G&B song of the week "እስኪነጋ ለምን አልጠብቅም"

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 25. 08. 2024
  • እስኪነጋ ብታገሰው ምናለበት
    እስኪነጋ ለምን አልጠብቅም/3/
    ድቅድቅድ ጨለማው ቢከበኝ በዙሪያዬ
    ፅልመቱ ቢያይልበትም በርትቶ ላይኔ
    ተስፋ ስቆርጥ ለሊት ረዝሞ ሲመሽብኝ
    ፀሐይ ወጥታ እንደማታውቅ እስኪመስለኝ
    ታዲያ ልቤን አስታግሼ ልጠብቀው እስከሚነጋ
    ያስበኛል አይተወኝም በጨለማ
    ደግሞ አንግቶት የነገን ቀን የሚሆነው አይታወቅም
    በመታገስ ለምን ታዲያ አልጠብቅም
    እስኪነጋ......
    በጨለማ ላራት መቶ አምሳ አመታት
    ተሰቃየ የእስራኤል ሕዝብ በባርነት
    ረዘመበት ያ ስቃዩ ተጨነቀ
    አምላክ የተወው የረሳው እየመሰለ
    ነገር ግን ዘመን መጣለት ባምላኩ ታሰበ ታየ
    ያ የጨለማ ዘመኑ ተገፈፈ
    ለኔም ነገ ይመጣልኛል ያ የበረከት ዘመኔ
    እስከኪነጋ እታገሰዋለሁ አምላኬን
    እስኪነጋ......
    የታመኑት ይቤዠናል ብለው አስበው
    ለሶሰት አመት ተኩል ሙሉ ተከትለው
    ዛሬ ግን በቀራኒዮ ተሰቀለ
    ከዚያም አልፎ በሰዎች እጅ ተገደለ
    ታዲያ ለሞተው እሬሳ እንዳይሽት ብለው አሰቡ
    ለሊቱን ሽቶ ሲቀምሙ አመሹ
    ማለዳ ተነስተው ሄደው ያዩት ነገር ገረማቸው
    ሬሳ ያሉት በትንሳኤው ቀደማቸው
    እስኪነጋ......
    በዙሪያዬ የምሰማው የማየው
    ግራ ተጋባ አዕምሮዬ ጨነቀው
    መልስ የለውም መላ ቅጡ የጠፋበት
    አንዱን ሲሉት ሌላው ደግሞ ሲፈስበት
    የግል የቤተሰብ ጉዳይ ያገር የዓለም አቀፉ
    ሁሉም መፍትሄ የሌለው ነው ከንቱ ክፉ
    ግን ልታገስ ለአንድ ቀን ልቤም ተስፋ ሳይቆርጥበት
    መላ መስጠት ለአምላኬ አያልቅበት
    እስኪነጋ......
    ከቁጥጥር ውጪ ሆነብኝ የምለው
    ቀን ከለሊት ሃሳቤን ሁሉ የገዛው
    አቤት ብዛቱ የፈተናው አይነቱ
    ለአይን ለጆሮ የሚሰቅ በየዕለቱ
    ለኔ እንጂ ላምላኬ ይሄ አይደለም ከርሱ በላይ
    ያነጋዋል የጨለመውን ሰማይ
    ከስጋቴ አሳርፎኝ ይሰጠኛል ፍፁም ዕረፍት
    እስኪነጋ......

Komentáře • 319

  • @hailuelias993
    @hailuelias993 Před 3 měsíci +5

    እናንተ የእውነተኛይቱ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በረከቶች ናችሁ። በእናንተ ሆኖ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን ሲያበጃት ሲያዘጋጃት ይገኛል። የጌታ ጸጋ ይትረፍረፍላችሁ እየጨመረ ይብዛ! የእውነት በጣም ነው የሚወዳችሁ።

  • @evatetho8401
    @evatetho8401 Před 9 měsíci

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤አሜን ንንንንንንንንን

  • @sahaysahay
    @sahaysahay Před 5 měsíci +1

    ❤❤❤❤❤😭😭😭😭😭አሜንንንንን እጠቢቃለሁ🙏🙏🙏🙏🙏

  • @eyerusalembeyene2336
    @eyerusalembeyene2336 Před 3 měsíci +1

    Amen

  • @Rimna-pk8pr
    @Rimna-pk8pr Před 4 dny

    አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-od7th8vh6g
    @user-od7th8vh6g Před rokem

