የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 36 | ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ | በማሙሻ ፈንታ | Matthew Teaching 36 | By Mamusha Fenta

Sdílet
Vložit
  • čas přidán 11. 09. 2024
  • #እነሆ_ንጉሥሽ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት
    #ከፍሬያቸውታውቋቸዋላችሁ
    📖 ማቴዎስ 7:15-20
    👑 በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ
    ⏰ ዘወትር አርብ ከ 11:00 ጀምሮ
    አድራሻ: ካዛንቺስ በመለስ ፋውንዴሽን ትይዩ ባለው ቅያስ ገባ ብሎ ወይም ከልቤ ፋና ት/ቤት ጀርባ
    📱+251-938-859999
    maps.app.goo.g...
    👑 በአካል መገኘት ለማትችሉ በቴሌግራም በዩቱብ እና በፌስቡክ ገጻችን በቀጥታ ስርጭት እንድትከታተሉ ጋብዘናችኋል።
    👑 / @equipmedia2577
    👑 t.me/Mamusha_F...
    👑 / equipmediamamushafenta

Komentáře • 88

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577  Před 11 měsíci +33

    #የአርብ_ምሽት_የትምህርት_ጊዜ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ተከታታይ_ትምህርት
    #በፍሬያቸው_ታውቋቸዋላችሁ
    📖 ማቴ 7:15-20
    - የተሰጠን መንፈሳዊ ህይወት፣ የእግዚአብሔር መንግስት፣ የእግዚአብሔር ልጅነት የከበረ ነው፣ ውድ ነው፣ ጥንቃቄ ይጠይቃል፤ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚመሩን ሀሰተኞች ስላሉ።
    - መንገዳችንን ስንኖር በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፤ ሀሰተኛና ተመሣሣይ መልዕክተኞች ፣ የውሸት መልዕክተኞች ስላሉ።
    - ሀሰተኛነት በዚህ ዘመን አልጀመረም፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፤ ከዲያብሎስ የጀመረ ነው።
    📖 ዘዳ 18:20
    - ሀሰተኛ ነብያት በድፍረት ወይም በሌላ አማልክት ስም (በሌላ መንፈስ) ይናገራሉ።
    - ቋንቋቸው ይለያይ እንጂ ሀሰትና ሀሰተኛ ነብያት የጥንት ናቸው።
    - የመጨረሻው ዘመን አንዱ ምልክት የሀሰተኞች መብዛት ነው።
    - ሀሰተኛ ነብያት፣ ሀሰተኛ ትምህርት አለ ማለት እውነተኛ የለም ማለት አይደለም።
    📖 2ጴጥ 1:
    📖 1ቆሮ- 14:3
    🚩 ሀሰተኞችን እንዴት እናውቃቸዋለን/ እንለያቸዋለን?
    - ሀሰተኛና እውነተኛ በኖረው እድሜ ብዛት አይለይም፤ በአዲስነት ሀሰተኝነት የለም፣ በመሠንበትም እውነተኝነት የለም።
    - ሀሰተኝነት በእድሜም በተቋምም አይለይም።
    - ሀሰተኞች በውጫዊ መልክ/ገጽታ አይለዩም። ጥንትም ዛሬም መልክን በማስመሠል ነው የሚመጡትና። ሀሰተኛን ሀሰተኛ ያደረገው መመሳሠሉ ነው።
    - ቁ.15 "የበግ ለምድ ይለብሳሉ.......ውስጣቸው ግን ተኩላ"
    📖 2ቆሮ 11:13
    - ራሳቸውን ይለውጣሉ፣ ለመምሰል ይሞክራሉ።
    📖 ዘዳ 13:
    📖 2ጢሞ 3
