ቅድስት ዮስቲና እና ቅዱስ ቆጵርያኖስ - ክፍል 1 / Saints Justina and Cyprian - Part 1 - Ye Kidusan Tarik

SdĂ­let
VloĹžit
  • čas přidĂĄn 22. 08. 2024
  • 💗 ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና 💗
    ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ #አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::
    በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም #ዮስቴና(የሴቶች እመቤት) ይባላል:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::
    በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ::
    ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ #ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::
    አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን #መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::
    ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት - የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኩዋን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ::
    "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ:
    ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
    ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ #ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
    አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና (Tunisia) ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቁዋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም መስከረም 21 ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::
    ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን:: አሜን
    ምንጭ ››› "ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Saints" የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
    የህን መንፈሳዊ ፊልም አዘጋጅተውና ተርጉመው ላቀረቡልን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡ አሜን፡፡
  • ZĂĄbava

Komentáře • 242

  • @netsanet.netsanet1256
    @netsanet.netsanet1256 Před 6 lety +101

    አሜን አሜን አሜን በውነት ቃል ህይወት ያሰማልን በገራችን ሆነን የማናይ0ውን በስደት እያየን እምነታችንን እንድናጠክር መንፈሳዊ ቅናት እንዲድርብን እያረጋችውን ነው ፀጋውን ያብዛላችሁ ብዙ የማናቀው እንድናውቅ በንባም እንድንታጠብም አርጋችውናል ቃል የለኝም በርቱ ይህን ታላቅ በረከት ለኛአ ለደካሞቹ የምታደርሱልን አባቶች ወንድሞች እህቶች እድሜ ከጤናአ ጋር ይስጥልን አሜን አሜን አሜን

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  Před 6 lety +5

      አሜን እህቴ

    • @user-te1ot3vs9f
      @user-te1ot3vs9f Před 6 lety +3

      Netsanet. አሜን አሜን አሜን Netsanet አሜን አሜን አሜን በእወነት ትክክል አገላለፅ ገልጸሽዋል

    • @user-ed9pz5ig5f
      @user-ed9pz5ig5f Před 6 lety

      አሜን የአባታችን የአባ ቢሶይ ወይም ቢሾይ መንፈሳዊ ፊልም ካላች ላኩልን እኔ በጣም ስለምፈልገው ነው እና በጣም አስተማሪ ስለሆነ ነው

    • @zahrazahra8887
      @zahrazahra8887 Před 5 lety

      አሜን

    • @user-sq5qn8es5b
      @user-sq5qn8es5b Před 4 lety

      አሜን አሜን አሜን❤❤❤

  • @tcxjhvc2190
    @tcxjhvc2190 Před 6 měsĂ­ci +5

    ይህን በረከት እድናይ የፈቀድክልን የእመ ብርሀን ልጅ ክብርና ምስጋና ላተ ይሁን👏👏👏❤❤❤❤❤

  • @hanamariyam829
    @hanamariyam829 Před 6 lety +74

    በመጀመሪያ ይህን እንድናይ የረዳን የድንግል ማርያም ልጂ እየሱስ ክርስቶስ ይመስገን በረከታቸው ይደርብን ላቀረቡልን እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላቸው

    • @mekdeszetewahedoegziabherm7438
      @mekdeszetewahedoegziabherm7438 Před 3 lety

      ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን እንጻፍ

  • @ejiguakebede457
    @ejiguakebede457 Před měsĂ­cem +1

    ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ሁሉም ነገር ክብር ክብር ክብር ምስጋና ይገባሃል የኔ አባት ተመስገን አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ይሁን 🙏🙏🙏🙏 አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @user-tj4lt5pj6b
    @user-tj4lt5pj6b Před 6 lety +40

    አመሰግናለሁ ። የልበ አምላክ የአባታችን ቅዱስ ዳዊት እባካቹህ ልቀቁልን

  • @fisehamaryam5983
    @fisehamaryam5983 Před 2 lety +7

    ስደቴ ለኔ የ ገዳም ህይወት ነዉ💓
    እግዚአብሔር ይመስገን

  • @tigistashuma6088
    @tigistashuma6088 Před 4 měsĂ­ci +2

    እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የፃድቃን፣የሰማይታት፣በረከታቸው፣ረዴታቸው፣ይድርብን

  • @alemtsehayworku7160
    @alemtsehayworku7160 Před 4 měsĂ­ci +2

    ቃለ ህይወት ያሰማልን በእውነት የቅዱሳ በረከታቸው ይደረብን

  • @tesfaneshmazengiya5867
    @tesfaneshmazengiya5867 Před 6 lety +31

    ቃለሂውትን ያሰማልን! !!የቅዱሳኑ እረዴት በርከታቸው ያሳድርብን !!!!