    አሜንንን አሜንንን አሜንንን 🙏🙏🙏🙏🤲🤲🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @melakuteka1955
    @melakuteka1955 Před 4 lety +35

    ለነ ችኩልነት ጌታ የላከልኝ ድንቅ መልእክት። እሺ እስኪነጋ እጠብቃለዉ።

  • @user-ng4sy1xq7e
    @user-ng4sy1xq7e Před 2 lety +1

    ቁዱሳን ሁላችዉሙ
    ተባረኩልኝ
    የሰራዊት እግዚአብሔር ይባረካቹው ተባረኩ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @bezatadele2575
    @bezatadele2575 Před 5 měsíci +1

    እስኪነጋ ለምን አልጠብቅም
    ነገ ሚሆነውን እኔ አላውቅም
    አሜን ጌታ ይጠበቃል ተባረክ!!!

  • @endalechwonde995
    @endalechwonde995 Před 3 měsíci +1

    ይህ መዝሙር “እስኪነጋ ለምን አልጠብቅም” ከተዘመረ 3 ዓመት ሆኖታል፡፡ ለእኔ ግን የጊዜው ቃል ሆኖልኝ ከብዙ ጭንቀት አሳርፎኛል፡፡
    እስኪነጋ መጠበቅ አቅቶኝ ዛሬ በጭንቀት ልፈነዳ የደረስኩባቸው ነገሮች ብዙ ሆነው አገኘኋቸው፡፡
    እስኪነጋ ልጠብቅ፣ ነገ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ልይ…ብዬ ሲነጋ ችግሩ የለም፡፡
    ለማንኛውም ነገር ዛሬ የሚመለከተው ጉዳይ ላይ ብናተኩር እንዴት መልካም እረፍት በሆነልን!
    የመዳን ቀን ብቻ ነው ዛሬ የተባለው፡፡
    G&B ministry ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርካችሁ

    • @getayawekal
      @getayawekal  Před 3 měsíci

      ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን ጌታ የሰራውን ምስክርነት ስላካፈሉን ጌታ ይባርኮ ይሄ ለኛም ለሌሎችም እምነትን ይጨምራል። አሜን

  • @danielmengesha7176
    @danielmengesha7176 Před 2 měsíci

    አሜን‼️እግዜር መልካም ነው። እግዜር የልጆቹን እንባ የሚያብስበት ቀን አለው።

  • @EnanaNorahun-yk9gu
    @EnanaNorahun-yk9gu Před rokem

    አሜን

  • @bamamedia6367
    @bamamedia6367 Před 4 měsíci +2

    ሕይወቴን ሁሌም የማድስበት መዝሙር ነዉ :: እንደገና እንደገና ሕይወት ያገኘሁበት የተባርኩበት መዝሙር ነዉ :: ዘመናችሁ ይባረክ :: እንደፈለጋችሁ ተባረኩልኝ!!

  • @elsabirhanu7803
    @elsabirhanu7803 Před rokem +1

    አሜን አሜን አሜን እክነጋ እጠብቃለው

  • @user-ht6fk4rc7z
    @user-ht6fk4rc7z Před rokem

    እግዚአብሄር ለእኔም ቀን አለው

  • @dameechiloo7079
    @dameechiloo7079 Před 4 měsíci +1

    All heavenly blessings be upon you! What a heartwarming and healing son❤

  • @areloyicha840
    @areloyicha840 Před rokem +1

    Amen Amen Amen Amen 🤲🤲🤲🙏🙏

  • @konjitaguade7255
    @konjitaguade7255 Před 2 lety

    ጌታ ይባረክ

  • @eyesusyadinal1444
    @eyesusyadinal1444 Před 2 lety +1

    እሺ ጌታ ሆይ እጠብቃለሁ👏👏👏👏👏👏

  • @AshenafiWyohannes
    @AshenafiWyohannes Před 2 měsíci

    የተወደዳችሁ ውዶች ጌታ ይባርካችሁ።ሁሌ በእናንተ ህይወት እባረካለሁ ይህ ፀጋ ይብዛላችሁ።

  • @fausiaeuthopia2708
    @fausiaeuthopia2708 Před 4 lety +2

    እጠብቃለሁ፣ጌታ፣እስክፈወስ፣አዉቃለሁ፣እንደማትረሳኝ፣አዉቃለሁ፣ተባረክ፣የእግዚአብሔር ፣ልጅ፣እጠብቃለሁ

  • @user-fh1gs7jy7s
    @user-fh1gs7jy7s Před rokem

    Amen!

