ካልቪኒዝም || "እግዚአብሔር የፈለገውን ማድረግ አይችልም" || የእግዚአብሔር ውሳኔ ወይስ የእኛ ድርሻ ||

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 20. 01. 2024
  • like, share and subscribe. ጌታ ይባርካችሁ!

Komentáře • 22

  • @user-rj3fz1nh6n
    @user-rj3fz1nh6n Před 6 měsíci +1

    Denk RNA clear temhert geta abzto yebarkot ❤❤❤

  • @yoa4954
    @yoa4954 Před 3 měsíci

    Pls we need in deepth more pls we need to know the truth ,
    May GOD bless You MKC

  • @mogesbalcha891
    @mogesbalcha891 Před 6 měsíci +2

    yoni tebarek.egziabher anten lebetekirstiyan silesete getan amesegnalehu.

  • @samsonadem
    @samsonadem Před 6 měsíci +2

    This is a great explanation. Thank you !!

  • @yoa4954
    @yoa4954 Před 3 měsíci +1

    I appreicate If Yoni have book on this subject..

  • @tadese1963
    @tadese1963 Před 6 měsíci +1

    Nice!

  • @mesybeshah7941
    @mesybeshah7941 Před 6 měsíci +1

    God bless u

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 Před 5 měsíci

    የእግዚአብሔር ልዓላዊ ምርጫና
    የሰው ነጻ ፈቃድ
    በድነት ዙሪያ ስለ የእግዚአብሔር ልዓላዊ ምርጫና ስለ ሰው ነጻ ፈቃድ የተጻፉትን በአግባቡ መረዳት ያስፈልጋል። ዛሬ ዛሬ አንዳንዶች ከሚገባ በላይ የሰው ነጻ ፈቃድ አኩስሰው የእግዚአብሔር ልዓላዊ ምርጫን ብቻ የሚያጎሉ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔር ልዓላዊ ምርጫን ገሸሽ አድርገው የሰው ነጻ ፈቃድ የሚያደምቁ ናቸው።
    የእግዚአብሔር ቃል ግን በተለያዩ ምንባቦች ሁለቱን ስለሚያወሳ "ዐውድ የትርጓሜ ንግሥት ናት" እንደሚባል ሚዛኑ ጠብቆና ቅደም ተከተሉ መሠረት አድርጎ ማየት ከተሳሳተ ድምዳሜ ሊታደግ ይችላል።
    በድነት ክንውን ቅደም ተከተል ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነው። ብዙዎች የድነት ቅደም ተከተል ባለማወቃቸው ወደ አንዱ ጽንፍ ሲያጋድሉ ይታያሉ። የድነት ቅደም ተከተል በላቲን (Ordo Salutis) የሚባል ሲሆን፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ (order of salvation) ይባላል። በድነት ሥራ ላይ ቀዳሚው እርምጃ የቱ ነው፣ ቀጥሎስ የቱ ይመጣል? የሚለው ጥያቄ በአግባቡ መዳሰስ ወሳኝ ነው።
    የድነት ሥራ ጠንሳሹ እግዚአብሔር በልዓላዊ ፈቃዱ እንጂ የሰው ምርጫ እንዳይደለ ከሚያሳዩ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች አንዱን ዛሬ ለማየት እንሞክራለን።
    እዚህ ላይለማሳየት የተፈለገው ድነትን ማን እንደ ጀመረውና ቀጥሎም ምን እንደ ተከተለ ለማሳየት እንጂ አንዱን አጉልቶ ሌላኛውን ለማኮስመን ከቶ አይደለም!
    "ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።" (ዮሐ 1:12-13)
    በቀዳሚው ቁጥር 12 ላይ ክርስቶስን ለተቀበሉትና በስሙም ላመኑት እግዚአብሔር የልጅነት መብት እንደ ሰጣቸው ይናገራል። ቁጥሩ የሰው ፈቃድን በግልጽ ያሳያል። ነገር ግን ቀጥሎ ያለው ቁጥር 13 "እነዚህም" ብሎ መጀመሩ ተቀብለውና ስሙን አምነው የእግዚአብሔር የልጅነት መብት እንዲያገኙ ያደረጋቸው ምክንያት ወይም ከዚህ በፊት ምን እንደተደረገላቸው ይገልጻል።
    ኢየሱስን ከመቀበላቸውና በስሙ አምነው የልጅነት መብት ከማግኘታው በፊት አንድ ወሳኝ መለኮታዊ ድርጊት ተካሄዷል። "እነዚህም" የተባሉት የተቀበሉትና በስሙ የሚያምኑት ሲሆኑ፣ የልጅነትመብትን ያገኙት ከእግዚአብሔር ስለ ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ በመወለዳቸው እንዳልሆነ ዮሐንስ ጽፏል።
    ስለዚህ ጌታን ተቀብለውና በስሙም አምነው የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት የተጎናጸፋት፣ ቀድመው ከእግዚአብሔር ስለ ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ በመወለዳቸው እንዳልሆነ ተጽፏል።
    ከዚህ ማጠቃለል የሚቻለው በድነት ቅደም ተከተል (order of salvation) ቀዳሚው ከእግዚአብሔር መወለድ ወይም ዳግም ልደት ቀጥሎ የሰው ፈቃድ እንደ ሆነ ነው። ማንም ከእግዚአብሔር ቀድሞ ሳይወለድ ክርስቶስን መቀበልና በስሙም ማመን አይችልም። ዳግም ልደት ወይም ከእግዚአብሔር መወለድ ሙሉ በሙሉ የመለኮት ሥራ እንጂ የሥጋና የደም ማለትም የሰው ድርሻ የለውም።

