ሀይማኖቴን ልቀይር ? ፍቅረኛዬን ልጣው ?

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 04. 2022
  • #fevenketema #wedding #artistfevenketema
    The official You tube Channel of Feven Ketema.
    Enjoy! Subscribe!
    Connect for more.
    / fevenketema
    / fevenketema. .
    fevenketema.com/
  • Zábava

Komentáře • 811

  • @haymanotimoges9118
    @haymanotimoges9118 Před 2 lety +137

    ፍቅረኛሽ ይቅር እንጂ ከሀይማኖት እሚበልጥ ነገር የለም

  • @beyeaynetu_832
    @beyeaynetu_832 Před 2 lety +82

    እህቴ ራኬብ የእውነት ምክራችን ፈልገሽ ከሆነ የመጣሽው ስሚኝ። ፍቅር ስሜት ነው። ነገ ትልቅ ቤተሰብ ትመሰርታላችሁ ከዛ ይሄ ፍቅር ከስሜት ወደ ኑሮ ወደ መምራት፣ ቤተሰብ ወደ ማስተዳደር፣ ልጆችን ወደ ራስ የመጎተት ነገር ይመጣል። ያኔ ልጆቻችሁን ምንድነው የሚሆኑት??? እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በኃይማኖታችን በጣም ስስ ነን። ለጊዜው ፍቅሩ የበለጠ ቢመስለንም ውሎ አደር ግን በጣም ብዙ ነገር ውስጣችን ስለሚገባ አሁን በወሰነው ነገር እጅጅጅጅግ በጣም ሲቆጨን ይኖራል። በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ደግሞ ትዳር ከተመሰረተ በኅላ በፍፁም መፋታት አይቻልም።
    የመጨረሻ ምክሬን ልምከርሽ። ለ15 ቀን ስልክሽን አጠፋፍተሽ አንዱ ገዳም ሄደሽ ሱባኤ ግቢ። እዛ ያሉ የበቁ አባቶችን አማክሪ።በእርግጠኝነት ያኔ ትክክለኛ ውሳኔ ትወስኛለሽ። እመኝኝ ይሄን አድርጊውን እና እውነተኛ መልስ ታገኛለሽ

  • @ethio7706
    @ethio7706 Před 2 lety +17

    ሲጀመር ፍቅረኛን ወይም የወደፊት የህይወት አጋር የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው ታዲያ እሱ ሰቶኝ እሱ በሰጠኝ ነገር ፈጣሪን መካድ ሀጥያት ነው በዛላይ የሰጠህኝን ንሳኝ እንደማለት ነው ደግሞ ፈጣፊ እንድትመልሽው ሊሆን ይችላል የሚሰጥሽ እንጂ መጥፊያሽ እንዲሆን አይደለም ለኔ ነብስ ተጠያቄ እኔ እንጂ የስጋ ፍለጎቴ አይሉ አብሬው የምሆነው ሰው አይደለም ተጠያቄው ሴቶችዬ ወንድ ልጅን ውደዱ እንጂ አታምልኩ እግዚአብሔር ብቻ አምልኩ እምነትሽን ስትቀይሬ ወንድየው አንተነህ አምላኬ ብለሽ ጣኦትሽ አድርገሽዋል ማለት ነው ለሁሉም አስተዋይ ልቦናን ያድለን በሀረፈ
    ሳብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

  • @fhnotlozatube
    @fhnotlozatube Před 2 lety +74

    ከእምነት በላይ ምንም የለም።

  • @s5b394
    @s5b394 Před 2 lety +34

    "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ፤ ፅድቅ ከአመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሀንም ከጭለማ ጋር ምን ህብረት አለው?" 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:14
    በሀይማኖት ድርድር የለም አለቀ!

    • @senayetedema5238
      @senayetedema5238 Před 2 lety +1

      ተባረኪ ሊያውም ድንግልን ክዶ ባል ባፍንጫዬ ይውጣ

    • @a-d-o-r-5100
      @a-d-o-r-5100 Před 2 lety +2

      ጌታን ካልተቀበለች ሴት ጋር በትዳር መኖር አስቸጋሪ ነው: ዳንስ መጠጥ ok ነው ከሚሉጋር:: የእግዚያብሄር ቃልም ከማያምኑ ጋር ሚለው ማይመች አካሄድ ያለው ይህንኑ ንው:: church ውስጥ ምን የመሳሰሉ ጌታን ሚያውቁ ሴቶች ሞልተውልሀል አይንህን ክፈት ያለበለዚያ ዋጋ ትከፍላለህ:: ልጆችህንም ዋጋ ታስከፍላለህ

    • @senayetedema5238
      @senayetedema5238 Před 2 lety +1

      @@a-d-o-r-5100 ጌታን ካልተቀበለች ጋ ላልሽው ከተቀበለች ቆየች ስንት ጌታ እንዳለ እኔንጃ መጠጥና ዳንስ ምንም አይደለም ይላሉ ላልሽው ደግሞ ጠጡ ደንሱ ይላል የነሱ መፀአፍ ቅዱስ ካልሽ ምራፍና ቁጥሩን ፃፊልኝ በተረፈ መጠጥም ሆነ ዳንስ ከጴንጤ በላይ አለ እንዴ ተደብቃችሁ ሰው እንዳያየኝ እያላችሁ አይደለም እንዴ የምትጋቱት ሰውን እንጂ እግዚአብሔር የማትፈሩ አስመሳዬች

  • @user-gd4fy4ub3f
    @user-gd4fy4ub3f Před 2 lety +12

    የሰው ፍቅር ያልቃል የክርስቶስ ፍቅር ሁሌ አዲስ ነው በዚሁ ቀጥለሽ በሐይማኖት ሳትግባቢ ብትጋቡ ትዳራቹ የፀና አይሆንም ልጅ ይመጣል ልጄቼን ማቁረብ አትችይም ክርስትና አታነሺም የሚል ፀብ ይመጣል በአጠቃላ እረፍት አታገኚም በቅርብ እንደዚ የማውበው ሰው አለ

  • @flagottegenawnega648
    @flagottegenawnega648 Před 2 lety +25

    ሀይማኖት ለድርድር ሊቀርብ አይችልም ።ሩታ ውነትሽን ነው እንደኔ በሀይማኖትሽ ፅኝ በሏት እግዚአብሔር ትልቅ ነው ትርሳው

  • @dagemadera4378
    @dagemadera4378 Před 2 lety +9

    መነኮሳት እኮ የክርስቶስ ፍቅር ከሁሉም መብለጡን በግልጽ ያስተምሩናል ።..የኔን ታሪክ በአጭሩ ላስረዳችሁ እኔም ሊዲያ የምትባል የprotastant እምነት ተከታይ ነበረችኝ በፍቅር አንድ 3 ወር አብረን አሳልፈናል...እና ጓደኞቼ የቤተክርስቲያን ደቀ መዝሙር ስለነበሩ ግንኙነቱን አቋርጥ አሉኝ እኛም በጣም ፍቅራችን እየሞቀ የመጣበት ሁኔታ ላይ ነበር..ከዛ ነገርኩዋት እኔም በእምነቴ አንተም በሀይማኖትህ የሚል ሀሳብ ነው ያላት 😳 በነገሬ ላይ የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ነበርን አሁን 12ኛ ደርሰናል ..እና ግንኙነቱን በቀጥታ ከኔ በኩል ይቋረጥ የሚል ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ተቀበለችው እሷ ግን ለአንድ ሳምን ያክል ከልቤ ልትጠፋ አልቻለችም..አልቅሰን ነው የተለያየነው ።
    እና በአጭሩ ማንም ምንም ከክርስቶስ አይበልጥም ።