  • @kenyaalolawaqqaa3680
    @kenyaalolawaqqaa3680 Před 2 lety

    Amen 🙏 🙏 🙏 🙏 ebifaamaa

  • @emudemissieyeeyesus7610

    Amen amen amen 😭😭😭😭😭እስኪነገ ለምን አልጠብቀም 😭😭😭

  • @wondimuwakjira2373
    @wondimuwakjira2373 Před 3 lety +1

    Ameeeeeeen Ameeeeeeen

  • @hiwotwoldearegay3800
    @hiwotwoldearegay3800 Před rokem

    ሊነጋ ሲል እጅግ ይጨልማ

  • @hanokfisahaye7097
    @hanokfisahaye7097 Před 4 lety +2

    Amen Amen Jesus Kristus Amen Jesus Kristus Amen Jesus Kristus Amen Jesus Kristus Amen Jesus Kristus Amen Jesus

  • @bekelusolomonmekonnenhaile9732

    This the best gift of songs updates song

  • @user-ob1xd7kt4h
    @user-ob1xd7kt4h Před 6 měsíci

    አሜንንንን እግዚአብሔር አምላክ ይባረክ ❤❤❤❤❤

  • @mulumulu6526
    @mulumulu6526 Před 2 lety

    Geta enanten sileseten enameseginewalen tebarekuligh eshi eskinega etebikalew

  • @gezeshegmichael3899
    @gezeshegmichael3899 Před 2 lety +15

    በተለያ ምክንያት በህይወት ዝዬ ለፀሎት ተንበርክኬ እየፀለይኩ ከዩቲዩብ መዝሙር ስመርጥ ያገኘሁትና በህይወት በተክክል ያለሁበትን ቁልጭ አድርጎ ያሳየኝ፣ ጌታን በትዕግስት እንድጠብቀው ያስተማረኝ በእንባ ያዳመጥኩት መዝሙር ነው። ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ።

  • @meseretldamenu9841
    @meseretldamenu9841 Před 3 lety +1

    አሜን አሜን

  • @sirgutealemayehugatayebare1543

    Ameeeen Gata zamanaheune yebarake.

  • @emebettarekegn6078
    @emebettarekegn6078 Před 2 lety

    እናንተ ብሩካን ተዉልድ ዘመናችሁ ይባረክ

  • @emudemissieyeeyesus7610

    Amen🥺🥺🥺😭😭😭lene new yimezimur

  • @MathathaHappy
    @MathathaHappy Před 4 měsíci +1

    Amen ❤🙏

  • @aberasheaberashe1458
    @aberasheaberashe1458 Před 3 lety +1

    ሳሚች አለጣግብም በእውነት ተበርክ

  • @mebrahtuabraha7756
    @mebrahtuabraha7756 Před 2 lety

    አዎ ያየረዘመ የመሰለኝ ሌሊተ ይነጋሌ ጌታ ሆይ እባክህ ትግስትና ፅናት ስጠኝ

  • @genetendale8131
    @genetendale8131 Před rokem +3

    ጌታ ይባርክህ ወንድሜ ጌታያውቃል ሁሌምመዝሙራችሁ የማያረጅ የሚያበረታ ነው

  • @rametodamissie8916
    @rametodamissie8916 Před 2 lety

    Eg/r zemanachun berkoalina teberaku bizu midritun ahunim wuresu!!!!!!!!

  • @shitaberhanu8987
    @shitaberhanu8987 Před 3 lety +1

    Yecelemewun semay anegalign destan belibe cemere getaye.ameseginalew

  • @dessaababa8820
    @dessaababa8820 Před 2 lety

    ዘመነችሁይበረክረዥምዕድሜታመኘሁለችሁ🍇🌹🍓🙇🙇🙏🙏

  • @yoditbeyenemebrahtu5188
    @yoditbeyenemebrahtu5188 Před 4 lety +1

    Amen.

