ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 1 / Saint Moses the Black Part - 1

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 29. 08. 2024
  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን
    ​​ታላቁ አባት አቡነ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ተጋድሎአቸውን የፈጸሙት ግን በግብፅ ነው፡፡
    መጀመሪያ ላይ እንደ አብርሃም በየዋህ ልቡና ሆነው ስነ ፍጥረትን በመመራመር
    እግዚአብሔር አምላካቸውን ያገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ወላጆቻቸው ፀሐይ
    ያመልኩ ስለነበር ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአት በሠሩ ቁጥር ‹‹ተው አምላካችን
    ፀሐይ ይጣላሃል›› ይሏቸው ነበር፡፡ እሳቸው ግን ባደጉ ጊዜ ቀማኛ ዘራፊ ሆኑ፡፡
    እየዘረፉ ብዙ ይመገቡ ስለነበር ከትልቅነታቸውና ኃይለኛነታቸው የተነሳ ‹‹በገ
    ፈጅ›› እየተባሉም ይጠሩ ነበር፡፡
    ብዙ ወርቅ ከባለ ሀብቶች ሰብስባ ለነዳያንና ለቤተክርስቲያን ልትሰጥ ትሄድ
    የነበረችን አንዲት ክርስቲስቲያን ሴት ልጅ ሙሴና ግብረ አበሮቻቸው ለወርቁ
    ሲሉ እርሷንም ማርከው ወሰዷት፡፡ ማታ ላይ ስለ ውበቷ ሲያወሩ እርሷ ግን
    ‹‹ስምህ ማን ነው?›› ስትላቸው ‹‹ሙሴ ነኝ›› ቢሏት ‹‹ይሄ ስምኮ እጅግ የተባረከ
    ስም ነው….›› ብላ ስለ ሊቀ ነቢያት ሙሴና ስለ ክርስቶስ አስረዳቻቸው፡፡ ከዚህ
    በኋላ በወላጆቻቸው ስለ ፀሐይ አምላክነት ሲነገራቸው ያደጉትን ነገር
    መመርመር ጀመሩ፡፡ ‹‹ፀሐይ አምላክ ከሆነ እስከዛሬ ድረስ ሽፍታና ዘራፊ ሆኜ
    ሰው ስገድልና ይህን ሁሉ ኃጢአት ስሠራ እንዴት ፀሐይ ሳታቃጥለኝ ቀረች?
    ደግሞም ፀሐይ ጠዋት ወጥታ ማታ ትጠልቃለች ይህችስ እንዴት አስገኚ
    ልትሆን ትችላለች ለራሷ አስገኚ አላት እንጂ…›› በማለት ፀሐይን፣ ጨረቃን፣
    እሳትን፣ ነፋስን በየተራ አምላክ መሆናቸውን አለመሆናቸውን በሚገባ ከፈተኑና
    ከመረመሩ በኋላ ‹‹የፀሐይ የጨረቃ የሁሉ አስገኚ አምላክ ተናገረኝ›› ብለው
    ሲጸልዩ ከሰማይ ድምፅ መጥቶላቸው ወደ ገዳም ሄደው ከአባቶች ትምህርተ
    ሃይማኖትን እንዲማሩ ተነገራቸውና ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄደው መምህር
    ኤስድሮስ ሁሉንም ነገር አስተምረው ለማዕረገ ምንኩስና አበቋቸው፡፡
    መጀመሪያ ወደ ገዳሙ ሲሄዱም ይዘርፉበትና ይቀሙበት የነበረውን ስለታም
    መሣርያ እንደያዙ ስለነበር ያዩአቸው መነኮሳት ሁሉ ‹‹ሊገድለን መጣ›› ነበር
    ያሉት፡፡ ከዚህም በኋላ ለመነኮሳቱ ሁሉ የሚላላኩ ሆኑ፡፡ ትንሹም ትልቁም ‹‹ሙሴ
    ይህን አድርግልኝ›› ይሉታል እርሱም ሁሉንም እሺ ይላል፡፡ ራሱን በትሕትና ዝቅ
    በማድረግ በተጋድሎ እየኖረ ተአምራትን ማድረግ ጀመረ፡፡ በጸሎቱ ዝናብ ያዘንብ
    ነበር፤ ለቅድስና ደረጃ ከበቁም በኋላ 40 ዓመት ሙሉ ከሰው ሳይገናኙ ብቻቸውን
    ዘግተው ከኖሩ በኋላ ለ500 መነኮሳት አበምኔት ሆነው ተሾሙ፡፡ ቀን ወንጌል
    ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት እየተነሱ ከበረሃ ሄደው ለሁሉም መነኮሳት ውኃ
    ይቀዱላቸው ነበር፡፡ አገልግሎታቸው የታይታ እንዳይሆንባቸው አረጋውያን
    መነኮሳት መተኛታቸውን ካረጋገጡ በኋላ የግብፅ በረሃን አቋርጠው ከሩቅ ሥፍራ
    ሄደው ውኃ እየቀዱ መነኮሳቱ ሳያዩአቸው በየደጃፋቸው ላይ ያስቀምጡላቸው
    ነበር፡፡
    ብዙ መነኮሳትም ወደ አቡነ ሙሴ እየመጡ የሕይወትን ትምህርት ይማሩ ነበር፡፡
    በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ ሙሴን ‹‹አንድን አገልጋይ ባጠፋው ጥፋት
