+ ገድለ አባ በግዑ + ሰምታችሁ በረከትን አግኙ

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 31. 05. 2021
  • የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik የፌስቡክ ገፅ
    - / %e1%8b%a8%e1%89%85%e1%...
    +++አባ በግዑ+++
    አባ በግዑ፡- አባ በግዑ በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፡፡ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፡፡ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው ሀገር ይገባል፡፡ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፡፡ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፡፡ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፡፡ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡
    በእንደዚህ ያለ የውንብድና ሥጋ ብዙ ዓመታት ከኖረ በኋላ አባ በግዑ በስም ክርስቲያን ነበረና ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንፈስ አነሳስቶት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ፡፡ ካህኑም ባየው ጊዜ ከመንገድ ገለል አደረገውና ‹‹የሕይወት ዘመንህን ሁሉ በከንቱ አሳለፍክ ዛሬ ስማ ልንገርህ፣ በዘመንህ ፍጻሜ እግዚአብሔር ይጎበኝሃል፣ በመንፈስ ቅዱስም ያድርብሃል፣ ፍጹም መነኩሴ ትሆናለህ፣ በብዙ መከራና ተጋድሎ ትኖራለህ በዚያም የነፍስህ መዳኛ ይሆናል፣ እግዚአብሔርንም ደስ ታሰኘዋለህ›› አለው፡፡ ከዚህም የበዛውን ብዙ ነገር ነገረው፡፡
    ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቁርባን ተቀበለ፡፡ ወደቤቱም ከተመለሰ በኋላ ካህኑ የነገሩትን እያሰበ ‹‹እስከመቼ በስንፍናዬ እኖራለሁ? እስከመቼስ የነፍሴን መዳኛ ሳላስብ እኖራለሁ? …›› እያለ አሰበ፡፡ ከዚህም በኋላ ከዘመዶቹ ተለይቶ ከሀገሩ ወጥቶ ሄደና ወደ ባሕር ዳርቻ ደርሶ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን እጅ ነሣ፡፡ ከመነኮሳትም ማኅበር ገብቶ እነርሱን ማገልገል ጀመረ፡፡ አባ በግዑ በእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ልቡ ተመልሶ ከመነነ በኋላ ግን እስከሞተበት ዕለት ድረስ የላመ እህል ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ምግቡን የዛፍ ፍሬና ሜዳ ላይ የሚበቅል ቅጠል አደረገ፡፡ ዓቢይ ጾም ሲመጣም ከሰኞ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ምንም ሳይቀምስ የሚጾም ሆነ፡፡ ውኃንም ሳይጠጣ ኖረ፣ ማንም ሰው ሳያውቅብ ለ5 ወር ምንም ውኃ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡
    ከ5 ወር በኋላም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ አባ በግዑ መጣና ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሰላም ለአንተ ይሁን! በምን ትታወካለህ? ምንስ ያሳዝንሃል? ››አለው፡፡ አባ በግዑም ‹‹ጌታዬ ከውኃ ጥም የተነሣ በጣም ስለተጨነቅሁ ነው›› አለው፡፡ መልአኩም ነጥቆ ወደ ገነት ወሰደውና ከገነት ቅጠል አንሥቶ አቀመሰው፡፡ ወዲያም የአባ በግዑ ሰውነት ታደሰች፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ውኃ ሳልጠጣ ተጋድሎዬን እፈጽም ይሆን!›› የሚለው የኅሊና መታወክ ከእርሱ ጠፋለት፡፡
    ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ በግዑ ለሚወደው ለአንድ ወዳጁ ለማንም እንዳይናገር በእግዚአብሔር ስም ካስማለው በኋላ ለ5 ወር ምንም ውኃ እንዳልጠጣ ምሥጢሩን ነገረው፡፡ ያ ወዳጁም ይህን ሲሰማ ደንግጦ አለቀሰ፡፡ አባ በግዑም አብሮት አለቀሰ፡፡ ወዳጁም ‹‹እስከዛሬ ከውኃ የተከለከለ በማን ዘንድ ሰማህ? አሁንም ቅዱሳን መነኮሳትና አበ ምኔቱ አያምኑህም፡፡ ይህን ምሥጢር ዛሬ ብሸሽግ በመጨረሻ ይገለጣል፡፡ ሕዝቡ፣ ነገሥታቱና መኳንንቱም ይህን ነገር ይሰማሉ ነገር ግን አያምኑም፡፡ አሁንም የምነግርህን ስማኝና ትኅርምቱን ትተህ ውኃ ጠጣ›› አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑም ‹‹የነገርከኝ ሁሉ እውነት ነው ሐሰት የለውም ነገር ግን እኔ ከዚህ በኋላ እስክሞት ድረስ ዳግመኛ ውኃ እንዳልጠጣ ስለ እግዚአብሔር ትቻለሁ፡፡ ሰዎች ባያምኑ እኔ ምን ገዶኝ፣ ነገር ግን በዚህ ገድል እግዚአብሔር ረዳት ይሆነኝ ዘንድ ጸልይልኝ›› አለው፡፡
    ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ብረት አመጣና ሰንሰለቶችን ይሠራለት ዘንድ ለአንጥረኛ ሰጥቶ አሠራ፡፡ ያንን ወዳጁን ጠራውና እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር እንዲያስረው አዘዘው፡፡ ‹‹አበ ምኔቱን ጥራልኝ›› አለውና ጠራለት፡፡ አባ በግዑም አበ ምኔቱ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ሲመጣ በፊቱ ሰገደለትና ‹‹አባቴ ሆይ! የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እፈጽም ዘንደ በላዬ ላይ ጸልይልኝ›› አለው፡፡ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ከበዓቴ አልወጣም፣ ሰውም ወደኔ አይገባም›› አለው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐም በላዩ ከጸለየለት በኋላ ‹‹ለእኔም ጸልይልኝ›› አለው፡፡ አባ በግዑም በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን በአባ ኢየሱስ ሞዐ እጅ ቁርባንን ከተቀበለ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር ታስሮ ብቻውን ዘግቶ በጽኑ የተጋድሎ ሕይወት ኖረ፡፡ በዓቱንም ዙሪያውን መውጫ መግቢያ እንዳይኖረው መረገው፡፡ ለምግብ የሚሆነውን የዛፍ ፍሬና የሜዳ ቅጠል ማስገቢያ የሚሆን ትንሽ ቀዳዳን አበጃና ያ ወዳጁ ያስገባለታል፡፡ አባ በግዑም ያንን በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ይመገባል፡፡
    የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንዲህ ዓይነት ጽኑ በሆነ የተጋድሎ ሕይወት ሲኖር ሰውነቱ ላይ ከቆዳውና ከአጥንቱ በቀር የሚታይ ነገር እስኪጠፋ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ፡፡ ውኃንም እስከ ሰባት ዓመት ድረስ አልጠጣም፡፡ መቆምም አይችልም ነበርና መነኮሳቶቹ ለቁርባን በቃሬዛ አድርገው ወደ ቤተ ክርስቲያን ይወስዱት ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንደዚህ ዓይነቱ ለመስማት በሚከብድ እጅ የበዛ ጽኑ ተጋድሎ ካደረገ ከብዙ ድካም በኋላ በዚህች ዕለት ታህሳስ 27 ቀን ዐረፈ፡፡ ጌታችንም ተገልጦ ታላቅ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ የአባ በግዑ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፡፡
    ወዳጆች ሆይ! ይህንን ማን ያምናል!? ለሰው ምንም ውኃ ሳይጠጣ ሰባት ዓመት መኖር ይቻለዋልን!? ‹‹በብዙ ሲጋደሉ እንደኖሩ የቅዱሳንን ገድላቸውን ሰምተናል፡፡ ነቢይ ዕዝራ የዱር ዛፍ ፍሬ እየተመገበ ውኃም እየጠጣ በምድረ በዳ እየጾመ ኖረ፡፡ ነቢይ ኢሳይያስም የሜዳ ጎመን እየቆረጠ ከእርሱም እየተመገበ ውኃም እየጠጣ በተራራ እየጾመ ኖረ፡፡ እግዚአብሔር ስሙን ‹የበረሃ ኮከብ› ብሎ የጠራው የመነኰሳት በኩር የሆነ አባ እንጦንስና አባ መቃርስም በደረቅ ኅብስትና በውኃ ብቻ ሲጋደሉ ኖሩ፡፡ እኚህ ምድራዊያን ሲሆኑ ሰማያውያን ሆኑ፡፡ ነቢይ ኤልያስም በኅብስትና በውኃ ብቻ በምድረ በዳ ሲጋደል ኖረ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ግን ሰባት ዓመት ሙሉ ውኃ ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ከመነነ በኋላ እስከሞተበት ዕለት ድረስ እህል የሚባል አልቀመሰም፡፡ እርሱ ግን ራሱን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያደርግና በትህትናም ሆኖ ስለ ኃጢአቱ ሁልጊዜ ያለቅስ ነበር፡፡
    ይህም የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ይህን ሁሉ የተጋደለ በራሱ ኃይል አይደለም፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው እንጂ፡፡ አንተም ወንድሜ ሆይ ራስህን ዕወቅ፡፡ ምንም ተጋድሎን ብታደርግ ጾምኩ፣ ተራብኩ፣ ስለ እግዚአብሔርም ብዬ ራሴን አደከምኩ፣ እግዚአብሔርንም ስላገለገልኩ በሥራዬም እድናለሁ አትበል፡፡ መጨረሻህን አታውቅም፡፡ አንተ ግን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ራስህን ኃጥእ አድርግ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ያጸድቅሃልና፡፡ ወዳጄ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትመሰገን ራስህን አታመስግን፤ ሌሎችም ያመሰግኑህ ዘንድ አትውደድ፡፡ ክብር ታገኝ ዘንድ ትሕትናን ገንዘብ አድርግ፡፡›› (ገድለ አባ በግዑ)

