🔴ሕግን ልፈጽም መጥቻለሁ || የተራራው ስብከት Epi 3

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 23. 04. 2024
  • #like #Share #Subscribe @arganon @janderebaw_media
    🔴ሕግን ልፈጽም መጥቻለሁ || የተራራው ስብከት Epi 3
    / @arganon
    ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ።
    እግዚአብሔር ያክብርልን!!
    Any way of reproducing, reposting & reusing of this video is prohibited by ARGANON.
    ©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2016|2024
  • Zábava

Komentáře • 11

  • @user-iv6zs6fp3m
    @user-iv6zs6fp3m Před 2 měsíci

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ጸጋውን ያብዛልን የሰማነውን በልቦናችን ያኑርልን

  • @GenetYosef-il4kw
    @GenetYosef-il4kw Před 2 měsíci

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን ጸጋውን ያብዛልን የሰማልነው ብልቦናችን ያኑርልን

  • @user-md6ni8zn4j
    @user-md6ni8zn4j Před 2 měsíci

    ቃል ሂወት ያሰማልን ወንድማችን❤

  • @tsehayyemicheal7203
    @tsehayyemicheal7203 Před 3 měsíci

    እግዚአብሔር ይባርካቹህ , በሦስቱንም ፖርት ነው የተመለከትኩ በጣም ብዙ ነገር ነው የተማርኩበት::

  • @seblekahsay6417
    @seblekahsay6417 Před 3 měsíci

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን

  • @kerenanseba8769
    @kerenanseba8769 Před 3 měsíci

    ጾም ቆኖና ወይስ ዶግማ፧?

  • @yeabsiraminewyelet157
    @yeabsiraminewyelet157 Před 3 měsíci

    ለሚዲያው አንድ ጥያቄ አለኝ
    ስታስተምሩ አባቶቻችን አባቶቻችን ትላላችሁ። የእናንተ አባቶች የትኞቹ ናቸው? የመናፍቃን አባቶች መሆን አለባቸው። እነሱ ናቸው ያለነጠላ በሱፍ ፣ በሸሚዝ ፣ በቲሸርት የሚያስተምሩት።
    እኛ የምናውቃቸው አባቶች እንደ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ፣ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ፣ መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ ያሉት ለቃለ እግዚአብሔር ክብር ስለሚሰጡ ሲያስተምሩ አንድም ቀን ያለነጠላ አስተምረው አያውቁም።
    ነጠላ እንድትለብሱ ስንት ሰው ይንገራችሁ? ስንት ጊዜስ ይነገራችሁ?
    ሥርዓት ለመጣስ ሰበብ መደርደር ምን የሚሉት ፋሽን ነው?

    • @humanalltoohuman
      @humanalltoohuman Před 3 měsíci

      "ፈሪሳዊ ክርስትና" መቼም እጅግ ከባድ ነው።
      በክርስቶስ ዘመን የነበሩ ፈሪሳውያን ከጌታ ትምህርት ይልቅ የሚያሳስባቸው ጥቃቅኑ ነገር ነበር። እነርሱም ጌታችንን ሲቃወሙ ለአባቶቻችን ሥርዓት ተቆርቁረናል የሚል ምክንያት ነበራቸው። ከጌታችን ፈውስ ይልቅ በሰንበት መፈወሱ፥ ከትምህርቱም ይልቅ ሐዋርያት በሰንበት እሸት ቀጥፈው መብላታቸው ይቆረቁራቸው ነበር። የፈሪሳዊያንም ጉዳይ ከትምህርት ሳይሆን በውጪ አማኝ መስሎ ለመታየት ስለሆነ ጉዳያቸው "ነጠላ" ነበር፥ ጌታም ሲገስጽ "ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ" (ማቴ 23:5) አልነበረም የተባሉት? ነጠላ የትክክለኛ ትምህርት መለኪያ ቢሆን፥ ቀድመው የሚጸድቁት ፈሪሳዊያን ነበሩ!
      የቃለ እግዚአብሔር ክብር የሚገለጠው በነጠላ ከሆነ፥ ተነስተን የግብጽ ኦርቶዶክሳውያንን እናውግዛ! የሕንድ ኦርቶዶክሳያንም ይወገዙዋ! ኦርቶዶክሳዊነት የሚለካው በነጠላ ከሆነ፥ ነጠላ ለብሰው የተሐድሶ ትምህርት ያስተምሩ የነበሩትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሰን እንጥራቸዋ! ጥምጣም አድርገው በፕሮቴስታንት አዳራሾች ሲዘሉ የነበሩትም ይመለሱዋ!

    • @yeabsiraminewyelet157
      @yeabsiraminewyelet157 Před 3 měsíci

      ያለህ የነገሮች አረዳድ መቼም ግሩም ነው እጅግ ግሩም።
      ከዚህ በፊት ነጠላ ላለመልበስ ይቀርብ የነበረው ምክንያት (የማታለያ ምክንያት) ወጣቱን ለመሳብ የሚል ነበር። አሁን ደግሞ ከዛ በባሰ ሁኔታ ለስህተታችሁ የግብፅ እና የሕንድ ክርስቲያኖችስ መች ይለብሳሉ የሚል ሆኗል።
      እሺ የግብፅ ክርስቲያኖች (ሴቶቹ) ሱሪ ለብሰው ቤተ መቅደስ መግባት ኖርማል ነው። ታዲያ ኢትዮጵያም እንደነሱ በሱሪ ቤተመቅደስ መግባት አለባቸው?
      ልቀጥል የግብፅ ቤተክርስቲያን ሎቱ ስብሐት ክብር ይግባውና የጌታን ስጋ እና ደም ሳትሸፍን ሁሉም እያየው ነው የምታቆርበው ታዲያ የእኛም ቤተክርስቲያን እንደዚህ ታድርግ? ለጥፋት ምክንያት መደርደር ፣ ሌላውም እኮ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ ማላከክ ልክ አይደለም።
      ሥርዓት የተሰራው ለእኛ እስከሆነ ድረስ መተግበር አለብን። አለበለዚያ የማንተገብረው ከሆነ ከመጀመሪያውስ ለምን ተሰራ? አበጀው ብለህ ፈሪሳዊ እያልክ ታፌዛለህ ደግሞ
      አሽቃባጭ

