ዳጉ - የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና አዲሱ አዋጅ Etv | Ethiopia | News zena

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 4. 04. 2024
  • ዳጉ - የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና አዲሱ አዋጅ #ebc #etv #news #zena
    #EthiopianBroadcastingCorporation #viral
    ፌስቡክ - / ebczena
    የመዝናኛ ዩትዩብ - / @ebcentertainment3193
    የፕሮግራም ዩትዩብ - / @ebcprogramanddocument...
    የአፋን ኦሮሞ ዩትዩብ - / @etvafaanoromoo
    የልጆች አለም ዩትዩብ - / @etvyelijochalem-nr8oj
    የኢቢሲ ሳይበር ዩትዩብ - / @ebccyber-tz4hk
    የኢቢሲ ሬዲዮ ዩትዩብ - / @ebcradio-cw6qs
    የሶማልኛ ቋንቋ ዩትዩብ - / @etvaf-soomaali
    የትግርኛ ቋንቋ ዩትዩብ - / @etvtigrigna-zl3rr
    የአፋርኛ ቋንቋ ዩትዩብ - / @etvqafarafihexxa-vx2kg
    የኢቢሲ ቋንቋዋች ዩትዩብ - / @ebclanguages532
    የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዩትዩብ - / @ebcworld6854
    #ebc #etv #news #zena
    #EthiopianBroadcastingCorporation #Fraternity
    #ethiopiannews #newsdaily #dailynews #redsea #abiyahmed #ethiopian #ebc #etv #news #EthiopianBroadcastingCorporation #ethiopiannews #newsdaily #Sport #dailynews #redsea #abiyahmed #ethiopia #ministryofeducation #NewsWaveNow #MediaPulseUpdate #CurrentAffairs #GlobalInsightHub #NewsVistaNetwork
    #InfoStreamUpdate #PressPlayReports #WorldViewUpdate #InfoBeaconChannel #NewswireExpress #Viral
    #NewsMindsToday #MediaEcho2023 #InsightLiveNow #GlobalNewsBeat #UpdateVibesNow #InfoSphereLive #CurrentPulseNet #WorldView2023 #ArtificialIntelligence #AI

Komentáře • 228

  • @mekonnengeberemichael7532
    @mekonnengeberemichael7532 Před 3 měsíci +31

    የጤፍን ዋጋ መቆጣጠር ያልቻለ መንግስት በግል ንብረቴ ላይ ሲወስን በጠም ያሳዝናል

  • @millimilli-cq5dh
    @millimilli-cq5dh Před 3 měsíci +21

    አከራይ ቤቱን የስራው ደም ተፍቶ
    ከግለስብ ከባንክ ተበድሮ ነው
    ስለዚህ ህጉ አከራዬችን ታሳቢ አላደረገም

    • @tirudelewnetu6071
      @tirudelewnetu6071 Před 2 měsíci

      ehet majoritewn new mayet akeray eko abezagnaw endesw yemaykotiru alu

    • @HappyCells-vl4ym
      @HappyCells-vl4ym Před 2 měsíci +1

      አልማከራየት መብት ነው. ስለዚህ ተከራይም መጎዳቱ አይቀርም ይምስለኛል.

    • @tesfayefida2837
      @tesfayefida2837 Před měsícem +1

      መንግስት አሁን ያረገው ሁለት አመት ተከራዩ እንዳይለቅ ቢረዳውም መንግስት በመብራትና ውሀ ያረገው ጭማሪ ለቤት ኪራዩ ማሻቀብ ትልቅ አስተዋፅዖ አርጒል።ስለዚህ መንግስት የራሡን ጭማሪ ማስተካከል አለበት።

  • @yaredmuluneh1858
    @yaredmuluneh1858 Před 3 měsíci +21

    መንግሥት በሚሰጠው አገልግሎት ላይ አንደፈለገ በመጨመር ላይ ነው የአፈር የግድግዳ ና ጣራ የኪራይ ግብር የልማት የመብራት ውሃ... ኑሮ ለሁሉም ነው የጨመረው ሁል ጊዜ አከራይን ክፉ አናድርግ መልካም አከራይ መኖራቸውን ማሰብ ጥሩ ነው።

  • @henokgirma6552
    @henokgirma6552 Před 4 měsíci +22

    የጀርመንን የተከራይ አከራይ ህግ እንደ ምሳሌ መወሰዱ ተገልጾአል።በጀርመን ህግ የኪራይ ሽፋን የሁለት ወይም ሶስት ወር ኪራይ በቅድሚያ አከራዪጋ ይቀመጥና ተከራዪ ሲለቅ እንደ ማሳደሻ ይያዛል።ቤቱ ግን በጥሩ ሁኔታ ከተረከበ ገንዘቡ ይመለሳል። ይህ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በደንቡ የተካተተ አይመስለኝም።

    • @user-gy7xs6qx9b
      @user-gy7xs6qx9b Před 4 měsíci

      A Security Deposit. Our system isn't up to par for such task yet... what happens when the landlord refuses to return the money for whatever reason...and dispute arise.

