ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2024
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች፤ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው። ጨረታው ነገ ረቡዕ ነሐሴ 1፤ 2016 እንደሚካሄድ ባንኩ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል።
    በ2000 ዓ.ም. የጸደቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ፤ ባንኩ የውጭ ሃገር ገንዘቦችን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም “ለመግዛት፣ ለመሸጥ እና ለመያዝ እንደሚችል” ይደነግጋል። ባንኩ ይህንን መሰረት በማድረግ በቅርቡ ያወጣው መመሪያ፤ ብሔራዊ ባንክ ህጋዊ እውቅና ላላቸው ባንኮች የውጭ ምንዛሬን በጨረታ ሊሸጥ እና ከእነርሱ ሊገዛ እንደሚችል አስፍሯል።
    ብሔራዊ ባንክ ይህን መሰሉን ጨረታ የሚያካሄደው፤ “በውጭ ምንዛሬ ገበያ ለሚታዩ የተዛቡ ሁኔታዎች” መፍትሔ ለማበጀት መሆኑ በመመሪያው ላይ ተቀምጧል። እንዲህ አይነት ጨረታዎች በውጭ ምንዛሬ ገበያ “ግልጽነት እና ገበያን መሰረት ያደረገ የዋጋ ትመናን ለማበረታታት” እንዲሁም በገበያው የሚፈጠሩ “መዛባት እና የቢሆን ግምቶችን (speculation) የመከላከል” አላማን ያነገቡ መሆናቸውንም መመሪያው ገልጿል።
    (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

Komentáře • 1