Komentáře • 109

  • @user-zg3dy8cv6d
    @user-zg3dy8cv6d Před 7 měsíci +3

    ያባታችን ያባ በግዑ ርድኤት በርከታቸው ፀሎታቸው ይደርብን አሜን

  • @user-qo9eh9yf4e
    @user-qo9eh9yf4e Před dnem

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን የቅዱስ አባ በግዑ በረከት ይደረብን❤ በዚች ምድር ቸሩ ፈጣሪየን እደኔ ያሳዘነ የለም። አቤቱ የአባቶቸ አምላክ ማረኝ💔💔💔😢

  • @user-qu2cn7ms2h
    @user-qu2cn7ms2h Před 4 dny

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወትን ያሠማልን❤ የአባ በግዑ በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ፫

  • @-dl5s
    @-dl5s Před 9 měsíci

    Amen amen amen kel hiwet yasemalin ❤❤❤

  • @user-ok1qf1zh7s
    @user-ok1qf1zh7s Před 2 lety +1

    አሜን አሜን አሜን በረከታችሁ ይደረብኝ

  • @jacobtesfay5967
    @jacobtesfay5967 Před měsícem

    Amen Amen Amen kale hewt ysmalna 💙🙏💙🙏💙🙏

  • @fairoozfairooz3607
    @fairoozfairooz3607 Před 2 lety +6

    አሜን አሜን አሜን ቃለ በረከት ያሰማልን የቅዱስ አባ በግዕ በረከት ቃል ኪዳን ይጠብቅን ይሄን እደሰማ የፈቀደ አምላካችን ስሙ የከበረ የተመሰገነ ይሁን