    - ከእግዚአብሔር የሚመሥል፣ የተኮረጀ ነገር ያደርጋሉ። የሠራ የመሠለ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።
    📖 ሐ.ስራ 20:29-30
    - የሀሰተኛ ነብያት መለያ አንዱ መልካቸው ያምራል፤ በውስጣቸው ግን ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ናቸው።
    📖 ይሁዳ 3: "ጨካኝ የባህር ማዕበል"
    📖 ሕዝ 22:25-29 "የሚናጠቅ አንበሳ"..... "የስስትን ትርፍ ለማግኘት"...."ገለባ የሌለው ጭቃ"
    📖 ኤር 23 ....ሰላም ሳይሆን ሰላም ነው ይላሉ
    📖 ኤር 8:11...በጥቂቱ ይፈውሳሉ
    - የሀሰተኛ ነብያት ገበያ የሚደራው በሰዎች ቁስል ላይ ነው።
    - የጌታን ስም የጠራ ሁሉ የተባረከ አይደለም፤ ዲያቢሎስም ጥቅስ እየጠቀሰ መጥቷል።
    📖 ማቴ 7:15
    🚩 ሀሰተኛ ነብያትን በፍሬአቸው እናውቃቸዋለን።
    - መልክ ሊኮረጅ ይችላል፤ ፍሬ አይኮረጅም።
    - ሁለት አይነት ዛፎች አሉ
    1) ጤናማ ዛፍ (መልካም ፍሬ የሚያፈራ)
    2) ክፉ ዛፍ (ክፉ ፍሬ የሚያፈራ)
    - ፍሬ ማፍራት ጊዜ ይጠይቃል፤ ፍሬ ተጠብቆ ነው የሚገኘው።
    - ፍሬ የጉባኤ ወይም የተከታይ ብዛት አይደለም። ኢየሱስ 12 ሰው ይዞ ነበር የኖረው።
    - የህዝብ ብዛት ሀሰትን እውነት አያደርግም።
    - እውነት በለበት ዘንድ ጉባኤ ሊሞቅ ይችላል እንጂ የሞቀ ጉባኤ ሁሉ እውነት አለበት ማለት አይደለም።
    - ፍሬ ቆይቶ የሚገኝ ህይወት ነው።
    - የክርስቶስን ህይወት ታይበታለህ? ከህይወቱም መልካም ፍሬ ትለቅማለህ? ይህንን ነው መጠየቅ።
    - ሀሰተኛ ነብያት ስህተት ይሰራሉ እውተኛ ነብያት ምንም ስህተት አይሰሩም ማለት አይደለም።
    - የህይወታችን ግብ ኢየሱስን ከመምሰል ካነሰ ሀሰተኞች ያገኙናል።
    - የህይወታችን ግብ ኢየሱስን መምሰል፣ ባህሪውን፣ ትህትናውን መምሰል፣ የመንፈስ ፍሬ በህይወታችን መገለጥ መሆን አለበት።
    - ከፍ ያለ ግብና አላማ ከያዝን ማንም እየጎተተ አያወርደንም።
    - የመሬት አላማ ከያዝን ለሀሰተኞች እንመቻለን።
    - ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ የሚወስደው እርሱን የመሠሉትን ነው።
    - በሙሽራው ቦታ ሚዜ አናስገባ፤ እኛ የሙሽራው ነን።
    🙏 የተሰጣችሁ ህይወት መጫወቻ አይደለም፤ ተጠንቀቁ፣ ማነው የሚያስተምራችሁ? ማነው የሚያገለግላችሁ? ማነው እጁን የሚጭንባችሁ? ማነው የሚመክራችሁ? የእውነትን ቃል ተማሩ፤ በእውነት ቃል ብሰሉ፤ ለዚህ አለም አትስገዱ፣ ለምታዩት፤ ለምትሰሙት፤ ለምትሔዱበት ተጠንቀቁ!! ለምን? ጎዳናው አጥፊ ነው።
    🙏 አሏችሁ ወይ የምታውቋቸው፤ ፍሬአቸውን ያያችሁ መምህራን? አሏችሁ ወይ የሚመክሯችሁ ሰዎች? አሏችሁ ወይ አብያተ ክርስቲያናት? የቤተክርስቲያን መሪዎቻችሁን ምክር ስሙ፣ መካሪ ይኑራችሁ፣ በየመንገዱ፤ በየቦታው የምትገኙ አትሁኑ፣ ማንም የሚያገኛችሁ፤ ማንም ትንቢት የሚሠጠው አትሁኑ፣ ማንም እጁን እንዲጭንባችሁ አትፍቀዱ፣ አትንከራተቱ፣ የእውነትን ቃል ተማሩ፣ በቤተክርስቲያን ተተከሉ፣ ሊያጠፏችሁ ከሚመጡ፤ የበግ ለምድ ከለበሱ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ ተጠንቀቁ።
    - በሰው ተሰናክላችሁ ቤተክርስቲያን መምጣት አታቁሙ፣ አገልግሎት አታቁሙ፣ እውነት የለም አትበሉ፤ አለ! እርሱን ፈልጎ ማግኘት እግዚአብሔር ያድርግላችሁ።

  • @captainayub6482
    @captainayub6482 Před 6 měsíci +1

    እንኩዋን አድሶ መለሰህ መንፈሱን አበዛብህ ከልጅነት አልፈህ የእግዚአብሔር ድምፁ ነህ ያቁይልን አብዝቶ ይባርክህ ያንተን ጨረስክ 🕊⚓️🐑🙏🏽ዓሜን እልልልልል ⚖️🏃🏾‍♂️

  • @abebaseyiume8949
    @abebaseyiume8949 Před 10 měsíci

    ዶክተር ማሙሻ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመንህን በዚህ ወንጌል እዉነት ይጠቅልለዉ ይጠብቅህ ወንድምዬ

  • @John-gr8yk
    @John-gr8yk Před 5 měsíci

    ጌታ ባንተ ይባርክርኛል ጌታ ይመስገን

  • @yygigg2938
    @yygigg2938 Před 11 měsíci +9

    አባታችን ማሙሻዬ ፀጋዉ ይብዛልህ
    ስለ አንተ እግዚአብሔር አምላኬን አመሰግናለሁ አሁንም እግዚአብሔር እዉነተኛን ሰራተኛ ያብዛልን በኢየሱስ ስም አሜን❤🙏

  • @amanueltadesseofficial8122
    @amanueltadesseofficial8122 Před 10 měsíci

    O, lord Jesus help us to follow you in your preferred paths amen.

  • @TaberkElias-ts4sz
    @TaberkElias-ts4sz Před 6 měsíci

    Gat lazalalam yebarek mamushi❤❤❤❤

  • @saramesfin6511
    @saramesfin6511 Před 11 měsíci +12

    ማሙሻ በዚህ ዘመን እውነትን ስለምትሰብክ ጌታ ይባርክህ:: አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልግህን ሁሉ ይሙላብህ::

  • @mesiyohans1760
    @mesiyohans1760 Před 10 měsíci

    ኣይ እግዛኣቤሕረ ባዘማኑ ሁሉ ላረሱ ቅረታሆቺን ያሲቃረል dr m a❤❤

  • @mamojoffe6778
    @mamojoffe6778 Před 9 měsíci

    Thank you Dr Mamusha! እንግዲህ ጆሮ ያለው ይስማ : ልቦና ያለውም ያስተውል ።

  • @bogaleagga9026
    @bogaleagga9026 Před 10 měsíci

    አሜን🙏🏾

  • @bitaniyaelias6514
    @bitaniyaelias6514 Před 10 měsíci

    God bless you Dr, Mamusha. you speak the truth boldly.

  • @user-hq3gy2rl5r
    @user-hq3gy2rl5r Před 10 měsíci

    ዶ/ር ማሙሽ ጌታ ይባርክክ ፀጋውን ያብዛልህ ካሳሁን ነኝ ከሻሸመኔ

  • @fetenechtadesse4978
    @fetenechtadesse4978 Před 10 měsíci

    ዘመንህ ይባረክ ወንድም ማሙሻ

  • @idhdudga7544
    @idhdudga7544 Před 8 měsíci +1

    Tebreke bewunte ❤❤❤❤

  • @user-qp9bx3cs9i
    @user-qp9bx3cs9i Před 10 měsíci

    ከዓባይነሀ ዶ/ር ማሙሻ እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡

  • @tse-melash4902
    @tse-melash4902 Před 11 měsíci +4

    እረ በጌታ ጆር ያለዉ ይስማ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ዶ/ር ማሙሻ

  • @eliasgelan5735
    @eliasgelan5735 Před 11 měsíci +2

    እግዚአብሔርን ስለአንተ በዚህ አገልግሎት ሁሉ ለምታገለግሉ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ❤ እንደዚህ በድፍረት እና በግልጥ የእግዚአብሔርን ቃል በመንፈስ ለማስተማር ስለምተጋ ተባረክለኝ❤

  • @nitreworkmulat9461
    @nitreworkmulat9461 Před 5 měsíci

    እግዚአብሔር ይባርክህ ይባርካችሁ ሁላችሁንም

  • @eyerusbirhanu3592
    @eyerusbirhanu3592 Před 8 měsíci

    Amen àmen menkate yhunln... bless you Dr mamush ❤️🙏🙏👍

  • @hanaweba1541
    @hanaweba1541 Před 11 měsíci +5

    ይሄን የሰማ አካሄዱን ያስተካክላል። በዛ ላይ ከትምህርት በ ኧላ አዳዲስ ነብሳትን ስለምትጠራ ተባረክ ይህ ነዉ ዋናዉ የስብከታችን አላማ።

  • @Jesusislove-gf3ox6wo8m
    @Jesusislove-gf3ox6wo8m Před 11 měsíci +5

    እግዚአብሔር ሆይ ስለ ዶክተር ማሙሻ ተመስገን!!🙏
    እግዚአብሔር አንተ ታማኝ አምላክ ነህ ህዝብህን በጨለማ የማትተው ቅሬታዎችን የምታስተርፍልን ነህ እና ተባረክ እናመሰግንሃለን!! አሁንም ብዙ ጸጋ ጨምርላቸው ጌታ ሆይ!! በእኛ ድክመት እንዳይታክቱ ከማስተማር በጸጋህ አበርታቸው!!🥺🙏❤

  • @adonayfentie2575
    @adonayfentie2575 Před 10 měsíci

    ተባረክ❤❤❤

  • @marthakifle5060
    @marthakifle5060 Před 11 měsíci +2

    እንዳንተ ያሉ ሰዎችን እግዚአብሂር ያብዛልን። ዘመንህ ይባረክ።

  • @ምህረትየበዛላትነኝ

    ብሩክ ነህ ማሙሻ ይብዛልህ 🙏🔥🔥🔥

  • @anjelaanjela4791
    @anjelaanjela4791 Před 11 měsíci +1

    ጌታ እየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ዶክተር ማሙሻ በትምህርትህ በጣም እየታነፅን ነው thank you

  • @marthamule9997
    @marthamule9997 Před 11 měsíci +1

    እግዛብሔረን ስለሰጠት ጥበብ አመሰግናነሁ ዘመንህ ህይወት ይባረክ ለትውልድ ሁሉ የሜሆን የሜያነ ቃል ስግዛብሔረ ይባረክ

  • @mulugetaangisew4826
    @mulugetaangisew4826 Před 11 měsíci +3

    ጌታ ዘመንህን ይባርክ።ዠ

  • @hamelmalargu6894
    @hamelmalargu6894 Před 11 měsíci +1

    ዋው ሁሌ ጌታ እረዳህ እውነትን ስለምታወራን/ስለምታስተምረን/ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርክህ

  • @tseghewoldu4016
    @tseghewoldu4016 Před 10 měsíci

    May God bless you and uses u more and more 🙏

  • @lilybehailu3042
    @lilybehailu3042 Před 10 měsíci

    በጣም የገባኝ ነገር
    ሴጣን ሚመስል ነገር ነው ሚሰጠው
    እግዚአብሔር ግን የሆነ እውነት ያለበት የሚታይ ነገር ነው ሚሰጠን ሚያስተምረን

  • @serkadisasfaw7721
    @serkadisasfaw7721 Před 11 měsíci +1

    ዶ/ር ማሙሻ እግ/ር አብዝቶ ይባርክህ እንደዚህ እውነቱን ስላስተማርከን 🎉

  • @admasmitachew131
    @admasmitachew131 Před 11 měsíci +4

    God bless you more and more 🙏

  • @addisisuendalew3547
    @addisisuendalew3547 Před 10 měsíci

    በእንባና በእልልታ የሰማሁት ድንቅ ስብከት! በብዙ የተባረኩብህ ወንድሜ ማሙሻ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ፣ ፊቱንም ያብራልህ፣ ትጋትም ይስጥህ።🙌
    ቅዱስ ሆይ ቃል እውነት ነው በእውነትህ ሁሌም ቀድሰን።🙇🙇🙇

  • @SaronAbera19
    @SaronAbera19 Před 11 měsíci +1

    እግዚአብሔር ቤተሰብህን አንተን ይባርክ።
    እሱን በመፍራት ደግሞም በንሰሀ ያቆይህ ።
    በጣም አመሰግናለሁ ምን ያህል እግዚአብሔር በቃሉ እንዳበረታኝ እንደረዳኝ ሞትን ቆሜ የምጠብቅ ሴት ለሞት የተሸከምኩትን ደዌ ስሙን ያስቀየረኝ ብታድነኝም ባታድነኝም አንተ መልካም ነህ ያልኩበት መልካም ፍፌ ያበቀልኩበት ቃል ያሰማኸኝ መልካም አባት ነህ ።
    Equip media እባካችሁ አሳዩልኝ

  • @Ova-7311
    @Ova-7311 Před 11 měsíci +2

    ቡሩክ ነህ ዶር, ጌታ ይብዛልህ, ሃለሉያ

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Před 11 měsíci +1

    ቃሉ በልቤ ፈሰሰ,አሜንንንን ተባረክ ዶክተር ማሙሻ❤❤❤

  • @dawitduga6570
    @dawitduga6570 Před 11 měsíci +3

    God bless you

  • @solomongeberekidan2904
    @solomongeberekidan2904 Před 11 měsíci +1

    እውነተኛ ት/ም ነው ።ብዙዎችን ኣሳቱ ዘረፉ ሰረቁ መድሀኒት ተው ብለው ገደሉ ።ጌታ ይባርክህ ይህእውነተኛ የእ/ር መልእክት ነው።

  • @saradalma9089
    @saradalma9089 Před 11 měsíci +1

    ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክዎት የእግዚአብሔር ሰው

  • @kokebetadesse6026
    @kokebetadesse6026 Před 11 měsíci +1

    ጌታ ኢየሱስ ለዘላለም አብዝቶ ይባርክህ

  • @belhumamo797
    @belhumamo797 Před 11 měsíci +1

    እውነት ነው ወንድማቸን ማሙሻ ብዙ ቤቱን ያረከሱ አሳቾ ቸ አሉ በነሱ የተሰናከሉ ጌታ እንደነሱ አደለምና ታማኝና ፍዋሽ አዳኝ ነው የኛ እየሱስ የእግዚአብሔር ልጀ ወረት የሌ ለበት ተ ባረክልን

  • @abenezerberassa3182
    @abenezerberassa3182 Před 11 měsíci +1

    ወንድም ማሙሻ ጌታ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @VoiceForJesus7
    @VoiceForJesus7 Před 10 měsíci

    I wish I have word to express my gratitude for this beautiful equip media God Jesus Christ bless this media I will share and will keep you guys in my prayers my name is abenezer mamo from Kansas

