Apostolic Church songs | አለሁኝ በሕይወት | Alehugn behiwot | Awassa Choir | የአዋሳ መዘምራን

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 10. 09. 2024
  • የአዋሳ ቅ/ሰበካ መዘምራን ከሐምሌ 09-11/2013 በአዋሳ እናት አጥቢያ በተዘጋጀ ጉባዔ የቀረበ መዝሙር
    ግጥም/Lyrics
    ላመስግነው እንጂ ደግሜ ደግሜ እንደገና
    ከቶ አይበዛበትም የከንፈሬን ፍሬ ልስጠው ምስጋና
    የልቤን ስብራት የነፍሴን ሀዘን እየጠገነ
    በመንገድ እየመራኝ ከፊት ለፊቴ እየቀደመ
    ቸርነት ምሕረቱን በሕይወቴ ዘመን ያላራቀብኝ
    በደሙ እየከለለኝ ጥበቃው በዝቶ ዛሬም አለሁኝ
    አለሁኝ በሕይወት አለሁ ምሕረቱ በዝቶ
    አለሁኝ በሕይወት አለሁ ጥበቃው በዝቶ
    አየሁኝ ይህቺን ቀን አየሁ በቸርነቱ
    አየሁኝ ዘንድሮን አለሁኝ በቤቱ
    1. በምድረ-በዳ ከቶ አልተወኝም
    ለአውሬ አሳልፎ ከቶ አልሰጠኝም
    በምድረ-በዳ ከቶ አልተወኝም
    መርዛማው እባብ አልነደፈኝም
    እንደዓይኑ ብሌን እየጠበቀ
    ኢየሱስ ለነፍሴ ተጠነቀቀ
    አለሁኝ በሕይወት...
    2. እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ምሕረት
    ጥበቃው ልዩ ፍቅሩ የአባት
    ትከሻው ሰፊ ሲሸከም አይዝል
    ወረት አያውቅም ሰለቸኝ አይል
    አቤት የእርሱ መውደድ እንዴት ድንቅ ነው
    አቤት የእርሱ ምሕረት እንዴት ሰፊ ነው
    አቤት የእርሱ ጥበቃ እንዴት ልዩ ነው
    በጊዜ በሁኔታ ማይቀየር ነው
    ብዙ በደሌን የማረልኝ
    ብዙ ጠልቼው የወደደኝ
    ይህቺን ቀን ማየት ሳይገባኝ
    በሕይወት የኖርኩት እኔ እኮ ነኝ
    አለሁኝ በሕይወት...

Komentáře • 58