    • @adanelema6916
      @adanelema6916 Před 4 měsíci +3

      ከጀርመን ጋር ኣታመሳስለን፣ከቤቶቹ ኣሠራር እስከ እድሳቱ የተሟላና የተስተካከለ ነው፣እኛ ግን ተከራዩ በት ውስጥ ተከራይቶ የሚገባው ኣንገቱን ለማስገቢያና ጎኑን ለማሳረፍ ብቻ ነው፣በተጨማሪ ጀርመን ውስጥ ቤት ከመከራየትሕ በፊት ኢንቬንተሪ የተደረገበትን ወረቀት ኣይተህና በወረቀቱም መሠረት ተከራይ ተቆጣጥሮ ኣይቶና ኣምኖ ነው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ኣይነት መብት ለኣከራይ መስጠት ማለት ገንዘቡን ውሰደው ማለት ነው፣

    • @user-op2mt8fg7u
      @user-op2mt8fg7u Před 2 měsíci

      መንግስት መቼ ለአከራዩ አሰበ ተከራይ ሰባብሮ ይወጣል

    • @woderyeleshzeleke3032
      @woderyeleshzeleke3032 Před měsícem +2

      ህጉ የአከራይን መብት አልጠበቀም አከራይ ብዙ ለፍቶ እልበላም፣ አልጠጣም ብሎ የሰራውን ቤት ተከራይ ክራይ ባለመክፈል፣ቤትን ጽድቶ የተሰጠውን ብዙ አበላሽቶ ሲመልስ ቀበሌ እንካን ሄደን ተገቢ ምላሽ አይሰጥም ለምን ብሩን እንካን ተከራይ ከከፈለ ቀበሌው እንድንሰጠው ብር ይጠይቃል አከራይተን እኮ እኛ ተጠቃሚ አይደለም ቤተሰብ ነው ምናስተዳድርበት
      ይህ ነገርም መታየት አለበት
      2. የመሬት ግብርም ወጥ የሆነ አይደለም መታየት መጠናት አለበት
      ውሉ 2 አመት መሆኑ ጥሩ ነው
      ታክስ እንደማለት ነው ጥሩ ነው ግን ቀብሌና አንዳንድ ጉዳዩ የሚመለከተው ለአከራይም ተከራይ ከህጉ ውጪ ሲሆን ምላሽ መመለስ አለባቸው የምዝገባ ስርአቶች ያሉበትን ቦታም በግልጽ አስቀምጡልን ቀበሌ ግን እንዳይሆን

  • @dinkneshbulcha521
    @dinkneshbulcha521 Před 3 měsíci +6

    እንደገና መጤን ይኖርበታል፡፡

  • @user-jp2zp8ek9j
    @user-jp2zp8ek9j Před 2 měsíci +3

    በጣም ነዉ የሚገርመዉ 40 /60 እጣ የወጣ ቾ ቤቶች ማስተላለፍ ይልቅ ግለሰብ የደከመበት ንብረት ላይ ለመዝረፍ አንድ ቀን የፈጣሪ ፍርድ ይመጣል ከገርግ ዘረፍ በምን ይለይል ምነዉ ጤፉ ላይ ብሰሩ ሰላም ላይ እንሁ ብሰሩ ጥሩ ነበር

  • @hdherhrh6052
    @hdherhrh6052 Před 2 měsíci +4

    እንዴ የናረውን የኑሮ ውድነት ቢቆጣጠር ደስ ይለኛ እንጅ በግል ንብርት ጣልቃ ባይገባ ጥሩ ነው

  • @user-el4ul5lj9l
    @user-el4ul5lj9l Před 3 měsíci +5

    ይህን፡ትልቅ፡አገር፡ዕውቀታቸው፡በሌላቸው፡በመሐይማን፡እጅ፡ካድሬዎች፡ካድሬዎች፡ወድቃ፡ የህዝቡን፡ቤት፡በግፍ፡አፍርሰው፡ህዝብ፡መጠጊያ፡አጥቶ፡ሊገለብጣቸው፡ንቅናቄ፡ሲነሳባቸው፡፡ ሰው፡ለፍቶ፡ጥሮ፡ግሮ፡በላቡ፡ያገኘውን፡ንብረት፡እኛ፡ባዘዝንህ፡እና፡ባወጣጠን፡መመሪያ፡ካላከራየህ፡ንብረትህን፡እንዘርፋለን፡ብለው፡አውጀዋል፡፡ለነገሩ፡መጥፊያቸውና፡መውደቂያቸው፡ሲቃረብ፡አዋጅ፡ማብዛታቸው፡የሚጠበቅ፡ነው፡፡

  • @godisgoodallthetime42
    @godisgoodallthetime42 Před 3 měsíci +8

    ፍትህ ለኮንደሚኒየም ቆጣቢዎች

  • @tsion3656
    @tsion3656 Před 4 měsíci +18

    ሌላ የሙስና መስመር እንዳይሆን ብዙ አከራዮች መተዳደሪያቸው ነው

  • @sarabekele6589
    @sarabekele6589 Před 3 měsíci +4

    ከዚህ በዋላ ቤት የሚሰራ የለም መንግሰት እየሰራ ያከራይ ኮንዶምንዬም 20 አመት ሀሰዝብ ቆጥቦ መሰራት ሲያቅተው የሰራውን ዜጋ ማጨናነቅ ነው

  • @solomonwoldegiorgis5429
    @solomonwoldegiorgis5429 Před 4 měsíci +6

    መንግሥት አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት እንደመቀነስ አድርጋለሁ ብሎ ለመናገር የሚያስችል እድል አምልጦታል የሚል እምነት አለኝ። ምክንያቱም አሁን ያለው የቤት ኪራይ ያለ አግባብ የናረ መሆኑ ስታወቅ ያንኑ ተቀብሎ የአዋጁ መነሻ ማድረጉ ተገቢ አይደለም።

    • @S-gd4tk
      @S-gd4tk Před 3 měsíci +1

      አከራዩም የገቢ ምንጩ ከሆነስ ሌላው ነገር ንሮ እንደት ይኑር ብሎ ማሰብ ግድ ይላል

  • @Amante2023
    @Amante2023 Před 3 měsíci +13

    ደላላላዎቹ ከመሀል መውጣት አለባቸው የሀገራችን ትልቁ የኑሮ ቀውስ የሚያባብሱ ደላላዎቹ ናቸው::

    • @HappyCells-vl4ym
      @HappyCells-vl4ym Před 2 měsíci +2

      ደልዳላ ምንድን ነው?

