን ማግኘት ችለን በአካል ልናየው ልንሰውማው ችለናል።ትምህርቶቹ እስካሁን አይረሱኝም ለምሳሌ የተከፈተ ሰማይ፣ንስር፣የንጉሱን ሰረገላ የሚጎትተው ማነው?፣ ዲሲብሽን ሌሎችም መንፈሳዊ ሕይወታችንን ከፍ ያድረጉ ትምህርቶች ነበሩ። ዛሬ ኢንተርቪውን ሳየው በጣም ነው ደስ ያለኝ። ቲጂዬ ጌታ ይባርክሽ እንግዳሽ አድርገሽ ስላቀረብሽው።

  • @tesfayefichala9036
    @tesfayefichala9036 Před 2 měsíci

    ከበፊት ጀምሮ በወንድማችን ዳን ስለሺ አገ/ት ከተባረኩ ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡ በአንድ ወቅት በትንቢተ ሕዝቅኤል 47 ላይ ተመሥርቶ ስለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ያቀረበው አስደናቂ የመገለጥ መልዕክት አለ፡፡ ቢቆይም ፈልጋችሁ በዩቲዩብ ብትለቁልን ብዙዎች ይጠቀሙበታል ብዬ አስባለሁ፡፡እርሱንም እናንተንም ጌታ ይባርካችሁ! አሜን፡፡

  • @user-vx1os3vj7l
    @user-vx1os3vj7l Před 2 měsíci +2

    God bless our brother, your blessing for all generations

  • @simegnashenafi9174
    @simegnashenafi9174 Před 2 měsíci +1

    ፓስተር ድሮ ልጅ ሆኜ በካሴት ስትሰብክ ነበር የማውቅህ በተለይ የአጋንንትን ሥውር አሰራር ያስተማርክበትን ት/ት አልረሳውም :: በአካል ስለየሁህ ደስ ብሎኛል be blessed !

  • @elsabethgebrecristos194
    @elsabethgebrecristos194 Před 2 měsíci

    ፓስተር ዳን በጣም ነበር አምወደው በአካል አላውቀውም ብዙ ስብከቶቹን ሰምቻለሁ የት ጠፍተህ ነው ፀጋ ይብዛልህ ድምፁን አወደዋለሁ🎉🎉🎉🎉ተባረክ

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 Před 2 měsíci +1

    እግዚአብሔር ይባርክሽ ቲጂ ከአንቺ እንግዶች ሁሌም እንደ ምለው በብዙ እየተማርና እየተባርክን ነዉ ጌታ ይባርክህ ፓስተር መልካም ምክር የሞላብህ 🙏🙌🙏
    Thank you 🙏🙌🙏

  • @AB-rf2tb
    @AB-rf2tb Před 2 měsíci

    ‘Open Heaven’ I heard in Toronto while he preach and which is my favourite message.

  • @meseretgebrehiwot935
    @meseretgebrehiwot935 Před 2 měsíci

    እግዚያብሄር እድሜ ጤና ይስጥህ አሁንም ትውልዱን ብታስተምርና ለትውልዱ የሚጠቅም የእግዝያብሄር ቃል እውቀት ብታስተምረን ለሁላችንም ይጠቅማል እግዚያብሄር አብዝቶ ይባርክህ

  • @tesfayemammo4481
    @tesfayemammo4481 Před 2 měsíci +2

    You are doing great getting us serious ministers, sister Tigist.

  • @fasilkidane3524
    @fasilkidane3524 Před 2 měsíci

    God bless you Teigey. I can' t wait l'm very interested to hear morm. Be blessed

  • @mulatukebede9656
    @mulatukebede9656 Před 2 měsíci +12

    Look, after 45 years speaking English it is very hard to speak Amharic only, so please understand our difficult ies

    • @masti1612
      @masti1612 Před 2 měsíci

      What? What world did you live? How about your family? You don't speak amharic at home? Woy gud

  • @user-ul8lh2kw2v
    @user-ul8lh2kw2v Před 2 měsíci +2

    ፓስተር ዳን ስለሺ በካሴት ነበር የማውቀው ወይም ስብከቱን እንሰማ የነበረው በ 1985. ዓም ዛሬ ገና በአካል አየውሁት አግዚአብሔር ይባርክህ 🙏🙏🙏

  • @user-ve7gj9fq4o
    @user-ve7gj9fq4o Před 2 měsíci

    ዳን ስለሺ ዘመንህ የተባረከ ይሁን

  • @gizawAdugna1243
    @gizawAdugna1243 Před 2 měsíci

    Paster Dan Sileshi, I remembered with the preaching about open heaven ..