  • @mikehaile5775
    @mikehaile5775 Před 2 lety +4

    አባ በግዕ ነምላክና ነጊርካ ብጰሎትካ ሓግዘና።ካብ ጰላኢ ድያብሎስ አድሕነና አሜን።ምስ አምላከይ አራክበኒ፡ፈጣርየይ ካብ ኩሉ ችግራት አድሕነኒ፡ ባርከኒ በእንተ አባ በጊዕ መሓረኒ ፡በእንተ አባ በጊዕ መሓረኒ፡በ እንተ አባ በጊዕ ባርከኒ አሜን። ኦ እየሱስ ክርስቶስ መሐረኒ አሜን

  • @misarkmisark3065
    @misarkmisark3065 Před rokem +2

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን የአባታችን የአባ በግዑ በረኬታቸው ይደርብን አሜን

  • @anabak2549
    @anabak2549 Před 2 lety +8

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን በረኬት ረደኤት ቃልኪዳናቸው በኛላይ ይደረብን

  • @merrygh
    @merrygh Před 9 měsíci

    አሜን አሜን አሜን በረከቱም ይሕደረና አባ በግዑ

  • @legessetsegaye7390
    @legessetsegaye7390 Před 2 lety +6

    አሜን፫ግዜ በረከታቸው ረድኤታቸው አድሮብኝ ከተያዝኩበት አኔን ክንፈሚካኤል እና ወለተሃናን ለምስክርነት ያብቃን ያድርገን።አሜን፫ግዜ ።

  • @hhhugj8789
    @hhhugj8789 Před 29 dny

    አሜን አሜን አሜን
    ቃለ ህይወትን ያሰማልን🙏🙏🙏♥♥♥

  • @AshenafiYergalem
    @AshenafiYergalem Před 4 měsíci

    የአባ በግዑ በረከታቸው ረደየታቸው ይደርብን።አሜንአሜንአሜን። ሰይፈ ሚካኤል በፀሎቶ ምህረትን ቸርነትን እንደደረግልኝ ፀሎትና በረከቶ አይለየኝ።አሜን አሜን አሜን።

  • @MekedsMerid
    @MekedsMerid Před 11 měsíci

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን በርከት ረድኤታቸው ቃልኪዳናቸው ይደርብን

  • @user-dj6tc9fo4u
    @user-dj6tc9fo4u Před 4 měsíci

    አሜን አሜን አሜን በረከታችው ይደሪብን ቃል ህይወት ያስማልን

  • @zenapzeenap-6716
    @zenapzeenap-6716 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህወት ይስመዐልና 🙏🙏🙏💒💒💒

  • @tigisttamiru5213
    @tigisttamiru5213 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወት ያሰማልን በርከታችሁ ይድረብን

  • @meherat938
    @meherat938 Před rokem

    የቅዱሳን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @MmMm-uh7yw
    @MmMm-uh7yw Před 2 měsíci

    አሜን የአባ በግዑ በረከታቸዉ ይደርብን አባቶቸ ወ/ፃዲቅ እያላችሁ አስቡኝ እባካችሁ በስደት ላይ ነኝ ችግር ዉስጥ ነኝ እየጨነቀኝ ነዉ አስቡኝ

  • @tigisttube6070
    @tigisttube6070 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መምህራችን

  • @etlmawmoges5058
    @etlmawmoges5058 Před 7 měsíci

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን

  • @user-ue5fw3bt8i
    @user-ue5fw3bt8i Před 27 dny

    የአባታችን በረከታቸው ይደርብን ስለ እሳቸው ብሎ ይማረን ይቅር ይበለ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቤቱ እንደ እኛ በደል እና ሀጢያት ሳይሆን እንዳተ ቸርነት ማረን ይቅር በለን የወለተ ማርያምን ነፍስ ስለሳቸው ብለህ ማርልኝ😢😢😢

  • @jemayenshreta8146
    @jemayenshreta8146 Před rokem +1

    የአባታችን የአባ በግዑ ቃልኪዳናቸው አይለየን ይባርከን ቃለሂወት ያሰማልን የሰማነውን በልባችን ያኑርልን አሜን!

