የኔ ወደፊት | Yene Wedefit |Aster Seyfu | አስቴር ሰይፉ | Apostolic Church of Ethiopia | lyrics |

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 12. 09. 2023
  • መኖርን ብቻ አይደለም ምፈልገው
    ለአንተ ለክብርህ ሆኜ መኖርን
    ማደግን ብቻ አይደለም ምፈልገው
    ወደ አንተ ወደ ሙላትህ ማደግን
    እድሜን ብቻ አይደለም ምፈልገው
    በዘመኔ ላገለግል ሀሣብህን
    አደራ እንዳያልፍ ህይወቴ ሳላይ ክብርህን
    በዘመን ፍጻሜ መጨረሻው ላይ
    ያለሁ ትውልድ ነኝ እኔ ጌታ ሆይ
    አለም በክፋቷ ተሞልታ በርኵሰት
    ብዙዎችን ትስባለች ወደ ሞት ለጥፋት
    እኔ ግን አንተ እንደምትበልጥ አውቂያለሁ
    ከሁሉ በላይ ከሚታየው ከሚሰማው በአለም ካለው
    የምድሩን ክፋት ነፍሴ ጠልቶታል ላንተ መኖር ነው ምፈልገው
    የኔ ወደፊት አንተ ምትከብርበት
    የኔ ወደፊት ላንተ ምኖርበት
    1,ብዙዎችን አሸንፎ ሊያጠፋ ካንተ ያራቃቸውን
    እንድበልጠው ባንተ ፀጋ እንድረታው ሚታገለኝን
    ያንተ ፍቅር በኔ በርትቶ የክብር እቃ እንድሆንልህ
    ሆኜ እንድገኝ በዚህም ዘመን ደስ የማስኝህ እንደ ልብህ
    በብርታት አይደል ወይ በሃይል
    በመንፈስህ ግን ይቻላል
    ይውረድልኝ ላንተ ይለኝ
    ይውረድልኝ ለአላማህ ይለየኝ
    2,በልቤ ያለው ብዙ ነው ልሆንልህ ምፈልገው
    በዘመኔ እንድትጠቀም አስከብሬህ ማለፍ እሻለሁ
    እንቅፋትን ሁሉ እየወጣሁ ጥሼ
    በሁለንተናዬ አንተን ብቻ አንግሼ
    ልገለጥ በናፍቆት ለጠበቀኝ ፍጥረት
    በጨለማ ላሉት በሚያበራ ህይወት
    ሩጫዬን በፅድቅ በፅናት ጨርሼ
    አክሊልን ልቀበል ሀገሬ ደርሼ
    ድል ነስቼው ባንተ ይህንን ክፉ አለም
    በመንግስተሰማይ ማረፍ ለዘላለም
    በብርታት አይደል ወይ በሀይል ..
    #apostolicchurchofethiopia #ethiopia #lyrics #apostolicsongs #apostolicchurch #besntu #eregnaye
  • Zábava

Komentáře • 11