    • @Amante2023
      @Amante2023 Před měsícem

      ስለ ድጋፋቹ አመሰግናለሁ..!! በመቀጠል አሁንም በድለላ ስራ ላይ ተሰማርቶ አግባብ ባልሆነ መንገድ ሕዝቡ እና ገበያውን ከመጠን በላይ የሚያዛቡትን ሕዝቡ ከመሀከሉ ማውጣት አለበት ያለዝያ የተረጋጋ እኮኖሚ መፍጠር አይቻል:: ሆን ብሎ ሕዝቡንና አገርቷን በድላላ አማካኝነት የሚዘርፉ ማቆም አለባቸው:: የቤቶች ልማትም በዝህ ላይ አጥብቆ መሰራት አለበት ይላለውኝ.!!

  • @sumeyanuredin8458
    @sumeyanuredin8458 Před 4 měsíci +7

    መንግስት ለራሱ ሲሆን በአዋጅ የፈለገውን ይቀይራል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ህገ እንስሳት (ህገመንግስት) ላይ የለም ይላል መሬት የግል መሆን አለበት የምን አባታችሁ ሊዝ ነው የዜጋን የቤት ባለቤትነት መግፈፍ ነው ሊዝ የሚባል ከመለስ ጋር መቀበር አለበት ።።

    • @ayeletefera8982
      @ayeletefera8982 Před 3 měsíci +1

      ለህዝብ ጥቅም በትክክል ከታሰበ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ለማስቻል ከሆነ እስኪ የሸቀጦች የዋጋ ንረትንም እንደዚህ ጣልቃ በመግባት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ይገባል ብዪ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም አሁን ሀገሪቱ በምትመራበት ኢኮኖሚ ሁኔታ ይህ የአከራይና የተከራይ የግል የውል ግንኙነት ነው፡፡ በህግ ደግሞ ውል በተዋዋይ ወገኖች ብቻ የሚወሰን ነው፡ ህገወጥ እስካልሆነ ድረስ፡፡ ስለዚህ ለህብረተሰቡ የታሳበ ከሆነ የፍጆታ እቃዎችም ላይ እንደዚሁ ጣልቃ ቢገባ በትክክል የተገልጋዩን ህብረተሰብ ፍላጎት ያማከለ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ 85 ፐርሰንት የህበረተሰብ ክፍል በግብርና ላይ የተመሰረተ ኑሮ የሚመራ ሆኖ ሳለ፤ ሸማቹ ህበረተሰብ 1 ኩንታል ጤፍ 14000 ብር ገዝቶ መጠቀም እና ሌሎችም የኑሩ ወድነቱን ከሚገመተው በላይ እድርጎ፤ ህበረተሰቡን፤ ውጥረት ውስጥ መክተት በራሱ ትልቅ የኢኮኖሚ ቀውሰ እያስከተለ ነው፤ የትምሀርት ቤት ክፍያም እንደዚሁ፤ ልክ እንደአከራይና ተከራይ መቆጣጥር ሲቻል ማለት ነው፡፤ ስሆነም ልክ እንዲዚሁ ሁሉ፤ የህበረተሰቡን ህይወት የሚያመሰቃቅሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ቢያደርግ ነው ይበልጥ ህብረተሰቡን ያማከለ ስራ ተሰርቷል ሊያስብል የሚቻለው፡፡

  • @mekiyasiraj5107
    @mekiyasiraj5107 Před 3 měsíci +4

    This is good but it favors more for tenants. Please check Kenyan tenancy agreement 1. there is always 2 ot 1 month deposit when you what to rent any type of the house. The deposit will be for any damage and renovation after every tenant. So owner get

  • @gessemmedia4116
    @gessemmedia4116 Před 3 měsíci +3

    የአንዳንድ አከራይና ተከራይ ሁኔታ ያሳዝናላ ሳሎኑን አከራይቶ መኝታ ክፍል ገብቶ በጓሮ የሚወጣ አከራይም እኮ አለ ወዶ ሳይሆን ኑሮው ነው

    • @alemfantsh1838
      @alemfantsh1838 Před měsícem

      እኔ አለሁ ልጅ ለማሳደግ ሳይተርፈኝ አከራይቸ ምኖር

  • @ethiohealth3602
    @ethiohealth3602 Před 3 měsíci +3

    ይህን ማድረግ የሚችለው የመንግስት አፓርታማ ላይ ነው እንጂ በግለሰብ ቤት አፈር ልሶ የሰራው ቤት ላይ ነው እንዴ ሚገርም ነው

  • @mame8874
    @mame8874 Před 4 měsíci +4

    ችግሩ እኮ ከአከራይ አይደለም ከመንግስት ነው መንግስት የኑሮ ውድነቱን ያስተካክል የግብር አከፋፈል ያስተካክል መንግስት ከአንድ ጭቃ ቤት 15,000 ሀያ ሺህ እያስከፈለ ተከራይ ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም

  • @derejelegessegurmessa1266
    @derejelegessegurmessa1266 Před 3 měsíci +4

    ደሞዝ ዘሮ በሆነበት ሁኔታ የደሞዝ ገቢን መሠረት ማድረግ እንደት ይቻላል ? ተገቢ ያልሆነ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ÷ የኑሮ ውድነቱን ጫና እና ቤቱን ለማደስ በየጊዜው የሚወጣውን ወጪዎችን ከግምት ማስገባት ተገቢ ነው

  • @user-ry5gi4ze4e
    @user-ry5gi4ze4e Před 3 měsíci +2

    ፍ ትህ ለአከሪይ ጋዜጠኝ ተከራያ ስለሆኑ በደስታ ነ የሚዘግቡት

  • @mame8874
    @mame8874 Před 4 měsíci +6

    ከደርግ ባሰ እኮ ይሄ መንግስት ኢሀድግዬ ማረን አጥፍተናል

    • @yonastaye8803
      @yonastaye8803 Před 4 měsíci

      ኢህአዴግማ ላይማር ተገንዞ ተቀብሮል። ከናፈቀህ ያለበት ቦታ ሄደህ ናፍቆትህን ብትወጣ መልካም ነው። ናፍቆትህን የምትወጣበት ጊዜ ይሁንልህ መልካም መንገድ!!!😂😂😂

  • @girmamishamo6681
    @girmamishamo6681 Před 4 měsíci +8

    ኮምዩኒስት መንግሥት መጣ ማለት ነው ?

