ርዕስ፡- አነጋጋሪው ኢየሱስ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 22. 08. 2024
  • ርዕስ፡- አነጋጋሪው ኢየሱስ #በቄስ ዶክተር ገለታ ሴሜሶ #2021 Qes Dr geleta simeso #2021 ethiopia protestant #sbket

Komentáře • 11

  • @user-cc3tx7rs6o
    @user-cc3tx7rs6o Před 5 měsíci

    ጌታ ይባርክህ ዶክተር
    ❤❤❤❤❤❤

  • @lemlemghebremedhinweldeghi5205

    I am blessed , thanks Dr. Geleta for amazing God's Word!!

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 Před 2 lety

    Amennnnnnn hule ale kegone abate eyesus yimetal

  • @Ethiopiatomorrow
    @Ethiopiatomorrow Před 2 lety

    May God bless you absolutely the true servant of God!

  • @selamademsung5995
    @selamademsung5995 Před 2 lety

    አሜን

  • @ameleworkaddisie1257
    @ameleworkaddisie1257 Před 3 lety

    GBU

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 Před 2 lety

    Amennnnnn

  • @asterhaile1788
    @asterhaile1788 Před 2 lety

    አስተምሮትህ ድግል ማርያም በጌታ ፊት የሚቆመው መላእኩ ቅዱስ ገብርል አክብሮ ነው ያበሰራት አንተ ምነው እንደመንደር ልጃገረዶች አቃለልካት አንተ እናትህህን አታከብርም ጴንጤዎ በማርያም ትቀናላችሁ ታዲ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከናንተ እናት እንዲወለድ ትፈልጉ ነበር እኔ በጣም ይገርመኛል

  • @fekadubarke6987
    @fekadubarke6987 Před 3 lety

    ዳ/ር ገለታው አነጋጋሪ ነው ስላልከው ኢየሱስ ላነጋግርህ ኢየሱስ ላንተ ማነው?ማንስ ብለህ ተቀበልከው?የተወለደልንና የተሰጠን ወንድ ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ብለክ ነው የተቀበልከው ወይንስ ልጅን የሰጠንም እግዝአብሔርም ራሱ ነው ትላለህ?

    • @finotarega5512
      @finotarega5512 Před 3 lety +2

      " ኢየሱስን ተቀብለሀልን?? "
      ይህ ንግግር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይስ በልምድ የመጣ ?
      አንድ አንድ ጊዜ በቡድን ማሰብን ትቶ በግላችን ፣ እና ለግላችን ማሰቡ ጥሩ ነው። ሰከን ባለ ስሜት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረንን ቃል እንመርምር። ቃሉን ስናነብ ለማሸነፍ ወይም ለመሸነፍ ሳይሆን ለማወቅ እና ለጥቅማችን ብለን ልናጠና ይገባል ።
      መፅሐፍ ቅዱስን መርህ አድርጎ የሚማማር ሰው መሃከል አሸናፊም ተሸናፊም የለም ሁሉ ለቃሉ ይገዛልና ።
      በጭንቅላታችን ላይ የሚብሰከሰውና አጥሮ የያዘን፥ ‘‘የትኛው ቡድን እንዲህ ያምናል?፣
      የትኛውስ ነው እንዲህ የማያምነው?
      ትክከለኛው ካቶሊክ ነው??
      ወይስ ኦርቶዶክስ ??
      ፕሮቴስታንት ነው ወይስ ተሀድሶ ?? ’’ የሚለውን ውጤት አልባ ክርክር ወደጎን ትተን ‘‘መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ያለው እውነት፣ የትኛው ነው?’’ በሚል መንፈስ ርዕሰ ጉዳዩን እንመርምር ።
      ለመሆኑ ኢየሱስን መቀበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወይ ?
      መቀበል የሚለው ቃል ምን ማለት ነው ??
      መቀበል ማለት ፦ ይሁንልኝ፣ አሜን፣ እስማማለው፣ ይህንኑ አረጋግጣለው፣ የራሴ አድርጌዋለሁ፣ እወስዳለሁ፣ ወ.ዘ.ተ የሚሉ ትርጉሞች አሉት። እነዚህን ትርጉሞች ከሚከተሉት የእግዚአብሔር ቃል ላይ እንፈልግ ፡- ለቃሉ እንድንሸነፍ መንፈሱ ያግዘን ።
      አሜን
      መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ መቀበል ይቅርና በክርስቶስ የሆኑ ቅዱሳንንም በስሙ መቀበል እንዳለብን ይነግረናል ።
      ሀዋርያቱን...." ከማይቀበላችሁም " ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ ። ማቴ 10፡14
      ሀዋርያቱን ፦ ማቴ 10፡41 ነቢይን በነቢይ ስም " የሚቀበል " የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
      ምስክርነታቸውን እና ቃላቸውን መቀበል እንዳለብን ተገልጿል
      ዮሐ 3፡11 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም " አትቀበሉትም "። ዮሀ 3፡11
      ዮሐ 3፡32 ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ምስክሩንም " የሚቀበለው " የለም።
      ዮሐ 3፡3ምስክሩን " የተቀበለ " እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
      እንግዲህ ከላይ በቀረቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ፣ ‘መቀበል’ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መጠነኛ ግንዛቤ ከማግኘታችን በተጨማሪ ከጌታ የተላኩትን በስሙ መቀበል እንዳለብን ብሎም ቃላቸውን መቀበል እንዳለብን ተገልጿል ቃሉም ለመጽሐፍ ቅዱስ እንግዳ እንዳልሆነ የተረዳን ይመስለኛል።
      በመቀጠል ኢየሱስን መቀበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለመሆኑን እናያለን ።
      ኢየሱስን መቀበል
      ቆላ 2፡6 እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
      ዮሐንስ 1፡11-12 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ..ወገኖቹምአልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
      ማቴ 10፡40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
      ማርቆስ 9፡37 እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን
      ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው።
      ዮሐ 5፡43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁአልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።
      ዮሐ 13፡20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበልየላከኝን ይቀበላል።
      ከላይ በቀረቡት ማስረጃዎች መሰረት ኢየሱስን መቀበል፣ መናፍቃዊ ሃሳብ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት መሆኑን የተገነዘብን ይመስለኛል። ‘‘እናም አሁን ባላችሁበት ቅጽበት እኔ ኢየሱስን ተቀብያለሁ ወይ?’ ብሎ ራስን መጠየቅ ተገቢ ከመሆኑ በላይ ራሳችንን ልንጠይቅ ከሚገቡን ጥያቄዎች መካከል ዋነኛዎቹ ናቸው።
      ለመሆኑ መድሃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ያልተቀበልን ማንን ልንቀበል ነው? ይህን የእግዚአብሔር ልጅ ያልተቀበሉት አይሁድ ዮሐ 1፡11-12 ከእግዚአብሔር ፍርድ ስር ሆነዋል፣ እኛስ ልጁን ያልተቀበልን ከዚህ ፍርድ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?
      መፅሐፍ እንደሚነግረን የተቀበሉቱ ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ስልጣን ተሰጧቸዋል።
      የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን ደግሞ የመንግስቱ ወራሾች ነን ሮሜ 8፡17። እናም፣ ፍርድን ከመቀበል ይልቅ ኢየሱስን ተቀብሎ በእርሱ መመላለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነውና በሚረዳው ፀጋ ፊት እንሁን ቆላ 2፡6