  • @Hero_8.
    @Hero_8. Před 3 měsíci

    ሮሜ 9 እንዴት እናየዋለን

  • @hagereemedia
    @hagereemedia Před 6 měsíci +1

    ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። የተረጋጋና ጥልቀት ያለው ትምህርት ነው። ብዙ ተደራሲያን ማግኘት አለባችሁ። አዘጋጁ ወንድም ከቻልክ መልስልኝ።

    • @dokimazotest4393
      @dokimazotest4393 Před 6 měsíci

      Thank you. Send me your mobile number . Yonas

    • @asalefewwolde6616
      @asalefewwolde6616 Před 6 měsíci +1

      አሜን ወንድሜ ስለሚያበረታቱ ቃላቶችህ ጌታ ይባርክህ🙏 ልታገኘን ትችላለህ

    • @hagereemedia
      @hagereemedia Před 6 měsíci +1

      ከቻልክ በፌስቡክ Shawel Betru ብለህ መልዕክት ላክልኝ። ጌታ ይባርክህ።

    • @ydidiabitsue4061
      @ydidiabitsue4061 Před 5 měsíci

      አዳም ከሕይወት ዛፍ ዳግም እንዳይበላ ወደ ዔደን ገነት እንዳይገባ ከከለከለው በኋላ ከዛፎቹ መርጠን ለመብላት ወደ ዔደን ገነት ለመግባት ተፈቅዶልናል ወይ?