  • @sirgutretta9560
    @sirgutretta9560 Před 2 měsíci

    God bless you pastor Dan you are amazing preacher. Keep teaching the word of God you are inspiration to me.

  • @BetelihemSamuel-qc5hj
    @BetelihemSamuel-qc5hj Před 2 měsíci

    በጣም በጣም በጣም ደስ ብሎኛል ፓስተር ዳንን ስላየው ተባረኪ ድንቅ ሰው የተወደደ የእግዝአብሔር አገልጋይ ብዙን ጊዜ መክቱን ፈልጋለው በብዛት ቢለቅልን ለትውልድ ድምፀ ነው ተባረኪ

  • @samymulu7110
    @samymulu7110 Před 2 měsíci +4

    God bless you pastor Dan. I’ve learned so much from you over many years. Keep it up. And thanks TG for inviting such a Minister of The Lord.

  • @user-wy4ye8co7s
    @user-wy4ye8co7s Před 2 měsíci +1

    Betam yemwedew bezu besu agelglot
    tebarkealehu 🙏 pastor Egziyabher zemenhin yebarik 👏💥💥💥

  • @nazarethayer1208
    @nazarethayer1208 Před 2 měsíci +1

    Yet another great discussion, I can’t wait to get more insight next week, thank you TG

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel Před 2 měsíci

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ ።

  • @tebibu6963
    @tebibu6963 Před 2 měsíci

    i remember those days...had actually good prayer fellowship with this beloved brother!

  • @kumelgeremew9335
    @kumelgeremew9335 Před 2 měsíci

    ቲጊ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ ተባረኪ ጥያቄዎችሽ የንግግር ምጠናሽ ጨዋነትሽ እንዲሁም ሰው አክባሪነትሽ ደስ ይላል

  • @burtehussian7257
    @burtehussian7257 Před 2 měsíci +2

    ተባረኪ ትግስትዬ በቲቪ ነዉ የምከታተለዉ በጣም የምወድሽ ፀጋ የበዛልሸ አሜሪካ ነዉ ምኖረዉ እባክሽ ለረጅም ግዜ ባገኛቸዉ ከምላቸዉ ሰዉ ናቸዉ ፓስተር ዳንስለሺ እና ቶለሳ ጉዲና እባክሽ ስልካቸዉን ጠይቂልኝ 🙏🏻🙏🏻🙏🏻❤️💙

    • @HiwotYerdaw
      @HiwotYerdaw Před 2 měsíci

      Tolosa gudena live to USA so lanchy ethiopia deres selk kemteyek yalbut cherch Mehdi techyalsh Atlanta

    • @user-xr7ic1iw3j
      @user-xr7ic1iw3j Před 2 měsíci

      Hi my sister I will trying to find for you Dr kese Tolosa office phone.

  • @tsinulegeta6919
    @tsinulegeta6919 Před 2 měsíci

    ደስ ይላል ብዙ ተማርኩ፣ ቲጂ እግዚአብሔር ያክብርሽ በብዙ ትህትና እንደምትጠይቂና እንደምትሰሚ የፊትሽ expression ያስታውቃል እግዚአብሔር ይጨምርልሽ ተባረኪ

  • @paintedinHisPalm
    @paintedinHisPalm Před 2 měsíci

    ፓስተር ዳን በጣም የማከብረውና የምወደው ፓስተር ነው፡፡ የማልረሳቸው ብዙ የተቸገሩ ክርስቲያኖች እሱ ጸልዮላቸው ጌታ ድንቅ አድርጎላቸው አይቻለሁ፡፡ ከ40 አመት በላይ እንቅልፍ ተኝተው የማያውቁ እናት ፓስተር ጸልዮላቸው ሲመለሱ መኪና ውስጥ ነው መተኛት የጀመሩት፡፡ ቤት ደርሰው ለ14 ሰአት በተክታታይ ከተኙ ቦኋላ ተቀስቅሰው ነው የነቁት፡፡
    ጌታ አሁንም ከነቤተሰቡ በመንፈስ ቅዱስ ሃይልና በሙያም በረከት አድርጎ እንዲጠቅምበት ጸሎቴ ነው፡፡

  • @upright4363
    @upright4363 Před 2 měsíci

    ተባረኩ እጅግ ተጠቅመናል 🙏

  • @user-od1mg8qx8t
    @user-od1mg8qx8t Před 2 měsíci +1

    ተባረኩ

  • @user-xr7ic1iw3j
    @user-xr7ic1iw3j Před 2 měsíci +1

    Gash Tilahun Gugesa you Are blessed you are lucky person. Your wife she's so humble and bleesed ...that is your efforts with God .