    የተነሣ ጌታው መታው፡፡ አገልጋዩ ምን ማለት አለበት?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ አባ
    ሙሴም ‹‹አገልጋዩ ብፁዕ ከሆነ፣ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማለት አለበት››
    አሉት፡፡ ‹‹ሌላ አይጠበቅበትምን?›› ሲል ያ ወንድም ጠየቃቸው፡፡
    ‹‹አይጠበቅበትም፣ ለጊዜው ለጥፋቱ ኃላፊነቱን ወስዶ አጥፍቻለሁ ካለ ጌታው
    ይቅር ይለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ዓለማው በባልንጀራ ላይ ላለመፍረድ ነው፡፡ በእውነቱ
    ጌታችን የግብፅን በኩራት ሁሉ ሲመታ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት
    አልነበረም›› ብለው መለሱለት፡፡ ያም ወንድም ‹‹ምን ማለት ነው?›› አላቸው፡፡
    እሳቸውም ‹‹ሁላችንም የየራሳችንን ጥፋቶች ካየን የባልንጀራችንን ለማየት ዕድል
    አንሰጥም፡፡ በራሱ ቤት ሰው የሞተበት በጐረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይሄድም፡፡
    ለባልንጀራ መሞት ማለት ለራስ ጥፋት ትኩረት በመስጠት፣ የሌላውን ጥፋት
    ከቁም ነገር አለመቁጠር ነው፡፡ ማንንም አትጉዳ፣ በማንም ላይ ክፉ አታስብ፣
    ክፉ የሚሠራውን ሰው አትናቀው፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ በሚሠራ ሰው ላይ
    አትተማመን፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ ከሚሠራ ሰው ጋር አትደሰት፣ ለባልንጀራ
    መዋቲ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ አትማረር፣ ነገር ግን ሁሉንም
    እግዚአብሔር ያውቃል በል፡፡ ከሚያማ ሰው ጋር አትተባበር፣ በሐሜቱም
    አትደሰት፣ ወንድሙን የሚያማውን ሰውም አትጸየፈው፡፡ አትፍረድ ማለት ትርጉሙ
    ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ የጥላቻ ሀሳብ አይኑርህ፣ ጥላቻ ልብህን
    እንዲያሸንፈውም አትፍቀድለት፡፡ ባልንጀራውን የሚጠላውን አትጥላው፣ ሰላም
    ማግኘት ማለት ይህ ነው…›› ብለው መከሩት፡፡
    በዕድሜአቸው መጨረሻ አካባቢ ቡራኬ ለመቀበል ከመነኮሳት ደቀ
    መዛሙርቶቻቸው ጋር ወደ አባ መቃርስ ሄዱ፡፡ አባ መቃርስም ‹‹ልጆቼ ከናንተ
    መካከል በሰማዕትነት የሚሞት›› አለ ብለው ትንቢት ሲናገሩ ሙሴ ጸሊምም
    ‹‹አባቴ ያ ሰው እኔ ነኝ፣ ‹ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ› የሚል ቃል አለ፡፡
    ይህን ጊዜ በጉጉት ስጠባበቀው ነበር›› አላቸው፡፡ እንደተባለውም የበርበር ሰዎች
    ገዳሙን ዘርፈው መነኮሳቱን ሊገድሉ ሲመጡ ደቀመዛሙርቶቻቸው ‹‹ሸሽተን
    እናምልጥ›› ሲሏቸው አቡነ ሙሴ ግን ‹‹በጎልማሳነቴ ጊዜ ደም አፍስሼያለሁና
    አሁን የእኔም ደም ሊፈስ ይገባል›› በማለት ራሳቸውን ለመሰየፍ አዘጋጅተው
    ጠበቋቸውና በርበሮች ሰኔ 24 ቀን አንገታቸውን በሰይፍ ቆርጠዋቸዋል፡፡
    ፈርተውና ሸሽተው የነበሩት ደቀመዛሙርቶቻቸውም ተመልሰው አብረዋቸው
    ተሰይፈዋል፡፡
    የአባታችን የሙሴ ጸሊም ቅዱስ ሥጋቸው በገዳመ አስቄጥስ በክብር ይገኛል፡፡
    ግብፆች አቡነ ሙሴ ጸሊምን በእጅጉ ያከብሯቸዋል፡፡ በስማቸው ጽላት ቀርጸው
    ቤተክርስቲያን ሠርተው ሥዕላቸውን አሠርተው ገድላቸውን ጽፈው
    በስንክሳራቸው መዝግበው የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በደማቅ ሁኔታ ነው
    የሚያከብሩት፡፡ የአቡነ ሙሴ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው
    ይማረን፡፡ ኣሜን