    • @TH-qk6ez
      @TH-qk6ez Před měsícem

      ኮሚኒስት ቢያንስ መርዕና ፍልስፍና አለው። እነዚህ ፋሺስቶች ናቸው!!

  • @tesfayetenkir942
    @tesfayetenkir942 Před měsícem +2

    አይ መንግሥት የነጋዴን ሽያጭ መቆጣጠር ሲያቅተው በግለሰብ ቤት ላይ መጣ

  • @user-uf9si1lb5p
    @user-uf9si1lb5p Před 3 měsíci +3

    የመሬት ህግ ስርዓቱ(lease) ሲገርመኝ ቤት ማስተዳደር ቆይ በምን ተለየ ከቀበሌ/ fhc ቤቶች? የቢቱስ 'ባለቤት' ምንድ ነው የሚባለው?

  • @user-rz8ru3tb7i
    @user-rz8ru3tb7i Před 4 měsíci +3

    እሺ ይሁን እንበል እኔ የቀበሌ ቤት ተከራይቼ ነው ምኖረው በህጉ ደሞ የቀበሌ ቤት ማከራየት አይቻልም ይላል ይሄኛው በምን ህግ ነው ሚዳኘው

  • @user-et7wo4qe7m
    @user-et7wo4qe7m Před 3 měsíci +2

    ኮንዲኒየም ቆጥበን ለጫላ እየሰጣችሁ በሰው የግል ቤት እኛ እንወሰንልሀለን ማለት የደካማ መሪ አቅም ውሰንነት ያሳያል።

  • @ameleworkhaile3974
    @ameleworkhaile3974 Před měsícem +2

    First fix Nuro widinet.

  • @meselutadesse4925
    @meselutadesse4925 Před 3 měsíci

    ሰላም ጤና ይስጥልኝ በጣም ጥሩ እና ነፍሳችንን ሠቅዞ የያዘ ሀገራችንን እየወደድናት የዜግነት ድርሻችንን በየተሰማራንበት መስክ በመወጣት ውለታዋን ለመክፈል የምንታትር የመንግሥት ሠራተኞችን ተጣርቶ ከሚደርሰን ኔት ፔይ በላይ ስለሆነ የኑሮ ውድነቱን ለማካካስ የቤት ኪራይ አበል እንኳን ይታሰብልናል ብለን ጠብቀን በተስፋ ብቻ ያለን በመሆኑ እና ሠራተኛ ስለሆንን የግድ የምንሠራበትን ቢሮ ገፅታ ግንባታ ታሳቢ በማድረግ ያለንን ልብስ ለብሰን ሕዝብን ስናገለግል ከፍተኛ ተከፋይ እንመስላለን የሚከፈለን ደመወዝ ግን የቤት ኪራይ ለመክፈል እንኳን የማይችል ሲሆን የምግብ ፍጆታን እንግዲህ ምን እንደምንሆን መገመት አያዳግትም፡፡
    አዋጁ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ የቤት ኪራይ በባንክ እንድከፍል ስጠይቅ ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ከአዋጁ በኋላ የቤት ኪራይ በባንክ መክፈል እንዳለብንና አዋጁ በአፈጻጸም ሁኔታ ሳይሸራረፍ በአግባቡ የሚተገበርበት አስገዳጅ ሁኔታ ቢኖር ሌላው የምንከፍለው የቤት ኪራይና የቤቱ ሁኔታ አፈር ቤት ብሎኬት ቤት አፈር ቤትም ሆኖ ተገቢ ፅዳቱን የጠበቀና መሠረታዊ ፍላጐቶችን ያሟላ መሆኑ ተረጋግጦ ኪራይ የሚወሰንበት ሁኔታ ላይ ምን ሊሠራ ታስቧል፡፡
    አዋጆች ደንቦችና ሕጐች ይወጣሉ ችግሩ አፈጻጸም ላይ ስለሆነ ይህ የዜጋው ሠቆቃ የሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ እና ተጓዳኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ከህግ አውጪው ጀምሮ በተዋረድ ያለው አስፈጻሚ አመራር ለህሊናው እና በህጉ መሠረት ማስፈፀሙን በተመለከተ ተጠያቂነት ቢኖርበት አዋጁን በነበር ሳያስቀር ውጤታማ ያደርገዋል ለእኛም ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሰናል ብለን በተስፋ ረሃብ በግለሰብ ቤት ኪራይ ስቃይ ውስጥ ላለነውም እንደ ራስ ቤት ባይሆንም ከአለንበት የተሻለ ይሆን ይመስለኛል፡፡

  • @abaynehmulugeta1578
    @abaynehmulugeta1578 Před 3 měsíci +3

    ከባንክ ቀደም ሲል የተበደረ 1ሲሚንቶ ከ1500አሰከ 2000 ገዝቶየሰራበት አዳውን ለመክፈል በንኮች ይቀንሳሉ ወይ

  • @girmaeshetu3717
    @girmaeshetu3717 Před 3 měsíci +2

    ይህ በተከራይና በአካራይ የተደነገገው ደንብ በሁሉቱ መካካል ያለውን ግኑኝነት ግልፀ
    እያደረገ መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ይረዳል እላለሁ::

  • @menbereandre8860
    @menbereandre8860 Před 3 měsíci +8

    አሁን ዋናው እቅድ አከራይ ተካራይን ለማባለት እነሱ ታክስ መሰብሰ

  • @maryadam215
    @maryadam215 Před 3 měsíci +1

    Housing in Ethiopia is actually reasonable compared to other African countries

  • @coffeelatte6344
    @coffeelatte6344 Před 4 měsíci +2

    Good explanation it gives transparent approch between the government and the citizens.

