Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Yene mar አብዱ ኪያር - የኔ ማር - ከግጥም ጋር

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 7. 09. 2024
  • Subscribe to @Abdu Kiar on CZcams: / abdukiarmusic
    Follow Abdu Kiar online
    Facebook : / abdukiarmusic
    Instagram : / abdukiarofficial
    Twitter : / abdu_kiar
    Spotify : artists.spotif...
    Apple Music : / abdu-kiar
    የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት
    የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት
    ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ
    የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ
    ይሄ ሁሉ መባረክ እና ማማር
    ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር
    ውበት ቁንጅናሽን በቃል ለማስረዳት
    የቋንቋ እውቀት ያለው ያስፈልጋል ረዳት
    ቃላት ላይ ፊደል ላይ ስልጣን የሌለው ሰው
    አይችልም አይችልም ውበትሽን ሊገልጸው
    ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል
    ቁም ነገር አስቀርቶብሻል
    ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል
    ውበትን ይደብቅብሻል
    የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር
    የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር
    የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት
    የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት
    ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ
    የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ
    ይሄ ሁሉ መባረክ እና ማማር
    ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር
    የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም
    ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም
    የውበት መለኪያው ሳይለካ ኖሮ
    ውበት ማለት አንቺ ሆነሻል ዘንድሮ
    የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም
    ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም
    የውበት መለኪያው ራሱ ተለክቶ
    መለካቱን ትቷል ባንቺ ተተክቶ
    ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል
    ቁም ነገር አስቀርቶብሻል
    ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል
    ውበትን ይደብቅብሻል
    የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር
    የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር
    ግጥምና ዜማ አብዱ ኪያር

Komentáře • 23