Komentáře • 305

  • @user-vi4fz3di7c
    @user-vi4fz3di7c Před měsícem +1

    የቅዱስ ሙሴን ልብ የቀየረ እግዚአብሔር የኛንም ልብ ይቀይርልን ህብረታችን ከቅዱሳን ጋር ይሆን ዘንድ ፍቃዱ ይሁንልን የቅዱስ ሙሴ በረከት ረደኤት ይደርብን አሜን

  • @user-br8cz9kz2g
    @user-br8cz9kz2g Před měsícem

    የቅዱስ።አባታችን በረከቱ ይደርብን

  • @user-hm6mw7bb1l
    @user-hm6mw7bb1l Před 5 lety +50

    የቅዱስ ሙሴ ጸሊም በረከት ረዲኤቱ ይደርብን አሜን ቅዱስ እግዚአብሔር እድሜ ለንስሐ ይጨምርልን አሜን

  • @user-rt8ju3yx5o
    @user-rt8ju3yx5o Před 2 měsíci +1

    እንደ ሙሴ ፀሊም መጨረሻችንን አሳምረው

  • @MusmanMeo
    @MusmanMeo Před měsícem

    አምላኬ ሆይ እባክህ የኔንንም ልብ መልሰልኛ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

  • @user-rt8bz9pv1z
    @user-rt8bz9pv1z Před 2 měsíci

    አሜን አሜን አሜን አሜን❤🎉❤🎉❤🎉❤እልልልልልልል❤🎉❤🎉❤🎉❤🎉

  • @helenhelen349
    @helenhelen349 Před rokem +3

    እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ፅጋውን ያብዛላችህ አሜን የቅዱሳን የቅዱስ ሙሴ ጺለም እረዴት በረከታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብን አሜንብ አቤቱ አምላኬ ሆይ እዝነ ልቦናየን ክፈትልኝ💠💠💠

  • @user-jc1tm1jl8r
    @user-jc1tm1jl8r Před 5 lety +140

    በእዉነቱ ፀጋዉን ያብዛላችሁ እመብርሃን ታበርታችሁ አሜን የቅዱሳንን ታሪክ ለእኛ ማቅረብ በጣም ትልቅ በረከት ነው

    • @samer8063
      @samer8063 Před 4 lety +4

      አቤቱ አምላኬ ሆይ የቅዱሱ አባታችን ሙሴ መጨረሻው ያሳመርክ አምላክ ሃጥያቴ በደሌ ነውሬ ሳትመለከት የኔ ነብስ ከስምህ ከቤትህ ነብሴ አትለያት በረከታቸው ረዲኤታቸው በኛ በህዝበ ክርስትያኖች በአገራችን ኢትየጲያ ላይ ይሁን በኡነት የግብፅ ኦርቶዶክስች እግዝአብሔር ያበርታቸው

  • @tigistashuma6088
    @tigistashuma6088 Před 8 měsíci +1

    እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የፃድቃን፣የሰማይታት፣በረከታቸው፣ይደርብን፣፣ቃለሂወት፣ያሰማልን፣ተስፍ፣መንግስትን፣ያዋርስልን፣የአገልግሎት፣ዘመናችሁን፣ይባርክልን፣በእድሜ፣በጤናው፣ያኑርልን፣አይነልቦናችንን፣ያብራልንአሜን፣አሜን፣አሜን

  • @abcdefghhjklmnopabcdefghjk1255

    የቅዱሱ ሙሴ ፀሊሙ በረከትና ምልጃ በእኛ ላይ ይደርብን አምላኬ ሆይ አብዝቼ ልውደድህ

  • @abebahiluf459
    @abebahiluf459 Před rokem +1

    አባታችን በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁንልን ይደረግልን አሜን አምን አሜን
    ብዝ ነግር ለፍታቹ ለምታቀርቡልን አባቶቻችን ወንድሞቻች እናቶቻችን እህቶቻችን እግዚአብሔር ጻጋውን ያብዛላቹ