  • @aynalemmengestue3354
    @aynalemmengestue3354 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን እንካን አብሮ አደረሰን
    ቃለሂወትን ያሰማልን❤❤❤❤❤

  • @shiwayeyemariyamlij8549
    @shiwayeyemariyamlij8549 Před 2 lety +6

    ቃለህይወት ያሠማልን የአባታችን አባ በግዑ ረዴኤት በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን በእለተ እረፍታቸው ገድለቸውን እደሠማ የፈቀ አምላክ የድንግል ማርያም ልጅ እግዚአብሔር ይመስገን👏👏💞💞💞💞👏👏👏💒💒👏👏

  • @user-pb9iw9zq4s
    @user-pb9iw9zq4s Před 2 lety +1

    አሜን አሜን አሜን

  • @zainabhabshy1906
    @zainabhabshy1906 Před rokem +1

    ቃለ ህይወት ያሠማልን በድሜ በፀጋ ያቆይልን
    የአባታችን የአባ በግዑ ሃብተ ረዴኤት ከኛጋር ይሁን አሜን///

  • @user-yl4wn8qx9q
    @user-yl4wn8qx9q Před 2 lety +2

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን የቅዱሳን ፃለት ልመና ምልጃ አይለየን በርከታችህ ይድርብን

  • @masratbh5310
    @masratbh5310 Před 8 měsíci

    አሜን አሜን አብታችን በረከታቸው ይደርብን የሰማነውን በልባችን ያሳድርብን ለመምህርም ቃለ ህይወት ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንህንም ይባርክልን

  • @adonayeadule1073
    @adonayeadule1073 Před 10 měsíci

    አሜን ቃለህወት ያሠማልን ወንድማችን❤❤❤

  • @samriatube1683
    @samriatube1683 Před rokem

    Amen amen amen berktachew yideriben

  • @promobil5835
    @promobil5835 Před 11 měsíci

    Amen Amen Amen KAL hiwot yasemalen bendeme betena yitebekilen abatachin berketo yiderben yekidusu Abatachin berketachiw yiderben beberketachiw yasebun 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @yaredmokanint9257
    @yaredmokanint9257 Před rokem

    Amen Amen Amen 🙏.

  • @mherettsiduye5561
    @mherettsiduye5561 Před 2 lety +2

    ቃለ ሒወት የሰማልን ለኛም ላደመጥነም ረደኤት በረከታቼው ይደርብን አሜን

  • @user-vv8vz2un8j
    @user-vv8vz2un8j Před rokem

    አቤቱ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ስነ እነዚህ መስተጋድል ቅዱሳን ቃልኪዳን ስትል ማረኝ ከክርስትያን ወገን የሚያስቆጥር አንዳች ምግባር የለኝምና።

  • @askalemariyam8253
    @askalemariyam8253 Před 10 měsíci

    Amen Amen Amen bereketachw yedrbn❤❤❤❤

  • @user-tm9dm4ir7z
    @user-tm9dm4ir7z Před rokem

    Amen ye abatachen berektacha yedreben

  • @saabcell5625
    @saabcell5625 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመሰገን

  • @haydigetachew
    @haydigetachew Před 6 měsíci

    አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏

  • @user-gr8ml7ro8h
    @user-gr8ml7ro8h Před rokem

    እግዚአብሔር ይመሰገን አሜን አሜን አሜን

  • @sarbean4827
    @sarbean4827 Před rokem

    በረከት ረድኤት ናይ ኣቦና ይሕደረና

  • @Firu1221
    @Firu1221 Před 4 měsíci

    Amen brketu ydrsen egzhbher yetbkiln

  • @GOYtymo
    @GOYtymo Před rokem

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤

  • @user-pb9iw9zq4s
    @user-pb9iw9zq4s Před 2 lety

    አባበፆሎቱአስቡኝፍቅርቱአማኑኤል

  • @ArgashdastaArgashdasta
    @ArgashdastaArgashdasta Před měsícem

    ቃለሕይወት ያሰማልን።

  • @sofanitepilupader2424
    @sofanitepilupader2424 Před 2 lety +2

    የአባታችንን በረከታቸውን ያሳድርብን💠
    ቃለህይወትን ያሰማል በእድሜ በጤና ያቆይልን
    ቢሰሙት የማይጠገብ አገራችንን በፀሎት ማሩልን

  • @marwamengesha1763
    @marwamengesha1763 Před 2 lety +1

    ቃለ ሂወትን ያሰማልን የአባታችን የአባ በግዑ ረድኤት በረከቱ ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @AbdiiDabaluu
    @AbdiiDabaluu Před 4 dny

    አሜን 🙏😔

  • @user-on8tm5xb3r
    @user-on8tm5xb3r Před 9 měsíci +2

    የቅድሱንን መጋደል በስመማ ው ቁጥር እኔ ምንም መግባርና ስራ እንደሌለኝ አውቃለሁ የአባቶቼ ቅድሳን አምላክ ይማረኝ ይቅር ይበለኝ

  • @beba5182
    @beba5182 Před 11 měsíci

    Amen 🙏

  • @elissafikir6718
    @elissafikir6718 Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜንአሜን

  • @amanuelbesrat3430
    @amanuelbesrat3430 Před 2 lety

    Ye abatachen bereket yedereben..........amennnn.....

  • @BenjaminSibhatu-tu3mi
    @BenjaminSibhatu-tu3mi Před 11 měsíci

    Amen Amen Amen kale hiwet yasemaln bereket ina tselot yabatachin aba begio kehulachin ga yhun ina latatachin degmo idme ina tsegha Egziabiher yabzalachew bewinet dess yemil sbket ina nbab 🙏♥️🙏

  • @BelaYnesh-yi2ci
    @BelaYnesh-yi2ci Před 7 měsíci

    ኣሜንኣሜንኣሜን

  • @samrawitgetachew3144
    @samrawitgetachew3144 Před rokem

    kale hiwot yasemalin...memhr,ke bereketachew yasatfen.amen.

  • @vghhhj7363
    @vghhhj7363 Před 2 lety

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @solomongebermeskel3480
    @solomongebermeskel3480 Před 4 měsíci

    በረከታቸው ይድርብን

  • @user-pb9iw9zq4s
    @user-pb9iw9zq4s Před 2 lety

    እግዚአብሔር ይመስገን

  • @melleseabera5966
    @melleseabera5966 Před 3 lety +1

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን
    አባታችን በረከቶ ይደርብን አሜን

  • @khantaddgh2452
    @khantaddgh2452 Před rokem

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀሎት በረከታቸው የኣባ በግኡ ይደርብን 🙏🙏🙏

  • @user-gh2vy7ll3o
    @user-gh2vy7ll3o Před 3 lety +2

    አባቴ በረከቶ ይደርብኝ

  • @afcs7804
    @afcs7804 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን በእውነት የቅዱሳን በረከት እረደኤታቸው ይደርብን ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህራችን

  • @mesfinbirhane2445
    @mesfinbirhane2445 Před rokem +1

    Amen Amen Amen kalhewet yasemalin yabatachn bereketachew Amalajnetachew eredtachew yderbn egnanm lensha yabekan zend kidus fkadu yhunlin yenatun kidste kidusan dngl maryamn hager ethiopian tebkln enenm tebkegn kekifu neger Amen yderegln 💙💛❤🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏🙏💙💛❤🥰🥰🥰🥰🥰🥰💙💛❤🙏🙏🙏🙏🙏