  • @KabtamuFideno
    @KabtamuFideno Před 3 měsíci +2

    የነጻ ገበያ መርህን አይጻረርም ወይ
    በሌላ በኩል አንድ ቤትን ከፋፍሎ ማከራየት አይቻልም ወይ

  • @hassanjibicho
    @hassanjibicho Před měsícem

    የአከራይ ተከራይ አዋጅ መውጣቱ ጥሩ ነው ።ነገር ግን የተሠጠው የምዝገባ ግዜ አንድ ወር (30)ቀናት ያንሳል ።እስከ ነሐሴ ድረስ መራዘም አለበት ።የጥድፊያ መሆን የለበትም !

  • @aberabekele3585
    @aberabekele3585 Před 13 dny

    ህገ መንግሥታችንም ከተለያዩ አገራት ህጎች ከአገራችን ሁኔታ ጋር የሚሄዱ አንቀፆች ተወስደዉ የተዋቀረ ነዉ።

  • @faristube1982
    @faristube1982 Před 3 měsíci +1

    መንግስት ነካክቶት የተስተካከለ ነገር የለም የምግብ ሸቀጥ ከመወደዱ በፊት እንዲህ ነበር የሆነው ከዋጋ ቁጥጥር ይልቅ ባለሀብቱ ቤት እንዲሰራ ቢደገፍ ይሻለዋል

  • @rtfdift143
    @rtfdift143 Před 3 dny

    ኧረ የካርታ ማሰሪያ ዋጋ ይስተካከልልን ሰው ደፋ ቀና ብሎ ቤቱን ለመጨረስ እድሜውን ጨርሶ መኖር ሲናፍቅ ይሄ ሁሉ ጫና ግፍ ነው።

  • @HasnaAbu-yh3kt
    @HasnaAbu-yh3kt Před 3 měsíci

    አዋጁ ከመፅደቁ በፊት በውል ያልተያዙ ቤቶች አዋጅ ከፀጸቀ በኋላ ነባር ተከራይይ አጺስ ውል ይዋዋላል ወይስ አዋጅ አይመለከተውም?

  • @davidteklehaimanot4377
    @davidteklehaimanot4377 Před 3 měsíci

    Of course!

  • @saraayele-ww3sv
    @saraayele-ww3sv Před 3 měsíci

    በጣም ቆንጆ ናው ግን ግዜ ሚያጋትቱ ተቆጣጣርዎችንና በዘመድ በገዛ ቤትህ ሌላ ስው ጫናና ግዜህን እንዳይወስድ ጉዳዩ ማለቅ ሀለበት ተብሎ ሚወስንበትና ተቆጣጣርው ተጠንቅቆ ሚሰራበት ም ቢደረግ መልካም ናበር

  • @tsion3656
    @tsion3656 Před 4 měsíci +5

    3አመት ቤትኪራይ ሳይከፍል በቦሌ ክፍለ ከተማ ተከሶ በፍርድ ቤት ውጣ ውረድ ቆይቶ ከፍሎ እንዲለቅም ቢፈረድ እያስፈራራን ማስፈጸም አልቻልንም ብሎ ጠበቃውም ጉዳዩን አልከታተልም ብሎ አከራዩም ኤጀንሲ ጉዳዩን ትቶ እየኖረ ነው ፍትሕ የቱጋ ነው????????

  • @admasworkkasahun1442
    @admasworkkasahun1442 Před 4 měsíci +1

    ሄሉዬ በርቺ ብልፅግናን መንግስት ባልደግፍም እንዳቺ አይነት ጠንካራ ሴት እንስቶች ወደ ፊት ስለመጣቹ ተስፋ አለኝ Gimbechi❤

  • @mulugetameneberu1111
    @mulugetameneberu1111 Před měsícem

    የእኔን አኪራይቼ አኔ ደግሞ ሌላ ኑሮየን ለመደጉም ሥል ቅናሽ ቤት ተከራይቼ ብኖሮ ሁሉቱን እንዴት ማስታረቅ ይቻላል

  • @Ashenafi-kq3uo
    @Ashenafi-kq3uo Před měsícem

    አዋጁ ከወጣ በኋላ ራሴ እገባበታለሁ ውጣ እያሉ ነው የቤት ባለቤቶች ይቻላል ወይ? ከተቻለ ምንያክል ጊዜ ለተከራይ ይሰጠዋል?

  • @user-fu1os6my7r
    @user-fu1os6my7r Před měsícem

    ተከራይ የተከራየውን ቤት በራሱ ፍቃድ መልቀቅ ቢፈልግ አከራይ በምን መልኩ ግብር ይከፍላል?

