ልሙት እንዴ? | ጋሽ ንጉሴ ቡልቻ | Gospel Teaching | Protestant Ethiopia 2023 እውነት እና እውነት

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 23. 08. 2024
  • "እውነትና እውነት" የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚያጠነጥነው መፅሐፍ ቅዱሳዊ በሆኑ አስተምሮት ባሉ እውነታዎች ላይ ነው። በተመረጡ ርዕስ ዙሪያ የማስተማር እውቀቱ ያላቸው ሰዎች በማሳተፍ በርዕሱ ላይ በቂ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ይደረጋል።በተጨማሪም ሰዎች በቀላሉ የሚረዱትንና ሳቢ በሆነ አቀራረብ ሳይሰለች ማስተማርና እውነትን ማስያዝ እንዲችል ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህም ሰዎች ጥያቄ በሆነባቸው የመፅሐፍ ቅዱስ ሃሳቦች እና ርዕሶች ላይ ትክክለኛ እውነታውን(መልስ የሚሆናቸውን) እንዲያገኙእና አንድ ወጥ የሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዲኖር ይረዳል ።በመጨረሻም የልጁን መልክ ለመምሰል እለት እለት ራሱን የሚያስለምድ ሰውን ማየት እንችላለን ብለን እናስባለን።
    "ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ ከእርሱ የተነሳ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሰራ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ ራሱን በፍቅር በማነፅ አካሉን ያሳድጋል"
    ኤፌ 4፡15-16

Komentáře • 5

  • @bogaleagga9026
    @bogaleagga9026 Před rokem +1

    አሜን🙏🏾

  • @seyfedesalegn2962
    @seyfedesalegn2962 Před rokem +2

    Betam des yemil yemiyasitemir lekiristinachin meseretawi timirit new...egziaber yibarikachu

  • @user-gr3zv5mp4y
    @user-gr3zv5mp4y Před rokem +1

    እኔ በአጋንንት እስራት ውስጥ ሆኜ ሀጢያትን አደርግ ነበር የዝሙት መንፈስ ያስገድደኝ ነበር ጌታን ካገኘሁ በኋላ ባሰብኝ ከጴንጤዎች ጋር በድብቅ መዘሞት፤ብፀልይ ባለቅስ ሊተወኝ አልቻለም በፍፁም አጋንንት እንዳለብኝ አላውቅም ከኔ ድክመት እየመሰኝ ራሴን ኮነንኩ በመጨረሻም ባልመረጥ ነው ብዬ ጌታን ተውኩ በቅርብ በነብያት አገልግሎት አጋንንቱ ከላዬ ለቆ ወጣ ነፃ ሆንኩኝ አሁን ጌታን መታዘዝ ቀለለኝ አሁን የተመረጥሁ የመንፈስ ቅዱስ ንብረት ነኝ ስጋዬ መንፈሴም ነፍሴም። ስጋ ሀጢያት ቢሰራ ችግር የለውም ንፍስህ ድኖአል የሚለው ምንጩ ከግብረሶዶማውያን የመጣ ይመስለኛል 🙏🏼ተባረኩ 👋🏼

  • @yosephayele9626
    @yosephayele9626 Před rokem +2

    ጋሽ ንጉሴ ከ ተናገሩት እውነት የእውነት የገረመኝ እና ለቤ ውስጥ የተቀረቀረው እውነት፤የጸጋ ሁለት ገጽታ ያሉት ነው፤ ጸጋው ከኃጥያት ፍርድ ብቻ ሳይሆን ከኃጢያት እንድንርቅ ያስተምረናል፤ ጸጋው ለኃጢያት ፍቱን መፍትሄ ነው ይህ ጸጋ ደግሞ በክርስቶስ በጌታችን ተገልጾዋል። ጸጋው በኃጢያታችን እንዳይፈረድብን ነጻ ያወጣናል፣ጸጋው ኃጢያት እንዳይገዛን ያስተምረናል አሜን። ይህን ጸጋ ለሰጠን ለጌታችን ምስጋና ለሱ ብቻ ይሁን፤ እንግዲህ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።