  • @shashibazezew1573
    @shashibazezew1573 Před 2 lety

    🌹💐🌹💐🌹

  • @ArmanMalik-db1ey
    @ArmanMalik-db1ey Před rokem

    አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን አሜን የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን ከቃል ኪዳናቸውም ያሳትፈን ቸር አምላክ

  • @hanogg8115
    @hanogg8115 Před 2 lety +1

    Amennnn ye Abatachen bereketachew yedereben 🤲❤ kale hiweten yasemalen 🙏 ye agelegelot zemenachehu yetebarek yehun 🤲

  • @JeehJrjr
    @JeehJrjr Před měsícem

    ❤❤

  • @user-nj3fe5wc9o
    @user-nj3fe5wc9o Před 2 lety

    እሜን🙏🙏🙏🙏

  • @danielberhane440
    @danielberhane440 Před 9 měsíci

    እየሱስ ይሰበክ

  • @tsegaosman4546
    @tsegaosman4546 Před 3 lety +1

    Abat hoi bereketu ederebin amen amen amen

  • @mikehaile5775
    @mikehaile5775 Před rokem

    አምላክ ለአባ በግዑ ቃል ኪዳን እንደገባለት ገድልህ የሰማህ እሳት አያያትም።እስከ 7ትውልብ እምርሃለሁ። እንደተባለ ፍቃድህ ይሁን ገድሉ እንድንሰማ ሃይልና መንፈስ ቅዱስ ስጠን።
    አሜን አሜን አሜን።(3)

  • @meron4462
    @meron4462 Před rokem

    Kale hiwotin yasemalin

  • @user-nt3gt4cz7f
    @user-nt3gt4cz7f Před rokem

    አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ፀሎት ምልጃቸው አይለየን ቃለ ህይወት ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን 🙏❤❤❤❤❤

  • @shashibazezew1573
    @shashibazezew1573 Před 2 lety

    🤲🤲🤲🤲

  • @BelaYnesh-yi2ci
    @BelaYnesh-yi2ci Před 7 měsíci

    ❤❤❤❤

  • @demeweztasfaee3496
    @demeweztasfaee3496 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን በርከታቸው ቃል ኪዳናቸው ይደርብን😢

  • @user-sb9vi6qx1b
    @user-sb9vi6qx1b Před 2 lety +1

    አሜን አሜን አሜን በረከተወ ይደርብን💒💐

  • @shashibazezew1573
    @shashibazezew1573 Před 2 lety

    💚💛❤

  • @user-pb9iw9zq4s
    @user-pb9iw9zq4s Před 2 lety

    እውነት ነው😭😭😭😭😭😭💔💔💔

  • @senaitgebremedhin7460
    @senaitgebremedhin7460 Před 2 lety +1

    እግዚአብሔር ይመስገን
    አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን ክቡር መምህራችን
    የጻዲቁ አባታችን ቅዱስ አባ በግኡ ፀሎት በረከታቸው ይደርብነ

    • @legessetsegaye7390
      @legessetsegaye7390 Před 2 lety

      አሜን ፫ግዜ ለኔ ለኃጥያተኛውና በደለኛው በረከታቸው አድሮብኝ ከተያዝኩት በሽታ እንድነሳ ይሁንልኝ ይደረግልኝ ።አሜን፫ግዜ ።

  • @rahwateshme4709
    @rahwateshme4709 Před 2 lety +1

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ብረክታችው ይደርብን👏👏👏

  • @Raya-oz6gc
    @Raya-oz6gc Před rokem

    አሜን አሜን አሜን የባታችን በርከት አይለየንአሜን ፫//

  • @SemereGetachew-mt2zj
    @SemereGetachew-mt2zj Před 11 měsíci

    Amaen amaen amaen

  • @mussiematiwos6991
    @mussiematiwos6991 Před 2 lety

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን
    ቃለ ሂወት የስማዓልና

  • @sarhku1173
    @sarhku1173 Před 3 lety +1

    አባት ሆይ በረከት ይደርብን
    አሜን አሜን
    አሜን

  • @belayneshbelaynesh8000
    @belayneshbelaynesh8000 Před 3 lety +1

    ያባታችን በረከታቸው ይደርብን

  • @mikehaile5775
    @mikehaile5775 Před rokem

    በእንተ በግዕ መሓረን ክርስቶስ አሜን(3)