  • @dinaoil5100
    @dinaoil5100 Před 3 měsíci

    አሰተያየት። መንግሰት። የቤት። ክራይን። እና የመኪና ክራይ። አከራዪ። በተለይ። ቤት። የሚያከራዪ ለቀበሌ አሰረክበዉ። መንግሰት።ራሱ። አከራይቶ። ብራቸዉን በ ባንከ ቢወሰዱ ለደህነ ነትም ለመቆጣጠር ይመቻል

  • @georgessaroufim7733
    @georgessaroufim7733 Před 3 měsíci +1

    ወይ ዘመን

  • @saraayele-ww3sv
    @saraayele-ww3sv Před 3 měsíci

    ይሄ ህግ ለሁሉም ስው ጠቃሚመሆኑ ን እረዳለሁ ናገር ግን በዚ ስር ሚያንገላቱን ስዎች ትክክለኛ ህግ እንዲከተሉ ጥብቅ ህግ መከተል እንዲችሉ

  • @bloomgoregina5078
    @bloomgoregina5078 Před 4 měsíci

    በሰለጠነው አለም 30% ከደሞዝ ሚከፈለው የቀበሌ ቤት ብቻ ነው ቀሪውን መንግሥት ነው ሚሸፍነው ሌላው rent control ነው እሱም በተረጋጋ ኢኮኖሚ 5% ባመት ነው ያም ሁሉም ከተማ አደለም ሌላው ህጉ ለሁሉ ነው ለምሳሌ ተከራዩ ሳይከፍል ቢሄድ ምን ማድረግ ይቻላል

  • @A_h_a_d_973
    @A_h_a_d_973 Před 2 měsíci +2

    እናመሰግናለን መንግሰት ቢያንስ በዚህ እንኳን ያግዘን

  • @tesfayeethiopia
    @tesfayeethiopia Před 4 měsíci +1

    እሄን የሚያህል ቤቶች መንግስት ሊገነባ ነው ቢባል ...
    ለምን ኮንዶሚኒየም ግንባታ ቆመ

  • @muke614
    @muke614 Před 3 měsíci

    የችግሩ መሰረት የኑሮ ውድነት ነው አከራይ የሚያገኘው የኪራይ ገቢ መተዳደሪያው በተለይ ድግሪ ይዘው ስራ ላላገኙት ልጆቹ በገቢው ስራ እንዲሰሩቡት ተጣበው ተጨናንቀው በጠባብ ቤት እየኖሩ ባሉበት ሁኔታ ለሚደረጉት ለውጦች ሁሉ ሚዛናዊ ቢሆን።ክራይ መክፈል የማይችል ስልሆነ ነው የተንጣለለ ቤት ተከራይቶ ሚኖረው?ባለቤቱ እኮ ከእነ ቤተሰቡ አከራይቶ ዝቅተኛ እና ጠባብ ቤት እየኖረ ነው።

  • @Awakedajene
    @Awakedajene Před 3 měsíci

    ተመስግን

  • @dumaarasoojjaato2171
    @dumaarasoojjaato2171 Před měsícem +1

    ሶሻሊዝም ተመልሶ መጣ ማለት ነው?🤔

  • @FoziAli-cx8ip
    @FoziAli-cx8ip Před 3 měsíci

    ተከራይ መብቱ ለሱ ብቻ መስሎት ከግንዛቤ እጥረት ምክንያት በተለይ በአከራይ ግቢ ውስጥ እየኖረ የሚረብሽ ሠላም የሚነሳ ከሆነ እንዴት ይፈታል። የግንዛቤ ችግር በሁለቱ መካከል ግጭት እንዳይፈጠር።

  • @ayelebedane2655
    @ayelebedane2655 Před 3 měsíci

    በጥናት ያልተደገፈ ሥራ ወይም ሕግ ውጤት ዬለውም። በጥናት ይሁን Please Please

  • @romanyosef7696
    @romanyosef7696 Před 3 měsíci

    Construction cost also very difficult any way being Fair is good.

  • @yordanosmearwi3339
    @yordanosmearwi3339 Před 3 měsíci +1

    How about those who are coming for vaccinations ( like 2 months or less) ?
    What if the renter has a loan against the house ( remember 17% interest from the bank ) how the renter covers the loan against the house if he or she has no rights to raise the rent
    Lot of people are renting their services or kitchen to fight the inflation right ? So if the government is implementing this policy the renter will claim back their kitchen and service rooms and which will result in housing shortages
    Most diaspora built or bought an apartment taking 401k or equity against their mortgage here , hopping they will get good rates from their tenants in ethiopia, now they will not buy a single house or apartment!!
    Last but not least before the parliament approves this ,did they discuss with their constituents ? I am afraid not !!

  • @wolansateshome6965
    @wolansateshome6965 Před 4 měsíci

    ይህ የደሞዝ ማነስና የጊዜውን የኢኮኖሚ ንረት ያላገነዘበ ክፍያ ስለሚከፈል ነው ከዚህ በኃላማ ቤት የሚሰራ ሰው አይኖርም ምክንያቱም ቤት አከራይ ግብር (የጣራና ግድግዳ) ሊዝ ያከራይ ተከራይ ስራ ከሌለው(ጡረተኛ)ከሆነ ኖሮበት ምንም አይተርፈውም እደሳም ለማድረግ አቅሙ አይችልም ስለዚህ እንደ ቀበሌ ቤት በረጂም ጊዜ ቤቱ ያረጅና እንደሰሞኑ ከተማ ማፍረስና ማደስ ልንገባ ነው የቀበሌ ቤት ሲወረስ ቤቱ ባለቤት ስለሌው 50 አመት ምንም እደሳና ጥገና ባለማግኘቱ የከተማውን ውበትና ገፅታ በማጠልሸቱ ወደማፍረስ ገባን የህ ነገር መል ሶሊደገም ነው ስለዚህ ይታሰብበት

  • @mesfinhailegiorgis7985
    @mesfinhailegiorgis7985 Před 3 měsíci +2

    Its illegal Law.

