ስጠኝ እስቲቃማ / stegn istikama

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 23. 08. 2024
  • አጫጭር ኢስላማዊ ግጥሞች በ አብዱሰላም ሻፊ (አቡ አብደላህ) /በዱንያም በአኪራም ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልገው እስቲቃማ (ፅናት ) እንዲሁም የሰው ልጆችን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ የሆነው ዕውቀት የተዳሰሱበት ዕውቀት ያስከብራል / ዛሬ tube /
    Islamic poems in Amharic by Abduselam Shafi (abu Abdellah ) / about patience, The most important key for success and the importance of knowledge @ zaretube ዛሬ .
    To get latest videos just subscribe now.
    / @zaretube1690
    ስጠኝ እስቲቃማ
    በሰጠኸኝ ኒዕማ መልካሙን ስሰራ
    ነብስያና ሸይጧን ቢዋጉኝ በጋራ
    እጄን ጭራሽ ሳልሰጥ ለጠላቴ አላማ
    መልካሙ ስራዬን ዘውትር እንድሰራ
    ለጋሹ ጌታዬ ስጠኝ እስቲቃማ
    ከመጥፎ ስራዬ በፀፀት ቶብቼ
    ዳግም ላልመለስ በነፍሴ ላይ ዝቼ
    ከተውባ በኋላ ከቶ እንዳላቅማማ
    ሐራም እንዳልሰራ ስጠኝ እስቲቃማ
    ቢበዛ ፀሎቴ ፆሜና ስግደቴ
    ልብሴን ሳስተካክል በማውቀው መስራቴ
    በፈርድ ላይ ሱናን ዘውትር ስተገብር
    ከቃልህ ማውቃትን ለሰዎች ስናገር
    ኢክላስ የለው ስራው ተብዬ ብታማ
    መልካም እንዳላቆም ስጠኝ እስቲቃማ
    ካለችኝ ትንሽ ሃብት ከኪሴ አውጥቼ
    ጀነት እንዳልገባ መልካሙን ሰርቼ
    ድህነት ቢዝትም በጭራሽ ላልሰማ
    በሰደቃ አበርታኝ ስጠኝ እስቲቃማ
    በረመዳን ላንድ ወር ኢማኔ ሞልቶልኝ
    በፆም በሠላቱ እንዳበረታኸኝ
    በዱዓ ጠንክሬ በዚክር እንዳረፍኩኝ
    ኢፍጣር ሰደቃ እንዳልተቻኮልኩኝ
    ሠላሳው ቀን አልፎ ሸዋል ስትመጣ
    ሻይጧንም ተፈቶ ከስሩ ሲወጣ
    እንዳይጎዳኝ ከቶ እንዳንስማማ
    አዛኙ ጌታዬ ስጠኝ እስቲቃማ ።
    ቅድሚያ ሰጥቼበት ሱብሂዬን ከንቅልፌ
    ቅዝቃዜውና ብርዱን አሸንፌ
    መስጂድ እንድሰግድ ሰላቴን በጀማ
    ወዳጁ ጌታዬ ስጠኝ እስቲቃማ
    እምነቴን እንድተው አስገዳጅ ቢመጣ
    ያለችኝ አንዷን ነፍስ በስቃይ ሊያወጣ
    ወይም በማጣቴ ኃብቱን ተመክቶ
    ሊያሸጣኝ እምነቴን በብር አሞኝቶ
    በድህነት ኖሬ ህይወቴንም ሸጬ
    ጀነትን እንዳገኝ እንዳልቀር ቋምጩ
    በአኺራ እንዳላፍር ፍርዳችን ሲሰማ
    ዛሬ በእምነቴ ላይ ስጠኝ እስቲቃማ ፡፡
    ሌሎች ስራዎቼ :-
    * ክብር ነው ባርነት ( ስለተውሂድ )
    • ክብር ነው ባርነት
    * ብቻ ሶብር እንጂ
    • ብቻ ሶብር እንጂ ምርጥ ግጥም በ አ...
    የብእሩ አርበኛ እና ሌሎችም
    • የብዕሩ አርበኛ እና ሌሎችም
    * ቢራቢሮው ልቤ እና ሌሎችም
    • ቢራቢሮው ልቤ እና ሌሎችም
    ስጠኝ እስቲቃማ እና እውቀት ያስከብራል • ስጠኝ እስቲቃማ / stegn isti...
    * በጭራሽ አትችልም
    • በጭራሽ አትችልም !!! ...
    #zaretube ዛሬ#ethiopian #saudi #uae #dubai #አሜሪካ #አስተማሪ #ዱባይ #abduselam #ethiopiancommunity #tewhid
    #ነሲሓ ቲቪ#Nesihatv#shorts #ኢስላማዊ #ግጥም በ አቡ አብደላህ ll #islamic #poem in Amharic by #abu Abdellah / #Abdusrlam Shafi #ethiopian #saudi #uae #dubai #አሜሪካ #ethiopiancommunity #አስተማሪ #nesihatv #nesiha-tv@zaretube ዛሬ

Komentáře • 18