  • @tsehayegetachew4599
    @tsehayegetachew4599 Před 11 měsíci

    ሁላችሁ አሰተማሬ አትሁኑ ይላል ቃሉ ሳያጠሩ ሳይማሩ የሳቱ ያሳቱ ብዙዋችን ያለደሜቸዉ መዳኔት አሰጥለዉ የገደሉ ጨካኞች ይፈረድባቸዋል እግዚአብሔር ቅሬታ አሉት ተባረክ ማሙሻ።

  • @user-ir2ug2my7c
    @user-ir2ug2my7c Před 11 měsíci +1

    አሜሜሜሜሜንንንንንን ጌታ ይባረክ ዶክተር ማሙሻ ❤ ❤❤🙏🙏🙏🔥🔥🔥

  • @user-br6dy5ce5x
    @user-br6dy5ce5x Před 11 měsíci +1

    Thankyou Mamusha, you are our blessing!!😍

  • @tsigeredaendale6434
    @tsigeredaendale6434 Před 11 měsíci +1

    I thank God about you! Dr. Mamusha...... you are a great blessing for us!

  • @merondebele4217
    @merondebele4217 Před 9 měsíci

    ❤❤❤

  • @romiegebreselassie3108
    @romiegebreselassie3108 Před 11 měsíci +1

    ውስጤ እረሰረሰች 🙏🙏🙏ተባረክ ወንድማችን

  • @habtsegy2663
    @habtsegy2663 Před 11 měsíci +1

    Amennnnn amennnnn tebarek p. Mamush wonderfull message❤❤❤❤❤

  • @zelalemtsegaye13
    @zelalemtsegaye13 Před 11 měsíci +1

    ተባረክልን ሌላ ምን እንላለን

  • @ephrembedada761
    @ephrembedada761 Před 11 měsíci +1

    Poster Mamusha God bless you and your service. It is my prayer to we have a person like you teach the truth for the truth of God.

  • @mail2hasset
    @mail2hasset Před 11 měsíci +1

    Tebarek Dr Mamusha

  • @MeleChego
    @MeleChego Před 10 měsíci

    The loyal servant of the Lord! Dear Dr.Mamusha we always rejoice in your teaching of the true Gospel. You hold the candle light in the age of deep darkness of false teachings and prophecies around Christ's Church in our Country today. Much love and respect ❤❤❤❤❤❤❤

  • @konjitguroro5982
    @konjitguroro5982 Před 11 měsíci +1

    Wow amazing messages may my lord help us!! God bless you!!!

  • @abeshasolomon1798
    @abeshasolomon1798 Před 11 měsíci +1

    ወገኖች፣ pin የተደረገው ላይ read more የሚለውን ተጭናችሁ የመልዕክቱን ጭማቂ ተመገቡ፤ ተባረኩ። ወንድም ማሙሻ ተባረክ! this is excellence. ጌታ አሁንም ጥበብ ይጨምርልህ።

  • @enkenyeleshlegesse7756
    @enkenyeleshlegesse7756 Před 11 měsíci +1

    Tsega yibizalih Dr

  • @HG-ww6fm
    @HG-ww6fm Před 11 měsíci +1

    God bless you 🙏 ... our father is coming soon!!!!

  • @ZoweKebede
    @ZoweKebede Před 11 měsíci +1

    My dear mamushey Good bless u ❤❤❤

  • @yodittekie9265
    @yodittekie9265 Před 11 měsíci +1

    👍👍👍👍👍👍👍👍👍

  • @yodittekie9265
    @yodittekie9265 Před 11 měsíci +1

    👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

  • @mememalase9018
    @mememalase9018 Před 11 měsíci +1

    Tebareku gate yebarkh ❤

  • @sedessiemulugeta2952
    @sedessiemulugeta2952 Před 10 měsíci

    What a wonderful teaching! May God continue to speak through you!

