ደራሲ ስንዱ አበበ የኔ ማስታወሻ አዲስ መጽሐፏ እና ስለግል ህይወቷ ተጨዋውተናል

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 09. 2024
  • ጋዜጠኛና ደራሲ ስንዱ አበበን በሁለት ነገር አስታውሳታለሁ። አንዱ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሕበር ወደ ሐመር ጉዞ አዘጋጅቶ በነበረበት ወቅት ከተጓዦቹ አንዷ ሆና ወደ ቦታው ከተጓዘች በኋላ በስፍራው ያየችውን ማስመሰልና ማታለል ዘርግፋ የፃፈችውና : ስለዚህ ስንዱ ስለ ሁለቱ ጉዳዮች የምትለን ነገር ይኖር ይሆን ????? የቅርብ ጊዜ ግብሯ ግን አሳታሚነት ነው።ሴቶች ባልበረከቱበት የመጻህፍት አሳታሚነት ዘርፍ ውስጥ በነበራት ቆይታ እንደዘበት ሊረሱ ፣ሊጠፉ ይችሉ የነበሩ ውብ የስነጽሁፍ ስራዎችን አሰባስባ ለንባብ ማብቃቷን ከውለታ የሚቆጥሩት ጥቂት አይደሉም።
    የስብሃት ገ/እግዚሃብሄር፣አውግቸው ተረፈ ፣ሙሉጌታ ተስፋዪ ፣ባሴ ሀብቴ ስራዎች የህትመት ብርሃን እንዲያገኙ አድርጋለች። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ መኖሪያዎን በአሜሪካ ምድር ያደረገችው ስንዱ፣ ከህትመቱ ዓለም ፊቷን አዙራለች።ለምን? ይሄንን እና መጻህፍትን ፤የህትመት ዘርፉን የሚመለከቱ ጉዳዮች አጋርታናለች።
    የተሰናዳችው ስንዱ!!
    በነ ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር የፍልስፍና ቅኝት ተቃኝታ በአያ ሙሌ ቅኔ ተደርድራ በጥሩ የጥበብ ዜማ የምትዜም ድንቋ ጋዜጠኛ ስንዱ አበበ ለኢትዮጵያ ሴት ጋዜጠኞች ትልቅ ተምሳሌት ናት።
    እነሆ ማስታወሻወቿን በመጽሐፍ መልክ አዘጋጅታ እንካችሁ ብላለች
    መጽሐፏን አንቡቡና ስንዱን አንብቧት!!!

Komentáře • 8

  • @user-rm3wn7kg7u
    @user-rm3wn7kg7u Před 3 lety +5

    በመረጃ ቲቨ በርዕዮት ፕሮግራም ላይ ቀርባ ነበር በወያኔ ብዙ መከራን ያሳለፈች ጋዜጠኛ ነች ጤናና እድሜ አብዝቶ ይስጥሽ

  • @ethiovacancy
    @ethiovacancy Před 3 lety +7

    የስንዱ መፀሀፍትን እድል ገጥሞኝ ባላነባቸውም የተለያዩ ቃለ ምልልሶቾን ሰምቸ ልጅት የትልቅ ቤተ መፀሀፍት ያህል በውስጧ የተከማቹና ለሌሎች ትምህርት ሊሆን የሚችል ሀያሌ የህይወት ልምዶችና በንባብ የካበቱ እውቀቶች እንዳሎት አይቻለው
    የሷን ማስታወሻ ማንበብ ያልኖርንባቸውን ጊዚያቶች መኖርና ያላየናቸውን ሰዎች ማግኘት ያህል ነው !

  • @tazmadrama8492
    @tazmadrama8492 Před 3 lety +4

    ስንዱ ድንቅ የስነ-ፅሁፍ ችሎታ አላት!መፅሐፉን በጉጉት እየጠበቅኩት ነው!

  • @sinidugebremichael1361
    @sinidugebremichael1361 Před 3 lety +4

    ድንቅ ሴት !!

  • @tazmadrama8492
    @tazmadrama8492 Před 3 lety +4

    ጎበዝ ሴት!

  • @Lijeyassu
    @Lijeyassu Před 2 lety +1

    ስንዱዬ አቦ ስወድሽ ለጥበብ ታመሻል ቆስለሻል ... ነፍሴ ሁሌም የአያ ሙሌን መፅሀፍ በማሳታምሽ ታመሰግንሻለች

  • @taem5615
    @taem5615 Před 3 lety +5

    ሰሞኑን ብዙ መፃህፍት ገበያውን ተቀላቅለዋል። እኔ ለማንበብ የጓጓሁት የSenedu Abebeን "የኔ ማስታወሻ"ን ነው። ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፦
    ፩) ስንዱ ደፋር ናት። ያመነችበትን ትፅፋለች። ስልጣን፣ ጉልበት ሳያስፈራት ትጋፈጣለች።
    ፪) ድፍረት ብቻውን አይበቃም። ስንዱ ድንቅ የስነጽሑፍ ችሎታ አለት። እስከአሁን 10 መፃህፍት ላይ እጇ አርፏል። ለጋዜጣ የፃፈቻቸው መጣጥፎች ተቆጥረው አያልቁም። በቅርቡ እዚሁ ፌስቡክ ላይ ያስኮመኮመችን ፅሁፍ ምስክር ነው።
    ፫) ስንዱ ከሃገራችን ትልልቅ የስነጽሑፍ ስብእናዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት ነበራት፦ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ባሴ ሃብቴ፣ ሙሉጌታ ተስፋዬ፣ አውግቸው ተረፈ(ሕሩይ ሚናስ) ወዘተ
    ባልጓጓ ነበር የሚገርመው!

  • @tazmadrama8492
    @tazmadrama8492 Před 3 lety +4

    Keber lemegebaw keber enest hulem kumneger yelelew ager awdame kemenankolepapes