እግዚአብሄርን (Egzihabherin) ዲቦራ ህብረት መዘምራን 2024

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 09. 2024
  • እግዚአብሄርን የሚያህል አምላክ ስለአለን
    ለምን / 2 እንሰጋለን
    በማጣት በማግኘት ከእኛ አይለየንም
    ለመውደዱ መጠን የለው መለኪያ የለውም
    ሁልጊዜ ከእኛ ጋር አብሮን ስለምኖር
    ምንም አይነካንም አለ እግዚአብሄር
    አልፋ አኦሜጋ ነው ፊተኛ ኃለኛ
    አምላካችን እሱ ነው ለኛ ብቸኛ
    ወረት የማያውቀው ፍቅሩ ህያው ነው
    አምላካችን እርሱ ከእኛ ጋር ነው
    የሚያስፈልገንን እርሱ ራሱ ያውቃል
    ስለ እኛ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ያስባል
    ሁሉን ነገራችን በሱ ላይ ትተን
    እንደ ቃሉ እንኑር ያ ነው ሚጠቅመን
    አንጠራጠረው ሁልጊዜ ታማኝ ነው
    ኪዳኑን ሚጠብቅ እሱ እግዚአብሄር ነው
    ፍፁም በመታመን እንደገፍ በእውነት
    እሱ ያኖረናል ጠብቆ በህይወት

Komentáře • 19