    • @ydidiabitsue4061
      @ydidiabitsue4061 Před 5 měsíci

      መስማትና ማየት በድነት የሚኖራቸው ድርሻ
      በድነት ቀዳማይ ሥራ ላይ መስማትና ማየት ግዴታ እንደ ሆኑ ከሕያው ቃሉ ማረጋገጥ ይቻላል። እነዚህ ሁለት ቁልፍ ሁነቶች ከሰውና በሰው የሚመነጩ ቢሚስሉም ጠንሳሹ ልዑል አምላክ እንደ ሆነ ከሕያው ቃሉ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።
      መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ከመስማት እንደ ሆነና መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ፣ ለመስማትም ሰባኪ እንደሚያስፈልግ፣ ሰባኪው ከእግዚአብሔር መላክ እንዳለበት ይናገራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ወንጌልን ሰምተው ለማመን የሚሰብከውን ካልላከ ለመዳን የሚሰማ ነገር አይኖርም። በዚህ ቀዳሚውና ወሳኙ የማዳን ሥራ ሰባኪውን የሚልከው እግዚአብሔር እንደ ሆነ መረዳት ይቻላል።
      ሌላው( ኢሳ 6:9) ምን እንደሚል እንይ፦
      እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ “ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።"
      መስማትን እንደሚችሉ ነገር ግን እንደማያስተውሉ፣ ማየትም እንደሚያዩ ነገር ግን ልብ እንደማይሉ እግዚአብሔር በኢሳይያስ ሰምተው ስለማያስተውልትና አይተው ልብ ስለማይሉት በአጽንኦት ይናገራል።
      ምንም እንኳ እምነት በመስማት ቢሆንም፣ ሰምቶው ካላስተዋሉ ስለ ሰሙ ብቻ አያምኑም። እዚህ ላይ የሰሙትን እንዲያስተውሉ የማድረጉ ሥራ የመለኮት እንጂ የሰው አይደለም። የሊዲያ ልብ ወይም ማስተዋል የከፈተ እግዚአብሔር እንደ ሆነ እናስተውል።
      ሰው እያየ ልብ ላይልም ይችላል። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያለውን የሰው ልብ እግዚአብሔር "ብርሃን ይሁን!" ብሎ ካላዘዘ፣ ሰው ቢያይም ልብ ብሎ መመልከት አይችልም። ስለዚህ በቅድሚያ እግዚአብሔር በልዓላዊ ትዕዛዙ በልብ ውስጥ ተንሰራፍቶ የነበረውን ጨለማ ብርሃን ይሁን ብሎ ካላሸሸው ሰው በብርሃኑ ብርሃንን ማየት አይችልም።
      በእነዚህ በሦስቱ ማለትም፦
      1) ለመስማት ሰባኪውን መላክ 2) ሰምቶ ለማስተዋል ጀሮን መብሣትና 3) በብርሃኑ ብርሃንን እንዲያዩ በልብ ውስጥ ያለውን ድቅድቅ ጨለማ በብርሃን ማሸሽ የሰው አንዳች ድርሻ ሳይኖራቸው በመለኮት የሚከናወኑ ቁልፍና ቀዳሚ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገሮች ቸል ካልን በድነት ቅደም ተከተላዊ (order of salvation) አሠራር ላይ ተፋልሶ ሊያጋጥመን ይቻላል። ከመስማት ጋር የሚቆራኘው ጀሮን የመብሳት ስእላዊ አገላለጽ ማስተዋልን የሚያሳይ እንደ ሆነና ጀሮን የሚበሳው ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።

  • @GligleBelesMkC
    @GligleBelesMkC Před 6 měsíci +1

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ እጀግ በጣም ጥሩ ለእንደዚህ ምላሽ አስፈላጊ ትምህርቶች ምላሽ መስጠት እንድሁም መጮህ ያለበትን በበቂ መልኩ ማጮህ አስፈላጊ ነው አሁንም ዝም አንበል ክብሩ ለእግዚአብሔር ይሁን

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 Před 5 měsíci

    "ሁሉም ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ፣ ኀሳብህ አይከለከልም" በማለት ኢዮብ የተናገረውስ እንጣለውን?

  • @lemma4223
    @lemma4223 Před 6 měsíci

    ዮኒ መቼም ለክርስትና አስተምህሮ ያለህን ምረዳት እና ምካታዊ አቋምህን እጅግ የማደንቀው ነው:: ተባረኩ ጅምሩ መልካም ነው በርቱ!
    ነገር ግን እየተነሳ ባለው የካልቪን እና አርመንን አስተምህሮ በተመለከተ መውጫ ወደሌለው ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ የሚያስገባ ነው :: ከዚህ ይልቅ ቤተክርስቲያናችን የምታምነውን መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ላይ ብናተኩር ህዝባችን እውነቱን በቅጡ ሲረዳ ሌላውን እራሱ መዝኖ ይተወዋል::

    • @solomongezachew
      @solomongezachew Před 6 měsíci

      ወንድሜ ለማ ሰላም ለአንተ ይሁን! ሀሳብህን ብረዳውም እኛ ጉንጭ አልፋ ነው ብለን የተውነውን ሌሎች በተለያየ መስክ ሌላኛውን ጽንፍ ከማራገባቸው የተነሳ፤ ወጣቶቻችን እና በቤተክርስቲያን ያሉ መሪዎች እንኩዋን ካልቪናዊውን አስተምህሮ የመሰረተ ክርስቶስ አስተምህሮ መስሎአቸው የከራከሩለታል ስለዚህ ዝም ብሎ ባላየ ማለፍ ተገቢ ስላልሆነ ነው። የምንቃወመው ለምን እንደሆነ በተገቢ መንገድ ማሳየት መቻል ጥሩ መሪነት ነው።

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 Před 5 měsíci

    አዘጋጁ የምናቀርበው ምልከታ እንዳሻህ ስለማስተላልፍ ተወቃሽ ነህ፣ ለእርምት ተዘጋጅ!