  • @user-le8mk5sb1r
    @user-le8mk5sb1r Před 2 lety +30

    ተንታኟን ደሞ በጣም ነውማደንቃት በትክክለኛው አገላለፅ ነው ያብራራችው የእንግዳሽ አድናቂ ነኝ

  • @weynshettesfaye6225
    @weynshettesfaye6225 Před 2 lety +58

    ፍቅር ከእምነት ይጀምራል ክርስቶስን ክዶ ፍቅር የለም እህቴ ሀይማኖት ከምንም ከማንም ይበልጣል ሀይማኖትሽን እዳትቀይሪ እግዚአብሔር ይርዳሽ

    • @MN-xf8xu
      @MN-xf8xu Před 2 lety

      ከርስቶሰን የካደው ማነው???ወየሱስ ከርስቶስ ጌታ ነው ስትባሉ ታብዱ አደል?? ከርስቶስ የሚያመልከወን ያውቃል

  • @user-tp8yz3el1m
    @user-tp8yz3el1m Před 2 lety +87

    ፍቅር ከእምነት ይጀምራል በእምነቴ ቀልድ የለም አገላለፃቹ ደስ ይላል ❤❤

    • @tsigemariyamtigi4393
      @tsigemariyamtigi4393 Před 2 lety +1

      በሃይማኖትሽ ፅኚ

    • @saronfikir5962
      @saronfikir5962 Před 2 lety +2

      በትክክል ፌቨን ልክ ናት ያችግን ልፈላሰፍ ትላለች ክክ ፍቅር ከክርስቶስ ከድንግል ማርያም ልጂ ይጀምራል በኔ እምነት ነው የሰውን አልቀምም በእምነቴ ግን አልደራደርም።

    • @buchigetachew3228
      @buchigetachew3228 Před 2 lety +1

      አብረን ከጋብቻ በፊት አብረን እንደር ያለ ጴንጤ ለእኔ ጴንጤ አይደለም

    • @user-ib5vr7db5t
      @user-ib5vr7db5t Před rokem +1

      ትክክል

  • @zewdneshzegeye9259
    @zewdneshzegeye9259 Před 2 lety +4

    መቀጠል የለባቸውም። ጌታ እየሱስን ለዚህ አለም ደስታ ብለህ አትለውጥ። ጥሩ ልጅ ልትሆን ትችላለች ነገር ግን በክርስቶስ እየሱስ አሀማመን እና ወንጌልን አለማወቅ በሕይወታችሁ ውሰጥ ገደል ነው።
    በርታ በጌታ ፅና ።
    እህታችንም ጌታ እንደጳውሎስ አይንሽን ያብራው

  • @tinbetdaniel9900
    @tinbetdaniel9900 Před 2 lety +72

    እኔ ብሆን ጊዜ ወስጄ ገዳም ሂጄ ፀሎት አረጋለው አባቶች አማክራለው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ደሞ ይረዳል ።

  • @berrybrook4180
    @berrybrook4180 Před 2 lety +127

    የክርስቶስ ፍቅር ይበልጣል ! በፍፁም እምነትሽን እንዳትቀይሪ ::

    • @hanateklehaymanot4299
      @hanateklehaymanot4299 Před 2 lety +1

      Kkkkk

    • @lubabalubaba6703
      @lubabalubaba6703 Před 2 lety +3

      ይሄው እኔየ ባሌን የመወደውን ባህሌን የልጁን አባት ፈትቸዋለሁ ሙስሊም አልሆን ሲለኝ እዉነተኛው አላህ መሆኑን ስረዳ ተፋታን በፊት ወድጀው አፍቅሬው ለሱ ክርስቲያን ሁኜየ ኑሬየ አለሁ ግን ወደራሴየ ስመለስ ፈታሁት ልጀን ይዤየ ከነልጀየ አልሃምዱሊላህ ሙስሊም ሆኩን እድሜየ ለዱአየ ፍቅሩን እረሳሁን ግዜየን በቁረአን ነው እማሳልፈው አልሃምዱሊላህ ከቅልፊየ ከጨለማ ወደ ብረሃን ገባሁ አልሃምዱሊላህ

    • @user-zt6wl5pe6u
      @user-zt6wl5pe6u Před 2 lety +7

      @@lubabalubaba6703 እውነት ብርሀን ክርስቶስ ጋር ነው ያለው መፀሀፍ ቅዱስ አንብበሽ ቢሆን ጥሩ ነበር ሳታነቢ ስለሆነ የሄድሽው ሳታነቢ ተመለስሽ የኦርቶዶክስን መፀሀፍ ቅዱስ አንቢቢ ተረጂ

    • @Sabrina-ek9cc
      @Sabrina-ek9cc Před 2 lety +1

       ያዉም የኦርቶዶክስ መፀሀፍ ቅዱሰ ነው እንዴ ሚነበበው እረ አታሰቁን

    • @hewan676
      @hewan676 Před 2 lety +1

      @@Sabrina-ek9cc ማለት

  • @mahidan4881
    @mahidan4881 Před 2 lety +8

    ፍቅር በቀላሉ ተይው ልማት ይከብዳል ነገር ግን አብዝቶ መጸለይ እና የእግዚያብሄርን ፍቃድ መጠየቅ ያስፈልጋል ምክንያቱም እግዚያብሄር ከኛ በላይ የሚጠቅመንን ስለሚያቅ

  • @fekertilahun5529
    @fekertilahun5529 Před 2 lety +27

    እውነተኛ ፍቅር ወይም ትዳር ከፈጣሪ ነው የሚሠጥሽ ቆም ብለሽ አስቢ ሁሉም ሠው በወጣትነት ብዙ መንገዶችን እንከተላለን ያአ የገር ግንፍፃሜ አብሮ አይዘልቅም ቅድሜያአ በሀይማኖትሽ ጠንካራ ሁኝ

  • @redetayalew1187
    @redetayalew1187 Před 2 lety +23

    ፍቅር ከእምነት ይጀምራል ክርስቶስን በሰው መቀየር ወደ ጥልቁ እሳት መወርወር የፈለገ ብቻ ነው

  • @bmm72
    @bmm72 Před 2 lety +5

    ከሀይማኖት የሚበልጥ ነገር የለም እህቴ በሀይማኖትሽ ፀጠሽ ተቀመጭ ያች ያለውን ማንም አይወስድብሽም የአሁኑን ምቼት አይተሽ ከሱጋ ብትሆኝ ዋጋ ያስከፍልሻል ከማይመስልሽ ሰው ጋር በፍፁም እንዳትጋቢ ፀልዩ እግዚአብሔር አምላክ ታሪክ ቀያሪ ነው ወደ ሀይማኖትሽ እንዲመጣ ከገባሁ ቡሀላ እቀይረው አለሁ ብለሽ እንዳገቢ በፍፁም !!!!!!

  • @user-mh1yc5vc5x
    @user-mh1yc5vc5x Před 2 lety +17

    ሀይማኖት ይቀድማል ለድርድር አይቀርብም ሀይማኖት ከምንም በላይ ነው

  • @negashahmed7907
    @negashahmed7907 Před 2 lety +13

    እኔ የምደግፈው ፌቨን መጀመሪያ የሰጠሸው ሀሳብ ደጋፊ ነኝ ፣ ነገ የተለያዩ ሃሳቦች ይመጣሉ አንድ መንገድ ላይ መሆን አለባቸው ወይ ፍቅር ማህበራዊ ነገሮች ውስብስብ ሊሆንብሽ ይችላል እፍ ያለ ፍቅር ይበርዳል አስቢበት !!!!!!!!!!!!! ???????????????

  • @user-mp3go3hj5q
    @user-mp3go3hj5q Před 2 lety +3

    እውነት ነው በእምነት መደራደር አይቻልም ከምንም በላይ የክርስቶስ ፍቅር ይበልጣል የመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መሆን መመርጥ ነው እህት እምነትሽን አስቀድሚ
    ትዳር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ለገሀነብ እሳት ከመሆን ቢቀት ይመርጣል እህቴ በደንብ አስቢ በት
    አንችና እሱ ብትስማሙ ለምሳሌ ልጅ ስውልዱ አንድን መናፍቅ አንዱን ወኦቶዶክስ ልታደርጊው ነው ወይስ?

  • @almazworkneh8255
    @almazworkneh8255 Před rokem +2

    የዘላለምን ሕይወት የሰጠው የሞተው ደሙን ያፈሰሰው ነው እንጅ የሚያድን ሀይማኖት አያድንም አያድንም ጌታ እየሱስ ህይወት ሊሆንልን የመጣው የሚያድነን እየሱስ ብቻ ነው

  • @user-nd3de5hs6i
    @user-nd3de5hs6i Před 2 lety +10

    በጣም የምወድሽ አርቲስት ነሽ ፌቨን በርቺ😍😍😍እኔ ባንቺ ቦታ ብሆን በእምነቴ አልደራደርም ለዘመኑ ፍቅር እምነትሽን እንዳትቀይሪ ባለታሪኳ😌

  • @asegedechanbesso1399
    @asegedechanbesso1399 Před 2 lety +19

    ወደዛ ሂጂ ነገ ደም እንባ እያለቀሽ መንገድ ዳር ትቆሚያለሽ አያዋጣሽም ከእመቤቴ ፍቅር ደግሞ ምንም አይበልጥም እንኳን ወንድ ህይወትም ይቀራል ከሀይማኖት በላይ ምንም የለም

    • @user-qs9gi6ck8c
      @user-qs9gi6ck8c Před 2 lety +1

      በትክክል ደግሞ ለሰው ነገ ሊረግጣት ዛሬ ሀይማኖት ያሥቀይራት ሰውኮ ተለዋዋጭ ተገለባባጭ ነው የሆነ እንከን ቢያገኝባት አሽቀጥሮ ነው የሚያሥወጣት እኔስ ከክርስቶስ ፍቅር ከድንግል ማርያም እናትነት ማንም ምንም የሚበልጥብኝ የሐም ሁሉ ከቱ የከቱ ከቱ

    • @hiwetkasahun9968
      @hiwetkasahun9968 Před 2 lety

      tebarek

  • @ababaabba1673
    @ababaabba1673 Před 2 lety +15

    የኔ ናት በመጀመሪያ እግዚአብሔር እዉነተኛ ዉሳኔ እድትወሰንኝ ይርዳሸ !!በመቀጠል አንቺ የሱ እምነት አምነሸ መቀበል ምትችይ በሆነ ማለት እሱ ሰለ ምታፈቅረዉ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖቱ ከልብሸ አምነሸ ምትከተዩ ከሆነ ብትቀይር ችግር የለም ።ለምሳሌ በኔ የደረሰ ልንገርሸ እኔ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ እሱ እስልምና ተከታይ ነው በጣም ተቃራራብን ፍቅር ጀመርን ግን በሁለታችን መካከል ያለው የሀይማኖት ልዩነት ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኛል ።አንድ ቀን ጠየኩት እኔ ሀይማነቴን ብጭራሸ አልቀይርም አንተ ምን ትላለህ አልኩት እሱም እኔም አለኝ ከዛ ተመካክረን ቀሰ በቀሰ ማቆም እዳለብን አሰብን እግዚአብሔር ረዳን አሁን ተለያይተናል ከእግዚአብሔር ሰላምታ ዉጭ ለኔ የለንም ሁለታችንም ሳንጎዳ እናንተም ተመካከሩ ወደ አንድ መምጣት ማትችሉ በሆነ

  • @selamawitworiku7022
    @selamawitworiku7022 Před 2 lety +15

    ፍቅር ከእምነት ይጀምራል እኔ የምልሽ ሀይማኖትሽን አትቀይር

  • @user-zy6oy8ru9x
    @user-zy6oy8ru9x Před 2 lety +10

    ሲጀመር ሀይማኖት ምንጋ አይወዳደር ከሰዉ ፍቅር የእግዚያአቤሄር ፍቅር ይበልጣል እግዚያአቤሄር የምናስተዉልበት ልቦና ይስጠን እኔ ብሆን ሀይማኖቴን ነዉ እምመርጠዉ ብዙወች እማቃቸዉ ከወለዱ ብሗላ ተለያይተዋል ለሰዉ ተብሎ ሀይማኖት አይቀየርም

  • @jesuschrist8298
    @jesuschrist8298 Před 2 lety +4

    የእግዝዚአብሔር ሀሳብ ካለበት እኛ ና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦችን ቢያፈልቁ አዳሟ ከሆነ ሔዋኑም ከሆነች እግዚአብሔር ያጣማረውን እንግዲህ ሰው አይለየው

  • @ermiasfekedegebreyohannis7299

    አብዛኛው comment ሰጪዎች ጋ ራስ ወዳድነት አለ ዋናው ነገር ፍቅራቸው ነው የሁለታቸው እምነት ወዳንዱ መስማማት ግድ ነው ካልሆነ ሁለቱም በየ እምነታቸው ሆነው ይቀጥሉ የልጅ ጉዳይ ብዙም የሚያሳስብ አይመስለኝም በሱአም ቢቀጥሉ በሱ ልጆች የሁለቱንም አውቀው ይቀጥሉ ከዛ እውነት ወዳለበቱ መንገድ መሄዱ ምርጫው የናትና አባት ሳይሆን የልጆቹ ነው ግን በነጻነት ነው ማደግ ያለባቸው ዋናው በፍቅር መዝለቁነው እንደኔ ሁለቱ ወደ 1ዱ ቢመጡ የተሻለ ነው ተስማምተው እውነት አለ ወደሚሉት መሆን ይችላሉ በያሉበት መቀጠልም ይችላሉ ግን የኔ ይብስ የኔ የሚሉ ከሆነ መቻቻል የሌለው ፍቅር ከሆነ ይቅር

  • @shimelsassgda503
    @shimelsassgda503 Před 2 lety +133

    በአጭሩ ኬብሮን ሀይማኖት መለወጥ ከሀጢያት ሁሉ ሀጢአት ነው

    • @bitaniamesfin6073
      @bitaniamesfin6073 Před 2 lety +4

      በየትኛው ጥቅስ ላይ ነው እንደዛ የሚለው አባባል ነው እንጂ

    • @danayithabte4733
      @danayithabte4733 Před 2 lety +7

      That’s what happened to me but it’s better not to change any religion for relationships

    • @peacelove4778
      @peacelove4778 Před 2 lety +9

      @@bitaniamesfin6073 አባባል አይደለም በአፍጢሙ ይደፋ እንጂ ወይ ንክች በሐይማኖቴ

    • @user-qs9gi6ck8c
      @user-qs9gi6ck8c Před 2 lety +3

      ከምንምና ከማንም በላይ ሀይማኖት ለምን ቤተሠብ አይሆንም ለምን እናቴ አትሆንም ከሀይማኖት በታች ከክርስቶስ በታች ነው ሁሉም እህቴ ኬብሮን ሀይማኖትሽን ለወንድ ብለሽ እንዳትቀይሪ ከፈለገ እሱ ይቀየር

    • @user-gf8lx3wu7x
      @user-gf8lx3wu7x Před 2 lety +3

      @@bitaniamesfin6073 እኳን ፍቅረኛ እናቴ እኳን ከሃይማኖቴ በታች ነች እናቴ በሃይማኖቴ ከመጣች ጥንቅር ትለለች እንጂ በሃይማኖቴ ድርድር አለቅም

  • @muiu5374
    @muiu5374 Před 2 lety +8

    ለምን ጥንቅር አይልም ፍቅረኛው ፍቅር ከእምነት ይጀምራል አከተመ። እኔም በሀይማኖትሽ አንቺም በሀይማኖትሽ ብሎ ነገር የለም በትዳር ውስጥ ❌

  • @talesokitayta2632
    @talesokitayta2632 Před 2 lety +16

    ምስጥሩ ያለው ሐይማኖት መቀየሩ ጋ ሳይሆን የሕይወት አዳጝ የሆነውን ክርስቶስን ማመን ነው።

  • @alemneshbeyene5539
    @alemneshbeyene5539 Před 2 lety +1

    ክርስቶስ ስለኛ የሞተበት ምክንያት ፍቅርነው የተዋህዶልጆች አንድ ጌታ፣ አነድ ሀይማኖት፣አንድጥምቀት ነው ኩራታችን ይህን እምነት የሰጠን ቅዱስ አምላካችን እናቱ ከእናታችን ከመብራሀን ጋር ኬብርእና ምስጊና ይድረሳቸው አሜን በሉ የኔ ተወዳጅ ተዋህዶዎች

  • @asnilulit4878
    @asnilulit4878 Před 2 lety +1

    ኬብሮን ፍቅር በጣም ደስ የሚል ነገር ነው ነገር ግን በሀይማኖት የተለያየ ሰው አብሮ መኖር አይቻልም አብረን መኖር እንችላለን ብትይ እንኳን ቀጣይ ህይወትሽ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር ነው ሚጠብቅሽ ልጆችም ስታፈሩ የትኛው ትክክል እንደሆነ መምረጥ ይከብዳቸዋል እና ደግሞ የኔ ሀይማኖት ትክክል ነው ብለሽ ታምኛለሽ አደል ስለዚህ ሀይማኖትሽን ይዘሽ ኑሪ

  • @tigest6117
    @tigest6117 Před 2 lety +3

    ይሄ ታሪክ ምንም አይነት ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስ የኔም ታሪክ ነው እኔ ትንሽ ስለምበልጠሽ ሰለኖርኩበት ልምከርሽ አትግቡ በሰላም ተለያዩ 10 አመት በሗላ ልጅ ሲመጣ እኔ ክርስትና አስነሳለሁ እሱ አታስነሺም ጪቅጭቅ ፈጠረ ተለያየን ከወለዳችሁ በሗላ ከምትለያዩ አሁን ወስኝ እህቴ እማይፀፅትሽን ውሳኔ ነው መወሰን።

  • @eyerusalem9504
    @eyerusalem9504 Před 2 lety +3

    ኬብሮን በመጀመርያ ሀይማኖቱን የሚቀይር ከሆነ ለመጨረሻ ጊዜ ጠይቂው አይ ካለ መለያየት ነው ያለብሺ ፍቅር በስሜት የሚገነባ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው የሚገነባው አንድ ጌታ አንድ ሀይማኖት አንድ ጥምቀት ኤፌሶን 4÷5
    ከልጁ ጋር ፈፅሞ መቀጠል የለብሺም ፍቅር ቢቀር ነገ ሌላ ታገቢያለሺ ለዛውም የምድር ደስታ የስጋ ደስታ ነው በዚህ ምድር የሚቀር ነው ነገር ግን ሀይማኖትሺን ብታጭ የነፍስም የስጋም ማጣት ነው ፈጣሪን የከዳ የሲሆል እሳት ነው የሚጠብቀው ቀድሞውኑ ምክን አያስፈልግሺም አንች አስበሺ የምትወስኝው ነገር ነው ከቤተሰቦችሺና ከጓደኞችሺ ለዘለለ ሀሳብ አንሰጥሺም ፍቅር ስንጀምር መጀመርያ ከእግዚአብሔር እንጀምር ፍቅር እግዚአብሔር ነው

  • @gltube4471
    @gltube4471 Před 2 lety +27

    እረ አትጃጃይ በያት ፍቅር ከእምነት ይጀምራል ሆሆ ምንም ምክክር አያስፈልገዉም ።

  • @woinshetayalew1694
    @woinshetayalew1694 Před 2 lety +2

    ፍቅር አይቀድምም እምነት ነው የሚቀድምው ብዙ ግዜ ፍቅር ተብሎ ይገባና ከተወሰነ አመት በሗላ ትዳሩ የማይቀጥል ሊሁን ይችላል ቢቀጥልም ደስታ የሌለው ነው የሚሆነው ነው

  • @user-ov2ft5mn1i
    @user-ov2ft5mn1i Před 2 lety

    እህቴ በጣም ይከብዳል ፍቅር መለትኮ ቃሉን ስለማናቀው ነው ወደስሜት እምቀይረው የእግዚአብሔር ቃል አታቁምና ትስታላችሁ ይላል ፍቅር ማለት ሶስት ናቸው እነሱም አቭ ወልድ መፈስ ቅዱስ ናቸው ፍቅር ማለት እውነት ነው እውነት ማለት ክርስቶስ ነው ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው ይለል ።እህቴ እምነትሽን አተዳትቀይሪ ሁለተኛ ሞት ነው ስጋውይይ ፈለጎትሽን ማሸነፍ አለብሽ አቭሷ እምነት ሽን እማይመስል ማግቫት ይቅርና አብርን እድንቨል እድንጠጣ አይፈቀድልንም ፀሎት እማይፈታው ችግር የለም ፀሎት አድርጊ ለዛኝቱ ስአሊት ምህረት አወላዴት አምላክ እመ ብዙሀን ንገሪያት ችግርሽን ትፍታለሽ አመብርሀን ለበቁ አባቶች ተናግርሽ ፀሎት ያድርጉልሽ !!!

  • @tsega9038
    @tsega9038 Před 2 lety +1

    በዘፈን ያደገ ትውልድ እኔም ባይማኖቴ አንቺም ባይማኖትሽ እያለ ገደል ገባ ተረት ተረት እየሰማ
    ጌታ ኢየሱስ ይበቃል

  • @titieti1880
    @titieti1880 Před 2 lety +1

    እውነት ነው ሩታዬ እኛ በፈቀድነው ሳይሆን ፈጣሪ ባለው ነው የሚሆነው ማንም ስው የሚመኘውን ወይም አፍቃሪና ተፈቃሪ ተገናኝቶ አያውቅም ፈጣሪ ካልፈቀደው

  • @user-wm9ym2eo4h
    @user-wm9ym2eo4h Před 2 lety

    ኬብሮምዬ እኔ የምልሽ ነገር ቢኖሮ ፀሎት አርጌ ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኚ እራሱ ፈጣሪ መልሱን ይመልስልሻል ሲጀመር የናተ ግንኝነት ከታሪክሽ እደሰማሁት የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው ብዬነዉማስበው ስለዚ ባትለያዩ ጥሩ ይመስለኛል ጊዜ ወስደሽ ካምላክ ጋር ተነጋገሪ

  • @azamerafenataw6105
    @azamerafenataw6105 Před 2 lety +5

    እኔ ለእህቴ የምመክራት ሀይማኖቷል አጥብቃ ትያዝ
    ሀይማነት የግልነው ሀገር የጋራነው የሚባለው ለጎርብትና ነው ለትዳር ጓደኛ ሀይማኖት የተለያየ እረ ይገርማል
    የአክስቴን የትዳር ሂወት ላካፍላችሁ አክስቴ ኦርቶዶክስ ናት ባለቤቷ ሙስሊም ነው ተጋብተው ሁለት ልጆች ወልደው ተለያዩ ልጆቹ ኦርቶዶክሳዊ ሆኑ ከአክስቴ ጋር ሆኑ ከዚያ አክስቴ ከሌላ አንድ ልጂ ወለደች ባለቤቷም እንዛው ከዚያ ሁለቱም ከሌላ ሰው ወልደው ከተለያዩ ቡሀላ እንደ አዲስ ተሞሸሩ እርሱ ከእስልምና ወደ ኦርቶዶክስ ሃይማኖቱን ቀይሮ ።
    ነገር ግን አንደኛው ልጃቸው በሚገርም ሁኔታ ፍቅረኛዋ ሙስሊም ሆነ ለ10 ዓ.ም እኔ አልቀይርም እኔም እያሉ ኖሮ ከዚያም በ11 ዓ. ም እርሷ ቀይራ አብረው መኖር ጀመሩ በአሁኑ ጊዜ የሶስት ልጆች ወላጆች ናቸው ነገር ግን የቤተሰብ ፍቅር የለም ።
    ከዚህ የተማርኩት ሀይማኖት የግል ነው የሚለው ጥቅስ ለጉርብትና ብቻ ነው

  • @meskeremmengste7365
    @meskeremmengste7365 Před 2 lety +4

    እግዚአብሔር ይርዳሽ ድንግል ማርያም ትርዳሽ ktgabaw bwhala yrasen ymil nger ylem balna mist and nachew ehte haymanot ybltal እግዚአብሔር አምላክ esun slmrtsh ytshale ystshal

  • @user-ty6ec3nt1v
    @user-ty6ec3nt1v Před 2 lety

    ኤክሮምዬ እኔ እምልሽ ነገር ቢኖር ከምንም በላይ የማትለወጥ የማትቀየር ሀይማኖት ናት ለዛውም እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ። እምነትሽን እንዳትቀይሪ ከሀፂያት ሀፂያት ነው ከምንም በላይ ሀይማኖትሽን ጠብቂያት ልቦናሽን ይመልስልሽ ፈጣሪ

  • @semumuhadin8251
    @semumuhadin8251 Před 2 lety +4

    አንዳንድ ኮመንታተሮች ግን ከመፃፋቹ በፊት አንዴ ሳይሆን ሶስቴ አስቡ የደረሰበት ነው የሚያውቀው ከባድ ነው

  • @user-yk9ez9uj6y
    @user-yk9ez9uj6y Před 2 lety +1

    ፍቅር ጡሩ ነገርነዉ ነገርግን የሠዉ ፍቅር ከክርሥቶሥ ፍቅር አይበልጥ ሥለዚህ በሀይማኖት ድረድር የለም ሥሚ እህታችን የተለያየ እምነት ለናተ ሣይሆን ለልጆቻችሁ ነዉ ጉዴቱ እደኔ ሀሣብ ነዉ💚💚💚

  • @felegehiwotalamrew6633
    @felegehiwotalamrew6633 Před 2 lety +16

    በጣም ከባድ ነው በፍፁም አብረወው መሆን የለባቸውም

  • @hyme7165
    @hyme7165 Před 2 lety +1

    ፍቅር ከእምነት ይጀምራል ከኔ እናቱን ወይም ሚሥቱን ያሥበለጠ ለኔ ሊሆን አይችልም ይላል አምላካችን በማይታበይ ቃሉ በፆም በፆሎት በርች እህታችን በፆሎት የማይፈታ ነገር የለም በሀይማኖቴ አልደራደርም💒👈

  • @user-ok1bt6wx1g
    @user-ok1bt6wx1g Před 2 lety +5

    አገላለፃችሁ በጣም በጣም የትልልቅ አባቶች ምክር ነው ተባረኩ

  • @zahrabintbabatube5921
    @zahrabintbabatube5921 Před 2 lety +2

    እኔም አልቀይርም እኔም አልቀይርም ከማለት ግን ማንበብ መወያየት ይበልጣል እናቱ በእምነት ውስጥ ሚስጥር ለኛ እማይገባን ነገር እሚባል ነገር የለም እና ለምን ኦርቶዶክስ እንደማይሆን ለሚጠይቅሽ መፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ መልስ መስጠት አለብሽ በሎጂክ በተረትተረት ሳይሆን ከመፀሀፉ ካልቻልሽ ለእራስሽም ሳይገባሽ ለምን ትከተያለሽ ሁለታችሁም አንብቡ ተወያዩ ወደ አንድ ተጠቅለሉ እንጂ በአንድ ቤት ሁለት እምነት ይከብዳል በጣም በቤተሰብ ጫና የምታምኝው እምነት ዋጋ የለውም ነፃነት ሊሰጧችሁ ግድ ነው

  • @user-gd4fy4ub3f
    @user-gd4fy4ub3f Před 2 lety +4

    አንቺም በሐይማኖትሽ እኔም በሐይማኖቴ የሚለው ተረት አይሰራም ኬብሮን አሁን በፍቅር ስላላቹ ብኋላ የሚመጣው መዘዘ ከባድ ነው የሚሆነው ፍቅር ያልቃል የአሁኑን ሳይሆን መየት ያለብሽ አርቀሽ ነው ማሰብ ያለብሽ ብዙዎችን አይተናል ልጆች ካፈሩ ብኋላ በሐይማኖት አለመግባባት ትዳራቸው ሲበተን የአሁኑን ፍቅር ብቻ አታስቢ ብኋላስ ብለሽ አስቢ ከባድ ነው የሚሆነው

  • @selamgondereiwa5202
    @selamgondereiwa5202 Před 2 lety +1

    ኪብሮም መጀመሪያ ፍቅር እግዚአብሔር ነው ከምንም በላይ ሃይማኖታችን ይበልጣል ትዳር ነው ያሰብሽው አንተም በሃይማኖትህ እኔም በሃይማኖቴ የሚባለው ለትዳር ሳይሆን ለማህበራዊ ስራ ነው በበለጠ ከነብስ አባትሽ የህይወት ምግብን እንዲመክርሽ በመፅሃፍ ቅዱስ ያለውን ከአባቶች ስሚ ።ሳየው ደነገጥኩ ለምትይው በቀን ከምናያቸው ሁሉ ልንደነግጥ ልናደንቅ እንችላለን ነገር ግን ሁሉን ልናገባው አይደለም እኛ ያሰብነውን ሳይሆን ፈጣሪ በቤቱ ያለውን ያሰበልነን ይስጠናል ያለእምነትሽ እየሆነ ከፈጣሪ ነው የተሰጠኝ ብለሽ አታስቢ ኦርቶዶክስ ከሆነ አግቢው አንች ግን ከቀጥተኛዋ እምነት ወደ ጭፈራው አለም ባትገቢ እመርጣለሁ

  • @jemilayimam5949
    @jemilayimam5949 Před 2 lety +7

    የሚወለዱትም ልጆች ወደ ማንኛው ይሆናሉ
    ከሀይማኖት በላይ ምንም ነገር የለም
    ፍቅሩን ደሞ ለምትገዥው አምላክሽ ዱአ አርጊ /ጰልይ/ እንድትረሽው

  • @genatworkugenetworku6227
    @genatworkugenetworku6227 Před 2 lety +6

    እኔ እንደ አንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ አስተያየቴ አምላክ በባልም ሆነ በሚስት አይተካም እግዚአብሔር ለትዳር ሲባል አይለወጥም ፍቅር እግዚአብሔር ነው
    ከቀየረ ይቀይርላት ካላመነበት ይቁም
    ጣዖት ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ቤት አይኖርም።

  • @n.medhanialem5978
    @n.medhanialem5978 Před 2 lety +2

    አሁን ሔብሮን ያወራችው ግዜያዊ የስጋ ፍቅር ነው :: ትዳር ላይ ግን እየቆዩ በሔዱ ቁጥር ፍቅሩ ያልቅና እንደ ወንድምና እህት ነው የምተያዩት ምክንያቱም ልጅ ሲወለድ ሁሉም ይቀየራል

  • @tg3766
    @tg3766 Před 2 lety

    ይህን ላይፍ ሁሉም ሠዉ ባይባልም ብዙዎቻቺን አልፈንበታል ይሆናል ብለን የጊዜአዊ ሥሜታቺንን ብንከተልም በፍፁም ዘላቂነት የለዉም በምንም አይነት ሥለዚህ ባለታሪካቺን እህቴ እባክሺ እራሥሺን ጨክኝበት ሥሬሥ ሆነሺ እራሥሺን ከሥሜታዊፍቅር እድትወጪ ተቆጪዉ በኡነት ነዉ እምልሺ ህይወትሺ ይመሠቃቀላል።

  • @ematbemary8257
    @ematbemary8257 Před 2 lety +1

    ሲጀመር መጀመሪያውኑ ከሀይማኖቴ ተቃራኒ የሆነን ሰው በፍቅርም አላስበዉም ምክንያቱም ከሀይማኖቴ የሚበልጥ የለም ቆሜ ብቀርስ ደፋር በእምነትሽ ፅኝ የሰው ፍቅር ያልቃል የእግዚአብሄር ይበልጣል

  • @Nolawieneye
    @Nolawieneye Před 2 lety

    በጣም ከባድ ነው:: እምነት ይበልጣል!!! ተለያዩ!!!