  • @user-mp5tq2qj1g
    @user-mp5tq2qj1g Před 3 měsíci

    ጥሩ ማብራሪያ ነዉ እናመሰግናለን

  • @user-hr9ux9ze5o
    @user-hr9ux9ze5o Před 4 měsíci

    ጥሩ ነው ግን ሱቅ እያከራዪን ያሉትንም ዋጋ ቢስተካከልልን ጥሩ ነበር

    • @menelikmukemil1519
      @menelikmukemil1519 Před 4 měsíci

      ሱቅ ቤት አይደለም business ነው ካላዋጣህ ዞር በል

    • @Hkim185
      @Hkim185 Před 3 měsíci

      ​@@menelikmukemil1519
      ሱቅ አምሰት አመት ነወ ሊዙ ሰልጥን

  • @fk3365
    @fk3365 Před 3 měsíci

    የኑሮ ውድነትን የሚደጉመው አከራይ ነው ወይሥ ?
    አከራዩን የኑሮ ውድነቱ አይመለከተውምን ? ያ አከራይም መተዳደሪያው ሥለሆነ የኑሮ መወደድ እንጂ ቤት ኪራይን ያናረው ሰዎች የመጨመር ፍላጎት እራሱ ብዙ አይታይም ነበር ። አሁን ግን ሁሉን በርደን አከራይ ላይ የመጣል ነገር ያለ ይመሥላል ።

  • @saraayele-ww3sv
    @saraayele-ww3sv Před 3 měsíci

    ባለቤቶች ለራሳቸው አንድ ክፊል ውስጥ እየኖረሩ ገቢ ስለሌለው ቸው ገቢ አድርገው የሚኖሩትን ገቢው ማይመጣጠን ከሆና ባለቤት እራሱ ወይም ቤተስቡ እንዲኖርበት ቢያስወጣ ግዴታው ምንድንናው

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤❤❤mandisni Mannii murtii ida'amuun hawaasaa
    Eegumsa keeesa jiraa Biyyaaf garuu Minister fayyaa Dr Kalee Dhibee wal'ansaa English language

  • @alemayheugerachew4545
    @alemayheugerachew4545 Před měsícem

    What If The Owner Wants To Demalish The Existing House & Build New G+...Could you Brief The Proceder? Thanks.

  • @user-nx2zy3uj5m
    @user-nx2zy3uj5m Před měsícem

    የክራይ ዋጋ መነሻ በካሬ ሊቀመጥ ይገባል ዋናው መፍትሄ እዚ ነው ያለው ካልሆነ የተቀመጠው መፍትሄ ሙሉ ኣይሆንም

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤Eegumsaa Dr Helan Devoted to see ida'amuun mandisni Manneen jireenyaafi nageenyaa nageenyaa mariidhaa
    Gidduu ilmaaniin keessummaa Rabbiin isinirraa haa jallaatuu

  • @tesfayetenkir942
    @tesfayetenkir942 Před měsícem

    መንግሥት መጀመሪያ የራሱን ኮንደሚኒየም አይቀንሥም ደሞ ሌላ ደሞ የሀከራይ ተካራይ የግብር ታክስ ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጎበት እንዴት ነው የሚካሄደው በጣም ነው የሚያሳዝነው

  • @user-ev7xq1yj6v
    @user-ev7xq1yj6v Před 4 měsíci +4

    መወገዳቸዉ ስለማይቀር ይቀባጥሩ ሰዉ ባገሩ መነር ያልቻለበት ዘመን ዉዳቂ መንግስት እና ከንሰሳት በታች የሆኑ ተላላኪዎቸ

  • @foziamohammed5998
    @foziamohammed5998 Před 3 měsíci

    ባለሀብቱ በቤት ልማት እንዳይሳተፍ ያደርጋል።

  • @muke614
    @muke614 Před 3 měsíci

    የኑሬ ውድነት አርግቡ አከራይ ከዚህ ውጭ ስላልሆን

  • @AnguachMelese
    @AnguachMelese Před 3 měsíci

    መጀመሪያ የኑሮ ውድነትን ማርገብ አለበት መንግስት ኑሮ ጣራ ወጥቶ እንዴት ነው ቤት ኪራይ ላይ ቁጢት ማለት ።

  • @redeatabebe7247
    @redeatabebe7247 Před 4 měsíci +1

    ተከራይስ መልቀቅ ቢፈልግ ከሁለት ዓመት በፊት

  • @selamyeshi9871
    @selamyeshi9871 Před 3 měsíci

    እናየዋለን

  • @aishaaisha7983
    @aishaaisha7983 Před 3 měsíci

    የአደገ፡አርንሲታይየግስታቸው፡ለሕዚቡአቅም፡አደኛሕዝቡሥራአለው፡እኛጋ

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤ Eegumsaa iccittii gzx yaa kolfaa karaa hoji yaadattii deebi'ee Nageenyaa fi jaalalaarraa
    Yaa❤❤Beekumsii yaa Kolfa Garaa hayyootaaf haatii ilmaan Biyyaaf Beekumsii Eegumsaa kolfee Garaa wliin fayyaan

  • @aishaaisha7983
    @aishaaisha7983 Před 3 měsíci

    የኢቲዮጵያሕዝብጎዳናነውያለው?እደአቅማቸው፡የሥራ፡እቅስቃሴ፡ድሕነትአቅማቸውንያከትታልውይ?

  • @user-wn2gi6lq4i
    @user-wn2gi6lq4i Před 3 měsíci

    በኔ በኩል የሁለት አመት እንዳይወጣ ከተደረገ ስርዐት የሌላቸው ሰዎች አሉ ይህን ሰው ሁለት አመት ሙሉ ሲባላ ይኖራል ማለት ነው?በገዛ ንብረቱ መቃጠል ማለት ነው

  • @romanyosef7696
    @romanyosef7696 Před 3 měsíci

    The tax payment is very high the tenant pay 2 taxes one is for the house and will pay rent tax almost pay half of the rent.

