1. እንዲህ ነው ነገሬ ll ዶ/ር. ልዑል ግርማ ll Endih New Negere ll Dr. Leul Girma l New Album 2024

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 8. 09. 2024
  • Songwriter Dr. Leul Girma (መዝሙር ፀሐፊ ዶ/ር. ልዑል ግርማ)
    ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ አዳዲስ ዝማሬዎችን ያገኛሉ።
    By subscribing this Channel you will get New gospel Songs.
    #አምልኮ #protestant_song #Amharic gospel song #ወንጌል #2024 #ኢየሱስ #ፕሮቴስታንት #አዲስ_መዝሙር
    Leul Girma-Lula በሚለው Artist name, Spotify ላይ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ስቶሮች ላይ የአልበሙን ኦሪጅናል Audio ማግኘት ትችላላችሁ
    የንጋት ኮከቤ አልበም👇
    ከየንጋት ኮከቤ አልበም ጋር የተያያዙ እውነታዎች
    ▶በ3 ትልልቅ ስቱዲዮዎች ውስጥ ላለፉት 6 ዓመታት እየተሰራ ቆይቷል
    በAB Studio
    በShakura Studio እና
    በNiftalem Studio
    ▶በዚህ አልበም ላይ ወደ አስር የሚጠጉ አንጋፋ ሙዚቀኞች ተሳትፈውበታል
    1. አቤኔዘር ታፈሰ (ኤቢ)
    2. ዝናው ካሳ (ማሜ)
    3. ዘርይሁን ማርቆስ
    4. ቃለአብ ጠቅል
    5. ዘርይሁን በለጠ
    6. ናትናኤል ገ/ፃድቅ
    7. ይበልጣል ትእዛዙ
    8. ደግሰው አበበ
    ሌሎችም በአንዳንድ ምክንያት ስማቸው ያልተጠቀሰ ሙዚቀኞች ተሳትፈዋል።
    ▶ይህ አልበም ከ20 ጊዜ በላይ Final Master እስከሚሆንበት ቀን ድረስ በጥንቃቄ ሳንሱር ተደርጓል
    ▶አልበሙ የያዛቸው መልዕክቶች
    ▷ወንጌል
    ▷አምልኮ
    ▷መፅናናት
    ▷ተግሳፅ እና የንስሀ መልዕክት
    ▷ለቤተክርስቲያን የተፃፈ ጠንካራ መልዕክት
    ▷ለትውልድ እና ለመሪዎች የተፃፉ ጠንከር ያሉ ሀይለቃሎች
    ▷ሀገራዊ እና ማህበረሰባዊ መልዕክቶች
    ▶በአልበሙ ውስጥ የተካተቱ የሙዚቃ ስልቶች
    ▷ችክችካ
    ▷ወሎ ሪትም
    ▷ትዝታ
    ▷ሬጌ
    ▷ሮክ (ሶፍት)
    ▷ዋልዝ
    ▷አፍሮ ቢትስ
    ▷ዲስኮ
    ▶ማሳሰቢያ (N.B.)
    ሁሉም መልዕክቶች የተፃፉት ከመዝሙር ፀሐፊው ግለ ህይወት ሁኔታዎች እና ምስክርነቶች እንዲሁም እንደ ክርስቲያን ማህበረሰብ እና እንደ ሀገር ሁላችንም ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ እና እውነት የያዘ ነው እንጂ ሀይማኖት ተኮር እና የሰውን ስሜት ለማስደሰት የተፃፈ አይደለም።
    ምክንያቱም አንዳንዶቹን መዝሙሮች ስታዳምጡ ግር እንዳይላችሁ እና ያልተለመደ አይነት መልዕክት እንዳይሆንባችሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
    ተባረኩ!
    እንዲህ ነው ነገሬ
    ---------------------
    የሰማይ በረከት ወደኔ ተልኳል
    አቤት ሠረገላው እንደጉድ ተጭኗል
    አብርሀምን ጠርቶ ደጋግሞ ባረከው
    ፀሐይዋ ወጥታለች ዘመኑ የኔ ነው
    እንዲህ ነው እንዲህ ነው ነገሬ
    ዘግቶታል ደፍኗል መቃብሬን
    የውለታው ብዛት ሸክም ያለባችሁ
    ዘምሩ ከኔጋር ዕልልታን ይዛችሁ
    እንዲህነው እንዲህነው ነገሬ
    አንተይሁን ስትል የማይሆን ይሆናል
    ቃልህ በገባዖን ፀሐይን አቁሟል
    የምስራቅን ነፋስ አንዴ ሥትልከው
    ውሽንፍሩን ይዞ ሸለቆዬን ሞላው
    "የሰማይ በረከት"
    ---//---
    አህዛብን በስም ኑብሎ ሲጠራ
    ተማረከ ልቤ ሲመጡ በተራ
    የእኔም ተራ ደርሶ ወጣችልኝ ፀሀይ
    ጠላቴ ይደንግጥ ድኛለሁ መስቀልላይ
    እዩት ሰናክሬም እንዴትነው ትዕቢቱ
    በእየሩሳሌም ሰራዊት ማዝመቱ
    የአሶር ፈረሶች አለማወቃቸው
    የይሁዳ አምላክ ሰባብሮ ጣላቸው
    ጠላቴን ለመምታት መልአክ ተልኳል
    በገዛ ልጆቹ ሰናክሬም ወድቋል
    "እንዲህ ነው ነገሬ"
    በሸለቆ መሀል የደረቀ አጥንት
    ቢመሥል ነገሬ ተሥፋ የሌለበት
    ቃልንተናገረ ጅማት አወጣብኝ
    በፍቅሩ ደግፎ አለት ላይ አቆመኝ
    (ከትቢያ አንስቶ ሰራዊት አረገኝ)
    እንግዲህ ልዘምር
    እንዲህ ከሆነማ
    መሰንቆውን ምቱት
    በዋሽንቱ ዜማ
    ---//---
    ማዕበሉ ሲጮህ ድምፁ ከፍብሎ
    ሰውም ሲደነግጥ አቅም ክንዱ ዝሎ
    አምላኬ ሲመጣ ወጀቡ ይሰክናል
    እንደ ኩሬ ውሀ ተዋርዶ ዝምይላል
    አይአንተ ማዕበል እንዲያ ስትደነፋ
    ምስጋና እንደሆን ከኔ አፍ ላይጠፋ
    ምንም ባይሆንልኝ ማመስገን አውቃለው
    ይመጣል ወዳጄ ፍቅሩን አይቻለው
    ጠላቴን ለመቅጣት ባህሩን ገስጿል
    ግዙፉም ማዕበል እንደኩሬ ሆኗል
    እንዳህ ነው እንዲህ ነው ነገሬ
    ዘግቶታል ደፍኗል መቃብሬን
    የመስቀሉ ጌታ ከሞት ያዳናችሁ
    ዘምሩ ከኔጋር ዕልልታን ይዛችሁ
    እንዲህነው እንዲህነው ነገሬ
    ...
    እንዲህነው እንዲህነው ነገሬ
    እንዲህነው እንዲህነው ህይወቴ
    እንዲህነው እንዲህነው ነገሬ
    (ዜማ, ግጥም እና ቅኔ)
    መዝሙር ፀሐፊ
    ዶ/ር. ልዑል ግርማ