  • @habeshahabesha7180
    @habeshahabesha7180 Před 2 lety

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን በረከታቸው ይደርብን

  • @gullkhan2434
    @gullkhan2434 Před 2 lety

    ቃል ሂወት ያሰማልን

  • @GenetHaile-lt1
    @GenetHaile-lt1 Před 9 měsíci

    Gedl New weys gedal

  • @asfawbono8250
    @asfawbono8250 Před 12 hodinami

    አባታችን ይቅርታ አድርጉልኝ አበቶችም ድያቆናትም ገድሉን ስያነቡ ለራሣቸው ያኔባሉ ማለቴ ሰያነቡ ድምፅ አውጥቶ ክርስትያኖች አንድሴሙ አያነብ ስያነብም የማንቤብ ችሎታ የሌለ ድያቆን ያነባል መለቴ እዬፌራ ስሌምያነቡ የክርስትያንን ጆሮ አይስብም ና ይህ ነገር እንድሻሻል እነፌልጋለን የማንቤብ ችሎታ የለሌ ድያቆንም ሆኔ ቄስ አያነብ መጀመርያ የማንቤብ ችሎታቼው ያዳብሩ ምመናንን በቻ አትወቅሱ መጄመርያ ብቃት ከናቴ ይጄመር

  • @rahelwoldu5259
    @rahelwoldu5259 Před 3 lety

    Selam

  • @alexanderdawit2804
    @alexanderdawit2804 Před rokem

    Amen Amen Amen kalehiwet yasemalin memhir

  • @user-mn4xd6se2p
    @user-mn4xd6se2p Před měsícem

    መዝሙሮቹን ፃፉልን እባካችሁን

  • @user-sf2rg6mw7e
    @user-sf2rg6mw7e Před 7 měsíci

    አሜንአሜንአሜንበረከትህይደርብንአባቴሆይ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @Afari.MadSleuthExportedSalt
    @Afari.MadSleuthExportedSalt Před 10 měsíci

    እብድ ውሻ ግማታም

  • @geneteshetu-iz1lm
    @geneteshetu-iz1lm Před 19 dny

    አሜን አሜን አሜን

  • @legessetsegaye7390
    @legessetsegaye7390 Před 2 lety +1

    እግዚአብሔር ይመስገን

    • @legessetsegaye7390
      @legessetsegaye7390 Před 2 lety

      በፀሎት ያስቡኝ አባቴ አልጋ ከያዝኩኝ አመታት ተቆጠሩ ክንፈሚካኤል ነኝ።

    • @legessetsegaye7390
      @legessetsegaye7390 Před 2 lety

      ንሠሐ ገብቼ ለመቁረብ እንኳንም አልቻልኩም ሳልቆርብ ሆስፒታል ገብቼ ኦፕራሲዮን ተደርጌ ወጣው ኢትዮጵያ ላሉት ለወንድሜ ንሠሐ አባትዐብነግራቸው ልጄልጄ ዶክሮቹ ላይ አድሮው በእለተ ቀኑ24ይዘህ የገባኻቸውፀበልናዕምነት በተክልዬ አማካኝነት ቆርብሐል ተጠንቀቅ አሉኝ።

    • @user-qo9eh9yf4e
      @user-qo9eh9yf4e Před dnem

      እመብርሀን ታስበን😢​@@legessetsegaye7390

  • @user-fp6ts5bx5b
    @user-fp6ts5bx5b Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን