Video není dostupné.
Omlouváme se.

ቢሾፕ ደጉ ከበደ ለ 50 አመታት የሰበከው የተሳሳተ ወንጌል | Heretical Oneness Doctrine in Ethiopia copied from UPC Ep 95

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 09. 2023
  • የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊጂሰስ በመባል የሚታወቀው ቤተእምነት በጣም አደገኛ እና መፅሀፍቅዱስን የሚፃረር የሀሰት እምነት ነው:: ኢየሱስ ኢየሱስ ይላሉ ግን የመፅሀፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ፈፅሞ አይቀበሉም:: በወንጌል የሚያምኑ ይመስላሉ ግን የአዲስኪዳንን ወንጌል ፈፅሞ ወደጎን በማለት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ዶክትሪን እና ሀይማኖታዊ ህግጋቶቻቸውን ከመፅሀፍ ቅዱስ በላይ የሚያምኑ ወገኖች ናቸው:: ምእመኖቻቸውም መፅሀፍ ቅዱስን እያነበቡ ስለ አምላካቸው ከማወቅ ይልቅ ድርጅቱ እና የድርጅቱ አስተማሪዎች የሚሉትን ብቻ እንዲቀበሉ ይገደዳሉ:: ኢየሱስን መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በቅጡ ሳያምኑ እና ሳይቀበሉ የውሀ ጥምቀት የዘላለም ህይወት ያስገኛል ብለውም ያምናሉ::
    በአጭሩ መፅሀፍ ቅዱስን ያለአግባብ በአውዱ እና በስርአቱ ካለማንበብ እና ካለመረዳት የተነሳ የተፈጠረ ድርጅት "CULT” ነው:: ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ ማንነት ላይ እጅግ በጣም ስተዋል!
    ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የወልድ እና የመንፈስቅዱስን መለኮታዊነትን የሚክድ ቤተእምነት ነው:: አንዱ እግዚአብሔር ወይም አንዱ መለኮት በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስቅዱስ ተገልጦ እንደሚኖር አያምኑም::
    በኦንሊጂሰስ አስተምሮ በስጋ የተገለጠው ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ነው:: ኦንሊጂሰሶች የወልድን ዘላለማዊነትም ይክዳሉ:: የእግዚአብሔር ልጅ ለነሱ ከድንግል ማርያም የተወለደ የስጋ ሰውነት ብቻ ነው:: ስጋውንም ሰማያዊ ወይንም መለኮታዊ ከሰማይ የመጣ ስጋ ነው እንጂ የዳዊትን ዘር በስጋ ተካፈለ ብለው አያምኑም:: (ሮሜ 1:3, ሮሜ 9:5, ዕብ 2:14, ራእይ 22:16)
    ልጁ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ የምድር እና የሰማይ ፈጣሪ መሆኑን ይክዳሉ (ዕብ 1:2, ዕብ 1:10, ቆላስያስ 1:16) የእግዚአብሔር ልጅ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ከአባቱ ጋር ይኖር የነበረ መሆኑንም አያምኑም (ዮሀ 1:1, ዮሀ 6:38, ዮሀ 16:28, ዮሀ 17:5)
    ኦንሊጂሰሶች እባካችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ለመፅሀድፍቅዱስ ስልጣን ሰጥታችሁ ለህሊናችሁ ታማኝ በመሆን ቃሉን ካነበባችሁት ሳታውቁት የወደዳችሁት የመፅሀፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በሙላት ይገለጥላቹሀል:: የኢየሱስ ማንነት ላይ መሳሳት ከዘላለም ህይወት መጉደልን ያስከትላል:: 1ኛ ዮሀ 5:12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። እባካቸሁ ከቃሉ ጋር እግዚአብሔር እየተማፀናችሁ ጊዜ አሳ ልፉ:: እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጥላችሁ ወዳጆቼ!

Komentáře • 11

  • @user-of9dn5ox1z
    @user-of9dn5ox1z Před 5 měsíci +2

    በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ልጅ ስም የመገለባበጥ ወንጌል የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የተጣላ የአጋንንት ትምህርት ከምድራችን ላይ የተገለበጠ ይሁን። አሜን

  • @user-gd3dx8fx4t
    @user-gd3dx8fx4t Před 2 dny

    ቢሾብ ደጉ በጣም የሚገርሙ ጥበበኛ አሳች ናቸው ማስመሰል ይችላሉ ሁሌም እኛብቻ የእኛ ብቻ ሰማያዊ ሥጋ ማለት ያጋንንት መንፈስ ነው ኢየሱስ አብ አይደለም የእግ/ር ልጅ ነው አስቡበት

  • @sirakmekonnenofficialchann9051
    @sirakmekonnenofficialchann9051 Před 10 měsíci +2

    ላኪና ተላኪ ነበረ ክርክሩ አየተገለባበጠ ሆነ እነዚህ ሰዎች ከአጋንት ከጥልቁ ከጨለማው ገዢ ነው መገለጡን የሚቀበሉት

  • @yossihana8406
    @yossihana8406 Před 10 měsíci +1

    Yemegelebabeti menfes Be Yesus sim yetemeta yihun

  • @protestantmezmur11
    @protestantmezmur11 Před 10 měsíci +1

    ❤❤❤ tebareklgi

  • @wendimtakelku2087
    @wendimtakelku2087 Před 10 měsíci +2

    The Father gave his Son. The Son was sent by the Father. John 3:16 and John 6:44.

  • @BirhanuGizachew-pf9xs
    @BirhanuGizachew-pf9xs Před 10 měsíci +1

    Bicha egizabher yirdachew

  • @user-of9dn5ox1z
    @user-of9dn5ox1z Před 5 měsíci +2

    በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ልጅ ስም የመገለባበጥ ወንጌል የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የተጣላ የአጋንንት ትምህርት ከምድራችን ላይ የተገለበጠ ይሁን። አሜን

  • @user-of9dn5ox1z
    @user-of9dn5ox1z Před 5 měsíci +1

    በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ልጅ ስም የመገለባበጥ ወንጌል የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የተጣላ የአጋንንት ትምህርት ከምድራችን ላይ የተገለበጠ ይሁን። አሜን

  • @user-of9dn5ox1z
    @user-of9dn5ox1z Před 5 měsíci +1

    በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ልጅ ስም የመገለባበጥ ወንጌል የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የተጣላ የአጋንንት ትምህርት ከምድራችን ላይ የተገለበጠ ይሁን። አሜን