Komentáře • 12

  • @WoynshetAbebe-fu3mg
    @WoynshetAbebe-fu3mg Před měsícem +4

    ድንቅ መዝሙር በፍቅር ደግፎ ዐለት ላይ ያቆማል አሜን አሜን!!!!!!!

  • @girmaabate9823
    @girmaabate9823 Před měsícem +1

    ጌታ ይባርክህ የኔ ልጅ

  • @JossyZelalem
    @JossyZelalem Před měsícem +1

    ተባረክ ዶ/ር ድንቅ ዝማሬ ነው መስማት ማቆም አልቻልኩም Amazing song

  • @kidisthailugospelsong2428
    @kidisthailugospelsong2428 Před měsícem

    ተባረክ!!!

  • @GirmaAbate-tl6cl
    @GirmaAbate-tl6cl Před měsícem +1

    እጅግ የሚገርምና የሚባርክ መዝሙር ነው።ጌታ ከዚህ በላይ ይጨምርልህ ልጄ ።

  • @EdenGirma-po7zv
    @EdenGirma-po7zv Před měsícem +1

    ተባረክ ወንድሜ 🙏

  • @zerituzemach4357
    @zerituzemach4357 Před měsícem

    ጠላቴ ይደንግጥ ድኛለሁ መስቃል ላይ 😇
    be blessed

  • @moviehub2687
    @moviehub2687 Před měsícem

    በጣም ግሩም ስራ ነው ዶክተር እንኳን ጌታ ረዳህ ተባርከንበታል🙏

  • @marpetyy9030
    @marpetyy9030 Před měsícem

    Be blessed.

  • @samiegate2272
    @samiegate2272 Před měsícem

    God bless u

  • @bitagr4002
    @bitagr4002 Před měsícem

    May God Blesse u🙋

  • @BeteiBekle
    @BeteiBekle Před měsícem

    ❤❤❤❤❤