  • @meseret3674
    @meseret3674 Před 5 lety +49

    አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን የኛንም እዲው የቆሸሽው ህይወታችን በቀናው መንገድህ ምራን 😭😭😭

  • @abebaembiale3452
    @abebaembiale3452 Před rokem +1

    Berktachewu yderibine❤❤❤❤❤

  • @GugGg-sr5pe
    @GugGg-sr5pe Před 5 měsíci +9

    አባቶቻችን በረከታቸዉ ይደርብን የኛንም እዲዉ የቆሸሽ ህይወታችን በቀናዉ መንገድ ምራን😭😭😭😭😭😭😭

  • @user-dx3kl4ph2d
    @user-dx3kl4ph2d Před 3 lety +3

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን ሙሴ ፀሊም በረከታቸውን እና ርዲኤት አይለየን ልቢ ልድያ የከፈተ አምላክ ልባችን ይክፈትልን አሜን አሜን አሜን

  • @user-sc6pf7mu4p
    @user-sc6pf7mu4p Před rokem +1

    ተመስገን አምላኪ ለኛም ለሀጢታኞቺ ልጆች በንፁልባችን ወዳታ እዲንመለስ እርዳን

  • @tcxjhvc2190
    @tcxjhvc2190 Před 6 měsíci +2

    የሙሴን ልብ የቀየርህ ክርስቶስ ሆይ ይኔንም ልብ እባክህን ለውጠኚ 😊😊😊😊

  • @user-ck4uk9km5i
    @user-ck4uk9km5i Před 5 měsíci +5

    በእውነት ፀጋውን ያብዛላችው እመ ብርሃን ታብርታችው የቅዱስንን ታሪክ ለእኛ ማቅረብ በጣም ትልቅ በረከት ነው የልድያ ልቦና የከፈተ ለእንየ ኃጥያተኛው ልጅህን ልቦናየ ክፈትልኝ 😢😢😢😢

  • @user-om9sj8ys4q
    @user-om9sj8ys4q Před rokem +3

    በእዉነት ፀጋዉን ያብዛላችሁ እመብርሀን ታብርታችሁ የቅዱሰ ሙሴ ብርከት ይደርባችሁ አሜንንንንን

  • @adisadisorthodoxtewahedo4524

    የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን

  • @behafetabehafeta5376
    @behafetabehafeta5376 Před rokem +2

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ቃለበረከትን ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን

  • @TheKf320
    @TheKf320 Před rokem +5

    ቃለ ሕይወት ያጽምእ ለነ አሜን✝️✝️✝️

  • @HappyEagle-xo4bh
    @HappyEagle-xo4bh Před 4 měsíci

    ቃለ ህይዎት ያሰማልን

  • @HelenHelu-l1s
    @HelenHelu-l1s Před 23 dny

    Amen amenkale hywet yasemaln amen

  • @yayshmazengya7812
    @yayshmazengya7812 Před 5 lety +6

    የቅዱሳን በርከት ይደርብን

  • @umarahmed2862
    @umarahmed2862 Před 5 lety +29

    እውነተንኛውን መንገድ የመራህ እግዚአብሄር ይመስገን አሜን

    • @mesitubehulugeb88
      @mesitubehulugeb88 Před 3 lety +5

      አቤቱ ጌታ ሆይ የሙሴን ልብ የመለስክ እኛንም የንስሀ እንባ ስጠን
      ይቅር ባይ ቸር እርሁሩህ አምላካችን የተመሠገነ የተከበር ከፍ ከፍ ያለ ይሁን

    • @igzabrehifikrnew2143
      @igzabrehifikrnew2143 Před 3 lety +1

      አሜን አሜን አሜን

  • @topiyadejene1117
    @topiyadejene1117 Před 5 lety +5

    Amen Amen Amen Kale hiwot Yasemalen

  • @beletubeletu3155
    @beletubeletu3155 Před 5 lety +6

    አሜንአሜንአሜን

  • @user-hx3dd4xt5m
    @user-hx3dd4xt5m Před 5 lety +13

    በእውነት ፀጋውን ያብዛላችሁ

  • @yordanosteshome3910
    @yordanosteshome3910 Před 5 lety +5

    አሜን አሜን አሜን

  • @soretigosa6088
    @soretigosa6088 Před rokem

    bewunet egzabiber enegni abatochachen ebarkachewu yenesun tsega yalabesen

  • @Natinati-up7gf
    @Natinati-up7gf Před 3 měsíci

    የቅዱሳን ንበርከትይደርብን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ለንሰሀያብቃን❤❤

  • @yeshehtio5101
    @yeshehtio5101 Před 3 lety +6

    አምላኬ ሆይ እባክህ የኔንም ልብ መልሰልኛ😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @maretegeng3172
    @maretegeng3172 Před 5 lety +9

    Amen amen amen kalehiwot yasemalen yeqedusan bereket begnalayi yiderben kefel 2leqequlen👏👏👏👏👏🥀🥀🥀🥀

  • @Meysawkassa19
    @Meysawkassa19 Před 10 měsíci +1

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  • @user-gk4oz2dr3j
    @user-gk4oz2dr3j Před 3 lety +2

    እግዚአብሔር ማር ነው አልፎም ፍቅር ነው♥♥♥♥

  • @satsshdjs4340
    @satsshdjs4340 Před rokem +1

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወትን ያሠማልን

  • @user-ph8rl9yn2s
    @user-ph8rl9yn2s Před 5 měsíci

    😢😢😢😢በረከታቸዉ.እረዲታቸዉ.የአባታችንየደረበን😢😢😢😢😢

  • @user-wv2qd9lp4f
    @user-wv2qd9lp4f Před 3 lety +5

    የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፫ አቤቱ አምላኬ ሆይ የኛንም አይነ ልቦናችንን ይግለፅልን አምላኬ ሆይ የእውነት ክርስቲያን አዲርገኝ ልንስሀ ሞት አብቃን አምላ ኬ ሆይ 😭😭😭😭😭😭😭

  • @user-jc5xu2vg5x
    @user-jc5xu2vg5x Před 11 měsíci

    የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸዉ አይለየን

  • @user-um6ys9cr3t
    @user-um6ys9cr3t Před 5 lety +21

    ተመሥገን አምላኬ ዛሬም የጠፉትን መንገድህን አሣያቸው ወደ ቤትህ መልሣቸው አሜን ፫

  • @zewduaddisu7966
    @zewduaddisu7966 Před 8 měsíci

    አሜን + አሜን + አሜን + እግዚአብሔር ይመስገን አመላኬ ተመስገን ፈጣሪ አሜን አባታችን ሙሴ 🙏🤲🌹📚🌹🤲🌹📚🌹🤲🇪🇹🤲🌹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🅰️🙏

  • @user-hw3ue5xn1n
    @user-hw3ue5xn1n Před 7 měsíci +1

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወትን ያሰማልን

  • @user-uf5fz9nx8s
    @user-uf5fz9nx8s Před 5 lety +9

    የቅድሳኑ በረከት ይደርብን

  • @user-ts6qd7xn3t
    @user-ts6qd7xn3t Před 3 lety +2

    የቅዱስ ጸሊምና የነ ቅዱስ መቃርስ የአባቶቻችን በረከት ይደርብን እኛንም ከዚህ ከቆሸሸ ህይወታችን አዉቶ ወደ ትክክለኛው መንገድህ ምራን አምላክ ሆይ ለንሳሀ አብቃኝ በሐጢያት የረከስኩና ያደፍኩ ነኝና 😭😭😭😭😭😭

  • @seninegiyetewahdotemari5381

    የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን ፫

  • @user-ls9sp9bx5f
    @user-ls9sp9bx5f Před 5 lety +49

    ለኔም ለንሳአ ያብቃን ቀና መንገዳች ይምራን ከአዛብ አገረ ያውጣን ድሮ የሌለ ስደት አውን ያመጣነው ጉዞ ይቁም ሁላችንም ለሀይማኖታችን ንኑር ሁላችንም ማወቅ የሚገባን ገንዘብ ምድራውይ ነው ለንሳሀ ንመለስ