  • @tsinulegeta6919
    @tsinulegeta6919 Před 4 lety +20

    የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ የማደንቅበት ለእናንተ የማያልቅበት ዝማሬ ነው በእውነት እግዚአብሔር ን ስለዚህ ልገሳው ይድነቃችሁ ።
    እግዚአብሔር ይመስገን ወደእርሱ የሚያሳይ ዝማሬ ኑው ዛሬም

  • @tilahunchali6699
    @tilahunchali6699 Před 2 lety

    amen

  • @bahiruadamu9023
    @bahiruadamu9023 Před rokem

    ጌታ ዘመነቹዉን ይባሪክ

  • @teklebayiru5392
    @teklebayiru5392 Před 5 měsíci +2

    ትባረኩ ወንድማችን ጌታያውቃል እህታችን ብሩክታዊት እናታችን ወንጌላዊት ጥሩወርቅ እና መላው የልጅ ልጆች ከአገልግሎታችሁ ጭምር ለምልሙልን ፀጋው ጥቅማችን አደሪጋችሁ

  • @eyesusyadinale4048
    @eyesusyadinale4048 Před 4 lety +8

    አሜን ተባረኩ።መጠበቅን እንድንችል ጌታ ኢየሱስ ይርዳን።ዘመናችሁ ይባረክ።🙋🙋🙋❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏

  • @endaleteshome6980
    @endaleteshome6980 Před 2 lety

    አሜን ተባረኩ

  • @tessydaniel9739
    @tessydaniel9739 Před 4 lety +12

    የተወደዳችሁ የእ/ር ቤተስቦች ሁሉን በጌታ ቃል የሚስራባችሁና ፣ቃሉንና ድምፁን እየ እስማችሁ የምታስትምሩ ቅዱሳን ወገኖቼ የጌታ እየሱስ ክርስቶስ ስላምና ፍቅር ለዘለአለም ከእናንተ ጋር ይሁንንንንን። በጣም እወዳችኋለሁ ። ተባረኩልኝ።

  • @bekelusolomonmekonnenhaile9732

    GOD BLESS YOU OFFCOARSE WE MUST WAIT GOD

  • @sammyalemu5248
    @sammyalemu5248 Před 4 lety +3

    ሁሌም ጌታን መጠብቅ ይሁንልን። ውድ ወንድማችን እጅግ ተባረክ።

  • @tsidutaye1285
    @tsidutaye1285 Před 8 měsíci

    ❤❤ Amen Amen sweet song God bless you and your family more

  • @habtezemen2369
    @habtezemen2369 Před 4 lety +1

    Amen Amen Amen Amen Amen!!!!
    Jesus is Lord!!!
    Geta yawkal ,tebarekilin!!!!!

  • @user-nj9jd2wy9t
    @user-nj9jd2wy9t Před 2 lety

    ጌታአብዝቶ ይበርከችሁ አሜን

  • @meskerem.m3161
    @meskerem.m3161 Před 3 lety +1

    አሜን አሜን አሜን አሜን
    አሜን አሜን አሜን
    አሜን አሜን❤❤❤🙏🙏

  • @meskeremsimonwake505
    @meskeremsimonwake505 Před rokem

    Ahun lalehubet yi zmare melkt new tebaraku

  • @mulukengetahun2094
    @mulukengetahun2094 Před 5 měsíci +1

    Tebrak❤❤

  • @zenebechhunde4447
    @zenebechhunde4447 Před 4 lety +1

    Geta Yesus Yibarkih Yenegen mane Yawkal

  • @tenagneworkzergaw259
    @tenagneworkzergaw259 Před 2 měsíci

    እግዚአብሄር በስጣችሁ አገልግሎት ክዘላለም እስከ ዘላለም ስሙ ይባረክ አያልቅበትምና እናንተንም አምላክ😢 ፍፃሜአችሁን ያሳምርላችሁ ተባርኩ አገልግሎታችሁን በጣም ነው የማደንቀው ለሚሆነው ነገር ወይም ሊሆን ላለው የሚሰጣችሁን ዝማሬ ሳላደንቅ አላልፍም ተባረኩ።

  • @tebetekeste6345
    @tebetekeste6345 Před 4 lety +2

    Tebareku zemenachu yibarek G&B

  • @lalissa1744
    @lalissa1744 Před 2 lety

    It is a wonderful song, bless you.

  • @selomebeshash654
    @selomebeshash654 Před 3 lety

    Amen Getshye!!

