✍️

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2024
  • Leave me this year poem in my little boy and age where we ask him to leave me for repentance, may he make us an age that will return his eyes of mercy to us.
    ይህን ዓመት ተወኝ ግጥም በትንሹ ብላቴና እድሜን ለንሰሐ ተወኝ እያልን የምንጠይቅበት እሱም የምህረት ዓይኑን የሚመልስልን ዘመን ያድርግልን
    #Andit_Religion_Orthodox_Tewahdo #One_Church
    #One_Baptism
    #Integrated
    #orthodoxchurch
    #Ethiopia
    #አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
    #አንዲት_ቤተክርስቲያን
    #አንዲት_ጥምቀት
    #ተዋህዶ
    #orthodoxchurch
    #ኢትዮጵያ
    ግጥሙን በፅሁፍ ከዚህ በታች ታገኙታላችሁ
    ✍️#ይቺን_ዓመት_ተወኝ
    t.me/+LeMxwBvk...
    ሰከንድ ከደቂቃ እየተዛመደ
    ሰአት ከቀናት በአንድ ተራመደ
    ሳምንት ከወራት ፈቅዶ እየሄደ
    መንፈቅ ከዓመት በዓንድ እየነጎደ
    ዘመን እየተካ እኔነት ወረደ
    ከቅፍህ ወጥቼ ሕይወት ተሰደደ
    ባንተ ቤት ለመኖር ፍቅር መች ወደደ
    ለአፍታ ሳላስብ ሐሰት ተወደደ
    ያኛው ጊዜ አልፎ በእውነት ጊዜ ተነገደ
    ይችን ዘመን ተወኝ ወዳንተ እንድመጣ
    በትርህን መልስ ልጅህን አትቅጣ
    የንሰሐ እድሜ ጨምርልኝ ልምጣ
    ጊዜው እያለቀ ሕይወት ከተቀጣ
    እኔ ሳልማር ምህረት ሳልጠጣ
    በጋው እያለፈ ክረምቱ ከመጣ
    ዓመት ተተክቶ ክረምቱ ከወጣ
    ይህን ዘመን ልለፍ በንሰሐ ልውጣ
    t.me/+LeMxwBvk...
    እንደዚ ጠውልጎ ውብ የሆነው ገፄ
    ፍቅርን ቀይሬ በሥጋ ማመፄ
    የክፋት ሰንሰለት እንዲጠፋ ለምፄ
    ወዳንተ እንድቀርብ እንዲሰማ ድምፄ
    በአንተ ቤት ለመክበር አስቤ ስነሳ
    በክፋት ህሌና በዓለም እውነት እየከሳ
    እኔም ጠፍቻለው እድሜዬ ቀንሳ
    ይችን ዘመን ተወኝ ይቅርብኝ ወቀሳ
    በንሰሐ ልቅረብ በአንተ ፊት ልነሳ
    ምህረትክን ሳለብስ በንሰሐ ካባ
    ይህን ዓመት ተወኝ ፍቅርህን ላድርገው ሰገባ
    እሾህ አበቀለ በቅፍህ ሳልገባ
    ምህረትን ልልበስ ወደ አንተ ላንባ
    ዓመቱም ነጎደ እለፈኝ አምላኬ
    ዓመፅን ወደድኩኝ በዓለም ተንበርክኬ
    ከፊትህ ጠፋሁኝ ውበትን ማርኬ
    በአምሳልህ ሰርተከኝ
    ከአንተ እቅፍ ወጥቼ እኔ ወዴት ሄድኩኝ
    አምላኬ ይችን ዓመት ተወኝ
    ጌታዬ እድሜን ለንሰሐ አንተ ጨምርልኝ
    ጠፍቼ እንዳልቀር የዘንድሮን በፍቅርህ እለፈኝ
    t.me/+LeMxwBvk...
    ዓመትም ጨምሬ ፍሬን ሳላፈራ
    እንደዋለልኩኝ ያንተን ስም ሳልጠራ
    ቃዥቼ ቆሜያለው በዓለም ተራራ
    አለሁኝ በቤትህ ፍሬን ሳላፈራ
    ለም ምድረህ ጎስቁሏል በተራ
    ፍሬን ሳላፈራ እኔ አመላለስኩ
    የልቤላይ ፅላት ተሰባብሮ መስኩ
    ዛሬም ሳላፈራ በዓመፅ ደርቄ ጠበኩ
    ያላደረክልኝ ምን ነገር አለና
    በስቅላት ሞቴን አጥፍተህ ህይወቴ ሲፀና
    ይህ ሁሉ ሳይገባኝ ልቤ በዓለም ገባና
    ፈታኞ ሆኖ ቀርቧል አጥፍቶ ምስጋና
    የማትሰለቸኝ አንተ ስለሆንክ ልቁም ተነስቼ
    እስክቆም ታገሰኝ ፈራሁ ብርታትን አጥቼ
    ወዳንተ እንድቀርብ እጆቼን ዘርግቼ
    የኔን ክፋት ተወው እንዳልጠፋ ሞቼ