    • @gfftggt6311
      @gfftggt6311 Před 3 lety +3

      እውነትሽ ነው እማየ ስደት ይብቃ ስደት መረረኝ

    • @user-cw4co7ct7s
      @user-cw4co7ct7s Před 3 lety +1

      እግዝ አብሔር አምላክ ለሁም ፍጥረት አርአያስለሴ ልቦና ይውረድ እግዝ አብሔር አምላክ ምሕረት ይውርድ

    • @user-ly7vt4mx7o
      @user-ly7vt4mx7o Před 3 lety

      ለሁላችንም ያብቃን

    • @astertube8785
      @astertube8785 Před 3 lety

      አሜን አሜን አሜን

    • @tcxjhvc2190
      @tcxjhvc2190 Před 6 měsíci

      አሜን አሜን አሜን ለሁላችን ሀሳባችንን አሳክቶልን በአገራችን ሆነን ንስሐ ገብተን እሱ የምናመሰግንባትን ቀን ያቅርብልን❤❤❤❤❤

  • @hadasberhe4812
    @hadasberhe4812 Před 5 lety +8

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

  • @enatmesfin
    @enatmesfin Před 5 lety +10

    ቃል ሕይወት ያሰማልን አመሰግናለሁ:: ሁላችንንም በንሰሐ ያብቃን ሀጢአታችንን በደላችንን ይቅር ይበለን።

  • @user-ou2ho1vb3b
    @user-ou2ho1vb3b Před 5 lety +9

    *ቃለህይወትን ያሰማልን*

  • @user-uf3is3nu4u
    @user-uf3is3nu4u Před 3 lety +2

    አሜን አሜን አሜን የቅዱስ አባሙሴ ፀሊም በረከቱ አማላጂነቱ አይለየን

  • @user-dj4cq6up6j
    @user-dj4cq6up6j Před 4 lety +8

    😭😭😭እግዚአብሔር ሆይ እኔ ሀጢትኛዋን ልጀክን መልሰኝ 😭😭የሙሴ ልብ ግን ከእኔ ልብ እጀግ የዋህ ነው እኔ ግን ጠማማ ነኝ 😭😭እግዚአብሔር ሆይ መልሰኝ አንተ አምላኬ ነህና

  • @hanagosaye8136
    @hanagosaye8136 Před 3 lety +1

    ቸሩ መድሀኒአለም ሁላችንንም ወደ እሱ ይሰብስበን እኛ ሀፂያተኞች ነንና

  • @user-dr5xe1il2o
    @user-dr5xe1il2o Před 2 lety +11

    አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ የኛን የቆሸሸ ማንነታችን አንፃን😭😭😭😭😭😭የቅዱሳን አባቶቻችንን በረት ያሳድርብን🤲🤲🤲

  • @user-ls9sp9bx5f
    @user-ls9sp9bx5f Před 5 lety +9

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @asefumesele7875
    @asefumesele7875 Před rokem

    Amen Amen Amen

  • @sibihettube7340
    @sibihettube7340 Před 5 lety +30

    ቃለ ህይዎት ያሰማልን እናመሰግናለን የቅዱሳን ታሪክ ለኛ በተለይ ለወጣቶች በጣም አስፈላጊ ነው የበለጠ እንድትሰሩ እግዚአብሔር ይርዳቹ ለመስራትም ጣሩ

  • @user-wu4kv3eu1c
    @user-wu4kv3eu1c Před 5 lety +6

    የ ቅዱሳኑ በረከት እረዴት ይድረሰን የ ህይወትን ቃል ያሠማልንም
    አሜን አሜን አሜን🇨🇬🇨🇬🇨🇬

  • @user-bl4ej9nq7j
    @user-bl4ej9nq7j Před 5 lety +2

    ኣሜንንንን
    ኣሜንንንንን
    ኣሜንንንንንን ቃለ ሂወት ያሰማልን የኣባታችን የኣባ ሙሴ ፀሊም በረከት ረዲኤት ያሳድርብን

  • @mulu4327
    @mulu4327 Před měsícem

    Amen amen amen 🙏

  • @zeroxoxo1281
    @zeroxoxo1281 Před 5 lety +5

    amen amen amen

  • @AsefuGirmay
    @AsefuGirmay Před 26 dny

    ❤❤አሜንአሜንአሜን❤❤❤

  • @letagetahun9828
    @letagetahun9828 Před 8 dny

    Waaqayoo sagalee jireenya isin haa dhageesisuu

  • @aleminykgojamoneloveethio4654

    Amen Amen Amen Egezehbeher ymsagin La.zalalem

  • @kibrealemye8319
    @kibrealemye8319 Před 5 lety +2

    እደምወዳችሁ ውደዱኚ አባቶች በረከታችሁ ይደርብን ይህንን መንፈሳውይ ፊልም በአምላክ እረዳትነት የተወናችሁልን አባቶችና እህት ወድሞቻችን ልኡል እግዚያብሔር እረዢም እድሜና ጤናን ይስጥልን ያገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክልን ሁሌ ባይው ዩማይጠገብ ኤለመተሪ ፍልምናው የቅዱሳኖችንና የሰማእታትን መንፈሳዊይ ፍልም አዘጋጅታችሁ ለምትመግቡን እቁ የአምላክ ምርጥ አገልጋዮች አገልግሎታችሁን ይባርክልን አምላከ እስራኤል

  • @user-uq3hk5pk5v
    @user-uq3hk5pk5v Před 5 lety +6

    ቃለ ህይወትን ያሠማልን የአገልግሎት ዘመንክን ያብዛልን ይባርክልን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን ፍፃሜክን ያሳምርልን።እናመሠግናለን

  • @user-rw8vz7eq6q
    @user-rw8vz7eq6q Před 5 lety +18

    በእውነት ቃለ ህይወት ያስማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ የቅዱሳን በረከት ይድረሰን አሜን አሜን አሜን 👏🙏

    • @Warqitu-xv5ye
      @Warqitu-xv5ye Před rokem

      9L❤PPP😊

    • @Warqitu-xv5ye
      @Warqitu-xv5ye Před rokem

      9L❤PPP😊

    • @mnlj3105
      @mnlj3105 Před 11 měsíci

      አሜን አሜን አሜንንንንንንንን

    • @user-hw3ue5xn1n
      @user-hw3ue5xn1n Před 7 měsíci

      እግዚአብሔር አምላክ ያብርታቹሁ በርቱ❤❤❤❤❤❤የቅዱስ ሙሴ በርከቱ ረደቱ ይደርብን አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-tz1hf4dl4j
    @user-tz1hf4dl4j Před rokem +1

    እንኩዋን ለሙሜ ፀሊም አመታዊ በአል አደረሰን
    በረከቱ ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን አሜን አሜን አሜን

  • @sarasas1420
    @sarasas1420 Před 11 měsíci

    በጣም ደስ ይላል❤❤

  • @kgtube-nb2bl
    @kgtube-nb2bl Před 5 lety +10

    በእውነት ቃል ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛላችሁ ይሄን እንድናይና እንድንሰማ ላደርገን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን አሜን

  • @youtobe8685
    @youtobe8685 Před 3 lety +2

    ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር ወድማችን ኑርልን

  • @Ggg-vs1iy
    @Ggg-vs1iy Před 3 měsíci +1

    አሜን የቅዱስ ሙሴ ና እድሁም የሁላቸውም መነኮሳት ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን💐💚💚💛💛❤❤👏🙏🙏

  • @tcxjhvc2190
    @tcxjhvc2190 Před 6 měsíci

    ከዚህ ቤት ቻናል ብዙ እየተማርኩ ነው ፍፁም ባይምለስም ልቤ ግን አምናለሁ አድቀን እግዚአብሔርን ታመሰግናለች ነፍሴይሄን የምታቀርቡ ሁሉ እግዚአብሔር ያስባችሁ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @mihretyeamarulij2648
    @mihretyeamarulij2648 Před 4 lety +3

    በእውነት የአባታችን በርከቱ ይደርብን
    እናመሰግናለን

  • @burtukanfayisa3891
    @burtukanfayisa3891 Před rokem

    Egzaber yohe Maren🤲🤲🤲

  • @teduadaayal2841
    @teduadaayal2841 Před 3 lety +2

    የቅዱሳን በረከት ይድረሰን 🙏🙏🙏🙏🙏

  • @donaytroyal860
    @donaytroyal860 Před rokem +1

    ቃለህይወትን ያሰማል❤

  • @GgHh-qn4qg
    @GgHh-qn4qg Před 2 měsíci

    የቅዱሥ ሙሤ ፀጋው በረከቱ ይደርብን አሜን እኛንም ለንሥሀ ሞት ያብቃን

  • @user-cm5gv9yn2p
    @user-cm5gv9yn2p Před 2 lety +1

    በእውነት ፀጋውን ያብዛላችሁ
    የቅድስ ሙሴ በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @Em1mengste
    @Em1mengste Před rokem

    አቤቱ አምላከ ሙሴ እኔን ሀጢያተኛና ቆሻዋን ልጅህን አቤቱ ማረኝ😢😢😢የአባታችን የቅዱስ ሙሴ ፀሊም በረከትና ረድኤት ይደርብን በእውነት አሜን😢😢

  • @saragasa174
    @saragasa174 Před rokem +1

    AMN AMN AMN ❤️ ♥️

  • @esubalewkassie3331
    @esubalewkassie3331 Před rokem

    በጣም ጀግኖች

  • @user-yj3ei7xh9g
    @user-yj3ei7xh9g Před rokem +1

    አሜን

  • @helenhelen349
    @helenhelen349 Před rokem

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን አቤቱ አምላኬ ሆይ እኔን ሀፂጢተኛ በደለኛ ባሪያህን ማረኝ
    አቤቱ ጌታየ ሆይ ሀፂጢተ. እደሰማይ ከዋክብት እድ ምድር አሸዋ በዝቱል እጥፍም ነው አቤቱ ማርኝ
    አቤቱ አምላኬ ሆይ ማረኝ
    አቤቱ ጌታየ ሆይ ማረኝ
    አቤቱ ኤልሻዳይ ሆይ ማረኝ
    አቤቱ እየሱስ ሆይ ማረኝ
    አቤቱ አማኔኤል ሆይ ማረኝ
    አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ
    አቤቱ አዶናይ ሆይ ማረኝ ስለናትህ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ማረኝ😭😭😭😭