  • @betelemarega4932
    @betelemarega4932 Před 2 lety

    AMEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN AmEN

  • @tsionaboneh2269
    @tsionaboneh2269 Před rokem +1

    Ufffff I have no words to bless you may God fill you by his spirit more and more

  • @bekelusolomonmekonnenhaile9732
    @bekelusolomonmekonnenhaile9732 Před 10 měsíci +1

    God bless you

  • @aberanidane8912
    @aberanidane8912 Před 3 lety +1

    አረ ጌታ ይባርክህ

  • @gezahgnmeseret118
    @gezahgnmeseret118 Před 4 lety +1

    አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን ዝምንህ በኢየሱስ ስም ይባራክ ታባራኩ እስኪ ነን ለምን አልጠበቅም ንግ ምህናህን እኔ አልውቅም 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙌🙌🙌🙌🙏🙏

  • @eliasabebe4032
    @eliasabebe4032 Před rokem +1

    Wow በትክክል አሁን እያሳለፍኩ ያለውት ህይወቴን ነው የዘመርክልኝ😢😢እስኪነጋ እጠብቃለው😢😢

  • @asia2852
    @asia2852 Před rokem

    Ameeeeeeeeeeeeeeni tabikalo esikanage ameeeeeeeèeni ameeeeeèeeeeèeeni 🙏🙏🙏🙏🙇‍♀️🙇‍♀️🙇‍♀️🙇‍♀️🙏🙏🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏👏👏👏❤❤❤

  • @genetsade6865
    @genetsade6865 Před 4 měsíci +1

    እግዚአብሔረ አምላክ አብዝቶ ይባረክ
    እስኪነጋ መጠበቅ ይሁንልኝ ነገ ምን እንደምሆን አላዉቅም

  • @elsasamuel619
    @elsasamuel619 Před 2 lety +3

    በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል!!!!!
    #ጌታ_ይባርካችሁ!!!!!

  • @derejeabera941
    @derejeabera941 Před 8 měsíci

    ይህን መዝሙር ስትዘምር ለእኔ ብቻ የተዘመረ ጌታን እንድጠብቀው ጊዜ እንደቀረኝ ያስተዋልኩበት በብዙ እንባ በጌታ ፊት ከጌታ ጋር የተገናኘንበት ጊዜ ......የዛሬ 3አመት..... ጌታ ዘመንህን ይባርክ ጌትሽ

  • @kirsemekonnene6768
    @kirsemekonnene6768 Před 3 lety +1

    ጌታ የሰጠን በረከቶች በደሙ ተሸፍናችኃል

  • @selamawittamere8508
    @selamawittamere8508 Před 4 lety +3

    Very touching song

  • @seniathabtagbreal6727
    @seniathabtagbreal6727 Před 2 lety

    አሚን አሚን የጠበቀ አልከሰረም ከጊታ ከሙላቶ አልጉደለም ጊታሁይ ፀጋህ ይብዛልኚ !!!!!

  • @martatenker5973
    @martatenker5973 Před rokem

    ጌታ ይባረክ ተሰምቶ አይጠገብም ፀጋው ይብዛላቹ

  • @mozartbelachew298
    @mozartbelachew298 Před 4 lety +7

    አሜን እስኪ ነጋ እጠብቃለሁ ጌታ ሀይል ይሰጠኛል እጠብቃለሁ ለሀሬ
    እግዚአብሔር አምላክ ፀጋውን አብዝቶ አብዝቶ ያብዛላችው ከዚህ በላይ ተባረኩ!

  • @melakuteka1955
    @melakuteka1955 Před 4 lety +14

    I'm so blessed by this song. God bless you my dear brother Getish.

  • @misrakroyer234
    @misrakroyer234 Před 3 lety +1

    Egizabher melkam new....

  • @jesusmydadjesusislordnursa9632

    አሜን እግዚአብሔር ትልቅ ነው እስክ ነገሀ ለምን አልጣብቅም ነገህ የምሆናሁን እኔ አላቅም ታባርክ ታይሻው

  • @tedbirr12344
    @tedbirr12344 Před 3 lety +1

    እሽ አምለኬ እጣብቅሃለው

  • @l.m7401
    @l.m7401 Před 4 lety +9

    ተባረኩ! ተስፋ ሰጪ የሆነና ትዕግስትን የሚያጎናጽፍና የሚባርክ ዝማሬ ነው።
    አገልግሎታችሁ ይባረክ።

  • @miryamgoytom8240
    @miryamgoytom8240 Před 4 lety +2

    Tebarku sewdachu geta yebarkachu

  • @kakiregassa2974
    @kakiregassa2974 Před 4 lety +1

    እሰይ እየሱስ ክብር ላንተ ይሁን

  • @abuabi812
    @abuabi812 Před rokem

    ተባረክ

  • @abejeabushabejeabush-fe9lu
    @abejeabushabejeabush-fe9lu Před 10 měsíci

    ዘመንህ ይበራክ

  • @meserettaye2617
    @meserettaye2617 Před 3 lety +2

    በጣም የሚገርም መዝሙር ነው ልክ የኔን ጉዳይ አውቃችሁ የምትዘሙሩልኝ ነው የተሰማኝ ተባረክልኝ እስኪ ነጋ እጠብቃለሁ

  • @almazhaile1751
    @almazhaile1751 Před 4 měsíci +1

    Amen and Amen!!! Yes, May The Lord Jesus Christ bless you all!!! " OUR LORD IS SO FAITHFULL HE IS ALSO ALMIGHTY"

  • @KokobeSha
    @KokobeSha Před měsícem

    ተባረኩ

  • @Joshua.8704
    @Joshua.8704 Před 4 lety +6

    🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌😭 እስኪነጋ መጠበቅ የምንችልበትን አቅምና ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልን 😭😭😭😭😭😭🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌 መፅሐፍ እንደሚል (“የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፤ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።” - ምሳሌ 13፥12)
    *, መጠበቅ በጣም ከባድ ነገር ነው።🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌😭 እግዚአብሔር ፀጋ ያብዛልን። ያለ እግዚአብሔር ፀጋ ነገን በተስፋ መጠበቅ በጣጣም ከባድ ነገር ነው።
    🙌 ተባረኩ።❤

    • @yaredsemon2330
      @yaredsemon2330 Před 4 lety +1

      ምን እንደምል አላውቅም ያባቴ ብሩካን ተባረኩ እ/ር ፀጋውን ያብዛላችሁ።

  • @bbhuhh5737
    @bbhuhh5737 Před 4 lety +1

    እሰኪ ነጋ ለምን አልጠብቅም አሜን አሜን እጠብቃለሁ ተባረኩልኝ

  • @tsiondenbualaw4088
    @tsiondenbualaw4088 Před rokem +1

    Amen 🙏 stay blessed 🙏 🙌

  • @terunehgossaye2687
    @terunehgossaye2687 Před 2 lety

    አዎን እግዚአብሔርን የሚጠባበቁ አያፍሩም።እግዚአብሔር ፀጋውን አሁንም ያብዛላችሁ።

  • @merhawi9isak661
    @merhawi9isak661 Před rokem

    Egzabher zemenashu ybark

  • @dibora7910
    @dibora7910 Před 4 lety +2

    ameni ameni ba naziretu ba eyesusi simi tabaraku

    • @yohanistom6759
      @yohanistom6759 Před 4 lety +1

      ተባረኩ B&G

    • @yohanistom6759
      @yohanistom6759 Před 4 lety +2

      እንደናንተ ያለ መንጋትን የሚያውጂ ያስፈልጋል በጽናት በትጋት ይህንን ጭላማ ማለፋ በእንዲህ ያላ ዘመን ታስፈልጋላችሁ

    • @pixelpioneery
      @pixelpioneery Před 4 lety

      Zerachihu.....yibarek love you. ❤❤❤

    • @gebruwoldeyes9468
      @gebruwoldeyes9468 Před 4 lety

      Amen God bless you

  • @sarabekele3581
    @sarabekele3581 Před 2 lety +1

    አሜንን አሜንን ጌታ ቢዘገይም አይዘገይም የሚቀድመው የለም አዎ ይነጋል እንደጨለመ አይቀርም ተባረኩልኝ

  • @yeshibedada6087
    @yeshibedada6087 Před 2 lety +2

    የሚጠግን የሚደግፍ መዝሙር ሰምቼ ሰምቼ አልጠግብ አልኩ የተስፋ ቃል ያለው መልክትን ያዘለ እግዚአብሔር አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ

  • @asefashtekeste3386
    @asefashtekeste3386 Před 4 lety +3

    እግዚአብሔር መረጋጋትን ይስጠን ፣ተግሰን ከጠበቅነው ከመልካሙ አምላክ መልካም ነገር ይመጣል።አብረሃም እግዚአብሔርን ተማምኖ አገሩንና ወገኑን ትቶ ወጥቶ ነበር።ነገር ግን እስኪነጋ መጠበቅ አቅቶት እስማኤልን አምጥቶ እስከዛሬ ድረስ ለእስራኤል ጠላት አመጣ።
    እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ጌትዬ ጸንቶ መጠበቅን ያስተምራል።

  • @abarazabdola4078
    @abarazabdola4078 Před 4 lety +1

    Ameeeeeeen
    Endinxabiq Geta Eyesus yirdan
    Tabaraku Geta abizito ybarikachihu