    • @samsungsam4681
      @samsungsam4681 Před 3 lety

      አሜን እፍ ክርስቲያን መሆን እንዴት ደስ ይላል ትህትና ስርአቱ እንደ አባቶቻችን ቢንሆን 😭

  • @user-cx5bv8wh8z
    @user-cx5bv8wh8z Před 6 lety +17

    የቅዱሳን አምላክ የተመሰገን ይሁን ይህንን ላቀረቡልን እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ

  • @user-ri1qh5zn2g
    @user-ri1qh5zn2g Před 2 lety +1

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት በእውነት
    ከዝች አለም ፊልም ወደ መንፈሳዊ ፍልም እንድናይ ስለፈቀድክልን ክብር ምስጋና ይገበዋል
    የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ
    አቤት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖቴ ለዘላለም ትኖራለች
    ልቦናዬን ክፈትልኝ
    ይቺን አለም ተከታይ አታድርገን
    ገንዘብ ወዳጅ አታድርገን
    የእየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ያሸንፈን
    አሜን አሜን አሜን

    • @lemlemyoutube
      @lemlemyoutube Před rokem

      አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሳማልኝ

  • @tube7474
    @tube7474 Před 3 lety +5

    የቅዱስ ቆጵርያኖስ እና የቅድስት ዮስቲና በረከት ያሳድርብን ላቀረባችሁልን እግዚአብሔር ይርዳችሁ

    • @samsungsam4681
      @samsungsam4681 Před 3 lety

      አሜን 🤲🤲🤲

    • @lemlemyoutube
      @lemlemyoutube Před rokem

      አሜን አሜን አሜን

  • @AaAa-cq7oe
    @AaAa-cq7oe Před 2 lety +1

    አሜንአሜንአሜንየቅዱሣንበረከትይደርብን በስደትሆነን ስለሃይማኖት ስላስታማሩን በእውነት ፀጋበሰከትንያብዛላችሁ ቃለህይወትንያሰማልን ይሔን እንድናይ ስለፈቀደልን ለድንግልልጅ ለጌታችን መድሀኒታችን ለኢየሱስክርስቶስ ክብርምሥጋና ለዘለዓለምይሁን እኛንም የቅዱሳን በረከት ተካፋይ ያድርገን አሜን((3)) ወስብሀትለእግዚአቢሔር

  • @user-uk6wr3bt1k
    @user-uk6wr3bt1k Před 6 lety +7

    ይህን ላሳየን ለእግዚአብሔር ክብርና። ምስጋና። ይግባው የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብ አሜን

  • @user-gs6lu4zv1g
    @user-gs6lu4zv1g Před 4 měsĂ­ci +1

    አሜንአሜንአሜን፡ቃለህይወት፡ያሠማልን

  • @user-to9gr4vq2e
    @user-to9gr4vq2e Před 8 měsĂ­ci +1

    የዳዊት አምላክ እግዚ አብሔር ሆይ የቅዱሳኖች አምላክ የዳዊት ልጅ እግዚ አብሔር በቸርነትህ ህየኝ አሜን

  • @saratsfaye3187
    @saratsfaye3187 Před 6 lety +20

    የሰማእታቱን በረከት ያስድርብን በእውነት በእድሜ በፀጋ ያቆይልን ሰላምን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ይስጥልን በጣም እናመሰግናለን

    • @lolman7109
      @lolman7109 Před 4 lety

      የሰማእተቱን በታረከት ያስድርብን በእውነት በእድሜ በፀጋ ያቆይልን ስላምን ሀሉ እግዚአብሔር አምላክ ይስጥልን በጣም እናመሰግናለን

  • @meseretasafe3095
    @meseretasafe3095 Před 2 lety +2

    የቅድስት ዮስቲና በረከቷ ይደርብን!❤⛪🙏

  • @hayatalsh1394
    @hayatalsh1394 Před 2 lety +2

    ለመጀመሪያ ይህን እንድናይ የረዳን ልኡል እግዚአብሔር ክብር ምሰጋና ይግባዉ የቅድሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤

    • @hailahails8365
      @hailahails8365 Před rokem

      ❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏

    • @hailahails8365
      @hailahails8365 Před rokem

      አሜን💔🙏አሜን💔🙏አሜን💔🙏

    • @lemlemyoutube
      @lemlemyoutube Před rokem

      አሜን አሜን አሜን

  • @user-rz3oo5lb9b
    @user-rz3oo5lb9b Před 6 lety +6

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን የቅዱሳን ሰማእት ካሃናት ኣበው ሃወርያት ነብያት ፃድቃናት ኣምላክ እየሱስ ክርስቶስ የናዝሬቱ እየሱስ ይመስገን ድንግል ማርያም የኣለም ቤዛ ኣማላጅትዋ ከኛ ጋር ትሁን

  • @fggghjii4311
    @fggghjii4311 Před rokem +1

    ቃለ ህይወት ያሠማልን ይህን እንድናይ አይተንም የምንተገብረው እንድሆን ልኡል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን አሜን አሜን

  • @hdhfu4701
    @hdhfu4701 Před 5 lety +7

    አሜንንንንንንንንንንን ቃለ ሂወት ያሰማልን በውነት በጣም ደስ ይላል በአማርኛ አስተርጉማቹሁ ስለ ምታቀርብሉን በረከታቸው እና ሬድኤታቸው አይለየን አሜን

  • @yehualashetabebe939
    @yehualashetabebe939 Před 3 lety +6

    እንዲህ አይነቱ ፊልም እምነትን ለማጠናከር እጅግ አድርጎ ይረዳል በአሁኑ ሰአት የሚያስፈልገው እንዲህ ያለ
    ፊልም ነውና በርቱ ግፉበት እግዚአብሔር ያጠንቅራችሁ

  • @natuabraham612
    @natuabraham612 Před 4 lety +4

    እግዚአብሔር ጸጋኡ የብዝሓልኩም
    በረከት ናይ ቅድስት ዮስቲና የካፍለና

  • @user-fz2cl6iy3t
    @user-fz2cl6iy3t Před 9 měsĂ­ci

    የህንን እንድናይ እንድነሰማ ለፈቅደልን ለእርሱ ለሉኡለ እግዚአብሔር ከብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን አሜን (፫)➕🙏💐የእናታችን የሰማእቶ የቅድስት ዮስቲና እና የአባቶቻችን በርከት የደርብን አሜን(፫)➕🙏💐

  • @dandiidhugaatawahidhoodha3542

    Amen amen amen kale hiwot yesamelan 👏👏👏

  • @mekdesdagnaw3452
    @mekdesdagnaw3452 Před 6 lety +8

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን አሜን!!!

  • @GgHh-qn4qg
    @GgHh-qn4qg Před 8 měsĂ­ci

    አሜን አሜን አሜን በእውነት ቃለህይወትን ያሠማልን

  • @yohannisadmass5916
    @yohannisadmass5916 Před 4 lety +2

    የቅዱሳኖች በረከተሰ ይደርብን አሜን

  • @user-jc4xc9qt1t
    @user-jc4xc9qt1t Před 6 lety +3

    ቃል ህይወት ያሠማልን አሜንየቅዱሳን በርከት እረዴት ይደርብን ለምታቀሩቡልን ጸጋዉን ያብዛላቹሁ አሜን፫

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  Před 6 lety

      Amen

    • @mebrihitgebre9561
      @mebrihitgebre9561 Před 6 lety

      ተረት ተርቱ አስከመቸነው ራሱን ሰጥቶ ካዳነው ኣምላክ ህዝቡን ለይቶት የሚነረው ወሸት ነው አንዳለ ፈጠራ ነው ኢሄ ከፈጣሪ ኣይደለም ከስማይ በታች የአየሱስ ሰም ብቻ ነው ኣጋንንት የሚፈራው ኣትዋሹ መፅሓፍ ቅዱስ ኣንብቡየድንቁርና ዘመን ያብቃ በአየሱስ ስም ሁላቹ ኣሜን ኣላቹ ብዚ ተረት ኣሜን ብሎ መፃፍ ብቻለ ኣኣምሮአቹ ወንጌል ኣጥኑበት ኣንቡቡ አውቀት ኣርነት ያወጣል ማስተዋል ይስጣቹ የአስራኤል ኣምላክ