  • @mahimahi3467
    @mahimahi3467 Před 3 lety +1

    የአባታችን የቅዱስ ፀሊሙ ሙሴ እረድኤት በረከት ይደርብን አቤቱ ጌታ ሆይ ልቦናችንን መልሰው

  • @jemayenshreta8146
    @jemayenshreta8146 Před 8 měsíci

    ቃለሂወት ያሰማልን የፃዲቁ የሙሴ ፀሊም በረከት ከኛ አይለየን አሜን!!

  • @hanagosaye2992
    @hanagosaye2992 Před rokem

    የአባታችንሰ የሙሴ ፀሊምን ልብ የከፈትክ አባት የኔንም የሀፂያተኛዋን ልብ ከፍተህ ለንስሀ አብቃኝ ቸሩ መድሀኒአለም 🙏🙏🙏

  • @EtIeri-df9wk
    @EtIeri-df9wk Před 28 dny

    በረከታቹ ይደረብን አቦታቸ❤❤❤❤

  • @user-yy4gb7im3k
    @user-yy4gb7im3k Před 2 lety +2

    የእባቶቻችንፀጋና በርከታችው ይደርብን ኣሜን ኣሜን ኣሜን

  • @Jennifer-uo4lr
    @Jennifer-uo4lr Před 27 dny

    እኔንም ለንስሀ ለስጋዎ ለደሙ ያብቃኝ አሜን

  • @user-fv7yk7xx5j
    @user-fv7yk7xx5j Před rokem

    ያአባታአችን በረከት ይደርብን የኛንም አይነ ልቦናችነን ያአብራልን መጨረሻችነንም ያሳምርልን አሜን

  • @truwrkdefaru5434
    @truwrkdefaru5434 Před rokem +1

    ቃለ ህይወት ያስማልን የአባታችን በረከታቸው ይደርብን ❤❤❤❤የሊቀ ነቢያት ሙሴን በፈልገው አጣሁት😢😢😢በእናታችሁ ሊንኩን ላኩልኝ❤❤❤❤❤

  • @abrahamasefa4087
    @abrahamasefa4087 Před 9 měsíci +1

    yee abatachen muse berakata yideraben

  • @RajRaj-yv2fp
    @RajRaj-yv2fp Před 4 lety +1

    Ameen ameen ameeen kale hiywet yasemalin ye abatochachin bereket yidereblin

  • @masetwalesteble9403
    @masetwalesteble9403 Před 5 lety +55

    እነዉት ክርሰትና ክርስትና የሚሸት ቻናል ነዉ አይዞአችሁ በርቱልን እዚህ ለመድረስ ከባድ ዋጋና የዲብሎስ ዉጊያ እንደከፈላችሁበት እዉን ነዉ። ነገር ግን ዋጋችሁ ከላይ ከአርያም ነዉ በርቱ

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  Před 5 lety +8

      እናመሰግናለን፡፡ ፀሎታችሁ አይለየን

  • @demekecheadugna9642
    @demekecheadugna9642 Před 10 měsíci

    አሜን የአባታችን ሙሴ ፀሊም በረከታቸዉና ረዴታቸዉ ይደርብን የሙሴ ልብን የከፈተ አምላክ ልባችን ይክፈትልን

  • @Yada-j2r
    @Yada-j2r Před 5 měsíci

    Amen amen amen nay kudes mussi xelim bereket yhderena ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @zedyezufi34
    @zedyezufi34 Před 3 lety +6

    ጌታየ መድሀኒቴ እየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ልጅህ ከሙሴ የባስኩ በሀፅያት ያጨቀየሁና ያደፍኩ ነኝ እባክህ ልቤን ወዳንተ መልስልኝ ሀፅያቴን ሁሉ ይቅር በለኝ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙏

  • @user-fo2tj2rh9o
    @user-fo2tj2rh9o Před 3 lety +1

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን በእውነት ቃለህወት ያሰማልን የኣባታችን ፆሎት ይድረሰን ኣሜን ኣሜን ኣሜን🙏🙏🙏🙏

  • @werkitazarra4338
    @werkitazarra4338 Před rokem

    በእውነትቃለህይወት፣ያሰማልንየአባታችን፣በረከትይደርብን