    t.me/+LeMxwBvk...
    መላአክህን ሰምተህ ይህን ዘመን ተወኝ
    የፍቅር አምላክ ነህ የማትሰለቸኝ
    በይቅርታህ ጎብኘኝ
    ይህን ዘመን ተወኝ
    አውቃለው ታውቃለህ ቀጠሮ ሰጥቼ
    መቼ መጥቻለው በዓለም ቀርቼ
    በሰዙ ጊዜ አስቤ መጥቼ
    ተመልሼ ገባው ሐጢያቴን ፈርቼ
    እንዳላቀረቅር በበደሌ ዝቼ
    በወሬ እንደቀረው ታውቃለህ ፈርቼ
    አምና ይሄን ጊዜ ዘንድሮስ እንዳልኩኝ
    ዘንድሮም አለፈ ጊዜዬን ጨረስኩኝ
    ምንም ሳልለወጥ እያፈገፈኩኝ
    ዛሬ ነገ ብዬ ጌዜ ከሰረኩኝ
    እባክህ አምላኬ ዳግም ልለምንህ ይቺን ዓመት ተወኝ
    የማትሰለቸኝ አንተ ተነስቼ እስክቆም
    እባክ ታገሰኝ በቤትህ ልታከም
    ፍሬ የማይወጣኝ የደረኩኝ በዓለም
    እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ ቸሩ መድኃኒዓለም
    ዛሬም አልበቃኝም በሐጢያት መታመም
    የቃልህን ወተት በድንጋይ ልጅህ ላይ ስታፈስ ብትከርም
    ወደ ልቤ ሳይዘልቅ ቀረው ሳልታከም
    ፍቅርህን ጠግቤ እያገሳው አለው ሌሎች እየሰሙ
    በቤትህ መኖርን አልቻልኩም ሲጥመኝ ዓለሙ
    በቃልህ መክበርን አልቻለም ከበደኝ ቀለሙ
    ብዙ ጥቅስ ደረደርኩ ከመጽሐፍ አይቼ
    ለራሴ የሚሆን ጥቅስ አላገኘውም በዓመፅ ተኝቼ
    በአንተ ፊት ለመቅረብ አለሁኝ ፈርቼ
    ደካማ ትምህርት የማይገባኝ እኔ
    ይችን ዓመት ተወኝ ትንሽ ልማር ያርፍ እንደሆን አይኔ
    እባክ አልጥፋ አይቆረጥ ጎኔ
    በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ዝራብኝ በሰኔ
    ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬአቸው ሽታ እንዲደርሰኝ ለኔ
    መዓዛዬ እንዲለወጥ ይለፍ ይኬኛው ዘመኔ
    መሸከም የምትችል አንተ ዛሬም ተሸከመኝ
    እንዳንተ ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩኝ
    አታውጣኝ ከቅፍህ ፍሬን ሳላፈራ እንዳይቀነጥሱኝ
    ስፍራ የማልመርጥ በዓለም የተጣልኩኝ
    ፍሬ አልባው ኮብላዩ ደካማው ልጅህ ነኝ
    ባለ ምግባሮቹ ቅዱሳን እያሉ
    ልክ እንደ ዘንባባ የተዠረገጉ
    በፅድቅ ተጋድሎ ዓለምን የወጉ
    ከሊባኖስ ዝግባ እጅግ ይበዛሉ
    በገድል ቱሩፋት በፍቅር የታደሉ
    በውበት እነሱ ቅዱሳን ተባሉ
    እኔ መቼ ሆኜ ቦታ የምይዘው
    ዘርፋፋ ቀሚሷ ዓለም ያዳረሰው
    ስሮቿ በምድር ሞልቶ የሚታየው
    ጯፎቿ በሰማይ ደምቆ የሚያበራው
    እናትህ እኮናት ልባ ማይጨክነው
    ይችን ዓመት ተወኝ ከስሯ ሆናለው
    በናትነት ፍቅራ ባፈራ ምናልባት እለምንሃለው።
    user262443.pse...
    ይችን ዘመን ተወኝ እባክህ አምላኬ
    አንድ ዓመት ምንህ ናት ይቀየር ታሪኬ
    ልማፀንህ ልጅህ ፊትህ ተንበርክኬ
    ሺ ቀን አንድ ሰከንድ አየደለም ወይ ላንተ
    በሥጋ ህሌና ነብሴ እየሞተ
    ዓመት ኢምንት በአንተ ከከተተ
    ይህን ዓመት አልፎ ውስጤ ዳግም ከሞተ
    ስጠኝ እስከምለህ የዘንድሮን በፍቅርህ ልግባ ልካተት
    እባክህ አምላኬ ይችን ዓመት
    እቀፈኝ ልቅረብ ካንተ ፊት።
    በጋው እያለፈ ክረምት እየገባ
    ይችን ዓመት ተወኝ ንሰሐ እንድገባ
    እቀፈኝ በፍቅርህ ወደ ቤትህ ልግባ
    ሞት መምጣቱ አይቀር ዘሎ እንደሌባ
    user262443.pse...
    ✍️ሰኔ 18/2016
    ✍️ተፃፈ በትንሹ ብላቴና መምህር ገብረፃዲቅ።
    user262443.pse...

Komentáře • 23

  • @Madena-hh3jw
    @Madena-hh3jw Před měsícem

    አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @hagilmaryamHayela
    @hagilmaryamHayela Před měsícem +1

    ይችን አመት ተወኝ የሚለውን መንፈሳዊ ግጥም ላቀረበልን ለመምህራችን ቃለህይወት ያሰማልን እውነት ይህን አመት ተወን እውነት ይህንን አመት አምላክ መድኃኒዓለም ይተወን ይለመነን ወንድሜ መምህር በርታ እስኪ አቅም ያለን አዋተን አንድ ኮምፒተር እና ካሜራ እንግዛለት በማርያም ከቻላችሁ።

  • @ሀይለማርያምሰለሞን

    በእውነት ወንድሜ ይችን አመት ተወኝ ብሎ ላቀረበልን ቃለህይወት ያሰማልን ወንድሜ በጣም ደስ ይላል በርታ የተዋህዶ ልጅ የተዋሕዶ አርበኛ አሰበ መምህራንን ያድልልን
    ከላይ ኮሜንት ላይ ሞክሼ እንዳለው የአቅማችንን እናድርግ እናግዘው ከዚህ የበለጠ እንዲሰራ።

  • @SaraSara-hi4zj
    @SaraSara-hi4zj Před měsícem +1

    ሼር አድርጉ ስብስክራይብ ላይክ እናድርግ ለማይረባ ነገር ብር ታደርጉ የለ

  • @SaraSara-hi4zj
    @SaraSara-hi4zj Před měsícem

    በእውነት ቃለ ሕይወትን ያስማልኝ

  • @MjMJ-fr7rf
    @MjMJ-fr7rf Před měsícem

    ቃለ ህይወት ያስማልን

  • @Madena-hh3jw
    @Madena-hh3jw Před měsícem

    ወንዲማችን ቃለህዪወት ያሠማልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉

  • @BerciBerci-sc2go
    @BerciBerci-sc2go Před měsícem

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር

  • @AmSalu-c4w
    @AmSalu-c4w Před 23 dny

    🎉❤❤❤❤🎉🎉🎉❤❤❤🎉🎉

  • @Eyerus-er5ih
    @Eyerus-er5ih Před 29 dny

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህዎትን ያሰማልን 🙏🙏🙏

  • @Eyerus-er5ih
    @Eyerus-er5ih Před 29 dny

    ❤️🎉❤️🎉❤️🎉🙏🙏🙏

  • @user-gi9tg3dn1g
    @user-gi9tg3dn1g Před měsícem

    ቃል,ይሆት.ያሰሚልን

  • @almnatgete7566
    @almnatgete7566 Před měsícem

    Amen amen amen
    Qule hiwoet yesmalen wendmachen
    Tegwion ybzalesgh❤❤❤❤

  • @medhiamedhia8557
    @medhiamedhia8557 Před měsícem

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህውትን ያስማልን መምህራችን❤❤❤❤❤❤

  • @mebrattadese989
    @mebrattadese989 Před měsícem

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን

  • @BiragaGelanaw
    @BiragaGelanaw Před měsícem

    አሜን አሜን እውነት ነው መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @hao90
    @hao90 Před měsícem

    እግዚአብሔር ይመሰገን መምህር
    ቃለ ሕይወት በረከት❤❤🌹🌹🌹🌹🌹❤❤❤❤❤🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

  • @MisiMisi-je8tk
    @MisiMisi-je8tk Před měsícem

    ❤❤ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን❤❤❤❤❤

  • @eyerusemengstie5125
    @eyerusemengstie5125 Před měsícem

    ቃለ ህወትን ያሠማልን ወንድማችን❤❤❤❤❤❤

  • @TeketeleLerago
    @TeketeleLerago Před měsícem

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን ወንድማችን❤

  • @mawaysh
    @mawaysh Před měsícem

    💚💚💚💚💛💛💛💛❤❤❤❤❤❤

  • @Zemarittadelche
    @Zemarittadelche Před měsícem

    አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህራችን❤❤

  • @Madena-hh3jw
    @Madena-hh3jw Před měsícem

    ❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