  • @sallyiman7912
    @sallyiman7912 Před 6 lety +25

    ድሮም.እኛ.የስደት.ስዎች.እድለኞች.ነን.እግዚአብሔር. አምላክ.ሁሌም.የሚምፕራን.እንዲህ.አይነት.መንገድን.ነውና.አሁንም.ይከተለን.አሜን

  • @user-tv8qo4mu3g
    @user-tv8qo4mu3g Před 5 lety +4

    በእውነት ቃለ ህይወት ያሠማልን እግዚኣብሄር አምላክ ፀጋውን አብዝቶ ይድልልን

  • @user-yn9ge4ed8n
    @user-yn9ge4ed8n Před 5 lety +2

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ክብር ምስጋና ለሉዑል እ/ብሄር ይሁን

  • @user-fx1dp3lx8x
    @user-fx1dp3lx8x Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን በረከት ናይ ቅድስት ዮስትና እና ናይ ቅዱስ ቆብርያናስ ይሕደረና

  • @ebabu8698
    @ebabu8698 Před 5 lety +4

    በጣም አስተማሪ ነው እናመስግናለን እኔ በዙም አላቅም ነበር አሁን ግን እግዚአብሔር ይመስገን አሜንንንንንንንንን

  • @user-fv9id3fe9s
    @user-fv9id3fe9s Před rokem

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃል ህይወት ቃለ ሰናይ ቃለ ብርከት ይስመዐልና

  • @user-sm1wj6yb6f
    @user-sm1wj6yb6f Před 4 lety

    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን የፆድቃን የሰማህታት እረዴት በረከት ይደረብን

  • @iridjjdjjs5592
    @iridjjdjjs5592 Před rokem

    አሜን የቅዱሳን በረከት እረዲኤት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @yehualashetabebe939
    @yehualashetabebe939 Před 3 lety +2

    ይህ መንፈሳዊፊልም በአማርኛ ተዘጋጅቶ መቅረቡ እጅግ ደስ ያሰኛል የቅዱሳንንና የፃድቃኖችን የእምነታቸውን ጥንካሬ በግልፅ አጉልቶ የሚያሳይ ጉልህ ፊልም ነው ተመልካቾችንም ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገሰግሱ ያደርጋቸዋል ጠቃሚም ነው

  • @shalushalu8859
    @shalushalu8859 Před 10 měsĂ­ci

    በእውነት ቃለ ህይወት ያሠማልን በረከታችሁ ይደርብን ከአንድ ከእግዚአብሔር ውጭ
    ሌላ አምላክ የለም።

  • @selam801
    @selam801 Před 2 lety

    በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን የሰማዕቷ
    ቅድሰት ዮሰቲና በረከቷ ይደርብን

  • @user-or1lj8bl3v
    @user-or1lj8bl3v Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን
    ቃለህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ
    የአባቶቻችን እረደየት በረከትይደሪብን አሜን///፫

  • @user-tt6po5oh4g
    @user-tt6po5oh4g Před 5 lety +2

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያስማልን

  • @titigezaei138
    @titigezaei138 Před rokem

    Amen amen amen kale hiwet ysmealna

  • @Emabetdibaba
    @Emabetdibaba Před 2 lety

    በረከትሽ ይደርብን ቅድስት ዮስቴና ድንግል እና ቅዱስ ቆዽርያኖስ ሰማዕት በረካታችሁ ይደርብን

  • @enatmesfin
    @enatmesfin Před 5 lety +5

    እግዚያአብሄር ወደ እውነተኛው ትክክለኛው ሃይማኖት ይምራን ከእርኩስ መንፈስም እሱ ይጠብቀን ይህን ፊልም ለተሳተፉት ሁሉ እግዚያአብሄር ይሰጣችሁ አመሰግናለሁ በሃይማኖታችን ያፅናና

  • @user-wk8jr6xn8h
    @user-wk8jr6xn8h Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን

  • @SamsungaA-ow1gv
    @SamsungaA-ow1gv Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን
    ላቀረባችሁልንም ፀጋ በረከቱን ያድልልን
    ቃለ ሕይወትን ቃለ በረከትን ያሰማልን

  • @aberumusgun2533
    @aberumusgun2533 Před 5 lety +4

    amen amen amen

  • @etinishdubai8269
    @etinishdubai8269 Před 5 měsĂ­ci +1

    Amen amen amen

  • @hiewtdemelie6102
    @hiewtdemelie6102 Před rokem

    እግዚአብሔር ይመስገን በሰዉ አገር ሁነን ይህንን እንድንሰማ የፈቀደልን የቅዱሳን በረከት እረደታቸዉ ይደርብን ላቀረባችሁልን ቃለ ሒወት ያሰማልን