  • @abdeshokra5688
    @abdeshokra5688 Před 3 měsíci

    በግምት ነው የሚሰራው

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤❤❤ yaadii argii Danddeettiin eaa yaadachuu karaan gzx Kutaa odeeffaannoo barnootaa ummaataaf Yaadannoo telecommunications

  • @bereketbemenet503
    @bereketbemenet503 Před 3 měsíci

    መግስት የምሰራው መልካም በቅንነት ህግ ቢያወጣም እዚ ሀገር በማንኛውም ጉዳይ የአፈጻጸም ችግር አለ ለሙስና በጣም በር ይከፍታል አፈጻደም ላይ ባጠቃላይ ጥንቃቄ ይፈልጋል ‼️መግስት በሰው ንብረት ምናገባው እራሱ ሰርቶ ነው ገበያውን ማውረድ የምችለው ይህ ቀኝግዛት ነው በህዝብ መሀል ጣርነት መክፈትነው❌❌ 32:21

  • @marthasolomon7295
    @marthasolomon7295 Před 3 měsíci

    You said 6 month notice
    But the low side 2 month notice.
    Confusing

  • @ayelebedane2655
    @ayelebedane2655 Před 3 měsíci

    የቤት ክራይ በኢትዮጵያ በጣም ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ነው የሚባለው መነሻው ምንነው? አትስሳቱ በጣም ዝቅተኛ ። ያልተጠና ነገር ማውራት ጥሩ አይደለም ።

  • @abenezer7052
    @abenezer7052 Před 4 měsíci

    የቤት ክረይ ቢቻ አይደለም የተከራይ ችግር ውሃውንና ማብራት እያሉ 1000 ብር ጨምር ለውሃው 500 ጨምር እያሉ ተከረዩ እንድማረር የሚያደርጉ አሉና በዚህላይ ምን ታስቧል ?

    • @millimilli-cq5dh
      @millimilli-cq5dh Před 3 měsíci

      ምቀኛ
      አንተም እንደነሱ ቤት ስርተህ አክራይ

  • @tteklu
    @tteklu Před 4 měsíci

    Through all these loopholes Abye,the PM, is buying time to sit on his bottom for ever.

  • @user-vv9hm6cn6u
    @user-vv9hm6cn6u Před 3 měsíci

    በ መቶ ምን ያህል ነው የምንከፍለው

  • @weynshetadmassu3795
    @weynshetadmassu3795 Před měsícem

    አይ ተከራ አሁን የሚከፍለውን ከፍያ ተስማምቶ እየከፈለ እያወቀ በዚህ አዋጅ እንዲቀንስለት አንድ ተከራይ ሲጠይቅ ሰማው ሰውዬው የእራሱን ጥቅም ብቻ ነው የአከራዩ ቤቱን እንዴት እንደሰራው አያቅምና መንግስት ለተከራይ ብቻ የቆመ ይመስለዋል ወዳጄ አከራይም የመንግስት ዜጋ ነውና አሁን በምትከፍለው የሚቀጥለው ሚንስተሯ ተናግረው ነበር ተከራዩ እንዲቀንሱለት ይፈልጋሉ

  • @user-xz5ll5gi1n
    @user-xz5ll5gi1n Před měsícem

    Coraption, coraption, need to weed out coraption. የቀበሌ፡ ቤት ጠይቄ፡ / ሚልዮን ብር ጉቦ ነው፡ የጠየቁ ኝ ፣ወሪ፡ ብቻ፡ ስር ነቀል ለውጥ፡ ያስፈልጋል

  • @AnguachMelese
    @AnguachMelese Před 3 měsíci

    ግለሰብ መከራውን አይቶ የሰራውን ቤት እናንተ ልትወስንለት አትችለሉም ግብር ጣራ ላይ አውጥታችሁ ምን ማለት ነው ።

  • @S-gd4tk
    @S-gd4tk Před 3 měsíci +1

    ማ ሻእ አላህ የሂጃቧ ንግስት
    ሴት የምትዋበው በሂጃብ ብቻ ነው🎉❤❤በርች ውዷ

  • @user-gx8fw6zs9v
    @user-gx8fw6zs9v Před 4 měsíci

    ደቡብ ሚዕራብ ማጣት የማይገባው እንስት አመራር ነበረች አሁንም አልረፈደም ክልሉ ጠንካራ አመራር የሌለበት ከክልሉ ግብርና ቢሮ ሐላፊ ውጪ ጠንካራ አመራር የለውም ስለዚ ወይዘሮ ሄለንን መጠቀም አለበት ቢዬ አሥባለው

  • @girmatadesse-eq3gc
    @girmatadesse-eq3gc Před 3 měsíci

    አከራይ በቤቱ ላይ አትወሥንም ማለት ለህዝብ ማሠብ አይደለም እራ ሱ መንግስት ቤት ሲሸጥ በፈለገው የጨረታ ተመን አስቀምጦ አይደል ይሄ ትክክል አይደለም

  • @FoziAli-cx8ip
    @FoziAli-cx8ip Před 3 měsíci

    ችግር እፈታለው ብሎ ችግር እንዳይፈጠር። አንድ አንድ ተከራይ ፉከራ ጀምረዋል። ጥንቃቄ ይደረግ።

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤ Eegumsii maaf kolfuu didee? NAMNI YAADEE cuftinuu dafii hibadhu Beekumsii Eegumsaa haqaaf didee

  • @tesfayeethiopia
    @tesfayeethiopia Před 4 měsíci

    እናቴ ሚቆጣጠር መቼ ጠፍ ሚፈጥር እንጂ

  • @sifaanfayyaakoo7419
    @sifaanfayyaakoo7419 Před 3 měsíci

    ❤ Eegumsaa iccittii ijjis humna dhageeffatu qabsoo Ogeeyyiin fayyaan aswrwb hawaasaa mannii eeguu gurruma/riqicha Beekumsii Ogeeyyiin fayyaa teettuus Eegumsaa wawrwb deemsis hojii dhalootaa Worannoon manni barnootaa isinif haatayuu.

  • @neimanurya7377
    @neimanurya7377 Před 3 měsíci

    በኪራይ አለቅን ኧረ መላበሉን የቆጠብነውም አልወጣልን