  • @rutrtshe9628
    @rutrtshe9628 Před 2 lety +8

    እህቶቼ ...እምነት ..እምነት ..እምነት ።ይቀድማል
    ፍቅር ይልቃልም ይቀዘቅዛል ።

  • @selamawittesfaye3252
    @selamawittesfaye3252 Před rokem

    ሰላም ፌቨን የከፈትሽው ቻናል በጣም ደስ ይላል አስተማሪ ነው በርቺ ። ወደ ጉዳዩ ስንገባ ፍቅር ደስ የሚል ነገር ቢሆንም ሀይማኖት ግን ከባድ ነገር ነው በፍቅር ህይወት ስንኖር ያለው ግንኙነት እና ወደትዳር ስንገባ ያለው ህይወት አመለካከት በጣም የተለያየ ነው። አይደለም ልዩነት ኖሮሽ ይቅርና አንድ የሚያደርጉ እጅግ ብዙ ነገሮች ኖረው እንኳ ብዙ ፈተና አለ ስለዚህ ከጅምሩ አንድነት የሌለበት ነገር ውስጥ ባትገባ ጥሩ ነው። የልጅነት ፍቅር ትዝታው ብዙ ቢሆንም የገሀዱ አለም ህይወት ግን በአንድ ደራሲ አእምሮ ውስጥ ተፈጥሮ በደራሲው ፍላጎት ላይ ተመስርቶ እንደሚያልቅ አይነት ነገር የለም ስለዚህ እውነቱ አፍቅሮ መለየት ከባድ ቢሆንም ተጋብቶ ከመፋታት ይሻላል። ተጋብቶ መፋታት የእሷን እና የሱን ልብ ብቻ ሳይሆን የሚወልዷቸውን ልጆች ፣ ቤተሰቦቻቸውን ብሎም ሀገርን የሚጎዳ ጸያፍ ነገር ስለሆነ ተመሰጋግነው ቢለያዩ ጥሩ ነው። አመሰግናለሁ

  • @genzebmolloa7001
    @genzebmolloa7001 Před 2 lety

    ሀይማኖት ለምርጫ አይቀርብም የኔ ልጅ ፈጣሪሽን በፀሎት ጠይቂ ላንች ያለውን ይሰጥሻል ለማንኛውም ዛሬን ሳይሆን ነገን አስቢ ልጅ ይመጣል ነገ የትኛውን እምነት ይከተላል ብለሽ አስቢ ቆምብለሽ አስቢበት በሱቤተሰብ በአንችም ቤተሰብ ያለው ቅሬታ ሰላም አይሰጥሽም ቤተሰብ ደግሞ መሰረትነው መሠረትን ማቃል ነገእራስን ይጎዳል

  • @user-qq2qw9iz8k
    @user-qq2qw9iz8k Před 2 lety

    በጭራሽ እምነቷን መቀየር የለባትም እሱ ወደ እሷ ከመጣ እሰየዉ ትልቅ ነገር ነዉ አንድ የጠፋ በግ ወደ እግዚአብሔር አመጣች ማለት ነዉ ትፀድቃለች ነገር ግን አችም በሀይማኖትሽ እኔም በሀይማኖቴ መኖር እንችላለን አይጠበንም ቤቴ ብሎ ነገር አይሰራም ሁለት የተለያዩ ሀይማኖት በአንድ ወይም ከኦርቶዶክስ ወደሌላ መቀየር አይቻልም አይፈቀድም እህቴ እምነትሽን ጠበቅ አድርገሽ ያዥ ፀልይ በሱባዬ የድግል ማርያምን ልጂ ጠይቂዉ ከሁሉም ነገር የክርስቶስ ፍቅር ይበልጣል በተረፈ አይዞሽ እግዚአብሔር ይርዳሽ

  • @blenbilubelene4989
    @blenbilubelene4989 Před rokem

    የእኔ ታሪክ መሰለኝ ግን እኔ ሀይማኖቴ ይበልጣል ብዙ ስቃይ አለው ግን ሁሉም ያልፍል ሀገሬን ቀየርኩ ግን እግዚአብሔር ይርዳሽ እህቴ

  • @kedihabeshawittube7616

    ፊቪየ ፕሮግራሞችሽ በጣም የሚወደዱ ናቸው ቲክቶክ ላይ እየቆራረጡ ሳይ ነው ሙሉውን ለማየት ወደ ቤትሽ ሰብስክራይብ አድርጌ የመጣሁት በርች በምንድነው ላገኝሽ የምችለሁ አይተሽ ዝም እደማትይኝ ተስፋ አለኝ 😍💖

  • @user-lz1ed2xc3n
    @user-lz1ed2xc3n Před 2 lety +6

    ፍቅር ሲጀመር ከእምነት ይጀመራል የፈለገ ነገር ይቀራል እንጂ እምነቴ አልቀይርም ይቀራል ዘላለም ያውም ኦርቶዶክስ መመረጥነው

  • @hanankedir2659
    @hanankedir2659 Před 2 lety +12

    ፍቅርን ያሳወቀን አምላክ ይቀድማል ሃይማኖት ከሁሉም በላይ ነው

  • @rediteendetlarg4747
    @rediteendetlarg4747 Před 2 lety

    ዋው ፌቨን በጣም ነው የምታምሪው እምልልሽ አለሁ አቀራረብሽ ውብ ነው ባለታሪኳ እምነት መቀየር እኔ ብሆን አልስማማም ምክንያቱም ከክርስቶስ ፍቅረ የሚበልጥ አለ

  • @user-sr1ro7ut1t
    @user-sr1ro7ut1t Před 2 lety

    እር ጉድ ፍቅር እግዚአብሔር ነው ከሰው ፍቅር የእግዚአብሔር ፍቅር ይበጣል ጣወት እና ታቦት አድሁነዉ አያቁም እህቴ አስቢ ፍቅር እግዚአብሔር ነው

  • @mekutube6946
    @mekutube6946 Před 2 lety

    ገለፃችሁ በጣም ደስ ይላል በእናንተ ገለፃ ብቻ ተምራ መተው ትችላለች። ለማንኛውም ግን ፍቅር ፍቅር የሚሆነው ከጅምሩ ያለ እንከን ሲጀመር ነው በእምነት የመጣ ደግሞ ከባድ ነው ነገ ሕይወትን እኖራለሁ የሚል ባለተስፋ የቆመበትን መሰረት ማፅናትና ማነፅ አለበት እምነት ከሁሉም ይቀድማል ነገን ዛሬ ላይ ሆኖ መተለሙ መልካም ነው። ለጊዜው ለመተው የሚከብድ ይመስላል ግን ቀላል ነው ምክንያቱም ፍቅር ስሜት ስለሆነ ስሜትን ደግሞ በእምነት ሆኖ ማሸነፍ ነው ከዛ በእምነት የሚመስለንን ሌላ ፍለጋ መጀመር ይሻላል። በኋላ "ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ
    አሁን ምን ያደርጋል ወጭት ጥዶ ማልቀስ" እንዳይሆን ነገሩ አሁን ደጋግሞ አስቦ ከውሳኔ መድረስ ይሻላል

  • @qweqwe444
    @qweqwe444 Před 2 lety

    መጀመሪያ እምነትሽ አስቀድሚ እህቴ ከክርስቶስ ፍቅር የሚበልጥየለም ❤❤❤❤💒💒👏👏👏

  • @yemariam2110
    @yemariam2110 Před 2 lety +1

    Sewedachu two beautiful best actress. Nice to see you two. 🙂 wants to see you more.

  • @astedemamo4640
    @astedemamo4640 Před 2 lety +25

    ውዴ ቤተሰብ በእናንተ ህይወት አይወስንም ሁለታችሁ በደንብ ተነጋገሩ ፀልይ ሁሉም በእግዚአብሔር ፍቃድ ነው

    • @selamselam4350
      @selamselam4350 Před 2 lety +1

      ቤተሰብ ያልወደደው ትዳር አይፀናም

  • @littlekassa9718
    @littlekassa9718 Před 2 lety +10

    Haymanot is number one for tidar!

  • @astertamiru3963
    @astertamiru3963 Před 2 lety +18

    ሁለቱ እንቁወች ፌቨን እና ብሩክታዊት ባለ ማህተቦች ስታምሩ:: ወደ ሀሳቤ ስመጣ ፍቅር የተቀደሰ ነዉ ግን ደግሞ ሁለቱም እምነታቸዉ የተለያየ ከሆነ በሆላ ችግር ይፈጥራል አንደኛ ልጅ ሲመጣ የልጆቹ ሀይማኖት በጣም የከፋ ይሆናል ከሁለት አንድ ያጣ ይሆናሉ እና ባትገባበት ደስ ይለኛል ::

  • @roserose5889
    @roserose5889 Před 2 lety +2

    ፍቅር ከእምነት አይበልጥም ነገ ምን እንደሚፈጠር ገደል ይግባ

  • @mesaynegassa2636
    @mesaynegassa2636 Před 2 lety +11

    እውነትም ህይወትም ክርስቶስ ነው የሱን ተከታይ

    • @selammulatu3807
      @selammulatu3807 Před 2 lety

      ኦርቶዶክ ተዋህዶ ማለት እኮ
      እየሱስ ክርቶስን አምላኬ ብላ እንደናንተ አማላጅ አትልም በእግዚአብሔር የተወደዱትን ቅዱሳንን አክብራ ያለች እምነት ናት ሌላ አዲስ ጌታ የለም መናፍቆች እባካቹ ነቃ በሉ

    • @tsega9038
      @tsega9038 Před 2 lety +1

      @@selammulatu3807 ተረት ተረት አያድንም
      ማርያም ቁስቋም ሚካኤል ገብርኤል አባ እከሌ ደብተራ አይድኑም መናፍቅነት ነው
      ጌታ ኢየሱስ ይበቃሻል

  • @user-gm3kz4ii8u
    @user-gm3kz4ii8u Před 2 lety

    በእውነት ቆንጆ ፕሮግራም ነው የምር
    እስከዛሬ አለመከታተሌ😐

  • @halima8737
    @halima8737 Před 2 lety +13

    የሩታየን ሀሳብ እደግፋለሁ ወደአንድ ሀይማኖት ቢመጡ ደስ ይላል

    • @genettube277
      @genettube277 Před 2 lety +1

      እምነትን ከመካድ ቢለያዩ ይሻላል

  • @meklitsime7994
    @meklitsime7994 Před rokem

    እባካቹሁ ይህን ሰው እረፍ በሉት እኔሚ የንተው አይነት ህይወት ነው ያለን ግን ብዙ ዋጋ ከፌያለሁኝ :: የተገኝ አጋጣሚ ሁሉ ትዳር አይሆንሚ የለጌታ ሁሉ ሚ ባዶ ነውውው::

  • @fedilachef1471
    @fedilachef1471 Před 2 lety +1

    ሃይማኖታቸው ተመሳሳይ ነው ከባድ አይመስለኝም

  • @addis1999
    @addis1999 Před rokem

    ፈቪ programish arif nw..keep it up.ለጥቂት ቀደምሽኝ ያንችን program ለመጀመርያ ጊዜ ዛሬ ነው ያየሁት እንድህ አይነት program ለማዘጋጀት እቅድ ላይ ነኝ ካሰብኩ ቆይቷል። ዋናው ነገር ለባለታሪኮች መፍትሔ ያምጣ። ወደ ሀሳብ መስጠት ስመጣ፦
    ፨እነዝህ ጥንዶች የተለያየ ሀይማኖት ይዘው ወደ ትዳር ይግቡ ብዬ በፍፁም አላምንም።
    ፨even ለትዳር ብለውም አንዱ ወደ ሌላኛው ሀይማኖት እንድቀይርም አልመክርም፤ ግን እውነታውን ተረድተው ብቀይሩ ባይ ነኝ።
    እነዚህን ሁለት ዋና ዋና ነጥቦችን በጽሑፍ ለማብራራት ጊዜ አጥቼ ነው እንጅ ብዙ ምክንያቶች አሉ።

  • @user-wr5xq4vw3b
    @user-wr5xq4vw3b Před 2 lety +3

    ሀይማኖት ለድርድር አይቀርብም ፍቅር የቱንም ያህል ትልቅ ቢሆንም ከሀይማኖት አይበልጥም ።

  • @kibenshtumoro553
    @kibenshtumoro553 Před rokem

    የክርስቶስ ፍቅር ይበልጣል ብርሃነ ጨለማ አንድ ላይ ማኖር አይችልም የፍቅር እራስ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

  • @romanyosef7696
    @romanyosef7696 Před rokem +1

    ጤና ይስጥልኝ እመቤቴ:: ከምንም በላይ ፍቅር ይበልጣል ስንቱ ነው አንድ አይነት ሀይማኖት ተጋብተው ቤታቸው ጦርነት ስንት ደግሞ የተለያየ ሀይማኖት ተጋብተው የጋብቻ ምሳሌዎች ሲጀመር ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱ ጋር ወይም ከባሉ ጋር ይተባበራል ሁለቱ እንድ ይሆናሉ ነው:: ጎደኛ ምናምን ምንድነው ራሳችሁ ወስኑ እንዴት መሆን እንዳለበት ሰው አማክራችሁ ነገ የሚመጣውን እንዲህ ሲሉኝ ለማለት ካልሆነ ፀልዩ የመሻታችሁን እግዜር ያስተካክላል:: ፍቅር የአምላክ ነው::ሀይማኖት ጥሩ ነው ግን🙏🙏🙏

  • @amarehabesha5544
    @amarehabesha5544 Před 2 lety +1

    ትክክል ነሽ እሩታ

  • @user-vw3sb8dj2s
    @user-vw3sb8dj2s Před 2 lety +2

    መጀመሪያ እምነትነው ቢቀር ይሻላን አብሮ መኖናቸው እምነትሽን አትቀይሪ በሰማይ ቤታችን መጠየቅ አለና እንዳትጠየቂ ማህተብሽን አጥብሽ ያዥ እህትየ ፍቅር ጊዚያውይነው ክርስትናስ እና ማህተብሽ ዘላላማዊነው ለፍቅር አትሸነፊ ለማህተብሽ ተሸነፊለት እጅ!!!እንደማትቀይረ ተስፋ አደርጋለሁ 🙏Feven Agelalets shin Edegfew Alehu Adis gebinegn እንግዲህ እኔ ሷ ቦታ ብሆን በማህተቤ አልደራደርም እንዳትቀይሪ ባይነኝ

  • @abrehamtaeme921
    @abrehamtaeme921 Před 2 lety

    ሰላም እንዴት ናቹ እኔ በዚህ ህይወት ተሞክሮ አለኝ ሰው ከውጪ እንደሚያወራው አይደለም 7 አመት ኖሬያለሁ በጣም እጅግ በጣም ከባድ ነው እኔ እውነቱን ስነግርሽ ከመጋባታቹ በፊት ወደ አንድ እምነት መምጣት አለባችሁ እኔ በጣም እየተሰቃየሁ ነው በተለይ ልጅ ሲኖር ይከብዳል እንደምታስቢው አይደለም ለልጅሽ ምን እንደምታስተምሪው ትቸገሪያለሽ ነፃነት አይኖርሽም አንቺ ያለሽ አምልኮተ እግዚአብሔር ለነሱ ምንም ነው ሁሉ ነገር ይከብድሻል ማስጠመቅ ማቁረብ ትቸገሪያለሽ ልጆችን አባታችን ሆይ ማስባል አትቺይም ለዘላለሙ አሜን ብለሽ መቀጠል አትችይም እናቱ በጣም ብዙ ችግር አለው ባንድ እምነት መኖር እጅግ በጣም መልካም ነው ካለበለዚያ በጣም ፈተና ነው ብዙ ነገር የፀብ መነሻ ነው በዚህ ህይወት ውስጥ ልጆች ሰላም እንዲያገኙ አንቺም እሱም የሰላም ኑሮ ከፈለጋችሁ ወይ ባንድ እምነት ኑሩ አልያም አትጀምሩት እግዚአብሔር ያዘጋጀው ሌላ ህይወት ይኖራችኋል።

  • @a-d-o-r-5100
    @a-d-o-r-5100 Před 2 lety +1

    ሲጀምር እውነተኛ ፕሮቴስታንት ቢሆን ግንኙነት እናርግ አይላትም:: ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቃል የተከለከለ ነው::
    ሌላው እምነት አንድ መሆኑ ግድ ነው
    የእግዚአብሔር ቃልም ከማያምን ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመድ ይላ ል ፕሮቴስታንትም ይህን በብዙ ያከብራሉ እና እሱ ራሱ ይጋርማል ከሱዋ ጋር በዚ መልኩ መጠመዱ: ዝምብሎ በደንብ serious ያልሆነ ጴንጤ ነው:: ፍቅር ግን ማያደርገው የለምመቼስ::
    በራስ ካልደረሰም ለመፍረድ ይከብዳል

  • @martima4096
    @martima4096 Před 2 lety +1

    በነገራችን ላይ ከባድ ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ነዉ እኔም አልፌበታለሁ እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ላይ አብረን ነን

  • @azmeratesfazgi1159
    @azmeratesfazgi1159 Před 2 lety

    Rutha tebareki ❤

  • @tollimucaaiyesuskiristos9974

    Egziaberin be tsom be tsalot beti xayiq xiru newu indane asab 🙏

  • @user-ok1bt6wx1g
    @user-ok1bt6wx1g Před 2 lety +2

    ግን በፍፁም ፍቅር ከሀይማኖት አይበልጥም ፍቅር ከሁሉም ከሁሉም ይበልጣል ማለት ከሀይማኖትም አይደለም ፍቅር ከእምነት ይጀምራል የሚለውን ይፃረርብናል ስለዚህ ፍቅር ስንጀምር ከእምነት ጀምር
    በስሜት ስለደነገጠች ባሏ ነው ማለት አይቻልም

  • @aneshamood6033
    @aneshamood6033 Před rokem

    እኔ የምለው ነገር ሁሉም ሰው በአይማኖት የሰውን ፍቅር አታነካኩ ሁለቱ ከተዋደድ የአይማኖት ነገር እራሳቸው ይፈቱታል ለምሳሌ የንዋይን ሚሰት ያየ ከሷ ትልቅ ትምህርት ነው ሰንቱ ሙሰሊምና ክርሰቲያን ተጋብቶ ወልደው በሰላም ይኖራሉ ለእህቴ የምመክርሸ ሁሌም የሰው ልጅ በሰው ምክር ከመሰማት ከአላህ ጋር ተማከሩ በራሳችሁ ኢማን ይኑራችሁ ሰለዚህ አላህን በጥሩ ነገር ለምኝሌላው አላፊ ጠፊ ነው

  • @elsabetmekuante1558
    @elsabetmekuante1558 Před 2 lety

    ዋው እኔም እንደዚህ አይነት የፍቅር ታሪክ ነበረኝ። እኔ የመረጥኩት ሃይማኖቴን ነው ። እና ተለያየን አሁን ሁለታችንም የየራሳችን ህይወት መሥረተናል ። ከሃይማኖት ሚበልጥ ምንም የለም ምክንያቱም ባል እና ምስት አንድ አካል አንድ አምሣል ናቸው ። እስከመቸ የየግል ሃይማኖታቹህን ትከተላላቹህ ? በፍጹም አይታሠብም ። ስለዚህ ቆም ብለው ማሰብ መልካም ነው ።

  • @tadelebanti9607
    @tadelebanti9607 Před 2 lety

    Selam selam programshi betam Arif new. Enam be fikir hiwote lay chigr silgetemgn letemelkachi bitakerblign.

  • @tsiyontesema7535
    @tsiyontesema7535 Před 2 lety

    በጣም ይገርማል ይሄ የኔም ታሪክ ነው በጣም ይጎዳል እኔ ኦርቶዶክስ እሱ የሌላ እምነት ተከታይ ከአንድ አመት ተኩል በላይ አብረን ነበር ምንም ፍቅር ቢኖረን እምነቴ ይበልጣል

  • @felegushfelegush3912
    @felegushfelegush3912 Před 2 lety

    ፌቭየ በጣም አሪፍ ንግግር ነው የተናገርሽው ቅድሚያ እምነት

  • @hibirework1494
    @hibirework1494 Před 2 lety

    እርግጠኛ ነኝ የሚከተሉት እምነት ከቤተሠብ የተወረሰና በልማድ የመጣ ከሆነ ሊግባቡ አይችሉም። ግን የዘላለምን ህይወት ለመውረስ መከተል ያለብን እንደእግዚአብሔር ቃል የቱ ነው ካሉ? ወደ አንድነት ይመጣሉ ያኔ አምነውና ገብቷቸው ስለሆነ ሐይማኖቱን የሚከተሉት ይግባባሉ ወደ አንድነትም ይመጣሉ ያሠቡትን ያሣካሉ። ችግሩ ሁሉም የያዘውን ሐይማኖት የኔ ብቻ ነው ልክ እያለ መድረቅ ብቻ። ይህ የሠዎች የአስተሣሠብና የአረዳድ ችግር እንጅ የመዳን መንገድ አንድ ብቻ ናት። ሲጀመር እምነት እንጅ ሐይማኖት አያድንም። ወደ ጠያቂዋ ኬብሮን ስመጣ በኔ ይሁንብሽ ተጋቡ እልሻለሁ። ልጆች ራሳቸው ወስነው በሚከተሉት እምነት እንጅ ወላጆቻቸው በመረጡላቸው ሐይማኖት መጓዝ የለባቸውም ባይ ነኝ። የሚፀድቁት ባመኑት እንጅ በታመነላቸው መንገድ አይደለም። በሆነ ሰርክል ውስጥ ከተናቸው ዋ! ከዚች ንቅንቅ ትልና እያልን በማስፈራራት ዘላለማቸውን መወሠን ራሱ ሀጢያት ነው። የማወቅና የመጠየቅ መብታቸው ከመሉ ነፃነት ጋር ቢሠጣቸው መልካም ነው እላለሁ ምክንያቱም የግል ህይወት ነዋ! እስኪ አስቡት እግዚአብሔር እንድንከተል የሚፈልገው እምነት የትኛው ነው? እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ሠው የራሱን ይጠቅሳል ግን በፍፁም ሊሆን አይችልም። በዓለም ላይ ትክክለኛዋ አንዲት እምነት ናት ታዲያ ይሔ ሁሉ የሐይማኖት ጥርቅም ምን ሊውጠው ነው? ውድ አድማጭ ተመልካቾቼ እስኪ ለማወቅ እንጣር። "ህዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል" አይደል የሚል ቃሉ። ለማወቅ ስንጥር እግዚአብሔርም ይረዳናል። ካወቅን እምነታችን አንድ ናት ሌላው የክፉው ነው። አይ ኬብሮን ብዙ አስወራሽኝ። አመሠግናለሁ

  • @liyagebretsadik
    @liyagebretsadik Před rokem

    የክርስቶስ ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል የፆታ ደግሞ እስክታገቢው ነው