    • @humanalltoohuman
      @humanalltoohuman Před 3 měsíci

      @@yeabsiraminewyelet157 - ፈሪሳዊ ክርስትና ለመገለጥ ትንሽ ይበቃዋል። አያስችላችሁም፥ ቶሎ ወደ ስድብ ነው አይደል?
      የሚዲያውን ከሚዲያው ጋር ጨርስ። እኔ በግሌ እንደ አንድ ምዕመን ነው የምናገረው። አሁንም ግን እየተከተልክ ያለኸው ፈሪሳዊ ክርስትና መሆኑን በኮሜንትህ እያረጋገጥክልኝ ነው። 'ሥርዓት' የሚለውን ነው ደጋግመህ እያልክ ያለኸው፤ ፈሪሳዊያንምኮ ትልቁ ጭንቀታቸው 'ሥርዓት' ነበር። የክርስቶስ ትምህርት የሚገዳቸው አልነበረም። በወቅቱ እስራኤላዊያን መንፈሳዊ መቆርቆዝ ላይ መሆናቸው አላስጨነቃቸውም። በየቦታው ጌታን ይከሱ የነበሩት "ይህንን ሥርዓት ጣሰ'፥ 'ይህንን ሥርዓት አፈረሰ' እያሉ ነበር። አንተም እያልክ ያለኸው እንዲሁ ነው። ከላይ እንደጠቀስኩልህ፥ ክርስቶስ ራሱ "ለመታየት ሲሉ የሚያደርጉትን ሁሉ በሰው ፊት ያደርጋሉ፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የቀሚሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ።" (ማቴ 23፡5) ብሎ የገሰጻቸው ለዚሁ ነበር።
      የክርስትና ሥርዓት ዶግማ አይደለም። ሥርዓት እንደየሀገሩ የሚለያይ ነው። ከግብጽም ሆነ ከሕንድ የምንለየው ለዚህ ነው። እነርሱ የተለየ ሥርዓት ስላላቸው አይኮነኑም፤ እኛም የተለየ ሥርዓት ስላለን አንጸድቅበትም። እንዲያውም በተግባራዊ ክርስትና ሕንዶች እና ግብጻውያኑ እጅጉን ይበልጡናል! ሥርዓት ከጊዜው ጋር ሊለወጥ እና ሊሻሻል የሚችል ነገር መሆኑን ማስታወስ መልካም ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉትን ኦርቶዶክሳዊያን አንድ የሚያደርጋቸው ርትዕት እምነታቸው እንጂ ጥቃቅኑ ሥርዓት አይደለም። ክርስቶስም የሚያይልህ እምነትህን እና መልካም ምግባርህን እንጂ ሌላውን አይደለም። ነጠላ መልበስ አያጸድቅም፥ ነጠላ መልበስ አያስኮንንም። እኛን ሊያስጨንቀን የሚገባው ከልብ ማመናችን፥ በእግዚአብሔር ላይ መደገፋችን እና ሕግጋተ ወንጌልን መፈጸማችን ነው።
      "እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን" (2 ቆሮ 3፡6) እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፥ የሕግጋቱን ፊደል ሳይሆን መንፈሱን ብንመለከት ሥርዓትን መሠረት አድርጎ ሌላው ላይ ከመፍረድ እንድናለን።
      በነገርህ ላይ፥ በየጊዜው የኦርቶዶክሳዊያን ቁጥር እየቀነሰ ባለበት ሀገር፥ የሕዝቡ መጽናት እና የወጣው መመለስ እንጂ፥ ጥቃውን ሥርዓቶች እንቅልፍ አይነሱኝም። አንተን እንቅልፍ የሚነሳህ እርሱ ከሆነ፥ እንግዲህ በርታ!
      መልካም ጊዜ።

    • @yeabsiraminewyelet157
      @yeabsiraminewyelet157 Před 3 měsíci +1

      @@humanalltoohuman ስድብ ተሳደብክ ብለህ ልታሸማቅቅ ትሞክራለህ? ፈሪሳዊ እያልክ ለማፌዝ የምትሞክረው ምርቃት ነው እንዴ?
      ሲቀጥል ሥርዓት በቤተክርስቲያን ትልቅ ቦታ ባይሰጠው ኖሮ እንደ ፍትሐነገሥት ያሉ ጾም ፣ ጸሎት ፣ ምጽዋት ፣ ስግደት ፣ አለባበስ እንዴት መሆን እንዳለበት የሚነግሩ እንደነ መጽሐፈ ዲድስቅልያ ያሉ የሥርዓት መጻሕፍት ባልተጻፉ ነበር።
      ከሁሉም በላይ ማስታወስ ያለብህ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ የሥርዓት አምላክ እንደሆነ ነው።
      ነገሬን ስጠቀልለው ሥርዓትን አቅልለን አንየው። ይሄ ሚዲያ ወጣቶችን ለመሳብ በሎም ይሁን በሌላም ምክንያት መርሀግብር ለየት አድርጎ ማዘጋጀቱ መልካም ነው ያስመሰግነዋልም። ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ ያለ ነጠላ መቅረቡ ስህተት እንደሆነ አንተም አትክድም። ሥርዓትን ጥቃቅን እያሉ ማጣጣል ደግሞ አግባብ አይደለም።