  • @mbenti69
    @mbenti69 Před 2 měsíci

    Pastor Dan is a living Word.

  • @azebadmasu3058
    @azebadmasu3058 Před 2 měsíci +1

    ኦ ፓስተር ዳን በህይወቴ የማልረሰው ትምህርቱ "እግዚአብሔር ወዳሳየን ስፍራ እንዴት እንደርሳለን" የሚለውተ ትምህርቱ በካሴት ነበረ። አሁንም ካሴቱን ባገኝ ደጋግሜ መሰማት እፈልጋለሁ ።

  • @DeliverancetvEthiopia
    @DeliverancetvEthiopia Před 2 měsíci

    Thanks God ❤
    I love pastor Dr.Dan be blessed .

  • @tamirathailu2973
    @tamirathailu2973 Před 2 měsíci

    Tnx tg , God bless you.

  • @MesfinYirgu-dx1lg
    @MesfinYirgu-dx1lg Před 2 měsíci

    መጋቢ እግዚአብሔር ይባርክህ! መልዕክቶችህ ኃይል ያለባቸው፣ ከሰው ልብ የማጠፉ ናቸው።

  • @user-ff7zg6lu6y
    @user-ff7zg6lu6y Před 2 měsíci

    በፊት በካሴት ትምህርቱ እደነቅ ነበረ በኋላ ናዝሬት ሰሜን መሠረተ ክርስቶስ በእርሱ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቼ በአየር ላይ ተንሳፍፌ የተዘረርኩበት ጊዜ አረሳውም።ዛሬም ይህ የእግዚአብሔር ሰው ጸጋው ገና ፍሬሽ ነው።ተባረኩ ግሩም ምስክርነት ነው።

  • @tsigedinku2372
    @tsigedinku2372 Před 2 měsíci

    እግዚአብሔር ይመስገን እንዲህ ዓይነት የጌታ ሰዎችን ልምድ ምክር የጌታን ፍቅር ... መስማት መቻላችን እድለኞች ነን። እኔ ብዙ ባልገባኝ ጊዜ ፓስተርን በካሴት ላይ ስብከቱን ሳይ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ተረድቼበታለሁ። ከረጅም ጊዜ በኋላ ስላየሁት ደስ ብሎኛል ያንን ጊዜ አስታወስኩት ድምፁ እራሱ ፖወሩ... አንቺንም እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ!!!ዘመንህን ሁሉ ከነቤተሰቤህ ያለምልምልህ!!!! አሜን እንደ ሀሳብህ ስለሞላልህ!!! የነበረው የእግዚአብሔር ፍርሀት ይመለስልን ለምድሪቱ ለአገልጋዩ ለምእመኑ ሁሉ ያስፈልጋልና። እንዴት የእግዚአብሔር መገኘትን እንዳጣን የገለጥክበትን አገልጋይ የተባሉ ሁሉ ቢሰሙት እና ቢጠቀሙበት ጥሩ ነበር። እንደው እናንተ ቀደምት ጌታ ያገኛችሁ ያከበራችሁ ያገለገላችሁ አሁንም ያላችሁ አሁን ላሉት አገልጋዮችና ምዕመኖች ትምህርት በተወሰነ ቀን ብትሰጡን? በእርግጥ እግዚአብሔር ያላስነሳቸውን ያሳፍራቸዋል ግን ትውልድስ አይጠፋም ወይ? መመለስን የመሰለ ጥሩ ነገር የለም። እናመሰግናለን!!!

  • @eristiabekele7293
    @eristiabekele7293 Před 2 měsíci +1

    ፓስተር ዶክተር ዳን ስለሺ እናመሰግናለን የነጠረውን እውነት እየነገሩን ነው::

  • @BirualemTesfaye
    @BirualemTesfaye Před 2 měsíci +2

    This interview is worth watching... I really appreciate the host

  • @gemechubefikadu6973
    @gemechubefikadu6973 Před 2 měsíci +1

    The man I love and learned a lot from him. I was listened to his Audio teaching about evil spirit and their sign. God bless you Pastor Dan Silesh. God bless you Tigist for bringing Pastor to your show.

  • @turkatoturto4871
    @turkatoturto4871 Před 2 měsíci

    እግዚአብሔር ሆይ ምሣሌ የሆኑ እንደ ፓስተር ዳን አይነት ታላላቆችን አላሳጣሄንምና ክብርና ምስጋና ለዘለዓለም ለስምህ ይሁን!!

  • @jabez.m1048
    @jabez.m1048 Před 2 měsíci

    እግ/ር ይባርካቹ!!!