  • @zahrazahra8887
    @zahrazahra8887 Před 5 lety +4

    ቃለሂወትያሰማልን
    አሜን

  • @Hameremedia21
    @Hameremedia21 Před 4 měsĂ­ci

    ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ😍😘

  • @tesfaaa2487
    @tesfaaa2487 Před 2 lety

    አሜን 3 ቃለህይወት ያሰማልን

  • @user-pl7ty9jt9i
    @user-pl7ty9jt9i Před 6 lety +4

    AMeN Amen Amen በርከታቸው ይደርብን ላቀርቡልንም እድሜ ና ጤና ይስጥልን አሜን

  • @user-iu5cr2tg4b
    @user-iu5cr2tg4b Před 6 lety

    የቅዱሳን እሬድኢት የደርብን አሜን አሜን ቃለ ሕይውት ያስማልን አባታችን ተባረኩ

  • @user-qz3os2mv4s
    @user-qz3os2mv4s Před 6 lety +2

    kale hiwet yasemaln ye kidusan bereket na rediet yderbn

  • @mekidesschere5209
    @mekidesschere5209 Před 5 lety +2

    geta hoyi adinen yekidusan eredet bereket kegna gar yihun

  • @Linda-ee5kv
    @Linda-ee5kv Před 3 lety +1

    ቃለ ህይወት ያስማልን
    አሜን አሜን አሜን

  • @abebechtariku6554
    @abebechtariku6554 Před rokem

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን💒🤲🤲🤲🌿🌿🌿🕊🕊🕊🌻🌻🌻🤲

  • @hilinatariku5043
    @hilinatariku5043 Před 5 lety +1

    Amen amen amen kelheyot yasemaln berketachw yederbin

  • @abebahailu5423
    @abebahailu5423 Před 6 lety

    ቃለ ህይወት የስመዐልና አሜን አሜን የቅድሳኑ በረከት ይሕደረና

  • @user-vd8zt8fi6m
    @user-vd8zt8fi6m Před 6 lety +4

    አሜን ቃለሂወትን ያሠማልን ምልጃቸው አይለየን ማስተዋልን ያድለን

  • @lemlemyoutube
    @lemlemyoutube Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሳማልኝ

  • @attegebabege1245
    @attegebabege1245 Před 6 lety +2

    Kale hywot yasemaln
    Bereketachewu yderbn amen

  • @azmachsileshiyedinglimarya1306

    Arif new asitmari
    orthodox tewahedo lezlalem tinur
    Ethiopia bekibir lezlalm tinur
    😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

  • @zawdituuzawdituu7106
    @zawdituuzawdituu7106 Před 6 lety +3

    AMEN AMEN AMEN kale hewot yasemalin

  • @user-rt8bz9pv1z
    @user-rt8bz9pv1z Před měsĂ­cem

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤😢😢😢😢

  • @user-rd2uo7td6z
    @user-rd2uo7td6z Před 4 měsĂ­ci

    አሜን አሜን❤❤

  • @user-li3yy3vy7h
    @user-li3yy3vy7h Před 4 lety +2

    በረከታቸዉ ይደርብን🙏🙏🙏

  • @merkebtiti8483
    @merkebtiti8483 Před 6 lety +2

    amen kali hiwet yasemalin buzuh yemnawukw awukenali beteley besdet yalen yeortodhox teketwechiiiii hiwet selesetachun egzbher besmay bemdr hiwet ystachu ye ageligulot zemanchu ybarklin endeh endwek selerdachun betam enmesgnalen

  • @gfccucu4334
    @gfccucu4334 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን የሠማነዉን በልባችን ያሣድርልን

  • @samiraamira9609
    @samiraamira9609 Před 5 lety +2

    Amen Amen Amen Kaliyotn Yesmaln

  • @nebyatnebyatchelle1232
    @nebyatnebyatchelle1232 Před 6 lety +2

    Amen amen amen kale hiwet yasemalin

  • @miermier1299
    @miermier1299 Před 2 lety

    Amen Amen Amen

  • @user-tj2mx2fc3v
    @user-tj2mx2fc3v Před 2 lety

    በእውነት ቃል ህይወት ያሰማልን ✝️✝️

  • @nunuabate1667
    @nunuabate1667 Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወትን ያሰማልን👏💚💚💛💛♥♥