    • @adonayfentie2575
      @adonayfentie2575 Před 10 měsíci

      czcams.com/video/gbAjdXMbQb4/video.htmlsi=jDleDmY7vLziz0lO

  • @yodittekie9265
    @yodittekie9265 Před 11 měsíci +1

    Yes true God less

  • @RekikDerejeDegefu-he7gc
    @RekikDerejeDegefu-he7gc Před 11 měsíci +1

    Ene migermegn hasetegnot begara training yemiwesidu eskimesil dires nigigirachew lay genzeb, genzeb meat gize new miteraw. Ene yahunu hasetegnochin meleyet kelal new kifu fireyachew bande yitayal. Sewu rasu yeneway fikir nedobetal

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 Před 9 měsíci

    ማሙሻዬ ኢየሱስ ግን እውነት ነው አለቀ

  • @hermelabiyaznmekonnen2241
    @hermelabiyaznmekonnen2241 Před 11 měsíci

    Bezu sink eyesetachun nw tsegaw yichmrlachu

  • @nitreworkmulat9461
    @nitreworkmulat9461 Před 10 měsíci

    እባካችሁ ትምህርቱን ተክታታይ ማግኘትአልቻልኩም ብዙ ጊዜ ጽፌ ላችሁ ነበር እና ሁሉንም እንደዛ ብታረጉልን ብዙ መማር እንችላለን

  • @HannaTadesse-lo1ip
    @HannaTadesse-lo1ip Před 10 měsíci

    Hello, the question am going to rather here is not the topic you teaches now but am confused as soon as possible please answer me 🙏 1. What is faith?2.did Jesus was faithful? Or did he need to faith?
    3. Faith is dependence on …?
    4. Why we faith?
    5. Is our faith can make something or …?

  • @habtishjenbola367
    @habtishjenbola367 Před 11 měsíci

    ስንት ላስገባ ስንት እንዳወጣ

  • @user-ov8zk3yx1q
    @user-ov8zk3yx1q Před 11 měsíci

    ይሄ ቤተ ክርስቲያን የት ነው ልመጣ ፈልጋለው

    • @equipmedia2577
      @equipmedia2577  Před 11 měsíci +1

      በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ ዘወትር አርብ ከ11:00 ጀምሮ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ትምህርት ነው።
      አድራሻ: ካዛንቺስ በመለስ ፋውንዴሽን ትይዩ ባለው ቅያስ ገባ ብሎ ወይም ከልቤ ፋና ት/ቤት ጀርባ
      📱+251-938-859999
      👑 maps.app.goo.gl/7ffKT71PQgMrwA4X9

    • @amwon3708
      @amwon3708 Před 11 měsíci

      Kazanchis in front of Meles foundation

  • @amenkal8562
    @amenkal8562 Před 11 měsíci

    ቆይ ግን አጋንት የሚያሶጣ ደግሞም ስለ ቅድስና የሚሰብክ ግን ከተለያዮ ሴቶች ጋር ይተኛል ቀደም ሲል ትዳር ነበረው 4 ልጆችም አሉት ይጠጣል ይዘሙታል ፆም አያውቅም ይዘፍናል ግን አጋንት ያሶጣል ስለ ቅድስናም ይሰብካል ግራ ተጋብቻለሁ በዚህ ሰው

    • @alemkiru2012
      @alemkiru2012 Před 11 měsíci

      ቅድስና ማለት መለየት ነው ይሄሰው ከሃጢያት ሳይለይ ስለቅድስና የሚሰብክ ከሆነ ከዚህ ሰው መለየት ነው ይሄ ትምህርት እኮ ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል መጠንቀቅ ነው

  • @BirtukanKebededemise
    @BirtukanKebededemise Před 11 měsíci

  • @haregmulat1gmail
    @haregmulat1gmail Před 11 měsíci

    ተባረኩ ያገለገላችሁን😅

  • @MokeYaleMusica
    @MokeYaleMusica Před 11 měsíci

    God bless you