    • @betibeti72
      @betibeti72 Před 2 lety

      አሜን አሜን አሜን 😭🙏🥰🥰❤️

  • @hannaalemu86
    @hannaalemu86 Před rokem

    Amen amen amen ❤❤❤❤

  • @hiwat1931
    @hiwat1931 Před 5 lety +1

    Amen amen amen
    AMEN AMEN AMEN ✝️✝️✝️✝️✝️🙏🙏🙏⛪⛪⛪⛪Amen amen amen

  • @SaraSara-qp5sg
    @SaraSara-qp5sg Před 10 měsĂ­ci

    አሜን አሜን አሜን

  • @user-tu4zy8ob9f
    @user-tu4zy8ob9f Před 5 lety

    አሜን አሜን አሜን በእዉነትቃለህ ይወትንያሰማልን ፀጋዉንያብዛላችሁ

  • @user-dr5xe1il2o
    @user-dr5xe1il2o Před 3 lety

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸውን ያሳድርብን🙏🙏🙏🙏🙏

  • @assefachekun9788
    @assefachekun9788 Před 6 lety +1

    Amen Amen Amen kebre le amelakachen yehon le enatachen le kedeset degel mareyam yehon kale hieweten yasemalen abetu amelakena medehanete hoy orthodox yaderekegn cheru amelak hoy kebre mesegana late yehon amen

  • @ethiopialahulumadanata6187
    @ethiopialahulumadanata6187 Před 6 lety +2

    yekarstena amnat tewahedo lazalalam tanur amen amen amen

  • @romajanromajan8853
    @romajanromajan8853 Před 2 lety

    አሜን አሜን አሜን🤲🤲🤲

  • @user-pj3ry1qk1h
    @user-pj3ry1qk1h Před 6 lety +2

    Amen amen tsegawu yabzaln

  • @farhanulakbar4396
    @farhanulakbar4396 Před 5 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን

  • @user-dh7zc3sk8b
    @user-dh7zc3sk8b Před 6 lety

    የቅዱሳኑ ረድየት በረከታቸው ይደርብን አሜን ፫

  • @birtukanbirtukan4151
    @birtukanbirtukan4151 Před rokem

    ቃል ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ ወንድሞችችን

  • @atalelechhailu3166
    @atalelechhailu3166 Před 4 lety

    Amen Amen Amen
    Bereketachehu Yedereben

  • @gtadu7384
    @gtadu7384 Před 9 měsĂ­ci

    ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ይባርካችሁ
    አዘጋጆች ! እኛ ተመልካቾች ግን ምን ነካን ። እንዴት ላይክ ማድረግ ያቅተናል እያንዳንዳችን እራሳችንን እንጠይቅ ። ቅዱስ ልዑል መድኃኔዓለም ለተመልካቾች ሁሉ ልቦናን ይስጥልን !!!
    ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ሁሉንም ይባርካችሁ !!!

  • @user-ne7nd5od6k
    @user-ne7nd5od6k Před rokem

    ጸጋውን ያብዛላችሁ
    የቅዱስ ዳዊትን ልቀቁልን 👏

  • @waganeishtesfa3207
    @waganeishtesfa3207 Před 6 lety

    አሜን አሜን አሜን ቃል ሕይወት ያሰማልን አሜን

  • @ethunmandefiro95
    @ethunmandefiro95 Před 3 lety

    አሜን 3 ቃለሕይወት ያሰማልን አባታች

  • @user-ko7lb2fu8i
    @user-ko7lb2fu8i Před 6 lety

    አሜን ቃለህይወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን

  • @user-zc5mu8gl7u
    @user-zc5mu8gl7u Před 6 lety +1

    በእውነት ቃለ ህይወትን ያሰማልን ላቀርቡልንም በእውነት በጤና በውድሜ ይስጥልን የሰራዊት አምላክ

  • @zenamalika1662
    @zenamalika1662 Před 2 lety

    ቃለህይወትያሰማልን።በርከታቸውይደርብን

  • @asmaraethiopia4138
    @asmaraethiopia4138 Před rokem

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ብርከቱ ይደረብን

  • @user-ic4nf3pq1l
    @user-ic4nf3pq1l Před 2 lety

    ቃለ ህወተ ያሰማልን በእወነት በርክታችው ይደርቡነ🙏🙏🙏

  • @walelgnakele2437
    @walelgnakele2437 Před 5 lety +1

    እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛላችሁ።